በእምነት የመደገፍ ኃይል
ለመደገፍ ቀኝ እጃችሁን በማንሳት ፤የእርሱ አገልጋይ የሆኑትን፤ እንደምትደግፉአቸው፡፡ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ትገባላችሁ።
ብዙ ጊዜ የክህነት መሪዎች የሚያገለግሉአችው ሰዎች ስላላቸው የእምነት ድጋፍ ሲያመሰግኑ እሰማለሁ፡፡ ከድምጻቸው ስሜትም፣ ምስጋናቸው እውነተኛ እና ጥልቅ እንደሆን ታውቃላችሁ፡፡ የዛሬው አላማዬ በእርሱ ቤተክርስትያን ውሰጥ ለአግልጋዮች ስላላችሁ ድጋፍ ጌታ ለእናንተ ያለውን አድናቆት ለማስተላለፍ ነው፡፡ እናም በተጨማሪ እናንተን አበረታታችኃለሁ እንድትለማመዱና እንድታድጉ በዛው ኃይል በእምነትታችሁ ሌሎችን እንድተደግፉ፡፡
ከመወለዳችሁ በፊት ፤የዚህን አይነት ታላቅ ኃይልን አሳይታችኋል፡፡ ከስጋዊ ህይወት በፊት ስለነበረው መንፈስ አለም የምናውቀውን ወደ ኋላ አስቡት የሰማይ አባታችን ለልጆቹ ዕቅዱን አቀረበ። እኛ በዚያ ነበርን፡፡ ሳጥናኤል፤ የመንፈስ ወንድማችን፣ በነፃነት መምረጥ የሚያስችለንን እቅድ ተቃወመ፡፡ ይሖዋ፤ ውዱ የሰማይ አባታችን ልጅ፤ እቅዱን ደገፈ፡፡ ሳጥናኤል ተቃውሞውን መራ የይሖዋ የድጋፍ ድምፅ አሸነፈ፤እናም አዳኛችን ለመሆን ፍቃደኛ ሆነ፡፡
አሁን በስጋዊ ዓለም መሆናችሁ አብን እና አዳኛችንን እንደ ደገፍችሁ ማረጋገጫችን ነው፡፡ በምድራዊ ህይወት ሊያጋጥመን ስለሚችለው ፈተና ያለን እውቀት ውስን ቢሆንም እንኳን የደስታን እቅድ ለመደገፍ በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት እና የርሱን ድርሻ ማወቅ ይጠይቃል፡፡
የእግዚእብሔር አገልጋዮችን የመደገፍ እምነታችሁ በዚህም ህይወት የደስታቸሁ ልብ ሆኗል፡፡ ከሚሲዮናዊያን መጽሐፈ ሞርሞንን የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ፀልያችሁ እወቁ የሚለውን ግብዣ ስትቀበሉ፤ የጌታን አገልጋዮችን በእምነት እየደገፋችሁ ነበር፡፡ የመጠመቅ ግብዣን ስትቀበሉ፤የእግዚእብሔር ትሁት አገልጋይን እየደገፋችሁ ነው፡፡
አንድ ሰው እጁን በጭንቅላታችሁ ላይ ጭኖ ‹‹መንፈስ ቅዱስን ተቀበል›› ሲል፤ እንደ መልከፀዲቅ የክህነት ተሸካሚ እየደገፋችሁት ነው፡፡
ከዛን ቀን ጀምሮ፤በእምነት በማገልገል፤ ማንም ክህነትን ለሰጣችሁ እናም ለክህነት ክፍል የቀባችሁ ሰውን ደግፋችኋል፡፡
ቀደም ባለው በክህነት ተሞክሮአችሁ፤ ማንኛውም ድጋፍ የእግዚአብሔርን አገልጋዮች በቀላሉ የምናምንበት ክስተቶች ናቸው፡፡ አሁን፤ አብዛኞቻችሁ ድጋፍ የበለጠ ወደ ሚያስፈልግበት ስፍራ ተሸግራችኋል፡፡
ጌታ ማንንም በምንም ጥሪ የጠራቸውን ለመደፈፍ መርጣችኋል፡፡ ይሄ ምርጫ በአለም ዙሪያ ሁሉ በጉባኤ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ በዚህኛውም ተካሂዷል፡፡ በዚህ አይነት ስብሰባ ውስጥ፤ የወንዶች እና የሴቶች -የእግዚአብሔር አገልጋዮች- ስም ሲነበብ ሁላችሁም እጃችሁን በማንሳት ድጋፋችሁን እንድታሳዩ ትጋበዛላችሁ፡፡ የድጋፍ ድምፃችሁን መከልከል ትችላላችሁ፤ ወይም የድጋፍ እምነታችሁን ቃልመግባት ትችላላችሁ፡፡ ለመደገፍ እጃችሁን ስታነሱ፤ ቃል ትገባላችሁ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ትገባላችሁ፤ የእርሱ አገልጋይ የሆኑትን፤ እንደምትደግፉአቸው፡፡
እነዚህ ልክ እንደ እናንተ፤ ፍፁም ያልሆኑ ሰዎች ናቸው፡፡ ቃልኪዳናችሁን ለመጠበቅ ጌታ እንደ ጠራቸው እንደምታውቁ የሚያሳይ የማይነቃነቅ እምነትን ያሳያል፡፡ በተጨማሪ እነዛን ቃልኪዳኖች መጠበቅ ዘላለማዊ ህይወትን ያመጣል፡፡ አለመጠበቅ ለእናንተ እና ለምተወዱአቸው መከራን - እንዲሁም በእናንተ ኃይል ልታስቡት የማትችሉት ጥፋት ያመጣል፡፡
ኢጲስ ቆጶሱን ፤የካስማ ፕሬዝዳንቱን፤አጠቃላይ አመራሮቹን፤ እናም አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ትደግፋላችሁ ተብላችሁ ተጠይቃችሁ ወይም ልትጠየቁ ትችላላችሁ በጉባኤ ውስጥ ሊሆን ይችላል መሪዎችን እና አመራሮችን እንድትደግፉ የምትጠየቁት፡፡ አንዳንዴም ከኢጲስ ቆጶስ ወይም ከካስማው ፕሬዝዳንት ጋር በምታደርጉት ቃለመጠይቅ ላይ ይሆናል፡፡
የእኔ ምክር እነዚህን ጥያቄዎች ቀደም ብላችሁ፤ በተረጋጋ እና በፀሎት አእምሮ ሁናችሁ፤ እራሳችሁን እንድትጠይቁ ነው፡፡ ይህንን ስታደርጉ፤ የቅርብ ሐሳባችሁን፤ ቃላቶቻችሁን፤ እና ስራችሁን ወደ ኋላ ተመልከቱ፡፡ አንድ ቀን ጌታ ቃለ መጠይቅን እንደሚያደርግላችሁ አውቃችሁ ቃለመጠይቁን ሲያደርግላችሁ ልትመልሱለት የምትችሉትን መልስ አስቀድማችሁ ለማስታወስና ለማዘጋጀት ሞክሩ፡፡ሞክሩ፡፡ እራሳችሁን የሚከተሉትን አይነት ጥያቄዎች በመጠየቅ ማዘጋጀት ትችላላችሁ፡፡
-
እደግፋቸዋለሁ ብዬ ቃል ስለገባሁላቸው ሰዎች ድክመት አውርቻለሁ ወይም አስቤ አቃለሁ?
-
ጌታ እንደሚመራቸው ማርጋገጫ ፈልጌአለሁ?
-
በታማኝነት እና በጥንቃቄ አመራራቸውን እንከተለዋለን?
-
የእግዚአብሄር አገልጋዮች መሆናቸውን ሰላረጋግጠኩበት እይታ ተናግሬአለሁ?
-
በፍቅር ስሜት እና ስማቸው ጠቅሼ በተደጋጋሚ እፀልይላቸዋለሁ?
ለአብዛኞቻችን፤ እነዚህ ጥያቄዎች፤ ወደ ድንጋጤ እና ወደ ንስሀ ይመሩናል፡፡ ሌሎች ላይ ያለቅድስና እንዳንፈርድ ከእግዚአብሔር ታዘናል፤ በተግባር ግን ይሄን ለማስወገድ ከባድ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ከሰዎች ጋር የምንሰራቸው ነገሮቸ ሁሉ እንድንገመግማቸው ይመሩናል፡፡ በሁሉም የህይወታችን ሁኔታዎች ውስጥ፤ እራሳችንን ከሌሎች ጋር እናነፃፅራለን፡፡ ለብዙ ምክንያቶች ልናደርገው እንችላለን፤ አንዳንዶቹ ምክንያታዊ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ባአብዛኛው ጊዜ ግን ገምጋሚዎች አንድንሆን ይመራናል፡፡
ፕሬዝዳንት ጆርጅ ኪው ካነን የሰጡትን ማስጠንቀቅያ እንደ እራሴ ለእናንተ አስተላልፋለሁ፡፡ እውነቱን እንደተናገረ አምናለሁ ‹‹እግዚአብሔሄር አገልጋዮቹን መርጧል፡፡ መኮነን ካስፍለጋቸው ኩነኔ የእርሱ መብት እንዲሆን ወዷል፡፡ እንድንወቅሳቸው እና እንድንኮንናቸው ለእኛ በግል አልተሰጠንም፡፡ ማንም ሰው፣ምንም ያህል በእምነቱ ጠንካራ ቢሆን፤ ምንም ከፍተኛ ክህነት ቢኖረው፤በጌታ የተቀባው ላይ ክፉ ካወራ እናም ምድር ላይ ባለው በእግዚአብሔር ስልጣን ላይ እንከንን ካወጣ የእርሱን ደስ አለመሰኘት ያተርፋል፡፡ ከዚህ የመሰለ ሰው ላይ መንፈስ ቅዱስ እራሱን ያገላል፤ እርሱም ወደ ጨለማ ይሄዳል፡፡ ሁኔታው ይሄ ከሆነ፤ መጠንቀቅ እንዴት ጠቃሚ እንደሆነ አያችሁ?›› 1
እንደ እኔ እይታ በአለም ዙሪያ ያሉ የቤተክርሰቲያን አባሎች በአጠቃላይ እርስ በእርስ እናም በበላይነት ለሚመለከቷቸው ታማኞች ናቸው፡፡ ቢሆንም፤ ማሻሻያ ማድረግ ያለብን እና የምናሻሽላቸው ነገሮች አሉ፡፡ ሌሎችን በመደገፍ በኃይላችን ከፍ ልንል እንችላለን እምነት እና ጥረት ይጠይቃል፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ ልናደርጋቸው ይገባል ያልኳቸው አራት ጥቆማዎች እነዚህ ናቸው፡፡
-
ተናጋሪዎች የሚመክሮአቸውን የተወሰኑ ተግባራትን በመለየት ዛሬውኑ ተግባር ላይ ማዋል እንችላላን፡፡ ይህን ስናደርግ፤ እነርሱን የምንደግፍበት ኃይል ይጨምራል፡፡
-
በሚናገሩበት ወቅት መንፈስ ቅዱስ ቃላቶቻቸው ለምንወዳቸው የተወሰኑ ሰዎች ልብ ውስጥ እንዲገባ መፀለይ እንችላለን፡፡ በኋላም ፀሎታችን እንደተመለሰ ስንማር፤ እነዚህን መሪዎች ምንደግፍበት ኃይል ይጨምራል፡፡
-
ለተወሰኑት ተናጋሪዎች እንዲባረኩ እንዲሁም መልእክታቸውን ጎልቶ እንዲወጣ መፀለይ እንችላለን፡፡ ጎልተው ስናያቸው፤ እነእርሱን ለመደገፍ በእምነታችን እናድጋለን፤ እናም እስከ መጨረሻው ይዘልቃል፡፡
-
ከተናጋሪዎቹ መልእክት የግል ፀሎታችን እርዳታ መልስ ማዳመጥ እንችላለን፡፡ መልሱ ሲመጣ፤ እናም ይሆናል፤የጌታን አገልጋዮች ለመደገፍ በእምነት እናድጋለን፡፡
በቤተክርስቲያን የሚያገለግሉትን ድጋፍ ማሻሻል በተጨማሪ፤ ታላቅ ኃይላችን የሚጨምርልን ሌላ መንገድም እንዳለ እንማራለን፡፡ ለእኛም ታላቅ በረከቶችን ያመጣልናል፡፡ ይህም በቤት እና ቤተሰብ ውስጥ ነው፡፡
ከአባቱ ጋር በቤት ከሚኖር ወጣት የክህነት ተሸካሚ ጋር አውርቼ ነበር፡፡ አባታችሁ የእናንተን የእምነት ድጋፍ ሲሰማው ምን ማለት እንደሆነ ከራሴ ተሞክሮ ልንገራችሁ፡፡ በራሱ የሚተማመን መስሎ ሊታያችሁ ይችላል፡፡ ግን ከምታስቡት በላይ ፈተናዎችን ይጋፈጣል፡፡ አንዳንዴ ከችግሮቹ አሳልፎ የሚያስወጣውን መንገድ አያይም፡፡
አድንቆታችሁ ትንሽ ያግዘዋል፡፡ ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር ደግሞ የበለጠ ያግዘዋል፡፡ ነገር ግን በይበልጥ የሚረዱት ከልብ የመነጩ እንደዚህ አይነት ቃሎች ናቸው፤‹‹ አባዬ፣ ስለአንተ ፀልዬ ነበር፤ እናም ጌታ እንደሚረዳህ ተሰምቶኛል፡፡ ሁሉም ደህና ይሆናል፡፡ እንደሚሆን አውቃለሁ፡፡››
እንደዚህ አይነት ቃላቶች፤በሌላ አቅጣጫ፤ ከአባት ወደ ልጅ ኃይል አላቸው፡፡ ወንድ ልጅ ጠንካራ ጥፋት ሲያጠፋ፤ ምናልባትም መንፈሳዊ ነገር፤አልተሳካልኛም የሚል ስሜት ሊሰማው ይችላል፡፡ በዚያን ሰአት፤እንደ አባትነትህ፤ ምን ላድርግ ብለህ ስትጸልይ፤ መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ቃላት በአፍህ ውስጥ ከቶ ሊያስደንቅህ ይችላል፤ ‹‹ልጄ ፤ እስከመጨረሻው ድረስ አብሬህ ነኝ፡፡ ጌታ ይወድሀል፡፡ በእርሱ እርዳታ መመለስ ትችላላህ፡፡ እንደምትችል እና እንደምታደርገው አውቃለሁ፡፡ እወድኃለሁ፡፡››
በክህነት እና በቤተሰብ ውስጥ፤ እርስ በራሳችንን በእምነት መደጋገፍ መጨመር ጌታ እንድንፈጥረው የሚፈልገውን ፅዬን የምንገነባበት መንገድ ነው፡፡ በእርሱ እርዳታ እንችላላን፤ እናም እናደርገዋለን፡፡ ጌታን በሙሉ ልባችን፤ ጉልበታችን፤አእምሮአችን እና ኃይላችን ለመውደድ እና እርስ በእርስ እራሳችንን እንደምንወደው ለመዋደድ መማርን ይጠይቃል፡፡
ንፁህ በሆነው በክርስቶስ ፍቅር ስናድግ፣ ልባችን ይራራል፡፡ ያ ፍቅር ትሁት ያደርገናል እናም ንስሃ እንድንገባ ይመራናል፡፡ በጌታ እና እርስ በራሳችን ያለን መተማመን ይጨምራል፡፡ እናም ጌታ ቃል እንደገባው፤ አንድ ወደ መሆን እንሄዳለን፡፡2
የሰማይ አባታችን እንደሚያቃችሁ እና እንደሚወዳችሁ እመሰክራለሁ›› ኢየሱስ ህያው ክርስቶስ ነው፡፡ ይሄ የእርሱ ቤተክርሰቲያን ነው፡፡ የእርሱን ክህነት ተሸክመናል፡፡ የልምምድ ኃይላችንን ለማሳደግ እናም እርስ በእርስ ለመደጋገፍ የምናደርገውን ጥረት ያደንቀዋል፡፡ ይህን እመሰክራለሁ በቅዱሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፤ አሜን፡፡