አጠቃላይ ጉባኤ
የሃዋርያት እና የግል ቀጣይ የመገለጥ በረከቶች ህይወታችንን ለመምራት
የሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ።


2:3

የሃዋርያት እና የግል ቀጣይ የመገለጥ በረከቶች ህይወታችንን ለመምራት

ቀጣይነት ያለው ራዕይ ተቀብለናል እናም ጌታ ባዘጋጀው መንገድ እየተቀበልን ነው።

ዛሬ የሃዋርያት እና የግል ቀጣይ የመገለጥ በረከቶች ህይወታችንን ስለመምራት ንግግር አደርጋለሁ፡፡

አንዳንድ ጊዜ የጌታን አላማዎች ሳናውቅ እንኳን መገለጥ እንቀበላለን፡፡ በሰኔ 1994 (እ አ አ) ሸማግሌ ጀፈሪ አር.ሆላንድ ሃዋርያ ሆነው ከመጠራታቸው ትንሽ ቀደም ብሎ ሃዋርያ ሆነው እንደሚጠሩ አንድ ትንሽ ቆንጆ የመገለጥ ተሞክሮ ተቀብዬ ነብር፡፡ የክልል ተወካይ ነበርኩኝ እናም ያ እውቀት እንዲሰጠኝ ምንም ምክንያት አይታየኝም፡፡ በእንግሊዝ በ1960ዎቹ መጀመሪያ ወጣት ሚስዮናውያን ሳለን ጓደኛሞች ነበርን እናም ለሳቸው ጥልቅ ፍቅር ነበረኝ፡፡ ይህንን ተሞክሮው ለእኔ እንደ የደግነት ርህራሄ አየሁት፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ ወጣት ሚስዮናዊ በነበርንበት ጊዜ ተከታይ ሚስዮናዊ ባልደረባዬ ለነበረው ለሚያስደንቀው ሚስዮናዊ ጓደኛዬ ጌታ በአስራ ሁለቱ ውስጥ የሱ ተከታይ ሃዋርያ እንድሆን እያዘጋጀኝ እንደሆነ ተደንቄአለሁ፡፡1 አንዳንድ ጊዜ ወጣት ሚስዮናውያን ለታናሽ ሚስዮናዊ ጓደኛቸው ደግ እንዲሆኑ አስጠነቅቃለሁ፤ ምክንያቱም መቼ የበላይ ጓደኛቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ስለማያውቁ፡፡

ይህች የተመለሰች ቤተክርስቲያን በአዳኛችን በኢየሱስ ከርስቶስ እንደምትመራ ጠንካራ ምስክርነት አለኝ፡፡ ማንን ሃዋርያ አድርጎ እንደሚጠራ እና በምን ቅደም ተከተል እንደሚጠራ ያውቃል፡፡ የበላይ ሃዋርያውን ነቢይ እና ቤተክርስቲያኗ ፕሬዘዳንት እንዲሆን እንዴት እንደሚያዘጋጀውም ያውቃል ።

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በሙላት መመለስን አስመልክቶ የተወደዱት ነብያችን ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ዛሬ ጠዋት ለአለም ባቀረቡት ታላቅ የሁለት መቶኛ አመት አዋጅ ተባርከናል።2 ይህ በፕሬዚዳንት ኔልሰን የቀረበው አቅጣጫ ሰጪ መግለጫ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መነሻ፣ ህልውና እና የወደፊት አቅጣጫ ተከታታይ የመገለጥ መርህ መሆኑን ግልፅ አድርጓል። ይህ አዲስ አዋጅ አፍቃሪ አባት ከልጆቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ይወክላል፡፡

ቀደም ባለው ጊዜ ፕሬዘዳንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል እኔ ዛሬ ያሉኝን ስሜቶች ገልጸዋል፡፡ እንዲህ ብለዋል፤ “አመስጋኝ ልንሆንባቸው ከሚገቡን ከሁሉም ነገሮች በላይ ዳግም የተመለሰችው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ መሆኗ እና ቤተክርስቲያኗም በራዕይ አለት ላይ የተመሰረተች መሆኗ ነው።“ ቀጣይነት ያለው ራዕይ በእርግጥ የህያው ጌታ እና አዳኝ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የደም ስር ነው።”3

ነቢዩ ሄኖክ አሁን የምንኖርበትን ቀናት አስቀድሞ አይቶታል፡፡ ስለሚንሰራፋው ታላቅ ክፋት እና ስለተተነበየው “ታላቅ መከራ“ ጌታ ለሄኖክ አረጋግጦለታል፡፡ ሆኖም ጌታ “ነገር ግን ሕዝቤን አተርፋቸዋለሁ“ ሲል ቃል ገባ፡፡4 “እና ፅድቅን ከሰማያት እሰዳለሁ፤ እና ስለ አንድያ ልጄ፣ ከሙታን ትንሳኤውን፣ አዎን፣ እና ስለሁሉም ሰዎች ከሞት ስለመነሳት እንዲመሰክርም እውነትን ከምድር እልካለሁ።”5

ፕሬዘደንት ዕዝራ ታፍት ቤንሰን የሃይማኖታችን ቁልፍ የሆነው መጽሐፈ ሞርሞን ጌታ ለሄኖክ በተናገረው ቃል መሠረት ከምድር እንደወጣ በታላቅ ሃይል አስተምረዋል፡፡ አባት እና ልጁ እና መላእክት እና ነቢያት ለጆሴፍ ስሚዝ የተገለጡለት “በሰማያት በመመራት አስፈላጊ የመንግስት ሃይላትን ዳግም ለመመለስ ነበር፡፡“6

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በተከታታይ ራዕይ ተቀበለ። አንዳንዶቹ በዚህ ጉባኤ እየቀረቡ ነው። ብዙ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተቀበላቸው ራእዮች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ተጠብቀዋል። ሁሉም የቤተክርስቲያኗ መደበኛ ስራዎች ጌታ በዚህ የመጨረሻ ዘመን ለእኛ ያለውን ሃሳብ እና ፍላጎት ይይዛሉ፡፡7

ከእነዚህ ታላላቅ የመሠረታዊ ቅዱሳን ጽሁፎች በተጨማሪ ለሕያው ነቢያት በሚሰጥ ቀጣይ መገለጥ ተባርከናል ፡፡ ነቢያት “እርሱን ወክለው እንዲናገሩ ስልጣን የተሰጣችው የጌታ ወኪሎች” ናቸው።8

አንዳንድ መገለጦች ታሪካዊ ጠቀሜታ አላቸው፤ እንደዚሁም ሌሎቹ ደግሞ ስለ አስፈላጊ መለኮታዊ እውነቶች ያለንን ግንዛቤ ያሳድጋሉ እንዲሁም ለዘመናችን መመሪያ ይሰጣሉ።9

ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል በሰኔ 8፣ 1978 (እ.አ.አ) ክህነትን እና የቤተመቅደስ በረከቶችን ለሁሉም ብቁ የቤተክርስቲያን ወንድ አባላት ሁሉ ስለመስጠት ለተቀበሉት ራዕይ ከሚገመተው በላይ አመስጋኞች ነን።10

ያንን ውድ መገለጥ በተቀበሉበት ጊዜ ከነበሩ እና ከተሳተፉ ከአስራ ሁለቱ ከብዙዎቹ ጋር አገልግያለሁ። ፕሬዘዳንት ኪምባል እና እነርሱ እያንዳንዳቸው በግል ውይይቶች ውስጥ ስላገኙት ተሞክሮ ሀይለኛ እና አንድ የሚያደርግ መንፈሳዊ አመራር አረጋግጠዋል፡፡ ከዚያን ጊዜ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ ከተቀበሉት ራእይ በላይ እጅግ ኃያል መገለጥ እንደሆነ ብዙዎች ተናግረዋል፡፡

በአሁን ጊዜ በአስራ ሁለት ሐዋሪያት ቡድን ውስጥ እያገለገልን ያለነው በቅርብ ጊዜ ነቢያት በኩል ወሳኝ መገለጦች ስለመጡ ተባርከናል፡፡12 ፕረዘደንት ረስል ኤም ኔልሰን ስልጣን የተሰጣቸው የጌታ ወኪል ናቸው፣ በተለይ ቤተሰቦች የእምነት መሸጊያዎችን በቤታቸው እንዲገነቡ ከመርዳት፣ በሁለቱም የመጋረጃው በኩል ያለውን እስራኤል ከመሰብሰብ እና የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበሉ አባላትን በተቀደሰ የቤተመቅደስ ስርዓት ጉዳዮች ከመባረክ ጋር የተያያዙ ራዕዮችን በተመለከተ፡፡

በጥቅምት 2018 (እ.ኤ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ቤታችንን ለመባረክ አስፈላጊ ለውጦች በተዋወቁ ጊዜ “በቤተመቅደስ ውስጥ በቀዳሚ አመራር እና በአስራሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባላት ምክርቤት ወይይት… የተወደደው ነብያችን ከጌታ መገለጥን ከጠየቀ በኋላ … ሁሉም ጠንካራ ማረጋገጫ እንደተቀበሉ“ መስክሪያለሁ።”13

በዚያን ጊዜ ከቅዱስ የቤተመቅደስ ስርዓቶች ጋር የተገናኙ ሌሎች ራዕዮችን ተቀብለው ነበር ነገር ግን አልተገለጹም ወይም አልተተገበሩም ነበር።14 ይህ ምሪት በፕረዘደንት ራስል ኤም ኔልሰን የግል የትንቢታዊ ራዕይ ጀመረ ከዚያም በሂደቱ ውስጥ ለተሳተፉ ፍቅራዊ እና ጠንካራ ማረጋገጫ መጣ፡፡ ፕሬዘደንት ኔልሰን በተለይ የሴቶች መረዳጃ ማህበርን፣ የወጣት ሴቶችን እና የህጻናት ክህል ድርጅቶችን በበላይነት የሚቆጣጠሯቸውን እህቶች አካተዋል፡፡ በቤተመቅደስ ውስጥ የነበረው የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን የመጨረሻው ምሪት ጥልቅ መንፈሳዊ እና ሀይለኛ ነበር። እኛ እያንዳንዳችን የጌታን አስተሳሰብ ፍቃድ እና ድምጽ ተቀብለን እንደነበር አወቅን፡፡15

ቀጣይነት ያለው ራዕይ እየመጣ እንደሆነ እና ጌታ ባዘጋጀው መንገድ እየመጣ እንደሆነ በሙሉ ቁርጠኝነት እናገራለሁ። ፕሬዝዳንት ኔልሰን ዛሬ ጠዋት ያስተላለፉት አዲስ አዋጅ ሁሉንም ሰዎች የሚባርክ መገለጥ እንደሆነ እመሰክራለሁ፡፡

ሁሉም በጌታ ማዕድ ላይ እንዲታደሙ ግብዣችንን እናቀርባለን፡፡

ምስክርነታቸው ከቀነሰ፣ ንቁ ተሳታፊ ካልሆኑ ወይም ስማቸው ከቤተክርስቲያን መዝገቦች ከተወገደባችው ጋር እንደገና ለመገናኘት ያለንን ልባዊ ፍላጎት እናሳውቃለን። ሁላችንም ልናደርግ የሚገባንን ነገሮች ለመማር “የክርስቶስን ቃላት” ከጌታ ገበታ ላይ ከእናንተ ጋር ለመመገብ እንፈልጋለን፡፡16 እንፈልጋችኋለን! ቤተክርስቲያኗ ትፈልጋችኋለች! ጌታ ይፈልጋችኋል! የልባችን ፀሎት የአለምን አዳኝ ለማምለክ ከእኛ ጋር እንድትሳተፉ ነው፡፡ አንዳንዶቻችሁ በደል፣ ደግነት የሌለው ነገር ወይም ሌላ የክርስቶስ ዓይነት ያልሆነ ባሕርይ እንደተቀበላችሁ እናውቃለን። አንዳንዶች በእምነታቸው ላይ ምናልባት በተገቢ ደረጃ አድናቆት ያልተሰጣቸው፣ ግንዛቤ ያልተፈጠረላቸው ወይም ሊፈቱ ያልቻሉ ፈታኝ ነገሮች እንዳጋጠሟቸውም እናውቃለን፡፡

አንዳንድ በጣም ጠንካራ እና ታማኝ አባሎቻችን በሆነ ምክንያት በእምነታቸው ላይ ፈታኝ ሁኔታ ገጥሟቸዋል። ቤተክርስቲያኗን በመተው በሚዙሪ ፍርድ ቤት በጆሴፍ ስሚዝ ላይ የመሰከረበትን የደብልዩ. ደብልዩ. ፌልፕስን እውነተኛ ዘገባ እወዳለሁ። ንስሃ ከገባ በኋላ ለጆሴፍ ስሚዝ እንዲህ ሲል ጻፈለት “ያለሁበትን ሁኔታ አውቃለሁ፣ አንተም ታውቃለህ፣ እናም እግዚያብሄር ያውቀዋል እናም ጓደኞቼ ቢረዱኝ ለመዳን እፈልጋለሁ፡፡”17 ጆሴፍ ይቅር አለው፣ ወደስራ መለሰው ከዚያም በፍቅር አንዲህ ሲል ጻፈ “በመጀመሪያ ጓደኞች የሆንን በመጨረሻም እንደገና ጓደኞች ነን፡፡“18

ወንድሞች እና እህቶች ምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ቤተክርስቲያኗ እና አባላቱ እንደሚቀበሏችሁ እባካችሁ እወቁ!

ህይወታችንን ለመምራት የግል መገለጥ

የግል መገለጥ በትህትና ከጌታ መመሪያን ለሚሹ ሁሉ ይገኛል። የትንቢታዊ መገለጥን ያህል አስፈላጊ ነው። ከመንፈስ ቅዱስ የተገኘ የግል መንፈሳዊ መገለጥ ሚሊዮኖች ለመጠመቅ እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ለመሆን የሚያስፈልገውን ምስክርነት እንዲቀበሉ አስችሏል።

የግል መገለጥ ጥምቀትን ተከትሎ “መንፈስ ቅዱስን በመቀበል ከተቀደስን“ በኋላ የምንቀበለው ታላቅ በረከት ነው።19 የ15 ዓመት ልጅ ሳለሁ የገጠመኝን ልዩ መንፈሳዊ መገለጥ ማስታወስ እችላለሁ። ውድ ወንድሜ ሚስዮን እንዲያገለግል ላልፈለገው ውድ አባታችንን እንዴት መመለስ እንደሚችል ከጌታ መመሪያን እየፈለገ ነበር። እኔም በቅን ልቦና ጸለይኩ እናም የወንጌልን እውነተኛነት የግል መገለጥ ተቀበልኩኝ።

የመንፈስ ቅዱስ ሚና

የግል መገለጥ የተመሰረተው ከመንፈስ ቅዱስ በሚመጡ መንፈሳዊ እውነቶች ነው፡፡20 መንፈስ ቅዱስ የእውነቶች ሁሉ ገላጭ እና መስካሪ ነው፤ በተለይ የኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ ያለመንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን በትክክል ልናውቅ አንችልም፡፡ የእሱ ወሳኝ ሚና ስለ አባት እና ስለልጁ እንዲሁም ስለማእረጋቸው እና ክብራቸው መመስከር ነው፡፡

መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ላይ በኃይል ተጽዕኖ ያሳድራል።21 አንድ ሰው ካልተጠመቀ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ካልተቀበለ በስተቀር ይህ ተጽዕኖ ቋሚ አይሆንም። በንስሐ እና በይቅርታ ሂደት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ እንደሚያነጻ አካል ሆኖ ያገለግላል።

መንፈስ በሚያስደንቁ መንገዶች ይናገራል፡፡ ጌታ ይህንን የሚያምር መግለጫ ተጠቅሟል፤

“አዎን፣ እነሆ፣ በአንተ ላይ በሚሆነው እና በልብህም በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በአዕምሮህ እና በልብህ እነግርሀለሁ።

“አሁን፣ እነሆ፣ ይህ የራዕይ መንፈስ ነው፡፡”22

ምንም እንኳን ተጽዕኖው በሚያስደንቅ ሁኔታ ኃይለኛ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ በጸጥታ እንደ አንድ ትንሽ ለስላሳ ድምጽ ነው የሚመጣው።23 ቅዱሳን ጽሁፎች መንፈስ አእምሮአችን ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚያሳድር የሚያሳዩ ብዙ ምሳሌዎችን ያካትታሉ፤ ለአእምሯችን ሰላምን መናገርን ጨምሮ24 አእምሯችንን መያዝ፣25 አእምሯችንን ማንቃት26 እና ለአእምሯችን ድምጽን መላክ ያካትታል፡፡27

መገለጥን ለመቀበል የሚያዘጋጁን አንዳንድ መርሆዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፤

  • ለመንፈስ ምሪት መጸለይ በጥልቅ ክብር እና ትህትና መሻትና መጠየቅ ይኖርብናል28 እንዲሁም ትእግስተኛ እና ታዛዥ መሆን ይኖርብናል፡፡29

  • መነሳሳትን ለማግኘት መዘጋጀት፡፡ ይህ ከጌታ አስተምሮዎች እና ከትእዛዛቶቹ ጋር ስምሙ መሆናችንን ይጠይቃል፡፡

  • ቅዱስ ቁርባንን በብቁነት መቀበል፡፡ ይህንን ስናደርግ የቅዱስ ልጁን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በእራሳችን ላይ እንደምንወስድ እና እርሱን ሁልጊዜም እንደምናስታውስ እና ትእዛዛቱን እንደምንጠብቅ እንመሰክራለን እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር ቃል እንገባለን፡፡

እነዚህ መርሆዎች የመንፈስ ቅዱስን ማነሳሳት እና ምሪት እንድንቀበል፣ እንድንለይ እና እንድንከተል ያዘጋጁናል። ይህ “ደስታን [እና] … ዘላለማዊ ህይወትን የሚያመጡትን ሰላማዊ የሆኑትን ነገሮች ያካትታል፡፡”30

ቅዱሳን ጽሁፎቸን እና የወንጌልን እውነታዎችን በየወቅቱ ስናጠና እና የምንሻውን ምሪት በአእምሯችን ስናሰላስል መንፈሳዊ ዝግጁነታችን ያድጋል፡፡ ታጋሽ መሆንን እና ጌታ በፈቀደው ጊዜ ማመንን አስታውሱ። “ሆነ ብሎ ሊያስተምረን ሲመርጥ “ሁሉን በሚያውቅ ጌታ መመሪያ ይሰጣል፡፡31

መገለጥ በጥሪዎቻችን እና በስራ ምደባዎቻችን

መንፈስ ቅዱስ በጥሪዎቻችን እና በስራ ምደባዎቻችን ላይ መገለጥን ይሰጣል። ከእኔ ተመክሮ ትርጉም ያለው መንፈሳዊ ምሪት አብዛኛውን ጊዜ የሚመጣው ሃላፊነቶቻችንን በመወጣት ውስጥ ሌሎችን ለመባረክ ስንጥር ነው፡፡

ወጣት ኤጲስ ቆጶስ እያለሁ በንግድ ጉዳይ ለመሳተፍ አውሮፕላን ልሳፈር ጥቂት ጊዜ ሲቀረኝ ከአንድ ጥንዶች ተስፋ አስቆራጭ ጥሪ መቀበሌን አስታውሳለሁ፡፡ እነሱ ከመምጣታችወ በፊት እንዴት ልባርካቸው አንደምችል ለማወቅ ጌታን ለመንኩት፡፡ የችግሩ ተፈጥሮ እና መስጠት የሚገባኝን ምላሽ ተገልጾልኝ ነበር፡፡ ያ ገላጭ ምሪት እጀግ ትንሽ ጊዜ የነበረ ቢሆንም የኤጲስ ቆጶስ የጥሪዬን ቀዱስ ሃላፊነቶች እንድወጣ አስቻለኝ፡፡ በአለም ዙሪያ ያሉ ኤጲስ ቆጶሳትም እንዲህ ያሉትን ተመክሮዎች ከእኔ ጋር ይጋራሉ፡፡ የካስማ ፕረዘዳንት እያለሁ ጠቃሚ መግለጥን ብቻ አይደለም የተቀበልኩት የጌታን አላማዎች ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆነ የግል ማስተካከያንም እንጂ፡፡

በጌታ የወይን እርሻ በትህትና ስንሰራ እያንዳንዳችን ገላጭ ምሪትን ልንቀበል እንደምንችል አረጋግጥላችኋለሁ፡፡ አብዛኛው መመሪያችን የሚመጣው ከመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለተወሰነ አላማ በቀጥታ ከጌታ ይመጣል፡፡ እኔ በግሌ ይህ እውነት እንደሆነ እመሰክራለሁ። በአጠቃላይ ለቤተክርስቲያኗ የሚሰጥ መመሪያ ለቤተክርስቲያኗ ፕሬዘዳንት እና ነቢይ ይመጣል ።

እኛ የዚህ ዘመን ሃዋርያት ከወቅቱ ነብያችን ከፕረዘዳንት ኔልሰን ጋር ለመስራት እና ልመጓዝ መብት አግኝተናል፡፡ ዊልፈርድ ዉድረፍ ስለጆሴፍ ስሚዝ የተናገረውን እጠቅሳለሁ፤ ለፕረዘዳንት ኔልሰንም እውነት ነው፡፡ “የእግዚያብሄርን መንፈስ ስራዎች እና ለእርሱ የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጦች እና ፍጻሚያችውን ከእርሱ ጋር“ አይቻለሁ፡፡32

ዛሬ የእኔ ትሁት ልመና እያንዳንዳችን ህይወታችንን ለመምራት ቀጣይነት ያለው መገለጥ እንድንሻ እና እግዚያብሄር አባታችንን ስናመልክ በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መንፈስን እንድንከተል ነው፤ ምስክርነቴን የምተወው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው አሜን፡፡

ማስታወሻዎች

  1. በ1960ዎቹ የሚስዮናዊ አገልግሎት ለወጣት ወንዶች ከ 20 አመት ወደ 19 አመት ሲቀነስ እኔ 20 አመት ከነብሩት የመጭረሻዎቹ መካከል ነበርኩኝ፤ ሽማግሌ ጀፈሪ አር ሆላንድ አስራ ዘጠኝ አመት ከሆናቸው ከመጀመሪያዎቹ መካከል ነበሩ፡፡

  2. ራስል ኤም ኔልሰን “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት ዳግም መመለስ፤ የሁለት ምእተ አመታት መታሰብያ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣ “እርሱን ስሙ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020(እ.ኤ.አ) 91 ተመልከቱ። ይህ አዋጅ በቀዳሚ አመራር እና በአስራሁለቱ ሃዋርያት ቡድን በዚህ ጊዜ ከተሰጡት ከሌሎች አምስቶች ጋር ይቀላቀላል፡፡

  3. የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፤ ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል (2006፣ እ.ኤ.አ)፣ 243፤ ማቲዎስ 16፥13–19

  4. ሙሴ 7፥61

  5. ሙሴ 7፥62። ጌታም ቀጠለ “እና እንደ ጥፋት ውሃ ጽድቅና እውነት ምድርን እንድታጸዳት የእኔ ተመራጮቸ ከምድር አራት ማአእዘናት እንዲሰበሰቡ አደርጋለሁ” (ሙሴ 7፥62. መዝሙር 85፥11)፡፡

  6. ኤዝራ ታፍት ቤንሰን፣ “የዘመናዊ ራዕይ ስጦታ፣” ኤንዛይን፣ ህዳር 1986፣ እ.ኤ.አ 80።

  7. ኤዝራ ታፍት ቤንሰን፣ “የዘመናዊ ራዕይ ስጦታ፣” 80 ተመልከቱ።

  8. ሂው ቢ ብራውን፣ “ጆሴፍ ስሚዝ ከነቢያት መካከል” (አስራ ስድስተኛው ዓመታዊ የጆሴፍ ስሚዝ መታሰቢያ ስብከት፣ ሎጋን የሃይማኖት ተቋም፣ ታህሳስ 7፣ 1958 እ.ኤ.አ)፣ 7

  9. ሁ ቢ.በራውን “Joseph Smith among the Prophets,” 7 ይመልከቱ በሁሉም ሁኔታዎች መገለጦቹ ለቀደሙት ነቢያቶች ከተሰጡት የእግዚያብሄር ቃላት ጋር የሚስማሙ ናቸው፡፡

  10. Official Declaration 2; ደግሞም 2 Nephi 26:33ይመልከቱ፡፡ በመፅሐፈ ሞርሞን የተገለጸው የተተገበረው ትምህርት ራእይ ፣ “ሁሉም ለእግዚአብሔር አንድ ናቸው፣” እንዲሁም “ጥቁርም ነጭም፣ ባሪያውና ነፃው፤ ሴትና ወንድ” ሲል ያስቀምጣል፡፡2 ኔፊ 26፥33). ይህ አስገራሚ መገለጥ በቀዳሚ አመራር እና በአስራሁለቱ ሃዋርያት ቡድን በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ቅዱስ የላይኛው ክፍል የመጣ እና የተረጋገጠ ነው፡፡

  11. ብዙዎቹ ሃዋርያት መገለጡ ሃይለኛ እንደነበር እና በጣም ቅዱስ ከመሆኑ የተነሳ ምንም ቃላት ለመግለጽ ብንጠቀም በቂ አንደማይሆን እንዲሁም በተወሰነ መንገድም የመገለጡን ጥልቅ እና ሃይለኛ ተፈጥሮ እንደሚቀንሰው አመልክተዋል።

  12. ቤተሰብ፧ ለአለም የተላለፈ አዋጅሊያሆና፣ ጥቅምት 2017 እ.ኤ.አ፣ 145 ተመልከቱ። ይህ አዋጅ በሶልት ሌክ ከተማ ዩታ ውስጥ በመስከረም 23፣ 1995 (እ.አ.አ) በነበረው በሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ስብሰባ በፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ የተዋወቀ ነበር። በተጨማሪም ቶማስ ኤስ.ሞንሰን፣ “ወደ ጉባኤ እንኳን ደህና መጣችሁ፣” ሊያሆና ህዳር 2012(እ.አ.አ)፣ 4–5 ይመልከቱ፤ ፕረዘዳንት ሞንሰን ለሚስዮናዊ አገልግሎት የሚያስፈልገውን ዝቅተኛ የእድሜ ጣርያ አስታወቁ፡፡

  13. ኩዊንተን ኤል ኩክ፣ “ለሰማያዊ አባታችንና ለኢየሱስ ክርስቶስ ትልቅና ዘላቂ መለወጥ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.ኤ.አ) 11 ይመልከቱ

  14. በጥር 1፣ 2019 (እ.አ.አ) ​​ከቅዱስ የቤተመቅደስ ስርዓቶች ጋር የተገናኙ ራዕዮች በሁሉም ቤተመቅደሶች ተተግብረው ነበር። ስለቤተ መቅደስ ስርአቶች የተለዩ ዝርዝሮች በቤተመቅደስ ብቻ መወያየት እንደሚገባ መገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ነገርግን መርሆዎቹ በትምህርት ይሰጣሉ፡፡ የቤተመቅደስ ቃልኪዳኖች እና ስርዓቶች እናም እንዴት በእነሱ አማካኝነት አምላካዊ ሀይል ወደ ህይወታችን እንደሚፈስ ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር በቆንጆ ሁኔታ አስተምረዋል። (“ይህ ቤት ለስሜ ይገንባ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 እ.ኤ.አ 86)።

  15. ይህ ሂደት እና ስብሰባዎች የተደረጉት በጥር ፣የካቲት እና መጋቢት 2018 (እ.አ.አ) በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ነበር፡፡ የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን የመጨረሻው መገለጥ የመጣው በሚያዝያ 26, 2018 (እ.አ.አ) ነበር።

  16. 2 ኔፊ 32፥3ይመልከቱ።

  17. ቅዱሳን፤ የኋለኛው ቀን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ታሪክ መጽሃፍ 1፣ የእውነት መስፈርት፣ 1815–1846 እ.ኤ.አ (2018 እ.ኤ.አ)፣ 418።

  18. ቅዱሳን 1፥418።

  19. 3 ኔፊ 27፥20

  20. መንፈስ ቅዱስ የእግዚያብሄር ራስ አባል ነው፡፡( 1 ዮሃንስ 5፥7ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20:28ይመልከቱ) መንፈሳዊ አካል በሰው ቅርጽ እና አምሳል አለው፡፡ ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥22ይመልከቱ)፡፡ ተጽእኖው በማንኛውም ቦታ ሊሆን ይችላል፡፡ ከሰማይ አባት እና ከአዳኛችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በአላማ አንድ ናችው ።

  21. ስለ ክርስቶስ ብርሃን እና በክርስቶስ ብርሃን እና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ስላለው ልዩነት አጠቃላይ ግንዛቤ ለማግኘት የሚከተሉትን ተመልከቱ፣ 2 ኔፊ 32ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥7፣ 11–13፣ “የክርስቶስ ብርሃን፣” የመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት። እንዲሁም ቦይድ ኬ ፓከር፣ “የክርስቶስ ብርሃን፣” ሊያሆና፣ ሚያዚያ፣ 2005 እ.ኤ.አ 8–14 ተመልከቱ።

  22. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 8፥2–3

  23. ሄለማን 5፥30ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85፥6ይመልከቱ።

  24. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥23ይመልከቱ።

  25. ትምህርት እና ቃል ኪዳን 128፥1ይመልከቱ።

  26. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥13ይመልከቱ።

  27. ኤኖስ 1፥10ይመልከቱ።

  28. ማቴዎስ 7፥7–8ይመልከቱ።

  29. ሞዛያ 3፥19ይመልከቱ።

  30. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥61

  31. ኒል ኤ ማክስዌል፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ለእናንተ ልምድ ይሰጣችኋል (2007) እ.ኤ.አ፣ 31።

  32. ዊልፎርድ ዉድረፍ በ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፤ ጆሴፍ ስሚዝ (2007 (እ.አ.አ))፣ 283።