የመልከጸዲቅ ክህነት እና ቁልፎቹ
በቤተክርስቲያን ውስጥ የክህነት ስልጣን ስራ ላይ የሚውለው የዚያ ክህነት ስልጣን ቁልፍ ባለ የክህነት መሪ ምሪት ነው።
ወጣት ሴቶችን፣ ወጣት ወንዶችን እንዲሁም ሴቶችን እንዴት እንደሚባርክ ስላስተማሩን በሶስት ተናጋሪዎች ቀድሞ ስለተነገረው ስለ እግዚአብሔር ክህነት የበለጠ ለመናገር መርጫለሁ።
ክህነት ለእግዚአብሔር ስራ እንዲውል የእርሱም ልጆች እንዲጠቀሙበት በእምነት የሚያዝ የመለኮታዊ ኃይል እና ስልጣን ነው። ክህነት ማለት ወደ ክህነት ክፍል የተጠሩት ሰዎች ወይም ስልጣኑን የሚለማመዱት ሰዎች ማለት አይደለም። ክህነትን የሚሸከሙ ሰዎች ክህነት አይደሉም። የተሾሙትን ሰዎች ክህነት ብለን መጥራት ተገቢ ሳይሆን የክህነት ተሸካሚዎች ብለን መጥራት ግን ተገቢ ነው።
የክህነት ኃይል በቤተክርስቲያኑ ውስጥ እንዲሁም በቤተሰብ ውስጥም ይገኛል። ነገር ግን የክህነት ኃይል እና የክህነት ስልጣን በቤተክርስቲያን እና በቤተሰብ ውስጥ በተለየ መንገድ ተግባራዊ ይሆናል። ይህ የሚሆነው ጌታ በመሰረተው መርሆች አማካኝነት ነው። የእግዚአብሔር ዕቅድ አላማ ልጆቹን ወደ ዘላለም ሕይወት መምራት ነው። ሟች የሆኑ ቤተሰቦች ለዕቅዱ አስፈላጊ ናቸው። ቤተክርስቲያኗ የቤተሰብ ግንኙነቶችን ወደ ዘላለማዊነት እንዲሸጋገሩ ለማዘጋጀት አስፈላጊ የሆነውን ትምህርት፣ ስልጣን እና ስነስርዓቶች ለማቅረብ ትገኛለች። ስለሆነም ቤተሰብ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ጥንዳዊ የሆነ የማነቃቂያ ግንኙነት አላቸው። የወንጌል ሙሉነት እና ሥነ-ስዓቶች ማለትም ጥምቀት፣ ማረጋገጫ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ መቀበል፣ የቤተመቅደስ ቡራኬ እና የዘላለማዊ ጋብቻ የመሳሰሉት የክህነት በረከቶች ለወንዶች እና ለሴቶች በጋራ ይገኛል።1
እዚህ የምንናገረው ክህነት በወንጌል መመለስ መጀመሪያ ላይ የተመለሰው የመልከ ጸዴክ ክህነት ነው። ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ኳድሪ “የመንግስቱን እና የዘመኑን የጊዜ ሙሉነት ቁልፎች እንደተሸከሙ” ባወጁት በጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ተሾሙ (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 128፥20)። እነዚህ ቀዳማዊ ሐዋርያቶች ያንን ስልጣn ከአዳኙ ከራሱ ተቀብለዋል። በክህነት ውስጥ ሁሉም ሌላ ባስልጣናት ወይም ክፍሎች ለመልከጸዴቅ ክህነት ጥገኞች ናቸው ( ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 107፥5ተመልከቱ)፣ “ምክንያቱም የምሪትን ትክክለኛ መብት ይይዛል እንዲሁም በቤተክርስቲያን ውስጥ በሁሉም እድሜ በሚገኙ የዓለም ዙሪያ የክህነት ክፍሎች ኃይል እና ስልጣን አለው” (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 107፥8)።
በቤተክርስቲያን ውስጥ የታላቁ ክህነት ማለትም የመልከጸዲቅ ክህነት ስልጣን እና የአነስተኛው ወይም የአሮናዊ ክህነት ስልጣን ቁልፎቹን በተሸከመው በኤጲስ ቆጶስ ወይም በፕሬዝዳንት ምሪት ስር ነው የሚተገበረው። በቤተክርስቲያን ውስጥ የክህነት ስልጣን ልምምድን ለመረዳት መጀመሪያ የክህነት ቁልፎችን መርህ መረዳት ይኖርብናል።
የመንግስቱ የመልከጸዲቅ ክህነት ቁልፎች በጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ተሰጠ፣ ነገር ግን ይህ የክህነት ቁልፎችን መመለስ አላሟላም ነበር። የተወሰኑ የክህነት ቁልፎች በኋላ መጡ። የዚህ ዘመን የመጀመሪያውን በኪርትላንድ ኦሃዮ የሚገኘውን የቤተመቅደስ ቡራኬ ተከትሎ፣ ሶስት ነብያት ማለትም ሙሴ፣ ኤሊያስ እና ኤልያስ፣ ፕሬዘደንት አይሪንግ በጣም አሳማኝ በሆነ መንገድ እንደገለፁት “የዚህን ዘመን ቁልፎች” እንዲሁም እስራኤልን የመሰብሰብ እና የጌታ ቤተመቅደስ ስራ ቁልፎችን ጨምሮ መለሱ ( ትምህርት እና ቃልኪዳኖች፣ 110ተመልከቱ)።
በጣም የተለመደው የቁልፎች ተግባር ምሳሌ በክህነት ሥነ-ስርዓቶች አገልግሎት ውስጥ ነው። ሥነ-ስርዓት ማለት ቃል የመግባት እና በምላሹ በረከቶችን የመሰጠትን የሚጠቁም ተግባር ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሉም ሥነ-ስርዓቶች የሚከናወኑት ቁልፎችን በተሸከመው በክህነት መሪ አመራር ስር ነው።
ሥነ-ስርዓት ብዙውን ጊዜ የሚመራው የክህነት ቁልፎችን በያዘው ሰው ምሪት በክህነት ክፍል ውስጥ በተሾመ ግለሰብ ነው። ለምሳሌ የተለያዩ የአሮናዊ የክህነት ስልጣን ክፍሎች ተሸካሚ በቅዱስ ቁርባን ሥነ-ስርዓት ላይ የአሮናዊ ክህነት ቁልፎችን በተሸከመው በኤጲስ ቆጶሱ አመራር ስር ይመራል። በቤተመቅደስ ውስጥ ሴቶች በሚሰሩት የክህነት ሥነ-ስርዓቶች ተመሳሳይ መርህ ተግባራዊ ይሆናል። ምንም እንኳን ሴቶች ክህነትን ባይሸከሙም የቤመቅደስ ሥነ-ስርዓቶችን ቁልፎች በተሸከመ በቤተመቅደስ ፕሬዝዳንት አመራር ስር ቅዱስ የቤተመቅደስ ሥነ-ስርዓቶችን ያከናውናሉ።
ቁልፎችን በያዘው ምሪት ስር የሚከናወነው ሌላኛው የክህነት ስልጣን ምሳሌ በአጥቢያቸው ክፍሎች ውስጥ ወይም በሚስዮን ቦታ ወንጌልን እንዲያስተምሩ የተጠሩትን ወንዶች እና ሴቶች ማስተማር ነው። ሌላ ምሳሌዎች በአጥቢያ ውስጥ የመሪነትን ቦታ ይዘው በጥሪያቸው መሰረት በአጥቢያ ወይም በካስማ ውስጥ ቁልፎቹን በተሸከመ በክህነት መሪው አመራር ስር የክህነት ስልጣንን የሚለማመዱ ሰዎችን ይመለከታል። እንደዚህ ነው የክህነት ስልጣን እና ኃይል በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚተገበረው እንዲሁም የሚጣጣመው።2
የክህነት ስልጣን የሚለማመደው እና በረከቱ የሚገነዘበው በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተሰቦች ውስጥ ነው። ቤተሰብ ስል የተጋቡ የክህነት ተሸካሚ ወንድ እና ሴት እና ልጆች ማለቴ ነው። በሞት ወይም በፍቺ አማካኝነት የሚከሰቱ ልዩነቶችን እጨምራለው።
የክህነት ስልጣንን መለማመድ የሚቻለው ቁልፎችን በያዘው ግለሰብ ፍቃድ ብቻ መሆን አለበት የሚለው መርህ በቤተክርስቲያው ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው ነገር ግን ይህ መርህ በቤተሰብ ውስጥ ተግባራዊ አይሆንም። ለምሳሌ፣ አባት በተሸከመው የክህነት ስልጣንን ለቤተሰቡ ይመራል እንዲሁም ይተገብራል። ለቤተሰቡ የተለያዩ ድርጊቶችን ለመተግበር የክህነት ቁልፎችን ከያዘው ሰው አቅጣጫን ወይም ፍቃድን የመከተል ግዴታ የለበትም። እነዚህ የቤተሰቡን አባሎች ማማከርን፣ የቤተሰብ ስብሰባ ማድረግን፣ ለባለቤቱ እና ለልጆቹ የክህነት በረከቶችን መስጠትን ወይም ለቤተሰብ አባሎች ወይም ለሌሎች የፈውስ በረከቶችን መስጠትን ያካትታሉ።3 የቤተክርስቲያን ባለስላጣናት የቤተሰብ አባሎችን ያስተምራሉ፣ ነገር ግን ክህነትን ስልጣንን እንዴት በቤተሰባቸው ውስጥ መለማመድ እንዳለባቸው አያስተምሩም።
አባት በማይኖርበት ወቅት እናት የቤተሰብ መሪ የመሆን ተመሳሳይ መርህ ተግባራዊ ይሆናል። ከቤተመቅደስ በተቀበለችው ቡራኬ እና እትመት አማካኝነት በቤቷ ውስጥ ትመራለች እናም የክህነትን ኃይል እና በረከቶች ወደ ቤቷ ውስጥ ለማምጣት ሚና ትጫወታለች። በክህነት ውስጥ በሆነ ክፍል ሃላፊነት በተሰጠው ሰው ብቻ የሚሰጠው የክህነት ስልጣን በረከቶችን ለመስጠት ስልጣን ባይሰጣትም ሌሎች የቤተሰብ ምሪቶችን መተግበር ትችላለች። ይህን በማድረግ በቤተሰቧ ውስጥ ለምትመራቸው ልጆቿ ጥቅም ሲባል የክህነትን ኃይል ትለማመዳለች።4
አባቶች ክህነታቸውን በቤታቸው ውስጥ የሚያጎሉ ከሆነ፣ ከሚያደርጉት ማንኛውም ነገር ጎን ለጎን የቤተክርስቲያኗ ተልዕኮ ያሳድጋል። የመልከጸዲቅ ክህትን የተሸከሙ አባቶች ስልጣናቸውን “በአሳማኝነት፣ በታጋሽነት፣ በየዋህነት እና በትህትና እንዲሁም በእውነተኛ ፍቅር” መለማመድ አለባቸው (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 121፥41)። የሁሉንም ክህነት ስልጣን የመለማመድ ያህ ከፍተኛ መስፈርት ለቤተሰብ በጣም አስፈላጊ ነው። የክህነት ተሸካሚዎች ለቤተሰብ አባላቸው በረከቶችን ለመስጠት የክህነት ኃይል እንዲኖራቸው ትዕዛዛትን መጠበቅ አለባቸው። የቤተሰብ አባል በረከት ለማግኘት ለመጠየቅ እንዲፈልጉ የሚወደድ የቤተሰብ ግንኙነቶች እንዲኖር መኮትኮት አለባቸው። ወላጆች በቤት ውስጥ የበለጠ የክህነት በረከቶች እንዲኖር ማበረታታት አለባቸው።5
በእነዚህ የጉባኤ ስብሰባዎች ውስጥ፣ ከአስከፊው ወረርሽኝ የምድራዊ ስጋታችን አጭር መጠለያ ስንፈልግ፣ የዘለአለም መሰረታዊ መርሆችን ተምረዋል። እያንዳንዳችን እነዚህን የዘላለማዊነት እውነታዎች ለመቀበል ሰውነታችን “በብርሃን እንዲሞላ” አይናችንን “ማተኮር” እንዳለብን አበረታታለሁ።(3 ኔፊ 13፥22)።
በመጽሐፍ ቅዱስ እና በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ እንደተፃፈው ለብዙሃኖች በሰጠው ትምህርቱ አዳኙ ሟች የሆነው ሰውነት በብርሃን ወይም በጨለማ ሊሞላ እንደሚችል አስተማረ። እኛ በእርግጥ በብርሃን መሞላት አለብን እናም አዳኛችን እንዴት ይህን ማድረግ እንደምንችል አስተምሮናል። ስለ ዘላለማዊነት እውነታዎች መልዕክቶችን መስማት አለብን። ብርሃንን ወደ ሰውነታችን በምናስገባበት የአይናችንን ምሳሌ ተጠቀመ። አይናችን የሚያተኩር ከሆነ በሌላ አባባል ብርሃንን እና መረዳትን መቀበል ላይ ካተኮርን መላ ሰውነታችን ብርሃን ይሆናል” ብሎ ገለፀ (ማቲዎስ 6፥22፤ 3 ኔፊ 13፥22)። ነገር ግን አይናችን ክፉ ከሆነ ማለትም ክፋትን ካሻን እና ወደ ሰውነታችን ከወሰድነው፣ “መላ ሰውነታችሁ ጨለማ ይሆና” ብሎ አስጠነቀቀ (ቁጥር 23)። በሌላ ቋንቋ፣ በሰውነታችን ውስጥ ያለው ብርሃን ወይም ጨለማ የተማርነውን የዘላለማዊ እውነታዎችን እንዴት ማየት ወይም መቀበል እንደምንችል ላይ ይመረኮዛል።
የዘላለማዊነትን እውነታዎች ለመረዳት ለመሻት እና ለመጠየቅ የአዳኙን ምሳሌ መከተል ይኖርብናል፡፡ የሰማይ አባታችን የሚሹትን እውነታ ለእያንዳንዱ ሊያስተምር ፍቃደኛ እንደሆነ ቃል ይገባል ( 3 ኔፊ14፥8ተመልከቱ)። ይህን ካሻን እና ለመቀበል የሚያተኩር አይን ካለን የዘላለም እውነታዎች “እንደሚከፈቱልን” አዳኙ ቃል ይገባል ( 3 ኔፊ 14፥7–8፣ ተመልከቱ)።
በተቃራኒ ሰይጣን አስተሳሰባችንን ግራ ሊያጋባን ወይም አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ ለምሳሌ በእግዚአብሔር ክህነት አገልግሎት ላይ መንገድ ሊያስተን ይጓጓል። አዳኙ እንዲህ ብሎ አስጠነቀቀ፤ “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፣ ነገር ግን ውስጣቸው ነጣቂ ተኩላ ከሆኑ ከሀሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።” (3 ኔፊ 14፥15) ግራ ከሚያጋቡን ከተለያዩ ትምህርቶች ውስጥ እውነትን ለመምረጥ ሊረዳን ይህንን መሞከሪያ ሰጠን፤ “በፍሬዎቻቸው ታውቋቸዋላችሁ፣” ብሎ አስተማረ (3 ኔፊ 14፥16)። “መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፣ ወይንም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬን ማፍራት አይቻለውም” (ቁጥር 18)። ስለሆነም ስለተስተማሩት መርሆች እና ስላስተማሯቸው ሰዎች ውጤቶችን መመልከት አለብን ይህም ውጤት ፍሬዎቻቸው ናቸው። በቤተክርስቲያኗ ላይ ለምንሰማው ለብዙ ተቃውሞዎች ጥሩ ምላሽ ነው እንዲሁም ትምህርቶች እና ህግጋቶች እንዲሁም አመራር ነው። አዳኙ ያስተማረውን ፈተና ተከተሉ። ውጤቱ ወደሆነው ወደ ፍሬዎቹ ተመልከቱ።
ስለ ወንጌል ፍሬዎች እና ስለ ተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ስናስብ፣ በአባሎቿ የሕይወት ዘመን ውስጥ በምስራቃዊ ክፍል በሚገኘው ከሃገር ውስጥ ስብሰባ አንስቶ እስከ ከዩናይትድ ስቴትስ ውጪ በሚኖሩ የ16 ሚሊዮን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በሚገኙበት አባሎች ድረስ ቤተክርስቲያኗ እንዴት እንዳደገች ስንመለከት እንደሰታለን። በእዚያ እድገት፣ ቤተክርስቲያኗ አባላቱን ለማገዝ ያላት አቅም እንደጨመረ ይሰማናል። ትእዛዛቱን በመጠበቅ፣ በዳግም የተመለሰውን ወንጌል ለመስበክ፣ እስራኤልን ለመሰብሰብ እና ቤተመቅደሶችን በመገንባት ሀላፊነቶችን በመጠበቅ ረገድ እንረዳለን።
በሁለት ዓመት ውስጥ የተሰማንን እድገት ለማሳካት ጌታ አመራራቸውን በተጠቀመባቸው በነብዩ ፕሬዘደንት ረስል ኤም. ኔልሰን እየተመራን ነው። በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ በዳግም በተመለሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እድገታችንን እንዴት ማሻሻል እንደምንችል ከሚያስተምሩን ፕሬዘደንት ኔልሰን አሁን በመስማት እንባረካለን።
የእነዚህን ነገሮች እውነታ እመሰክራለው እንዲሁም ቀጥሎ ከምንሰማው ለነብያችን ጸሎት ለማድረግ ከእናንተ ጋር እቀላቀላለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።