የትንቢት መፈፀም
በኢየሱስ ክርስቶስ የወንጌል ሙሉነት መመለስ አማካኝነት እውን የሆኑት ትንቢቶች ብዙ ናቸው።
ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ የጆሴፍ ስሚዝን አብ እግዚአብሔርን እና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን ካለምንም ጥያቄ የተቀደሰ ደን ተብሎ በሚጠራበት ቦታ ያየበት የመጀመሪያ ራዕይ በምናከብርበት በዚህ ታሪካዊ የአጠቃላይ ስብሰባ ንግግር ለማቅረብ በመቻሌ ክብር ይሰማኛል። ያ ራዕይ የወንጌል መመለስ እና ከዛ በኋላ የተገለፁ ከመጽሐፈ ሞርሞን አንስቶ እስከ የክህነት ስልጣናት እና ቁልፎች መመለስ ድረስ፣ የጌታ ትክክለኛ ቤተክርስቲያን እና የእግዚአብሔር ቤተመቅደሶች መቋቋም፣ እንዲሁም በዚህ በኋለኛው ቀን ስራውን የሚመሩ ነብያት እና ሐዋርያት መጠራትን ያካተተ ታላቅ መጀመሪያ ነበር።
በመለኮታዊ ዕቅድ፣ የእግዚአብሔር የጥንት ነብያት፣ በመንፈስ ቅዱስ ሲመሩ፣ በቀናችን ስለሚመጣው ስለመጨረሻ ዘመን እና የጊዜ ሙሉነት መመለስ ተነበዩ። ይህም ስራ የጥንት ገላጮችን “ነፍሳት አነሳሳ”።1 ከዘመን ትውልዶች አንስቶ፣ ኢሳይያስ “ድንቅ ነገርን ተአምራትንም“2ብሎ ስለጠራው ስለእግዚአብሔር በምድር ላይ ስላለ ቤተመንግስት ተናገሩ፣ ህልም አዩ፣ ራዕይ አዩ እንዲሁም ተነበዩ።
በኢየሱስ ክርስቶስ የወንጌል ሙሉነት መመለስ አማካኝነት እውን የሆኑት ትንቢቶች የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ጨምሮ ብዙ ናቸው። ዛሬ፣ እንዲሁም፣ ከምወዳቸው መካከል የተወሰኑትን እጠቅሳለው። እነዚህን በውድ የህጻናት ክፍል አስተማሪዎች እና በመልአኳ እናቴ እግር ስር አማካኝነት ነው የተማርኩት።
በጌታ በኢየሱስ ክስቶስ እምነቱ እና በእግዚአብሔር መላዕክቶች አማካኝነት አንበሳዎችን የተከላከለው ዳንኤል፣ በራዕይ ስለቀናችን ካዩት መካከል አንዱ ነው። ለባቢሎናዊ ንጉስ ናቡከደነጾር ህልምን በመተርጎም ዳንኤል የጌታ ቤተክርስቲያን በመጨረሻው ቀናት “ካለምንም እጅ ከተራራ ላይ እንደተቆረጠ ትንሽ ድንጋይ”3እንደሚነሳ ተነበየ። “ካለምንም እጅ” ማለት በመለኮታዊ አመራር የጌታ ቤተክርስቲያን በስፋቱ መላ ምድርን እስከሚሞላ ድረስ “መቼም ላይወድም [ነገር ግን] ለዘላለም ሊቆም ይሰፋል”4ማለት ነው።
የዳንኤል ቃላት ዛሬ ከመላው ዓለም የቤተክርስቲያን አባሎች ይህንን ስብሰባ በሚመለከቱበት እና በሚሰሙበት ወቅት እውን እየሆኑ መሆናቸው ታላቅ ምስክር ነው።
ታታሪ ሐዋርያው ጴጥሮስ “ከዓለም ፍጥረት አንስቶ የሁሉም ነገር መመለሻ ጊዜ” ብሎ ገለፀው።5 ሐዋርያው ጳውሎስ በጊዜ ሙሉነት ወቅት እግዚአብሔር “ሁሉንም ነገር በክርስቶስ አንድ እድርጎ ይሰበስባል፣”6 “ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱ የመዓዘን ድንጋይ በመሆን” ብሎ ፃፈ።7 በሮም ጣልያን ቤተመቅደስ ቡራኬ በምሳተፍበት ጊዜ እነዛን ትንቢቶች በጠነከረ ሁኔታ ተሰሙኝ። ሁሉም ነብያት እና ሐዋርያት ልክ ጴጥሮስና ጳውሎስ እንዳደረጉት ስለዓለም አዳኝ ስለኢየሱስ ክርስቶስ እዛ እየመሰከሩ ነበር። ስለመመለስ፣ ወንድሞችና እህቶች ቤተክርቲያኗ በሕይወት ያለች ምስክር ናት እናም አባሎቻችን ደግሞ የእነዛ መለኮታዊ ትንቢቶች ምስክሮች ናቸው።
የግብፁ ዮሴፍ በኋለኛው ቀናት እንዲህ ይሆናል ብሎ ተነበየ፤ “ባለራዕይን ጌታ አምላኬ ያስነሳል፣ ለወገቤም ፍሬ የተመረጠ ባለራዕይ የሚሆን።”8 “የጌታን ስራ ይሰራልና።”9 ዮሴፍ ስሚዝ የዳግም መመለስ ነቢይ እሱ ገላጭ ነበር፡፡
ባለራዕዩ ዮሐንስ የመመለስን አስፈላጊ ነገሮች ስለሚያሰባስብ የሐያሉ መላዕክ እንዲህ ሲል ተነበየ፤ “በምድር ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፡፡”10 ሞሮኒ ያ መላዕክ ነበር፡፡ በመጽሐፈ ሞርሞን እንደተዘገበው የኛን ቀን ተመለከተ። በተደጋጋሚ መገለፆች ጆሴፍ ስሚዝን ለአገልግሎቱ የመጽሐፈ ሞርሞን ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት መተርጎም ጨምሮ አዘጋጀው።
ሌሎች ነብያትም ስለኛ ቀን ተንብየዋል። ሚልኪያስ ስለኤሊያስ “የአባቶችን ልብ ከልጆች ጋር፣ እናም የልጆችን ከአባቶች ጋር ስለሚተሳሰርበት” ሁኔታ ተናገረ።11 ኤሊያስ መጥቷል ስለሆነም ዛሬ 168 ቤተመቅደሶች ምድርን ከበው ይገኛሉ። እያንዳንዱ ቤተመቅደስ የተቀደሱ ቃኪዳኖችን በሚያደርጉ እና ለራሳቸውና በሞት ለተለዩ ዘሮቻቸው የስነስርዓት በረከቶችን የሚቀበሉ ብቁ የሆኑ አባሎችን ያገለግላል። ይህ በሚልኪያስ የተገለፀው ቅዱስ ስራ “ለፈጣሪው ለልጆቹ የዘላለማዊ መድረሻ ዕቅድ መካከላዊ ቦታ ነው።”12
በዛ በተተነበየበት ጊዜ ውስጥ ነው የምንኖረው፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ጊዜ የምናሰተናግድ ሰዎች ነን፤ እውነታዎችን፣ ቃል ኪዳኖችን፣ እና የዘላለማዊ ወንጌልን ቃል ኪዳኖች የሚሰሙትን እና የሚቀበሉትን የእግዚአብሔርን ልጆች ለመሰብሰብ ሃላፊነት አለብን። ፕሬዝዳንት ኔልሰን “በአለም ውስጥ ዛሬ ከሚገኙትታላቁ ፈተና፣ ታላቁ ምክንያት፣ እናም ታላቁ ስራ ነው” ብለው ይጠሩታል።13 ሰለዛ ተዓምር ምስክርነቴን እሰጣለው።
በዚህ ዓመት የካቲት ውስጥ በፕሬዛዳንት ረስል ኤም ኔልሰን በመሰየም የደርባን ደቡብ አፍሪካ ቤተመቅደስን ቡራኬ ሰጠሁኝ። በሕይወቴ ሙሉ የማስታውሰው ቀን ነበር። ከብዙ ጊዜ በፊት ኤርሚያስ “ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን”14ብሎ እንደተነበየው ወደ ወንጌል ከመጡ አባሎች ጋር ነበርኩኝ። የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት በመላ ዓለም ዙሪያ እንደ እግዚአብሔር ወንድና ሴት ልጆች፣ በወንጌል ውስጥ ወንድም እና እህቶች ሁላችንንም አንድ ያደርገናል። ምንም እንምሰል ምንም እንልበስ በሰማይ አባት ከመጀመሪያ ጀምሮ እስካሁን ቅዱስ የሆነ የቤተመቅደስ ቃልኪዳኖችን በመግባትና በመጠበቅ በቤተሰቦቹ በመቀላቀል ዕቅድ ውስጥ ሁላችንም አንድ ህዝብ ነን።
በ1834 (እ.አ.አ) በኪርትላንድ ኦሃዮ ትምህርት ቤት ውስጥ በአነስተኛ ለተሰበሰቡ የክህነት ተሸካዎች ዮሴፍ ስሚዝ እንዲህ ሲል ተነበየ “ዛሬ ምሽት የምትመለከቱት ትንሽ እጅ የሚሆኑ ክህነቶችን ብቻ ነው፣ ነገር ግን ይህች ቤተክርስቲያን ሰሜንና ደቡብ አሜሪካን ትሞላለች—ዓለምን ትሞላለች።”15
በቅርብ ዓመታት ውስጥ በዓለም ዙሪያ ከቤተክስቲያን አባሎች ጋር ለመገናኘት ተጉዣለው። በአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ሸንጎ ውስጥ ያሉ ወንድሞቼ ተመሳሳይ ሃላፊነት ነበራቸው። እስካሁን ከውድ ነብያችን ከፕሬዝዳንት ኔልሰን እንደ የቤተክርስቲያን ፕሬዘዳንትነት ስለሕያው ክርስቶስ ለመመስከር በሁለት ዓመት ቆይታው ውስጥ “32 ሃገራት እና ከዩኤስ ድንበሮች”16 ቅዱሳን ጋር እንዲገናኝ ከወሰደው የጊዜ ሰሌዳ ጋር ማን ይወዳደራል።
ወጣት ሆኜ የሚስዮን ጥሪ ስቀበል አስታውሳለው። ልክ እንደ አባቴ፣ ወንድሜ እና የእህቴ ባል በጀርመን ለማገልገል ፈለኩኝ። ማንም ሰው ወደቤት እስኪደርሱ ሳልጠብቅ ወደ ፖስታ ሳጥኑ በመሮጥ ጥሪዬን ከፈትኩኝ። በኒው ዮርክ ከተማ ዋና ጽፈት ቤቱ በሆነው ወደ ምስራቃዊ ግዛቶች ሚስዮን እንደተጠራው አነበብኩኝ። አዝኜ ስለነበር ወደ ቤት ገብቼ ለመፅናናት መጽሐፍ ቅዱሶቼን ከፈትኩኝ። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ እንዲህ የሚል አነበብኩኝ፤ “እነሆ፣ እናም አስተውሉ፣ በዚህ ስፍራ፣ በዚህ ክፍለ ሀገር አካባቢ ብዙ ህዝብ አሉኝ፤ እና ውጤታማ በር በዚህ አካባቢ፣ በዚህ በምስራቅ ምድር ውስጥ ይከፈታል።”17 በ1833 (እ.አ.አ) ለነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠው ያ ትንቢት ለእኔ ራዕይ ነበር። ጌታ እንዳገለግል ወደፈለገው ትክክለኛው ሚስዮን እንደተጠራው በዛን ጊዜ አወቅኩኝ። ስለ ታላቁ ተሃድሶ እና የሰማይ አባት ለጆሴፍ ስሚዝ “ይህ የምወደው ልጄ ነው ብሎ ስለተናገረው በማስተማር ሁለት ታላቅ ዓመታትን አሳለፍኩ። አድምጠው!”18
ለመላው ቤተክርስቲያን ታላቅ አስፈላጊነት ያለው ኢየሱስ ከርስቶስ ከመወለዱ ከ700 ዓመታት በፊት እንዲህ የሚለው የኢሳያስ ትንቢት ነው፤ “በዘመኑ ፍፃሜ የእግዚአብሔር ቤት በተራሮች ላይ ጸንቶ ይቆማል፣ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፣ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ።”19
ዛሬ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አባሎችና ጓደኞች የእነዚህን ስብሰባ መተላለፍ በኤሌክትሮኒክስ ቴሌቪዥን፣ ኢንተርኔት ዎይም በሌላ መንገድ ሲከታተሉ በአዕምሮዬ ውስጥ እስላለው። “በተራራዎች አናት ላይ” በጋራ እንደተቀመጥን አይነት ነው ያለነው።20 “ይህ ትክክለኛው ቦታ ነው” የሚሉትን የትንቢት ቃላት ብሪገም ያንግ ነበር የተናገሩት።21 “የምድርን ሃገራት በሚያስተዳድረው ፍቃድ እና ደስታ አማካኝነት”22ቅዱሳኖች የኔንም የመስራች ዘሮቼንም ጨምሮ በድንጋያማ ተራሮች ውስጥ ፂኦንን ለመገንባት ሰሩ።
ዛሬ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጎብኚዎችን በሳበ በቅዱስ ስፍራ ቆሜ እገኛለው። በ2002 (እ.አ.አ) የሶልት ሌክ ከተማ የክረምት ኦለምፒክ ቸጨዋታዎችን አስተናገደች። በስነስርዓቱ መክፈቻ ለይ የታበርናክል መዘምራን ዘመሩ እናም ከብዙ ሃገራት ለተውጣጡ እነግዶችና ተሳታፊዎች ቤተክስቲያኗ ኮንሰርቶችን እና ፕሮገራሞችን አበረከተች። በመላ ዓለም ለሚሰራጨው በምሽት ዜና የቲቪ ፕሮገራም ገፅ ላይ ቤተመቅደስን ማየቴን ሁሌም አስታውሳለው።
ለብዙ ዓመታት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንቶች፣ የብዙ ሃገራት ንጉሶች፣ ዳኛዎች፣ ጠቅላይ ሚንስትሮች፣ አምባሳደሮች እና ባለስልጣኖች ወደ ሶልት ሌክ ከተማ በመምጣት ከመሪዎቻችን ጋር ተገናኝተዋል። ፕሬዝዳንት ኔልሰን የቀለም ሰዎች ብልፅግና ሃገራዊ ስብሰባን፣ እንዲሁም በቀለም ላይ የማይወሰን የእኩልነት መብት ላይ በሚያተኩረው የዩናይትድ ስቴትስ ድርጅት መሪዎችን ተቀበለው አስተናገዱ። ፕሬዝዳንት ኔልሰን ለታላቅ መቻቻል እና በዓለም የዘር ስምምነት ሲጠሩ ከእነዚህ ጓዶች እና መሪዎች ጋር ትከሻ ለትከሻ አብሬአቸው መቆሜን አስታውሳለው።23
ብዙ ሰዎች ወደ ቤተመቅደስ አደባባይ መጥተው ከቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር ተማክረዋል። ለምሳሌ፣ በዚህ ባለፈው ሳምንት የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል ለመጀመሪያ ጊዜ ከኒው ዮርክ ከተማ ውጪ የተባበሩት መንግስታት 68ኛው የሲቪል ማህበር ጉባኤን፣ ዓለማዊ ስብሰባን ተቀብለን አስተናግደናል። ከቬትናም የሐይማኖት ግንኙነት ሃላፊ ጋር፣ ከኩባ፣ ፊሊፒንስ፣ አርጀንቲና፣ ሮማኒያ፣ ሱዳን፣ ኳታር እና ሳውዲ አረቢያ አምባሳደሮች ጋር ተገናኝተናል። የእስልምና የዓለም ቡድን ጠቃላይ ፀሐፊን እንዲሁ ተቀብለን አስተናግደናል።
እየገለፅኩኝ ያለሁት በዚህ በኋለኛው ቀናት ሃገራት “ወደ ጌታ ቤት ተራራ”24ይፈሳሉ የሚለውን የኢሳይያስ ትንቢት መሟላትን ነው። ታላቁ የሶል ሌክ ቤተመቅደስ በዛ ግዙፍነትና ክብር ባለው መካከል ላይ ቆሟል።
ምንም እንኳን ቦታዎቻችን ታላቅ ቢሆኑም መንፈስን፣ መልካምነትን እና የኋላኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንና የሰዎቹ ቸርነትን የሚታዩበት የኛ እግዚአብሔር እንደሚወደው መውደድ እና ለከፍተኛ ሃላፊነት ታታሪ መሆናችን ጆሴፍ ስሚዝ “የክርስቶስ መንስኤ”25ብሎ በጠራው የንፁህ ሐይማኖት እውነታ ነው ሰዎችን የሳበው እንጂ የመሬት አቀማመጡ አይደለም።
አዳኙ መቼ እንደሚመለስ አናውቅም፣ ነገር ግን እንደሚመለስ እናውቃለን። እርሱን ለመቀበል ብቁ ለመሆን እና ከብዙ ጊዜ በፊት ስለተተነበየው ነገር ኩሩ አባል ለመሆን በልባችንና በአዕምሮአችን መዘጋጀት አለብን።
ፕሬዝዳንት ረስል ኤም ኔልሰን በምድር ላይ የጌታ ነብይ እንደሆኑ እንዲሁም ከጎናቸው እንደ ነብያቶች፣ ገላጮች እና እንደ ባለ ራእይ የተሸሙ በእግዚአብሔር የተጠሩ ሐዋርያት እንዳሉ እመሰክራለው። እናም ውድ ወንድመቼ እና እህቶቼ መመለሱ ይቀጥላል።
ቃላቱ እውን እንደሆኑ በምመሰክረው በነብዩ ዮሴፍ ስሚዝ ትንቢት እዘጋለው፤ “የእውነት ሰንደቅ አላማ ተተክላለች፤ ያልተቀደሰ ማንም እጅ የስራውን እድገት ማቆም አይችልም፤ ስደትም ቢብስ፣ ወንበዴዎች ቢተባበሩ፣ የጦር ሰራዊቶች ቢሰበሰቡ፣ ሀሜተኞች ስም ቢያጠፉ፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር እውነት በድፍረት፣ በግርማ፣ በገለልተኝነት፣ በሁሉም አህጉራት ዘልቆ እስኪገባ፣ ሁሉንም ድንበር እስኪጎበኝ፣ ሁሉንም አገራት እስኪጠርግ፣ እናም እያንዳንዷ ጆሮ እስክትሰማ፣ የእግዚአብሔርም ዓላማ እስኪሳካ እናም ታላቁ ያህዌ ሥራው ተጠናቋል እስኪል ድረስ ይጓዛል።”26 የዮሴፍ ስሚዝ እነዚህ ምስክርነቶች እየተከናወኑ እንዳሉ እመሰክራለው።
የውድ ነብያችንን የፕሬዝዳንት ረስል ኤም ኔልሰን፣ የሐዋርያትን እና የሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎችን የተነሳሱ ምክሮችን ስትከተሉ እንዲሁም ስለቀናችን የተነበዩትን የጥንት ነብያትን ስትሰሙ በጥልቅ ልባችሁና ነፍሳችሁ በመንፈስና በመመለስ ስራ እንደምትሞሉ ቃል እገባው። የእግዚአብሔርን እጆች በሕይወታችሁ ውስጥ እንደምታዩ፣ መነሳሳቱን እደምትሰሙ፣ እንዲሁም ፍቅሩን እንደሚሰማችሁ ቃል እገባላችዋለሁ። አቻ የሌለውን ፍቅር ለማሳየት ስለወንጌሉ እና ቤተክርስቲያኑ መመለስ ክብር አቀርባለው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።