ክርስቶስ:- በጨለማ የሚበራው ብርሃን
የሚነደው የምስክርነት መብራታችሁ እየደከመ እንደሆነ ከተሰማችሁ እና ጨለማ ከቀረበ አይዟችሁ፡፡ ቃልኪዳንችሁን ለእግዝአብሔር ጠብቁ፡፡
በሴቶች መረዳጃ ህንፃ ውስጥ ያለው ቢሮዬ ፍፁም የሆነ የሶልት ሌክ የቤተ-መቅደስ እይታ አለው፡፡ ሁል ጊዜ አመሻሽ ላይ የቤተ መቅደስ የውጭ መብራት ይበራል፡፡ ቤተ-መቅደሱ ከመስኮቴ ውጭ በቋሚነት እየነደደ የሚበራ መብራት ነው፡፡
በዚህ ባለፈው የካቲት አንድ ምሽት ጸሐይዋ እንደጠለቀች ቢሮዬ ባልተለመደ መልኩ ጨልሞ ቀረ፡፡ በመስኮት ወደ ውጭ ስመለከት ቤተ-መቅደሱ ጨልሞ ነበር፡፡ መብራቶቹ አልበሩም፡፡ ድንገት የሃዘን ስሜት ተሰማኝ። ለብዙ አመታት በየምሽቱ ሳይ የነበረውን የቤተ-መቅደስ ጉልላት ማየት አልቻልኩም።
ብርሃን ለማየት ተስፋ ባደረኩበት ቦታ ጨለማን ማየቴ ፤ ለማደግ ከሚያስፈልጉን መሠረታዊ ነገሮች መካከል አንዱ ከብርሃን ምንጫችን ፤ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ተገናኝቶ መቆየት እንደሆነ አስታወሰኝ። እሱ የሀይላችን ምንጭ ፤ የአለም ብርሀን እና ህይወት ነው፡፡ ከእርሱ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ከሌለን መንፈሳዊ ሞት መሞት እንጀምራለን፡፡ ይህንንም በማወቅ ሁላችንም የሚገጥመንን አለማዊ ግፊቶችን ሴጣን ለመጠቀም ይሞክራል፡፡ ብርሃናችንን ለማደብዘዝ ፣ ግንኙነታችንን ለማሳጠር ፣ የሃይል ማመንጫውን ለመቁረጥ ፣ ብቻችንን በጨለማ ውስጥ ሊተወን ይሰራል፡፡ እነዚህ ጫናዎች በህይወት እስካለን የተለመዱ ናቸው፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ሊያገለን እና ብቸኛ ተጠቂዎች እንደሆንን ሊነግረን ይሞክራል፡፡
አንዳንዶቻችን በሃዘን ሽባ ሆነናል፡፡
ሀዘን ሲያሸንፈን ፣ ህይወት እጅግ በጣም ጎድታን መተንፈስ ሲያቅተን ፣ በእያርኮ መንገድ ላይ እንደነበረው ሰውዬ ስንደበደብ እና ለሞት ስንተው ክርስቶስ ይመጣል ፤ እናም በቁስላችን ላይ ዘይት ይቀባል ፣ በርህራሄም ያነሳናል ፣ ያለብሰናል ፣ ወደ ቤት ያስገባናል ፣ ይጠብቀናል፡፡ 1 በሀዘን ላይ ላለን “በጀርባችሁም እንኳን ሊሰማችሁ እንዳይቻላችሁ በትከሻችሁ ላይ ያለውን ሸክም አቃልላችኋለሁ፣…እኔ ጌታ እግዝአብሔር በአውነት በመከራቸው ጊዜ ህዝቡን እንደምጎበኝ ታውቁ ዘንድ ነው፡፡” ይላል፡፡”2ክርስቶስ ቁስልን ይፈውሳል።
አንዳንዶቻችን እንዲሁ በጣም ደክሞናል፡፡
ሽማግሌ ሆላንድ እንዲህ ሲሉ አፅናንተውኝ ነበር “ካለን ጥንካሬ በላይ በፍጥነት እንድንሮጥ አልታቀደም፡፡ ... ይህ ሆኖ ሳለ ፤ አውቃለሁ ብዙዎቻችሁ በጣም በጣም በፍጥነት ትሮጣላችሁ እናም የሃይልና የስሜታችሁ አቅርቦት አንዳንዴ ወደ ባዶነት ይጠጋል፡፡” 3 እንዲሆን የምንጠብቀው ሲያሳስበን አረፍ በማለት የሰማይ አባትን ምን መተው እንዳለብን መጠየቅ እንችላለነን፡፡ ምን አለማድረግን መማር ፤ ከህይወት ልምምዳችን ክፍል ነው፡፡ ቢሆንም አንዳንዴ ህይወት አድካሚ ትሆናለች፡፡ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” በማለት ቃል ይገባልናል።4
ክርስቶስ አብሮን ለመሆን እና ክብደታችንን ለማቅለል ፣ ለመጎተት ፍቃደኛ ነው፡፡ ክርስቶስ እረፍት ነው፡፡
አንዳንዶቻችን ከተለመደው ባህል ጋር የማንገጥም ሆኖ ይሰማናል
በተለያዩ ምክንያቶች ተቀባይነት ያለን ወይም የሚገባን አይመስለንም፡፡ አዲስ ኪዳን እየሱስ ለሁሉም ለመድረስ ያደረገውን ታላቅ ጥረት ያሳያል ፤ ለለምፃሞች ፣ ለቀራጮች ፣ ለህጻናት ፣ ለገሊላዊያን ፣ ለጋላሞቶች ፣ ፣ ለሴቶች ፣ ለአሕዛብ ፣ ለሃጢያተኞች ፣ ለሰማራዊያን ፣ ለባል የሞተባቸው፣ ለፈሪሳዊያን፣ ለሮም መቶ አለቃዎች ፣ ለዝሙት ፈጻሚዎች እና በአምልኮ ስርዓት ንፁ ላልሆኑ፡፡ በእያንዳነዱ ታሪክ ክርስቶስ በህብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ለሌላቸው ሲደርስ ነበር፡፡
ሉቃስ 19 በእያሪኮ ዘኪዎስ ስለሚባል አንድ የቀራጮች አለቃ ይናገራል፡፡ ክርስቶስ በመንገድ ሲያልፍ ለማየት አንድ ዛፍ ላይ ይወጣል፡፡ አጭር ፤ የሮም መንግስት ተቀጣሪ ነበር ፤ እንደ ጉቦኛና እንደ ሃጥያተኛ ይታያል፡፡ ኢየሱስ ዛፍ ላይ አየው ፤ ጠርቶትም “ዘኬዎስ ሆይ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ” አለው፡፡ 5 የዘኬዎስን ልብ መልካምነት እና ለሌሎች ያደረገውን ነገር ኢየሱስ ባየ ጊዜ የእሱን መስዋዕትነት አንዲህ ሲል ተቀበለ “እርሱ ደግም የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል” አለው።6
ክርስቶስ በርህራሄ ለኔፍያውያን “ ማናችሁም ከዚ እንዳትርቁ ማዘዜን ተገንዝባችኋል” ብሏል፡፡7 ጴጥሮስ በ ሃዋርያት ስራ 10 ላይ “እግዚአብሔር ማንንም ሰው ርኩስና የሚያፀይፍ ነው እንዳልል አሣየኝ” ሲል ያ ታላቅ መረዳት ነበረው፡፡ 8 አንዳችን ለሌላው ፍቅርን ማሳየት የክርስትያን ደቀ-መዛሙርቶች እና የኋላኛው ቀን ቅዱሳን ፅኑ ግዴታ ነው፡፡9 ክርስቶስ ለዘኬዎስ እንደሰጠው አይነት ተመሳሳይ ጥሪ ያቀርብልናል። ”እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለው ፤ ማንም ድምጼን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለው ከእርሱም ጋር እራት እበላለው እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል፡፡” 10ክርስቶስ በዛፋችን ላይ ያየናል
አንዳንዶቻችን በጥያቄዎች እየተወዛገብን ይሆናል
ከጥቂት አመታት በፊት መልስ ላገኝላቸው ባልቻልኳቸው ነገሮች አዝኜና ተበሳጭቼ ነበር፡፡ አንድ ቅዳሜ ንጋት ፤ አንዲት ህልም አለምኩ፡፡ በዚያ ህልም አንድ ትንሽ ቤት አየሁ ፤ እናም እዛ ሄጄ ውስጡ መቆም እንዳለብኝ ተረዳሁ፡፡ አምስት እጥፍቶች ከበውት ነበር ፤ ነገር ግን መስኮቱ ከዲንጋይ የተሠራ ነው። በጣም ጠባብ ስለነበረ ፤ ወደ ውስጥ ላለመግባት አጉረመረምኩ፡፡ ከዚያም የያሬድ ወንድም በትዕግስት ድንጋዮችን ወደ ንፁህ ብርጭቆ እንዳቀለጠ ወደ አዕምሮዬ ሀሳብ ገባ፡፡ ብርጭቆ ለውጥ ያደረገ ድንጋይ ማለት ነው፡፡ ጌታ የያሬድን ድንጋዮች ሲነካ በጨለማ መርከቦች ውስጥ ብርሃን አበሩ፡፡ 11 በድንገት ከማንኛውም ቦታ ይልቅ እዛ ቤት ውስጥ ለመግባት በፍላጎት ተሞላሁ፡፡ ለኔ “ለማየት” ዋነኛው እና ብቸኛው ቦታ ሆነ፡፡ ሲያስጨንቁኝ የነበሩ ጥያቄዎቼ አልሄዱም ፤ ነገር ግን ከነቃሁ በኋላ በጭንቅላቴ ውስጥ ደምቆ የነበረው ጥያቄ ፤ “አንዴት ነው አንደ ያሬድ ወንድም ድንጋይሽ ወደ ብርሃን እንዲቀየር እምነትሽን ልትጨምሪ ምችይው?” የሚል ነበር፡፡12
ሟቹ አዕምሮዋችን በተሰበሰበ ጥቅል መረዳትንና ትርጉምን እንዲሻ በስርዓት ተሰርቷል ፡፡ በህይወታችን ላይ ያለው መጋረጃ ለምን በጣም ወፍራም እንደሆነ ምክንያቶቹን ሁሉ አላውቅም፡፡ በዘላለማዊ እድገት ደረጃ ይህ ሁሉንም መልሶች የምናገኝበት ቦታ አይደለም፡፡ ይህ አርግጠኛነታችንን ወይም አንዳንዴ ተስፋችንን በማናያቸው ነገሮች መረጃ ላይ የምንገነባበት ደረጃ ነው፡፡ ማረጋገጫ ሁልጊዜ በቀላሉ ልንስላቸው በምንችላቸው መንገዶች አይመጣም ፤ ነገር ግን በጨለማችን ውስጥ ብርሃን አለ፡፡ እየሱስ “የአለም ብርሃን ህይወትም፣ እውነትም ነኝ” ብሏል፡፡13 እውነትን ለሚሹ ፤ በመጀመሪያ ፤ የሞኝነት ከድንጋይ የተሰራ ፤ አስፈሪ ጠባብ መስኮት ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን በትዕግስት፣ እና በታማኝ ጥያቄዎች ኢየሱስ የድንጋይ መስኮታችንን ወደ መስታወትና ብርሃን ሊቀይር ይችላል፡፡ክርስቶስ የሚታይ ብርሃን ነው፡፡
አንዳንዶቻችን መቼም በቂ እንደማንሆን ይሰማናል፡፡
በብሉይ ኪዳን ላይ ያለው አለላ ቀለም ደማቅ ቀይ ብቻ ሳይሆን ቶሎ ቀለም ተቀባይም ነው ፤ ይህ ማለት ከባዘቶ ጋር የተጣበቀ ደማቅ ቀለም ነው። እናም ምንም ያህል ጊዜ ቢታጠብ አይለቅም፡፡ 14 ሰይጣን ቦጌ ደማቅ ቀይ የተቀባ ፤ ነጭ ባዘቶ መቼም ተመልሶ ነጭ ሊሆን አይችልም በማለት ምክንያት ያቀርባል። ነገር ግን ክርስቶስ “መንገዴ ከመንገዳችሁ ከፍ ያለ ነው” ይላል፡፡ እናም የፀጋው ተአምር ከሃጥያቶቻችን ንሰሃ ስንገባ የሱ አለላ ደም ንፁ ያደርገናል፡፡15 ይህ ምክንያታዊ አይደለም ፤ ነገር ግን አውነት ነው፡፡
“እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።” 16 ጌታ በጥብቅ ፤ እሱ ወይም እሷ ” ፣ እነሆ ለሀጥያቶቹ ንስሀ የሚገባም ፣ ይቅርታን ይቀበላል ፣ እናም እኔ ጌታ ደግሜ አላስታውሳቸውም” ይላል። 17 በዋነኛነት ፤ ኑ እንወቃቀስ፡፡18 ስህተትን ሰርታችኋል ፤ ሁሉም ይጎለዋል፡፡ 19 ወደኔ ኑ እና ንስሃ ግቡ 20 ሀጥያቱን ደግሜ አላስታውሰውም፡፡21 ዳግም ሙሉ መሆን ትችላላችሁ፡፡22 ለናንተ የምትሠሩት ስራ አለኝ፡፡23ክርስቶስ ባዘቶን ነጭ ያደርጋል፡፡
ነገር ግን ተግባራዊ እርምጃዎቹ ምንድናቸው? ስንደክም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይል ዳግመኛ ለመገናኘት ቁልፉ ምንድነው? ፕሬዘዳንት ኔልሰን በጣም በቀላሉ አድርገው “ቁልፉ የተቀደሰ ቃልኪዳን መግባት እና ማድረግ ነው...”ብለው ተግረወዋል፡፡ ይህ የተወሳሰበ መንገድ አይደለም፡፡24 ክርስቶስን የህይወታችሁ ማዕከል አድርጉ፡፡ 25
የሚነደው የምስክርነት መብራታችሁ እየደከመ እንደሆነ ከተሰማችሁ እና ጨለማ ከቀረበ አይዟችሁ፡፡ ቃልኪዳንችሁን ለእግዝአብሔር ጠብቁ፡፡ ጥያቄዎቻችሁን ጠይቁ፡፡ በትዕግስት ድንጋይን ወደ መስታወት አቅልጡ፡፡ አሁንም ድረስ ወደሚወዳችሁ ክርስቶስ ተመለሱ፡፡
ክርስቶስ “እኔ በጨለማ የማበራ ነኝ እናም ጨለማ አይረዳኝም” ብሏል፡፡ 26 ይህ ማለት ጨለማ ምንም ያህል ቢሞክር ያንን ብርሃን ሊያስወጣው አይችልም፡፡ መቼም። የእሱ ብርሃን ከእናንተ ጋር እንደሚሆን ማመን እንችላለን፡፡
እኛ ወይም የምንወዳቸው ሰዎች ለጊዜው ሊጨልሙ ይችላሉ፡፡ በሶልት ሌክ ቤተ-መቅደስ ጉዳይ ፤ አስተዳደሪው ፤ ወንድም ቮል ኋይት የስልክ ጥሪ ወዲያውኑ ደረሰው፡፡ ሠዎች ልብ ብለውታልና፡፡ በቤተ-መቅደሱ መብራቶች ላይ ምን ችግር ተፈጠረ? መጀመሪያ ሠራተኛው በአካል እያንዳንዱን የቤተ-መቅደሱን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ማብሪያና ማጥፊያ ተጠቅሞ በእጁ አበራ፡፡ ከዚያም የሀይል መስጫ ውስጥ ባትሪዎችን ቀየሩ እና ምን መስራት እንዳቆመ ለማወቅ ፈተሹአቸው፡፡
መብራቶቹን በራሳችን ለመመለስ መሞከር ይከብዳል፡፡ ጓደኞች ያስፈልጉናል፡፡ አንዳችን ለሌላው እናስፈልጋለን ፡፡ ልክ እንደ ቤተ-መቅደሱ ሰራተኛ በአካል በመገኘት ፣ መንፈሳዊ ባትሪያችንን እንደገና በመሙላት ፣ የተበላሸውን በማስተካከል እርስ በራሳችን ልንረዳዳ እንችላለን፡፡
የግላችን መብራት ዛፍ ላይ እንዳለ አንድ ብቻ አንፖል ሊሆን ይችለል፡፡ ነገር ግን ትንሽዋን መብራታችንን እናበራለን፡፡ እናም በአንድነት ሚሊዮኖች ሰዎችን ወደ ቤተ-መቅደስ ቃልኪዳንና ወደ ጌታ መሳብ እንችላለን፡፡ ከሁሉም በተሻለ ፕሬዝዳንት ኔልሰን እንዳበረታቱን ቃል ኪዳናችንን በመጠበቅ ቀላል ተግባር ፤ የአዳኛችንን ብርሃን ወደራሳችን እና ለኛ አስፈላጊ ለሆኑ ሰዎች ማምጣት እንችላለን፡፡ ያንን ታማኝ ተግባር ጌታ በሃይልና በደስታ ፤ በተለያዩ መንዶች ይሸልመናል፡፡27
የተወደዳችሁ እንደሆናችሁ እመሠክራለው፡፡ ጌታ ምን ያህል እየሞከራችሁ እንደሆነ ያውቃል፡፡ መሻሻል እያሳያችሁ ነው፡፡ ቀጥሉበት፡፡ የተደበቀውን መስዋዕቶቻችሁን ሁሉ ያያል ፤ ለእናንተ እና ለምትወዷቸው መልካም ይቆጥራቸዋል፡፡ ስራችሁ የከንቱ አይደለም፡፡ ብቻችሁን አይደላችሁም፡፡ የእርሱ ስም አማኑኤል ማለት “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ማለት ነው፡፡28 በእርግጥም እርሱ ከናንተ ጋር ነው፡፡
ምንም እንኳን ከርቀት ለማየት ጨለማ ቢሆንም በቃልኪዳን መንገድ ላይ ጥቂት ተጨማሪ እርምጃዎችን ውሰዱ፡፡ መብራቶቹ ተመልሰው ይመጣሉ፡፡ እውነቱን በክርስቶስ ቃል እመሰክራለው፣ በብርሀን ተሞልተዋል ፤ ቃላቱም እንዲህ ይላሉ ፥ “ወደ እኔ ቅረቡ እና እኔም ወደ እናንተ እቀርባለሁ ፤ ተግታችሁም ፈልጉኝ እናም ታገኙኝማላችሁ ፤ ለምኑ ፣ ትቀበላላችሁ ፤ አንኳኩ ፣ ይከፈትላችሁማል።” 29 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።