አጠቃላይ ጉባኤ
ሰማያትን ለእርዳታ መክፈት
የሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ።


2:3

ሰማያትን ለእርዳታ መክፈት

በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን እምነት በስራ ላይ እናውል።

ምን አይነት ልዩ እና አስደናቂ ጉባኤ ነበር። ውድ እህት ላውዲ እና ኤንዞ፣ አመሰግናለሁ። እናንተ አስገራሚዎቹን የቤተክርስቲያኗን ወጣት ሴቶች እና ወንዶችን በሚገባ ወክላችኋል።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ዛሬ ስለቤተክርስቲያኗ፣ እንዲሁም አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በምድር ባገለገለበት ጊዜ ስለመሰረታት ያቺው ቤተክርሲያን፣ ዳግም መመለስ ብዙ ሰምተናል። ዳግም መመለሷ የተጀመረው በዚህ ጸደይ ከ200 አምታት በፊት እግዚአብሔር አብ እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ለወጣቱ ጆሴፍ ስሚዝ በታዩበት ጊዜ ነበር።

ከዚህ ድንቅ ራእይ ከአስር ዓመት በኋላ፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና አምስት ሌሎች እንደ ጌታ ቤተክርስቲያን ጀማሪ አባላት ተጠርተው ነበር።

በሚያዝያ 6፣ 1830 (እ.አ.አ) ከተሰበሰቡት ትንሽ ቡድኖች ከ16 ሚልዮን በላይ አባላት ያላት አለም አቀፍ ድርጅት መጥታለች። ይህች ቤተክርስቲያንም በአለም ዙሪያ የሰውን ስቃይ ለማስወገድ እና ለሰው ዘርም ከፍ ማድረጊያን ለመስጠት የምታከናውነውም በአለም ሁሉ ይታወቃል። ነገር ግን ዋናው አላማዋ ወንዶች፣ ሴቶች፣ እና ልጆች ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲከተሉ፣ ትእዛዛቱን እንዲያከብሩ፣ እና ከሁሉም በላይ ታላቅ ለሆነው በረከት፣ እንዲሁም ከእግዚአብሔር እና ከሚወዷቸው ጋር ለዘለአለም ለመኖር፣ ብቁ እንዲሆኑ ለመርዳት ነው።

በ 1820( እ.ኤ.አ) የተጀመረውን ክስተት ስናከብር፣ ጆሴፍ ስሚዝን እንደ እግዚአብሔር ነቢይ ብናከብረውም፣ ይህች የጆሴፍ ስሚዝ ቤተክርስቲያን እንዳልሆነች፣ ወይም የሞርሞን ቤተክርስቲያን እንዳልሆነች፣ ማስታወሱ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህች የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ናት። ቤተክርስቲያኗ ማን ተብላ መጠራት እንዳለባት እንዲህም አውጇል፥ “በመጨረሻዎቹ ቀናትም ቤተክርስቲያኔ የምትጠራው በዚህ፣ እንዲሁም በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣ ስም ነው።”

እንዴት የቤተክርስቲያኗን ስም የምንጠቀምበት መንገዳችንን ማስተካከል እንዳለብን ከዚህ በፊት ተናግሬአለሁ። ከዚያ ጊዜ በኋላም፣ ይህን ማስተካከያ ለማከናወን ብዙ ተደርገዋል። ይህን ጥረት ለመምራት እና በዚህ ምሽት የማስተዋውቃቸውን ሌሎች የተገናኙ ድርጊቶችን ሁሉ ለማከናወን ብዙ ላደረጉት ለፕሬዘደንት ኤም. ራስል ባለርድ እና ለአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባላት ታላቅ ምስጋና አለኝ።

የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ክፍሎች፣ የተዛመዳችሁ አካላት፣ እናም ሚልዮኖች አባላት—እናም ሌሎች—አሁን የቤተክርስቲያኗን ትክክለኛ ስም ይጠቀማሉ። የቤተክርስቲያኗ አስተዳደር ዘይቤ መመሪያ ተስተካክሏል። የቤተክርስቲያኗም ዋና ድህረገፅ ChurchofJesusChrist.org ነው። የኢሜል አድራሻዎች፣ የጎራ ስሞች እና ማህበራዊ ሚዲያ ሰርጦች ተለውጠዋል። ተወዳጆቹ ዘማሪዎቻችንም አሁን “የታበርናክል ዘማሪዎች በቤተመቅደስ አደባባይ” ተብለው ይጠራሉ።

ይህን አስገራሚ ጥረቶች ያደረግንበት ምክንያት የጌታን ስም ከእርሱ ቤተክርስቲያን ስናወጣ፣ እርሱን ከአምልኮታችን እና ከህይወታችን ዋና ትኩረት ሳይታሰብበት ስለምናወጣ ነው። በጥምቀት ጊዜ የአዳኝን ስም በራሳችን ላይ ስንወስድ፣ በሀሳቦቻችን እና በድርጊቶቻችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ለመመስከር ቃል እንገባለን።

ከዚህ በፊት፣ “የጌታን ቤተክርስቲያን ትክክለኛ ስም በዳግም ለመመለስ የምንችለውን ጥረት ካደረግን፣” እርሱ “ሀይሉን እና በረከቶቹን በኋለኛ ቀን ቅዱሳን ራሶች ላይ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መንገድ እንደሚያፈስ” ቃል ገብቼላችኋለሁ ነበር። ዛሬም ያን ቃል ኪዳን አሳድሳለሁ።

እርሱን ለማስታወስ እንዲረዳን እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንደ ጌታ ቤተክርስቲያን፣ ለመጠቆም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ያለውን ዋና ክፍል የሚያሳይ ምልክትን ለማስተዋወቅ እደሰታለሁ።

ይህም ምልክት የቤተክርስቲያኗ ስም በማዕዘን ድንጋይ ውስጥ ጨምሮ ይይዛል። ኢየሱስ ክርስቶስ ዋናው የማዕዘን ድንጋይ ነው።

አርማ በማእዘን ድንጋይ

በምልክቱ መሀከልም በቶርቫልድሰን የተሰራ የእብነ በረድ ሐውልት ክርስተስምስል ይገኛል። ይህም ከሞት የተነሳውን፣ ህያው ጌታ ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ ለማቀፍ ክንዶቹን ከፍቶ ያሳያል።

በምልክትም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በቅጥር ስር ቆሟል። ቅጥሩም ከሞት የተነሳው አዳኝ ከመቃብር ከተሰቀለበት በሶስተኛው ቀን እንደወጣም እንድናስታውስ ያደርጋል።

አዲስ የቤተ ክርስቲያን ምልክት

ይህ ምልክት ለብዙዎች የሚታወቅ መሆን አለበት፣ ምክንያቱም እኛ ለረጅም ጊዜ በዳግም የተመለሰውን ወንጌል ከህያው፣ ከሞት የተነሳ ክርስቶስ ጋር እናገኛኘው ነበርና።

አሁን ይህም ምልክት ለይፉ ፅሁፎች፣ ዜናዎች፣ እና የቤተክርስቲያን ዝግጅቶች የሚታይ ማስታወቂያ ይሆናል። ይህች የአዳኙ ቤተክርስቲያን እንደሆነች እና እንደ እርሱ የቤተክርስቲያኑ አባላት የምናደርገው ነገር ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ ማእከል እንዳደረገ ያስታውሰናል።

አሁን ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ሽማግሌ ጎንግ በግሩም ሁኔታ እንዳስተማሩት ነገ የፓልም እሑድ ነው። ከዚያንም በትንሳኤ የሚፈጸመውን ልዩ ሳምንት እንገባለን። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ አለምን በሁከት ላይ ባደረገበት ቀን እንደምንኖረው የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች፣ ስለክርስቶስ መናገር ወይም ስለክርስቶስ መስበክ ወይም ክርስቶስን የሚወክል ምልክትን መጠቀም ብቻ አይደለም ያለብን።

በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን እምነት በስራ ላይ እናውል።

እንደምታውቁት፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት በወር አንድ ቀን የጾም ህግን ይከተላሉ።

የጾም ትምህርት ጥንታዊ ነው። ይህም በመፅሐፍ ቅዱስ ጀግኖች ከመጀመሪያው ቀናት ጀምሮ የሚያደርጉት ነበር። ሙሴ፣ ዳዊት፣ ዕዝራ፣ ነህምያ፣ አስቴር፣ ኢሳይያስ፣ ዳኔል፣ ኢዩኤል፣ እና ብዙ ሌሎች ጾሙ እናም ስለመጾም ሰበኩ። በኢሳይያስ ፅሁፎችም፣ ጌታ እንዲህ አለ፥ “እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን ? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?”

ሐዋርያው ጳውሎስ የቆሮንጦስ ቅዱሳንን እንዲህ መከረ፥ “ለጾም እና ለጸሎት ትጉ።” አዳኝ ራሱም እንዳወጀው፣ አንዳንድ ነገሮች “ከጸሎትና ከጾም በቀር አይወጣም” ብሏል።

በቅርብም በማህበራሚ ማሰራጫ ቪድዮ ውስጥ እንዲህ ብያለሁ፣ “የእንደ ሃኪም እና የቀዶ ጥገና ዶክተር ለህክምና ባለሙያዎች፣ ሳይንቲስቶች እና የCOVID-19 (የኮሮና ቫይረስ በሸታ) ስርጭትን ለመቀነስ ቀኑን ሙሉ እየሰሩ ላሉ ሁሉ ታላቅ አድናቆት አለኝ፡፡”

አሁን እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዘደንት እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ፣ እግዚአብሔር “እርሱ ሁሉም ስልጣን፣ ሁሉም ጥበብ፣ እናም ሁሉም ግንዛቤ አለውና፤ ሁሉንም ነገር ያውቃልና፣ እርሱ እስከ ደህንነትም እንኳን ንስሃ ለሚገቡትና በስሙ ለሚያምኑት መሀሪ” እንደሆነ አውቃለሁ

ስለዚህ፣ በታላቅ ችግር ጊዜ፣ እንዲሁም በሽታ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ ሲመጣ፣ እኛ የምናደርገው በጣም ተፈጥሯዊ ነገር ቢኖር የሰማይ አባታችንን እና ዋና ፈዋሹ ልጁን፣ የምድር ህዝቦችን ለመባረክ አስደናቂ ሀይላቸውን እንዲያሳዩ መጥራት ነው።

በቪድዮ መልእክቴ፣ በእሁድ፣ መጋቢት 20፣ 2020 ዓ.ም. ሁላችንም በጾም እንድንጋራ ጋብዣለሁ። ብዙዎቻችሁ ቭድዮውን አይታችኋል እናም በጋራነት ጾማችኋል። አንዳንድ አላደረጉትም ይሆናል። ከሰማይ እርዳታን አሁንም ያስፈልገናል።

ስለዚህ በዚህ ምሽት፣ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ራሳቸውን ለብዙ ጾም እና ጸሎት እንደሰጡት በሞዛያ ወንድ ልጆች ምሳሌ፣ እና እንደ የሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ክፍል፣ ለሌላ የአለም አቀፍ ጾም ጥሪ አደርጋለሁ። ጤናቸው ለሚፈቅድላቸው ሁሉ፣ እንጹም፣ እንጸልይ፣ እናም በእምነት እንደገና አንድ እንሁን። ከዚህ አለማዊ ወረርሽኝ እፎይታ እናገኝ ዘንድ በጸሎት እንለምን።

ሁሉንም፣ የእምነታችን አባል ያልሆኑትንም ጨምሮ፣ በስቅለት እለት፣ የአሁኑ የወረርሸኝ ቁጥጥር እንዲደረግበት፣ ተንከባካቢዎች እንዲጠበቁ፣ ኢኮኖሚው እንዲጠናከር፣ እናም ህይወት መደበኛ እንዲሆን፣ በሚያዝያ 10 ቀን እንድንጾም እና እንድንጸልይ እጋብዛለሁ።

የምንጾመው እንዴት ነው? ሁለት ምግቦች ወይም ለ 24 ሰዓታት ያህል የተለመደ ነው። ነገር ግን፣ አዳኝ ለእናንተ ስላደረገው ከሁሉም ታላቅ የሆነውም መስዋዕት በማስታወስ፣ እናንተ ለራሳችሁ መስዋዕት ምን እንደሆነ ወስኑ። በአለም አቀፍ መፈወስ እንዲኖርም በአንድነት እንለምን።

የስቅለት እለት የሰማይ አባታችን እና ልጁ ሊሰሙን የሚችሉበት ፍጹምቀን ነው!

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ የምናከናውነው ስራ መለኮታዊ እንደሆነ ካለኝ ምስክር ጋር፣ ለእናንተ ያለኝን ጥልቅ ፍቅር እገልጻለሁ። ይህችም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ናት። እርሱም ዋና መሪዋ ነው እናም የምንሰራውን ሁሉ ይመራል። ለህዝቡ ልመና መልስ እንደሚሰጥም አውቃለሁ። ይህንን የምመሰክረው ቅዱስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።