አጠቃላይ ጉባኤ
የመመለስን እና የትንሳኤን መልዕክት ማካፈል
የሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ።


2:3

የመመለስን እና የትንሳኤን መልዕክት ማካፈል

ተሃድሶው የአለም ነው፣ እናም መልዕክቱ በተለይ ዛሬ በጣም አጣዳፊ ነው።

በዚህ የአጠቃላይ ስብሰባ ጊዜ በፊት ስለተተነበየው ስለሁሉም ነገር መመለስ፣ ”1 “በክርስቶስ ሁሉንም ነገር አንድ ስለማድረግ፣”2 ስለ ወንጌል ሙላት መመለስ፣ ክህነት፣ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ወደ ምድር ስለመምጣት፣ ሁሉንም “ትሃድሶ” በሚል ርዕስ ስር በማጠቃለል በደስታ ተናግረናል እንዲሁም ዘምረናል።

ነገር ግን መመለሱ ዛሬ ለምንደሰትበት ሰዎች ብቻ አይደለም። የመጀመሪያው ራዕይ ለጆሴፍ ስሚዝ ብቻ አይደለም የተሰጠው ነገር ግን “ጥበብ ለጎደለው”3ለማንኛውም ሰው እንደ ብርሃንና እውነት የተሰጠው ነው። መጸሐፈ ሞርሞን የሰው ልጆች ሃብት ነው። የደህንነት የክህነት ስነስርዓቶች በህይወት ለሌለውም ጨምሮ ለሁሉም ግለሰብ ነበር የተዘጋጀው። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እና በረከቶቿ ለሚፈልጉት ሰዎች ሁሉ የታቀደ ነው። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ለሁሉም የታቀደ ነው። ተሃድሶው የአለም ነው፣ እናም መልዕክቱ በተለይ ዛሬ በጣም አጣዳፊ ነው።

“ስለሆነም፣ የመጀመሪያው ትንሣኤ በመሆን፣ በስጋ በሞተው እናም ህይወቱን በመንፈስ ኃይል እንደገና በማንሳት ሙታን እንዲነሱ ባደረገው በቅዱሱ መሲህ መልካም ሥራና፣ ምህረትና ፀጋ በስተቀር፣ በእግዚአብሔር ፊት ማንም ስጋ ሊኖር እንደማይችል ያውቁ ዘንድ፣ እነዚህን ነገሮች ለምድር ነዋሪዎች እንዲያውቁት ማድረግ እንዴት ታላቅ ነገር ነው።”4

የነብዩ ወንድም ሳሙኤል ስሚዝ የመፀሐፈ ሞርሞን ቅጂዎች ቦርሳውን ሞልቶ አዲሱን መጽሐፍ ቅዱስ ለማካፈል እግሩን ካነሳበት ቀን አንስቶ፣ ቅዱሳኑ “ይህንን ነገር ለምድር ነዋሪዎች በሙሉ ለማካፈል” ካለማቋረጥ ተግተዋል።

በ1920 (እ.አ.አ.) በዛን ጊዜ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ሸንጎ አባል የነበሩት ሽማግሌ ዴቪድ ኦ መኬይ ዓመት የሚፈጅ የቤተክርሲቲያኗን ሚስዮኖች ጉብኝት ጀመሩ፡፡ በግንቦት 1921 (እ.አ.አ) የቶማስና የሳራ ሂልተን ሴት እና ሁለት ወንድ ህፃን ልጆች በተቀበሩበት በፋጋሊኢ ሳሞአ በምትገኝ በእንክብካቤ በተያዘች ትንሽ መቃብር ስፍራ ውስጥ ቆሞ ነበር። እነዚህ ህጻናት ታላቅየው ሁለት አመት ነበረ፣ ቶማስ እና ሳራ እንደ ወጣት የሚስዮን ጥንዶች በማገልገል ላይ ሳሉ በ1800ዎች (እ.አ.አ) በሞት ተለዩ።

ከዩታ ከመነሳታቸው በፊት ሽማግሌ መኬይ አሁን ባሏ ለሞተባት ለሳራ ወደ ሳሞአ መመለስ ስላልቻለች የልጆቿን መቃብር ሄዶ እንደሚጎበኝ ቃል ገባላት። ሽማግሌ መኬይ እንዲህ ብለው ፃፉላት፣ “እህት ሂልተን ያንቺ ሶስት ህፃን ልጆች ከሰላሳ ዓመት በፊት የጀመረውን ያንቺን ግርማዊ የሆነ የሚስዮን ስራ ቀጥለዋል።” ከዛም የራሳቸውን ስንኝ አብረውም አከሉ፤

በአፍቃሪ እጆች ሟች አይናቸው ተከደነ፣

በአፍቃሪ እጆች ትንሹ ክንዳቸው ተጣምሮ፣

በባዳ ምድር ምስኪኑ መቃብራቸው ተጌጠ፣

በእንግዶች ተከበረ በእንግዶች ታዘነ።5

ይህ ባለፉት 200 ዓመታት ውስጥ የመመለስን መልዕክት ለማካፈል መስዋዕት የተከፈሉ ጊዜን፣ ሃብትን እና ህይወትን የሚናገር ከሺዎች፣ ከመቶሺዎች ታሪክ አንዱ ብቻ ነው። የፊልጶስን ኑ እና እዩ የሚለውን ግብዣ የሚያስተጋቡ በሙሉ ጊዜ የሚስዮን ጥሪ ላይ በወቅቱ በማገልገል ላይ ባሉ ከ68,000 በላይ በሚሆኑ ወጣት ወንዶች፣ ሴቶች እና ጥንዶች፣ በቤተክርስቲያን አባሎች እናም ይህንን ተግባር በዓለም ዙሪያ ለመደገፍ በሚወጡት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮች ዓመታዊ ወጪዎች እንደሚመሰከረው ሁሉንም ሃገራት፣ ነገዶች፣ ቋንቋዎች እና ህዝቦችን ለመድረስ ያለን ፍላጎት ዛሬም አልቀነሰም6

ግብዣችን አለማስገደድ ቢሆንም፣ ህዝቦች አሳማኝ ሆኖ እንዲያገኙት ተስፋ እናደርጋለን። እንደዚያ ከሆነ፣ ቢያንስ ሦስት ነገሮች ያስፈልጋሉ ብዬ አምናለሁ፣ በመጀመሪያ፣ የእናንተ ፍቅር፣ ሁለተኛ፣ የእናንተ ምሳሌ፣ እና ሦስተኛ፣ የመፅሐፈ ሞርሞን አጠቃቀምዎ፡፡

መጀመሪያ፣ ግብዣዎቻችን የግል ፍላጎት መሆን የለባቸውም፣ ይልቁንም ራስ ወዳድነት የሌለበት ፍቅር የሚገልጽ መሆን አለበት።”7 ይህ ፍቅር ልግስና ተብሎ የሚጠራው የክርስቶስ ንፁህ ፍቅር ከጠየቅን የግላችን ይሆናል። “በፍቅሩ እንሞላ ዘንድ በልባችን ጉልበት በሙሉ ወደ አብ እንድንፀልይ”ተጋብዘናል እንዲሁም ታዘናል።8

ለምሳሌ፣ በአሁን ወቅት ከባለቤቷ ከፕሬዝዳንት ፍራንሲስ ሆ ቺንግ ጋር በሳሞአ አፒያ ሚስዮን ውስጥ እያገለገለች ባለች በእህት ሊኔት ሆ ቺንግ የተነገረ የህይወት ልምድን አካፍላለው። እህት ሆ ቺንግ እንዲህ ብላ አካፈለች፤

ከብዙ ዓመታት በፊት፣ ቤተሰባችን በላኢ ሃዋዪ ውስጥ ወደምትገኝ ትንሽዬ ቤት ውስጥ ተሸጋገርን። የቤታችን የመኪና ማቆሚያ የነበረው ቦታ ወደ አንድ ክፍል ተቀይሮ ጆናታን የሚባል ሰው ይኖርበት ነበር። ጆናታን በሌላ ስፍራ ጎረቤታችን ነበር። ጌታ በአንድ ላይ ያደረገን በአጋጣሚ የሆነ ስላልመሰለን፣ ስለፕሮግራማችን እና ስለቤተክርሰቲያን አባልነታችን የበለጠ ግልፅ ለመሆን ወሰንን። ጆናታን ጓደኝነታችንን ወደደው እንዲሁም ከቤተሰባችን ጋር ጊዜ ማሳለፍ ወደደ። ስለ ወንጌል መማርን ወደደ ነገር ግን ለቤተክርስቲያኗ ራሱን ለማስገዛት ምንም ፍላጎት አልነበረውም።

“ከጊዜ በኋላ ጆናታን አጎት ጆናታን የሚልን ቅፅል ስም በልጆቻችን አገኘ። ቤተሰባችን ማደጉን ሲቀጥል የጆናታን በኛ ላይ ያለውም ፍላጎት እንደዛው አደገ። ለዓመት በዓሎች፣ ልደቶች፣ የት/ቤት ክስተቶች እና የቤተክርስቲያን ፕሮግራሞች ለእሱ የምናደርገው ግብዣ ወደ የቤት ለቤት ምሽትቶች እና የልጆች ጥምቀቶች አደገ።

አንድ ቀን ከጆናታን የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። እርዳታ ይሻ ነበር። በስኳር በሽታ የተጠቃ ሲሆን መቆረጥ የነበረበት ከባድ በእግር በሽታ ተይዞ ነበር፡፡ የቤተሰባችን እና የአካባቢው አባላት ጎረቤቶቻችን በፈተናው ወቅት አብረነው ተጓዝን። በሆስፒታል ውስጥ ፈረቃን ወስደን እንዲሁም የክህነት በረከቶች ተሰጠው። ጆናታን በማገገም ውስጥ ሳለ በሴቶች መረዳጃ እህቶች እርዳታ መኖሪያ ቤቱን አፀዳንለት። የክህነት ወንድሞች ወደ ደጃፉ በር የሚያሸቅብ ደረጃን እንዲሁም በሽንት ቤቱ ውስጥ የእጅ መደገፊያን ገነቡ። ጆናታን ወደ ቤት ሲመለስ፣ በስሜት ተሞልቶ ነበር።

“ጆናታን የሚስዮን ትምህርቱን በድጋሜ መውሰድ ጀመረ። ከዓዲስ ዓመት መገቢያ አንድ ሳምንት በፊት ደውሎልኝ፣ ‘በዓዲስ ዓመት ዋዜማ ምን ለማድረግ አስበሃል?’ ብሎ ጠየቀኝ። ስለ ዓመታዊ ድግሳችን አስታወስኩት። ነገር ግን በምትኩ እንዲህ ብሎ መለሰ፣ ’ለጥምቀቴ ቀን እንድትመጣ እፈልጋለው! ይህን ዓመት በትክክል መጀመር እፈልጋለው’ ከ20 ዓመት ናና እይ፣’ ናና እርዳን፣’ እና ’ናና ቆይ’ በኋላ ይህ ውድ ነብስ ለመጠመቅ ዝግጁ ሆነ።

“በ2018 (እ.አ.አ) የሚስዮን ፕሬዝዳንት እና አጋር ሆነን በሳሞአ ስንጠራ፣ የጆናታን ጤና እየባሰበት ነበር። የኛን መመለስ ጠንካራ ሆኖ እንዲጠብቅ ተማጸንን። ለአንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ቀጠለ፣ ነገር ግን ጌታ ወደ ቤት እንዲመጣ እያዘጋጀው ነበር። በሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ) በሰላም አረፈ። ሴት ልጆቼ የአጎታቸውን የጆናታንን የመቃብር ስነስርዓት ተካፈሉ እንዲሁም በተጠመቀ ለት የዘመርነውን መዝሙር ዘመሩ።”

የመመለስን ወንጌል በማካፈል ውጤታማ እንድንሆን እስፈላጊ የሆነው ሁለተኛው ነገር በዚህ ጥያቄ ላስተዋውቃችሁ፤ ለሆነ ሰው ግብዣችሁ የሚስብ እንዲሆን የሚያደርገው ምንድን ነው? እናንተ እራሳችሁ እይደላችሁምን የሕይወታችሁ ምሳሌ? የመመለስን መልዕክት የሰሙና የተቀበሉ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአባል ወይም በአባሎች ላይ በተመለከቱት ነገር ነው የተሳቡት። ሌሎችን የተንከባከቡበት መንገድ፣ የተናገሩት ወይም ያልተናገሩት ነገር፣ በከባድ ሁኔታዎች ውስጥ ያሳዩት ቆራጥነት ወይም በቀላሉ የፊታቸው ገፅታ ሊሆን ይችላልe።9

ምንም ይሁን ምን ግብዣዎቻችን የሚስቡ እንዲሆን በተቻለን አቅም የተመለሰውን ወንጌል ልንረዳው እና ልንኖረው እንዳለብን እውነታውን ማምለጥ አንችልም። ይህም ብዙውን ጊዜ ዛሬ ላይ እውነተኛነት ተብሎ የሚጠራው ነገር ነው። የክርስቶስ ፍቅር በመሃላችን ካለ፣ ሌሎች ለእነሱ ያለን ፍቅር እውነተኛ እንደሆነ ያውቃሉ። መንፈስ ቅዱስ ውስጣችን ከተለኮሰ በነሱ ውስጥ ያለውን የክርስቶስን ብርሃን ያጭራል።10 ማንነታችሁ የኢየሱስ ክርስቶስን የወንጌል ሙላት ደስታን መጥተው እንዲለማመዱ ለምሰጡት ግብዣ እውነተኝነት አስተዋፅኦ ያደርጋል።

ሶስተኛ የምጠቅሰው ነገር ለዚህ ለመጨረሻው የወንጌል ዘመን ጌታ ለቀየሰው የመለወጥ መሳሪያ ስለሆነው መጽሐፈ ሞርሞን ያልተገደበ ግልጋሎት ይሆናል። የጆሴፍ ስሚዝ ትንቢታዊ ጥሪ ተጨባጭ ማረጋገጫ እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስ ሕያውነትና ትንሳኤ አሳማኝ ማስረጃ ነው። ስለ የሰማይ አባታችን የደህንት ዕቅድ የሚሰጠው መረጃ አቻ የለውም። መጽሐፈ ሞርሞንን ስታካፍሉ፣ ስለ መመለሱ ታካፍላላችሁ።

ጄሰን ኦልሰን ወጣት ልጅ በነበረበት ጊዜ ቤተሰቦቹና በሌሎች ሰዎች በተደጋጋሚ ክርስቲያን እንዳይሆን ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ነበር። ይሁን እንጂ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል የነበሩ ሁለት መልካም ጓደኞች ነበሩት እናም ብዙውን ጊዜ ስለሐይማኖት ይነጋገሩ ነበር። ጓደኞቹ ሺያ እና ዴቭ ሌሎች ለጄሰን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት እንዳይኖረው የሰጡትን ምክር በክብር ተቃወሙ። በመጨረሻም ይህ መጽሐፍ ጥያቄዎችህን ይመልሳል በማለት የመጽሐፈ ሞርሞን ቅጂን ሰጡት። እባክህን አንብበው።” በመጠራጠር መጸሐፉን ተቀብሎ በቦርሳው ውስጥ ከተተው መጸሐፉም ለብዙ ወራት እዛው ተቀመጠ። ቤተሰቦቹ እንዳያዩት መጸሐፉን ቤት ውስጥ መተው አልፈለገም ነበር እንዲሁም በመመለስ ሺያን እና ዴቭን ሊያስቀይምም አልፈለገም ነበር። በመጨረሻም መጸሐፉን ለማቃጠል ወሰነ።

አንድ ምሽት ክብሪቱን በአንድ እጁ መጽሐፈ ሞረሞንን ደግሞ በሌላው ይዞ ሊያቃጥለው ሲል በአዕምሮው ውስጥ እንዲህ የሚል ድምፅን ሰማ፤ “መጸሐፌን አታቃጥል ።” ደንግጦ ቆመ። ከዛም ድምፁ በምናቡ መስሎት ክብሪቱን በድጋሜ ለመጫር ሞከረ። በድጋሚ ድምፁ ወደ አዕምሮው እንዲህ ሲል መጣ፤ “ወደ ክፍልህ ገብተህ መጸሐፌን አንብብ።” ጄሰን ክብሪቱን አስቀምጦ ወደ መኝታ ክፍሉ በመሄድ መጽሐፈ ሞርሞንን በመክፈት ማንበብ ጀመረ። ብዙውን ጊዜ እስከ ጠዋት ረፋድ ሰዓታት ድረስ ቀን ከቀን ማነበቡን ቀጠለ። ጄሰን ማንበቡን ጨርሶ ሲፀልይ እንዲህ ብሎ ፃፈ፤ “ከአናት እራሴ አንስቶ እሰከ እግሮቼ ድረስ በመንፈስ ተሞላሁ። በብርሃን የተሞላ መስሎ ተሰማው። በሕይወቴ ውስጥ ያገኘሁት በጣም አስደሳች ልምድ ነበር።” መጠመቅን ፈለገ ከዛም እራሱ የወንገል መልዕክተኛም ሆነ።

ምናልባት ምንም እንኳን ከእውነተኛ ፍቅር እና ትህትና የመነጨ የመመለስን መልዕክት የማካፈል ግብዣዎቻችን አብዛኛውን ባይሆን እንኳ ብዙዎቹ ተቀባይነት ያጣሉ። ነገር ግን ይህን አስታውሱ ሁሉም ሰው ለእንደዚህ አይነት ግብዣ እጩ ነው፣—“ሁሉም በእግዚአብሔር አንድ ናቸው”11 ጌታ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን በምናደርገው እያንዳንዱ ሙከራ ይደሰታል፣ እንቢ የተባለ ግብዣ የጓደኝነት ማብቂያ ምክንያት መሆን የለበትም፣ ዛሬ የሌለ ፍላጎት ወደፊት አንድ ቀን ወደ ፍላጎት ሊቀየር ይችላል። ምንም ይሁን ምን ፍቅራችን የማይለወጥ ነው።

የወንጌል መመለስ በታላቅ መከራ እና መስዋትነት የመጣ መሆኑን አንንርሳ። ይህም ለሌላ ቀን ያለ ርዕሰ ጉዳይ ነው፡፡ ዛሬ መልሶ በተቋቋመው ፍሬ ውስጥ እንደሰታለን፣ እጅግ በጣም ከሁሉም የሚበልጠው በምድር እና በሰማይ የማሰር ኃይል መመለሱ ነው።12 ከዓመታት በፊት ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ ሂንክሊ እንደገለጹት “የወንጌል መመለስ ምንም ያህል ሃዘንና ስቃይ ቢያስከትልም፣ ቤተሰቦችን ለዘላለም ለመተሳሰር የቅዱስ ክህነት የማተሚያ ሀይል መመለሱ፣ ምንም ያህል ቢያስከፍልም ዋጋ የሚገባው ነው።”13

የመመለስ ቃልኪዳን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት መዳን ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ ከሃዘን፣ ከኢፍታዊነት፣ ከፀፀት፣ ከሃጢያት እንዲሁም ከሞት በእርግጥ የማዳን ኃይል ማስረጃ ነው። ዛሬ የዘንባባ ሰንበት ነው፣ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ የፋሲካ በዓል ነው። እንዘክራለን፤ የክርስቶስን ለሃጢያታችን መስዋት ለመሆን የከፈለውን መከራና ሞት ሁሌም እናስታውሳለን፣ እንዲሁም ያንን እጅግ ግሩም የሆነውን ሰንበት ከሞት የተነሳበትን የጌታን ቀን እናከብራለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤው ምክንያት መመለሱ ትርጉም አለው፣ ሟች የሆነው ሕይወታችን ትርጉም አለው፣ እንዲሁ በመጨረሻም በሕይወት መኖራችን ትርጉም አለው።

የመመለሱ ታላቅ ነብይ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ትንሳኤ ስላደረገው ሕያው ክርስቶስ የጊዜአችንን ገዢ ምስክርነት ሰጠ። “በህይወት አለ! እኛም በእግዚአብሔር ቀኝ አይተነዋልና።”14 በጆሴፍ እና ከእሱ በፊት በነበሩ ሐዋርያትና ነብያት እንዲሁም ከእሱ በኋላ በነበሩ ሐዋርያትና ነብያት ምስክርነት ላይ የራሴን ምስክርነት በትህትና አክላለው፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ ቃል የተገባው መሲህ ነው፣ የአብ የበኩር ልጅ ነው፣ እንዲሁም ከሞት የተነሳው የሰው ዘር ሁሉ አዳኝ ነው።

እንዲህ የሚለውንም አዋጅን እናረጋግጣለን “የዳግም መመለስ መልዕክትን በጸሎት የሚያጠኑ እና በእምነት የሚጸኑ ሰዎች ስለዚያ መለኮታዊነት እና አለምን ተስፋ ለተገባው ለጌታችን እና ለአዳኛችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ለማዘጋጀት ስላለው እቅድ የራሳቸውን ምስክርነት በማግኘት ይባረካሉ።”15 የክርስቶስ ትንሳኤ ቃል ኪዳኖቹን እርግጠኛ ያደርገዋል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።