የመንፈሳዊነትና የጥበቃ ምሽግን ገንቡ፡፡
የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ስንከተል፣ የአዳኝን የሃጢያት ዋጋ ክፍያ ስንጠቀምና ወደ ፊት በፍርሃት ሳይሆን በእምነት ስንገፋ ከባላጋራችን ማታለሎች እንሸሸጋለን፡፡
ወንድሞች እና እህቶች ይህ ጉባኤ ወደ መደምደሚያው ሲቃረብ ባለፉት ሁለት ቀናት በዚህ መድረክ ለሰማናቸው ለምክሮቹ፣ እውነቶች፣ እና ራእያት ለሰማያዊ አባታችን ምስጋናን አቀርባለሁ፡፡ የእርሱን ቅዱስ ቃል ለመናገር በተጠሩ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ተምረናል፡፡ በኋለኛው ቀን ራእዩ ጌታ “በእኔ ድምጽ ሆነ በአገልጋዮቼ ድምጽ ያም አንድ ነዉ.”ሲል ያስታውሰናል1
በዚህ የተሰበሰቡትን ሰፊ የቅዱሳን ጉባኤ ስመለከትና በአለም ዙሪያ አጠቃላይ ጉባኤን በመመልከት ላይ ያሉትን ሳስብ፣ በመጽሃፈ ሞርሞን ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ለኔፊያውያን ከትንሳኤው በኋላ በተገለጠበት ወቅት የነበረውን ስብስብ ያስታውሰኛል፡፡ ወንጌልን አስተማራቸውና እንዲህ ሲል አበረታታቸው “ስለዚህ ፣ ወደቤታችሁ ሂዱና፣ ስለተናገርኳችሁ ነገሮች አሰላስሉ፣ እናም ትረዱ ዘንድ በስሜ አብን ጠይቁት”2
“ወደቤታችሁ ሂዱና አሰላስሉ” የሚለው ነገር በዚህ በተቀደሰ ስብስብ በቤተክርስትያን አመራሮችና ነብያት የተነገረውን ቃል ወደ ልባችን መውሰድ ቀጣዩ ሂደት ነዉ፡፡ ክርስቶስን ያማከል ቤት ትንቢት እንደተነገረለት የእግዚአብሄር መንግስት በምድር ላይ በአንዱ ቀን ዲያቢሎስ “በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ይቆጣል እናም ጥሩ በሆነውም ላይ ለቁጣ ያነሳሳቸዋል” በተባለበት ወቅት ምሽግ ይሆነናል፡፡3
ሰዎች በታሪክ ሂደት ሁላ ጠላትን በውጪ ለማስቀረት ምሽጎችን ገንብተዋል፡፡ ብዙውን ጊዜ እነኚህ ምሽጎች እንደ ነብያት ያሉ ከአስፈሪ ሃይልና ከሚመጡ ጥቃቶች ማስጠንቀቂያ የሚሰጡባቸው የጥበቃ ማማን ያካተቱ ናቸው፡፡
በቀደሙት የዩታ አቅኚዎች ጊዜ የእኔ ቅድመ አያት ቶማስ ራዝባንድ እና ቤተሰቡ በውቧ ዋሳች የዩታ ተራሮች ውስጥ ከምትገኘው ሂበር ሸለቆ ውስጥ ከገቡትት ጥቂት የመጀመሪያ ሰፋሪዎች መሃከል ነበሩ፡፡
በ1985 (እ.አ.አ) ቶማስ ለራሳቸው ጥበቃ የተሰራውን የሄበር ምሽግ ግንባታ ደግፏል፡፡ በጣም ቀላል ቅርጽ ያለው ሆኖ ድንበሩ ከጥጥ ተክል ግንድ ጎን ለጎን ተቀምጠው የተሰራ ነበር፡፡ የጋራ ግድግዳ ያላቸው ከግንድ የተሰሩ ክፍሎች በምሽግ ውስጥ ተገንብተው ነበር፡፡ የተሰራው ስራ ለፈር ቀዳጅ ቤተሰቦች መሰረታቸውን በጣሉበት ወቅትና ጌታን በሚያመልኩበት ሁኔታ ደህንነታችወንና ጥበቃን ሰጥቷቸዋል፡፡
ለእኛም ቢሆን እንዲሁ ነው። ቤቶቻችን ከዚህ አለም ክፋት መሸሸጊያዎቻችን ናቸው ። በቤታችን የክርስቶስን ትዕዛዛት ለመከተል በመማር፣ ቅዱሳን ጽሁፎችን በማጥናትና በጋራ በመጸለይ፣ እርስ በርሳችን በቃልኪዳኑ ጎዳና እንድንጓዝ በመረዳዳት ወደ ክርስቶስ እንቀርባለን፡፡ በግል እና ቤተሰብ ጥናት አዲስ አጽኖት የተሰጠው የቤት ውስጥ ስርአተ ትምህርት ኑ ተከተሉኝ የሚለውየተቀረጸው “መለወጣችንን ለማጠናከርና ይበልጥ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንሆን” ለማድረግ ነው፡፡4 ይሄንን በማድረጋችን ጳውሎስ “አዲስ ፍጥረት” ሲል የጠራውን እንሆናለን5 ልባችንን እና ነፍሳችንን ከእግዚአብሄር ጋር በማጣመር፡፡ የጠላትን ብትር ለመመከት እና ለመጋፈጥ እንችል ዘንድ ይህ ጥንካሬ ያስፈልገናል ።
በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ላይ በተፈጠረ ታማኝነት ላይ ስንንኖር ፣ የመንፈስ ቅዱስን ሰላማዊ የሆነ መገኘት ይሰማናል፣ እርሱም ወደ እውነት ይመራናል፣ ለጌታ በረከት በብቃት እንድንንኖር ያበረታታናል፣ እግዚአብሄርም ህያው እንደሆነና እንደሚወደን ይመሰክርልናል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው በቤታችን ምሽግ ውስጥ ነዉ፡፡ ነገር ግን አስታውሱ፤ ቤቶቻችን ጠንካራ ሊሆኑ የሚችሉት በውስጡ እንደምንኖረው እንደያንዳንዳችን መንፈሳዊ ጥንካሬ ይወሰናል፡፡
ፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን እንዳስተማሩት “በሚመጡት ቀናት ያለ መንፈስ ቅዱስ መመሪያ፣ ምሪት፣ መጽናኛ እና ቋሚ ከሆነ ተጽዕኖ በመንፈሳዊነት ተቋቁመን ለመቀጠል አይቻልም” ብለዋል፡፡6 በዚህ ዘመን እንደ ጌታ ነብይ፣ ገላጭ፣ እና ራእይ ተቀባይነቱ፣ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን በምሽጉ ማማ ላይ እንደሚቀመጥ ጠባቂነቱ የጠላትን ወደፊት መግፋት ይታየዋል፡፡
ወንድምች እና እህቶች፣ እኛ ከሰይጣን ጋር ለሰው ልጆች ነፍስ ጦርነት ላይ ነዉ ያለነው፡፡ የጦር ሜዳው መስመር ከምድራዊ ሂዎታችን በፊት የተሳለ ነዉ፡፡ ሰይጣን እና አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት የሰማይአባታችን ልጆች ከእርሱ ከፍ ካለውየክብር እቅድ ፊታቸውን አዞሩ፡፡ ከዛ ጊዜ አንስቶ የጠላት ጭፍራዎች ታማኝ የሆኑትንና የአብን እቅድ የተቀበሉትን ሁላ ይዋጋሉ፡፡
ሰይጣን ቀናቱ ጥቂት እንደሆኑና ጊዜው እያጠረ መምጣቱን ያውቃል፡፡ እንደ ክፉ እና ጨካኝነቱ ሊያሸንፍ አይችልም፡፡ ቢሆንም የእያንዳንዳችንን ነፍስ ለማግኘት ያለው ትግል በርትቷል፡፡
ለራሳችን ጥበቃ ሲባል መንፈሳዊ የሆነና መጠበቂያ የሚሆን ምሽግን ለነብሳችን መገንባት ይኖርብናል፡፡ ክፉ በሆነው ሊናድ የማይችልን ምሽግ፡፡
ሰይጣን በግልጽም እባብ ነዉ፤ ጥበቃችንን ስናላላ፣ ተስፋ ስንቆርጥና በምንበሳጭ ወቅት ወደ አእምሮአችን እና ልባችን ሾልኮ ይገባል፡፡ በሚያጓጉ ነገሮች ይደልለናል፣ ሁሉም ቀላል እንደሚሆን ቃል የገባልናል፣ ወይም ዝቅ በምንልባችው ጊዜያት ጊዚያዊ የሆኑ ከፍታዎችን እንዲሰማን ያደርጋል፡፡ ኩራት፣ ክፋት፣ ቅናትና እና ንጽህና የጎደለን መሆንን እንደ ትክክል እንደሆነ እንዲሰማን ሲያደርግ እኛ “ልንደንዝዝ” እንችላለን፡፡7 መንፈስ ከእኛ ይርቃል፡፡ “ዲያቢሎስም ነፍሳቸውን እንዲህ ያታልላል እናም በጥንቃቄ ወደ ሲኦል ይመራቸዋል”8
በተቃራኒው የምስጋና መዝሙርን ወደ እግዚአብሄር ስንዘምር መንፈስ በሃይለኛው ይሰማናል እንደዚህ አይነት ቃላት ያላቸውን መዝሙሮች
የመንፈሳዊ ጥንካሬ ምሽግን ስንገነባ የጠላትን ወደፊት ጉዞ እንንዳለን፣ ጀርባችንን እናዞርበታለን፣ የመንፈስ ሰላምም ይሰማናል፡፡ ጌታችን እና አዳኛችን በምድረበዳ ሳለ በተፈተነበት ወቅት እርሱ እንዳለው የእርሱን ምሳሌ ተከትለን “ዞር በል ከፊቴ ሰይጣን” ማለት እንንችላለን 10 እያንዳንዳችን ከህይወት ተሞችሯችን በመነሳት ይሄንን እንዴት ማድረግ እንዳለብን መማር አለብን፡፡
የዚህ አይነቱ የጽድቅ አላማ በመጽሃፈ ሞርሞን በደንብ ተደርጎ ተብራርቷል ያም የጦር አዛዡ ሞሮኒ ኔፊያውያንን ከውሸታሞቹ፣ ደም ከተጠማቸውና የስልጣን ጥማት ካለባቸው አማሊኪያ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን መቋቋም እንዲት እንደሚችል ነዉ፡፡ ሞሮኒ ኔፊያውያንን “እናም በጌታ ይኖሩ ዘንድ እናም በጠላቶቻቸው የክርስትያኖች ጉዳይ ተብሎ የተጠራውን ይጠብቁ ዘንድ” እንዲከላከልለት ምሽግን ገነባ፡፡11 ሞሮኒ “በክርስቶስ ጽኑ እምነት ያለው ነበር,”12 እናም “የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ የሚጠብቅ… ክፋትን የሚቋቋም.”ነበር13
ላማናውያን ለውጊያ በመጡበት ወቅት በኔፋውያን ዝግጅት እጅግ ተደነቁ እናም ተሸነፉ፡፡ እናም ኔፊያውያን “ወደር በሌለው ሃይሉ ከጠላቶቻቸው እጅ ስላስለቀቃቸው ጌታ አምላካቸውን አመሰገኑ፡፡”14 ለውጪው መከላከያ ይሆን ዘንድ ምሽግን ገነቡ፣ እናም ውስጣቸውም ጥልቅ በሆነው ነፍሳቸው እምነታቸውን በኢየሱስ ከርስቶስ ላይ ገነቡ፡፡
በአስቸጋሪ ጊዜያት “ ይህንን ታላቅ ስራም ለመፈጸም በእግዚአብሄር እጅ መሳሪያ ለመሆ” እራሳችንን የምናጠናክርባቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው? 15 ቅዱሳን ጽሁፎችን እንመልከት፡፡
እኛ ታዛዦች ነን፡፡ ጌታ አባት ሌሂን ልጆቹን ወደ እየሩሳሌም ተመልሰው “ መዝገቦቹን ፈልገው ወደዚህ ወደ ምድረበዳ እንዲያመጡዋቸው” አዘዘው፡፡16 ሌሂ ጥያቄን አላነሳም ለምን እና እንዴት ብሎም አልተደመም፡፡ ኔፊም እንዲሁ “እሄዳለሁ፣ ጌታ ያዘዘኝንም ነገሮች አደርጋለሁ።” ብሎ ሲመልስም፡፡17
ልክ እንደ ኔፊ ባለው ፍቃድኛ የሆነ ታዛዥነት እንተገብራለን? ወይንስ ልክ እንደ ኔፊ ወንድሞች የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ጥያቄ ውስጥ ለመክተት እንዳዳለን? የነሱ እምነት መጉደል በስተመጨረሻ ከጌታ እንዳራቃቸው፡፡ ታዛዥነትን ከ “ልብ ቅድስና” ጋር 18ነው ጌታ ከኛ የሚጠይቀው፡፡
ኢያሱ እስራኤላውያንን ወደ ተስፋይቱ ምድር ይዞ ለመግባት ሲዘጋጅ “በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚያአብሄር ከናንተ ጋር ነውና ፅና አይዞህ፣ አትፍራ፣ አትደንግጥ” ያለውን ጌታ እናምናለን፡፡”19 ኢያሱም እነኚህን ቃላት አምኖ ህዝቡን “ ነገ እግዚአብሄር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ተቀደሱ” ሲል መከረ፡፡20 ጌታ የዮርዳኖስን ውሃ ከፍሎ የእስራኤላውያን የ40 አመት በበረሃ መንከራተታቸው ፍጻሜን አገኘ፡፡
የመጽሃፈ ሞርሞኑ ነብይ አቢናዳይ እንዳደረገው ሁሉ እኛም ለእውነት እንቆማለን፡፡ በንጉስ ኖህ እና ክፉ በሆኑት ቄሶቹ ፊት ታስሮ በቀረበ ወቅት አስሩን ትዕዛዛት አስተማረ ክርስቶስ“ በሰው ልጆች መካከል እንደሚወርድና ህዝቡንም እንደሚያድን” ሰበከ”21 ከዛም እርሱ በውስጡ ጠልቆ ባለው እምነት እንዲህ ሲል አወጀ “አቤቱ አምላኬ ነፍሴን ተቀበል”22 ካለ በኋላ አቢናዳይ “በእሳት ሞት ወደቀ”23
ቅዱስ ቁርባንን በመካፈልና በቤተመቅደስ በማምለክ ቃል ኪዳኖቻችንን እንገባለን እንዲሁም እናድሳለን፡፡ ቅዱስ ቁርባን የሰንበት አምልኳችን ወሳኝ ማዕከል ነዉ፣ “ሁልጊዜም የእርሱ መንፈስ ከእኛ ጋር ይሆን ዘንድ” ቃል ኪዳን የምንቀበልበት24 በዚህ የተቀደሰ ስነስርዓት የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በላያችን ለመውሰድ ቃል የምንገባበት፣ እርሱን ልንከተለው፣ እና እርሱ እንዳደረገው ሁሉ መለኮታዊ የሆነውን ስራው ለመስራት ሃላፊነታችንን የምንወጣበት ነው፡፡ በቤተመቅደስ “የዚህን አለም ነገሮች ወደጎን መተው”25 እና የጌታን አብሮነትና ድንቅ የሆነውን ሰላሙን እንዲሰማን ማድረግ እንችላለን፡፡ ከቅድመ አያቶች ከቤተሰቦቻችን እና ከአባታችን ጋር ስለሚኖረን ዘላለማዊ ህይወት ላይ ማተኮር እንችላለን፡፡ ፕሬዚዳንት ኔልሰን በቅርቡ በሮም “ከቤተመቅደሱ የሚመነጨው መልካም ሁሉ መመዘኛ የሌለው ታላቅ ነዉ” ማለታቸው አያስደንቅም፡፡26
በምናደርጋቸው ነገሮች ሁላ ጽናት ይኑረን፡፡ በየጊዜው የቱ ነው ትክክል የሆነውና ያልሆነው እያልን ለመወሰን በተደጋጋሚ ለመወሰን ከመጣር ይልቅ ግብረገብንና ማስተዋልን ማዳበር ይገባናል፡፡ ቀደምት የቤተክርስትያን ሐዋርያ የነበረው ጴጥሮስ ሲያስጠነቅቅ የተናገረውን ከልባችን ልንወስደው ይገባል፡፡ ማስጥንቀቂያውም “በመጠን ኑሩ ንቁም፣ ባላጋራችሁ ዲያቢሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና” ይላል፡፡27
ምሽጎቻችንን በትጋት ስናጠናክር ልክ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንሆናለን፣ እንደ እውነተኛ ደቀመዝሙሮቹ፣ የእኛ ነፍሳትም በርሱ ጥበቃ ስር ይሆናሉ፡፡
በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላችሁ የእናንተ ምስክርነት ለናንተ ምሽጋችሁ ነው ለነፍሳችሁም ጥበቃ፡፡ የእኔ ቅድም አያትና እንደሱ ያሉት ቀደምት ሰፋሪዎች የሂበርን ምሽግ ሲገነቡ፣ እያንዳንዱን ግንድ አንድ በአንድ ነበር ያስቀመጡት ምሽጉ “ሁሉ በጋራ እስከሚጋጠም”28 እናም ተጠብቀው ነበር፡፡ ምስክርነታችንም ልክ እንደዚህ ነው። አንድ በአንድ ከመንፈስ ቅዱስ ለራሳችን መንፈስ ሲናገረን ምስክርነትን እናገኛለን , የሚያስተምረንን “እውነትን ወደን የማይታይ.”29 የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ስንከተል፣ ከአዳኝን የሃጢያት ዋጋ ክፍያ ስንጠቀምና ወደ ፊት በፍርሃት ሳይሆን በእምነት ስንገፋ ከባላጋራችን ማታለሎች እንሸሸጋለን፡፡ ምስክርነቶቻችን ከሰማያት ጋር ያገናኙናል፣ እናም “በሁሉም ነገር እውነታ” የተባረክን እንሆናለን፡፡30 እናም ልክ በምሽግ እንደተጠበቁት አቅኚዎች ሁሉ በአዳኛችን እቅፍ ውስጥ በደህንነት የተከበብን እንሆናለን፡፡
ነብዩ ኢተር እንዲህ አስተማረ “ስለሆነም፣ በእግዚአብሔር የሚያምን በእርግጥ ለተሻለ ዓለም፣ አዎን፣ በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ በኩል ያለውን ስፍራ እንኳ ለማግኘት ተስፋ ይኖረዋል፤ ይኸውም ተስፋ በእምነት የሚመጣ ነው፤ ተስፋም ለሰዎች ነፍስ እንደመሃልቅ ነው፤ እነርሱንም ፅኑ እና የማይነቃነቁ እንዲሆኑ እናም ሁልጊዜም በርካታ መልካም ነገሮችን እንዲሰሩ፤ እግዚአብሔርንም እንዲያከብሩ ያደርጋቸዋል”31
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በጌታና በወንጌሉ ወደፊት ያለጥርጥር እንድትጓዙ በረከቴን እተውላችኋለሁ፡፡ የሚደናቀፉትን እጃችሁን በዙሪያቸው ላይ አድርጉ እና ባላችሁ የመንፈስ ጥንካሬ በፍቅር ወደ መንፈሳዊነትና የጥበቃ ምሽግ ምሯቸው፡፡ በምታደርጉት ነገር ሁሉ“ ልክ እንደ ኢየሱስ ለመሆን” 32 እሹ፣ ክፋትንና ፈተናን አጥፉ፣ልክ ትናንት በውድ ነቢያችን እንደተመከርነው ንስሃ ግቡ፣ በልባችሁ ታመኑ፣ ንጹህና ቀጥተኛ ሁኑ፣ ርህራሄንና ልግስናን አሳዩ፣ እናም ጌታችሁን እግዚአብሄርን በእውነተኛ ደቀመዝሙር መሰጠት አፍቅሩ፡፡
በወንጌል ላይ ያለን የኛ ምስክርነት፣ ቤታችን፣ ቤተሰባችን እና በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ያለን አባልነታችን የግላችን ምሽግ መጠበቂያ ይሆኑናል ክፉ ከሆነው ሃይል የሚከላከሉን፡፡ ይህንን የተቀደሰ ምስክርነቴን የምመሰክረው አዳኛችን እና ጌታችን በሆነው ስሙ በኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ፣ አሜን።