2010–2019 (እ.አ.አ)
በበረከት መትረፍረፍ
የሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


በበረከት መትረፍረፍ

እግዚአብሄር ለኛ ሊሰጣቸው የሚሻቸው ብዙዎቹ በረከቶች የኛን ድርጊት ይሻሉ፡፡ — በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ላይ የተመሰረተ ድርጊት፡፡

የሰማይ አባታችን እና ኢየሱስ ክርስቶስ እያንዳንዳችንን ለመባረክ ይፈልጋሉ፡፡1 እነኚህን በረከቶች እንዴት አድርግን ልንቀበላቸው እና ልናገኛቸው እንችላለን የሚለው ጥያቄ ለዘመናት የሃይማኖታዊ ክርክር እና ውይይት መንስኤ ሆኗል፡፡2 አንዳንዶች በረከቶች የልፋት ውጤት ናቸው ፤ ልንቀበላቸው የምንችለው በስራችን ብቻ ነው ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ እግዚአብሄር ማንን እና እንዴት መባረክ እንዳለበት ቀድሞ አዘጋጅቷል ስለዚህም እነዚህ ምርጫዎች ሊሻሩ አይችሉም በማለት ይከራከራሉ፡፡ ሁለቱም አቋሞች መሰረታዊ የሆነ ጉድለት አለባቸው፡፡ ከሰማይ የሚመጡ ማንኛቸውም በረከቶች “ለመልካም ስራ እንደሚሰጥ ሜዳልያ” በማጠራቀም የሚገኙም ሆነ ያለምንም ጥረት ልክ እንደ ሎተሪ እጣ ይወጣልኝ ይሆን እያልን የምንጠብቃቸው አይደሉም፡፡ አይደለም! እውነታው በቀላሉ በግልጽ የሚታይ አይደለም ፤ነገር ግን አፍቃሪ በሆነ የሰማይ አባት እና ወራሹ ልንሆን በምንችለው — በእኛ መሃከል ላለው ዝምድና ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ የተመለሰው ወንጌል ፣በረከቶች በፍጹም በስራ እንደማይገኙ ይገልጻል ፤ይልቁንም በመነሻው እና በሂደቱ በእኛ በኩል በእምነት ላይ የተመረኮዙ ተግባራት አስፈላጊነት አላቸው፡፡፡3

ምስል
የእንጨት ክምር

ከእግዚአብሄር በረከቶችን እንዴት እንቀበላለን የሚለውን ስንመለከት ከሰማይ የሚመጡ በረከቶችን እንደ ትልቅ የተከመረ እንጨት አድርግን እስኪ እንውሰዳቸው፡፡ የቁርጥራጭ እንጭቶች ርብራብ ከላዩ የተደረገበት የሳጋቱራ ቁልል መሃልን አስቡ፡፡ ከላያቸው አጣናዎች፣ ከዚያም ትናንሽ ግንዶች በመጨረሻም ትላልቅ ግንዶች ይደረጋሉ፡፡ የእንጨት ክምሩ ተቀጣጣይ የሆነን ብዙ ጋዝ በውስጡ ስለያዘ ሙቀትና ብርሃንን ለብዙ ቀናት መስጠት ይችላል፡፡ ከእንጨት ክምሩ አጠገብ የተቀመጠ ከፎስፈረስ የተሰራ ጫፍ ያለው አንድ የክብሪት እንጨት አለ ብላችሁ አስቡ፡፡4

ምስል
የእንጨት ክምር ከክብሪት ጋር

የእንጨት ክምሩ ያለውን ሃይል እንዲሰጥ ክብሪቱ ሊለኮስና ቁርጥራጭ እንጭቶቹ ሊያያዙ ይገባል፡፡ ቁርጥራጭ እንጭቶቹ በፍጥነት ይቀጣጠላሉ ከዚያም ተለቅ ተለቅ ያሉ እንጨቶችን ማንደድ ይጀምራል፡፡ እሳቱ አንዴ መቀጣጠል ከጀመረ እንጨቱ ነዶ እስኪያልቅ አልያም እሳቱ ኦክስጅን እስኪያጣ ድረስ መንደዱን ይቀጣላል፡፡

ምስል
የሚነድ የእንጨት ክምር

ክብሪት መጫሩና ቁርጥራጭ እንጨቶቹን መለኮሱ የእንጨቱን የመንደድ ሃይል እንዲወጣ የሚያደርግ ትንሽ ድርጊት ነው፡፡ 5 ምንም ያህል የእንጨቱ ክምር ብዛት ቢኖረውም እንኳን ክብሪቱ እስካልተጫረ ድረስ ምንም አይፈጠርም፡፡ ክብሪቱ ተለኩሶ ማገዶው ላይ ካልተደረገ በስተቀር ከክብሪቱ የሚወጣው ብልጭታ እና ሙቀት በጣም ትንሽ ነው እንጨቱ ውስጥም ያለው የመቀጣጠል ሃይል ሳይወጣ ይቀራል፡፡ ኦክስጅን በማንኛውም ሰአት የማይገኝ ከሆነ የመቀጣጠል ሁደት ይቋረጣል፡፡

በተመሳሳይ መንገድም እግዚአብሄር ለኛ ሊሰጣቸው የሚሻቸው ብዙዎቹ በረከቶች የኛን ድርጊት ይሻሉ፡፡ — በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ላይ የተመሰረተ ድርጊት፡፡ በአዳኝ ላይ ያለን እምነት የድርጊት እና የሀይል መርህ ነው።6 በቅድሚያ በእምነት እንተግብራለን፣ከዚያም ሃይል ይከተላል —እንደእግዚአብሄር ፍቃድና ጊዜ ፡፡ ቅደም ተከተሉ በጣም አስፈላጊ ነዉ7 የሚጠበቀው ድርጊት ሁልጊዜም ቢሆን በመጨረሻ ከምናገኘው በረከት ጋር ሲነጻጸር በጣም ትንሽ ነዉ፡፡ 8

የጥንት እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር በሚጓዙበት ወቅት በራሪ እሳታም እባቦች ወደነሱ በመጡ ጊዜ ምን እንደተፈጠረ ከግምት አስገቡ፡፡ መርዛማ በሆነ እባብ መነደፉ ለሞት የሚዳርግ ነበር፡፡ ነገር ግን በሙሴ ተቀርጾ ግንድ ላይ የተሰቀለን ከነሃስ የተሰራን እባብ በማየት ማንኛውም የተነደፈ ሰው መዳን ይችል ነበር፡፡ 9 ወደ አንድ ነገር መመልከት ምን ያህል ጉልበት ይጠይቃል? መመልከት የቻሉት ሁሉ የሰማይን ሃይል ማግኘትና መዳን ችለዋል፡፡ አንዳንድ እስራኤላውያን ወደ ብርማው እባብ ሳያዩ ስለቀሩ ሞተዋል፡፡ ምናልባትም ለመመልከት እምነት ጎድላሏቸውይሆናል፡፡ 10 ምናልባትም እንደዚህ አይነት ቀላል ድርጊት ቃል የተገባውን አይነት ድነት ያመጣል ብለው አላመኑም፡፡ ወይንም ደግሞ ፈቅደው የእግዚአብሄርን ነብይ ምክር ላለመስማት ልባቸውን አደንድነው ይሆናል፡፡11

ከእግዚአብሄር የሚፈሱትን በረከቶች የማነቃቃት መርህ ዘላለማዊ ነው፡፡ ልክ እንደ ጥንት እስራኤላውያን እኛም ብንሆን መባረክ እንችል ዘንድ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነታችንን ተግባራዊ ልናደርግ ይገባናል፡፡ እግዚአብሄር እንዲህ ሲል ገልጾታል “ይህ አለም ከመመስረቱ አስቀድሞ ሁሉም በረከቶች የሚመረኮዙበት በሰማያት ውስጥ ሊሻር የማይችል የታወጀ ህግ አለ-- እና የትኛውንም በረከት ከእግዚአብሄር ሰናገኝ፣ ሁሉም ነገር በተመረኮዘበት ለዚያ ህግ ታዛዥ በመሆን ነዉ፡፡” ይህን ህግ ካከበርን፣ በረከቶችን እንቀበላለን።12 ይህን ካልን ዘንዳ በረከት ለፍተን የምናከማቸው አይደለም፡፡ ይህ እሳቤ የተሳሳተ ነው ነገር ግን ብቁ ልንሆን ይገባናል፡፡ የኛ መዳን የሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ስራና ጸጋ ብቻ ነው፡፡ 13 የርሱ የኋጥያት ክፍያ መስቃዕትነት ግዝፈት ማለት የተከመረው እንጨት የማይለካ ሲሆን የኛ ትንሽ ድርጊት ቢለካ ዜሮ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ዜሮ ሊሆን አይችልም፣ አነስተኛም አይደሉም፣ በጨለማ ውስጥ የተለኮሰ ክብሪት ከብዙ ማይል ርቀት እንኳን ይታያል፡፡ በግልጽም፣ ከሰማይም ጭምር ይታያል ምክንያቱም የእግዚአብሄርን በረከት ለመለኮስ ጥቂት ብቻ ተግባር ስለሚጠይቅ፡፡ 14

የእግዚአብሄርን ተፈላጊ በረከቶች ለማግኘት በእምነት መተግበር አለብን፣ ያም ልክ እንደ ክብሪቱ ምሳሌነት በረከቱ የተገባበትን ሰማያዊ የሆነ ሃይልን መጫር እንችላለን፡፡ ለምሳሌ የጸሎት አንደኛው ክፍል እግዚአብሄር ያዘጋጃቸውን በረከቶችን ፣,ለኛ ሊሰጣቸው ያዘጋጃቸውን በረከቶች ከጠየቅን ብቻ የሚሰጠንን እንድንጠይቅ ነዉ፡፡15 አልማ ምህረትን ያገኝ ዘንድ አለቀሰ፣ ህመሙም ተቀረፈ፣ ከሃጥያቱ ትውስታ የነበረው መረበሹ ከዛ በኋላ አቆመ፡፡ ደስታው ሃዘኑን ሻረ፣ ይህም የሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ባለው እምነት አምርሮ በማልቀሱ ነዉ፡፡ 16 ለኛ የሚያስፈልገው የማነቃቂያ ሃይል በክርስቶስ ላይ በቂ እምነት ኖሮን እግዚአብሄርን በጸሎት በመጠየቅ የሱን ፍቃድ መቀበልና የሱን የመልስ ጊዜ መቀበል ነዉ፡፡

ብዙውን ጊዜ ለበረከት የሚፈለገው የማነቃቂያ ሃይል ከመመልከትና ከመጠየቅ የበለጠ ይፈልጋል ፣ ቀጣይነት ያላቸው ተደጋጋሚ የሆኑ በእምነት የተሞሉ ተግባራት ያስፈልጋሉ፡፡ በ 19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ብሪግሃም ያንግ የተወሰኑ የኋለኛው ቀን ቅዱሳንን በረሃማ በሆነው የሰሜን አሜሪካ ግዛት አሪዞናን እንዲገመግሙና እንዲሰፍሩበት አዘው ነበር፡፡ አሪዞና እንደደረሱ የተላኩት ቡድኖች ወሃ እጥረት አጋጥሞአቸው ስለነበር እንጠፋለን ብለው ሰጉ፡፡ እግዚአብሄርን እንዲረዳቸው ተማጸኑ፡፡ ወዲያውም ዝናብ ዘነበ በረዶም ጣለ ይህም በርሜሎቻቸውን በውሃ እንዲሞሉ፣ ለከብቶቻቸውን እንዲሰጡ ሆነ፡፡ ተበረታተውና ደስተኛ ሆነው ወደ ሶልት ሌክ ሲቲ በእግዚአብሄር ደግነት እየተደሰቱ ተመለሱ፡፡ በተመለሱበትም ወቅት የጉዟቸውን ዝርዝር ለ ብሪግሃም ያንግ ሲያቀርቡ መደምደሚያቸው አሪዞና ለሂዎት አመቺ ያልሆነ ቦታ እንደሆነ ነበር፡፡

ምስል
ብሪገም ያንግ

በሪግሃም ያንግ ሃተታውን ካዳመጠ በኋላ በክፍሉ ከነበሩት አንዱን ሰው ስለ ጉዞውና ስላጋጠማቸው ተአምር ምን እንደተሰማው ጠየቀው፡፡ ያም ሰው ፤; ዳኔል ደብሊው ጆንስ እምባ እየተነነቀው እንዲህ ሲል መለሰ “ከሞላሁ በኋላ ፣ እቀጥላለሁ፣ ድጋሚም እጸልያለሁ” አለ ወንድም ቢሪግሃምም እጁን ወንድም ጆንስ ላይ አድርጎ እንዲህ አለ “የሚቀጥለዉን የአሪዞና ጉዞ የሚመራው ሰው ይህ ነዉ” አለ፡፡ 17

ምስል
ዳንኤል ደብሊው .ጆንስ

ሁላችንም መንገዳችንን የቀጠልበትን እና በድጋሚ የጸለይንበትን ጊዜ እናስታውሳለን፣ ከዛም በረከት ተገኝቷል፡፡ የሚካኤል እና ማሪአን ሆልምስ ተሞክሮ ይህንን መርህ ያብራራልናል፡፡ ሚካኤልና እኔ እንደ አካባቢ ሰባዎች አንድ ላይ አገልግለናል፡፡ ሁልጊዜም ጸሎት እንዲያደርግ ሲጠየቅ እደሰት ነበር ምክንያቱም ጥልቅ የሆነዉ መንፈሳዊነቱ ግልጽ ነበር ፤ነከእግዚአብሄር ጋር እንዴት እንደሚነጋገር ያውቅ ነበር፡፡ እሱ ሲጸልይ መስማት እወዳለሁ፡፡ ማሪያን እና ሚካኤል እንደተጋቡ አካባቢ ግን ጸሎትን አያደርጉም ነበር ቤተክርስትያንም አይካፈሉም ነበር፡፡ በሶስት ትንንሽ ልጆቻቸውና በጣም ውጤታማ የሆነ የግንባታ ድርጅታቸው በጣም ባተሌ ነበሩ፡፡ ሚካኤል የሃይማኖት ሰው ነኝ ብሎ አያስብም፡፡ በአንዱ ምሽት ኤጲስ ቆጶሳቸው ወደቤታቸው መጥቶ ጸሎት ማድረግ እንዲጀምሩ አበረታታቸው፡፡

ኤጲስ ቆጶሱ ከሄደ በኋላ ሚካኤልና ማሪአን ለመጸለይ እንደሚሞክሩ ወሰኑ፡፡ ወደ መኝታ ከማቅናታቸው በፊት በአልጋቸው አጠገብ ተንበርክከው እናም ምቾት ሳይሰማቸው ሚካኤል ጀመረ፡፡ ከጥቂት አስቸጋሪ የሆኑ የጸሎት ቃላት በኋላ ሚካኤል ጸሎቱን አቋርጦ “ማሪአን ይህን ማድረግ አልችልም” አለ፡፡ ተነስቶ መሄድ ሲጀምር ማሪአን እጁን ይዛ ወደ እንብርክኩ መልሳው እንዲህ አለችው “ማይክ ይህን ማድረግ ትችላለህ፡፡ በድጋሚ ሞክር” አለችው፡፡ በዚህ ማበረታቻ ሚካኤል አጭር ጸሎትን አደረገ፡፡

እነ ሆልምስ በተደጋጋሚ መጸለይ ጀመሩ፡፡ ከጎረቤታቸው የመጣውን ቤተክርስትያን የመካፈል ግብዣም ተቀበሉ፡፡ ወደ መሰብሰቡያ አዳራሹ እየገቡ ሳለ የመክፈቻ መዝሙሩን ሲሰሙ መንፈስ “ይህ እውነት ነዉ” ሲል አንሾካሾከላቸው፡፡ በኋላም ማንንም ሳያይ እንዲሁም ሳይጠየቅ ሚካኤል ከመሰብሰቢያው ቦታ ቆሻሻ ያወጣ ጀመር፡፡ ይህንን በማድረግ ላይ ሳለ ጥልቅ በሆነ ስሜት “የኔም ቤት ነዉ” የሚል ስሜት አደረበት፡፡

ምስል
ወጣት ሚካኤል እና ማሪአን ሆልምስ

ሚካኤልና ማሪአን የቤተክርስትያን ጥሪን ተቀብለው በአጠቢያቸውና በካስማቸው አገለገሉ፡፡ እርስ በርሳቸውና ከሶስት ልጆቻቸውም ጋር ታተሙ፡፡ ተጨማሪ ልጆችም ተወለዱ የቤተሰቡም ቁጥር አስራ ሁለት ደረሰ፡፡ እነ ሆልምስ ሁለት ጊዜ የሚሲዮን ፕሬዝደንትና አጋር ሆነው አገልግለዋል፡፡

ምስል
ሚካኤል እና ማሪአን ሆልምስ ዛሬ

የመጀመሪያው አስጨናቂ ጸሎት ትንሽና በእምነት የተሞላ ተግባር ሰለነበር ከሰማይ በረከትን አውርዷል፡፡ ሆልምሶች ነበልባሉን በእምነት የመገቡት ቤተክርስትያን በመካፈልና በማገልገል ነዉ፡፡ ለአመታት የዘለቀው ጽኑ የሆነው ደቀመዝሙርነታቸው እስካሁን የቀጠለን ተቀጣጣይ እሳት ፈጥሯል፡፡

ምስል
ሰፋ ያለው የሆልምስ ቤተሰብ

ቢሆንም እሳት መቀጣጠሉን እንዲቀጠል እንጨቱም ሙሉ ሃይሉን መስጠቱን እንዲቀጥል የማያቋርጥ ኦክስጅን ማግኘት መቻል አለበት፡፡ ከሚካኤል እና ማሪአን ሆልምስ ማሳያ እንደምናየው እምነት በክርስቶስ ፤ ለነበልባሉ መቀጠል ፤ ቀጣይነት ያለው ተግባር ይፈልጋል፡፡ ጥቂት የሆኑ ተግባራት በቃልኪዳኑ ጎዳና ለመጓዝ የሚያስፈልገንን ነዳጅ ለማግኝት ሲያስችሉ ወደ እግዚአብሄር በረከቶችም ይመሩናል፡፡ ነገር ግን ኦክስጅን ማግኘቱ እንዲቀጥል እንደተምሳሊታዊነት እግራችንም መንቀሳቀሱን መቀጠል አለበት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ምግባችንን ከየት ማግኘት እንዳለብን ለማወቅ የሚረዳን ራእይ ከመምጣቱ በፊት ቀስትና ጋሻ መስራት ይኖርብናል፡፡ 18 አንዳንዴ መርከብ እንዴት እንደምንገነባ ራእይ ከመቀበላችን በፊት ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት አለብን፡፡19 አንዳንዴም ከጌታ ነብይ በቢመጣ ትእዛዝ ያለችንን ትንሽ ዱቄትና ዘይት ተጠቅመን ዳቦን በመጋገር የማያልቅ የዘይት ክምችትና የተትረፈረፈ በርሜል ሙሉ ዱቄትን መቀበል እንችላለን፡፡ 20 እንዳንዴም “እረፉ እና እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ” እንዳለዉ የሱን ጊዜ መጠበቅ ይኖርብናል፡፡21

ማንኛውንም በረከት ከእግዚአብሄር ስትቀበሉ መደምደም የምትችሉት ያንን በረከት ያገኛችሁት በበረከቱ ላይ የተጣለውን ህግ ተወታችኋል፡፡22 ነገር ግን አስታውሱ “ሊሻር የማይችል” ህግ በሰአት ይገዛል፣ ያም ማለት በረከቶች የሚመጡት በእግዚአብሄር ጊዜ ሰሌዳ ነው፡፡ የጥንት ነብያት የሰማያዊ ቤታቸውን ሲሹ 23“እነዚህ ሁሉ አምነዉ ሞቱ፣ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፣ ዳሩ ግን ከሩቅ አዩትና ተሳለሙት፣ በምድሪቱ እንግዶችና ምጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ” ፡፡24 ከእግዚአብሄር የምንፈልገው በረከት ሳይመጣ ቢዘገይ ልንበሳጭ አይገባም ከዚህ የበለጠስ ምን ማድረግ ይጠበቅብኛል ብለን ማሰብ የለብንም፡፡ በተቃራኒው የነብዩ ጆሴፍ ስሚዝን ምክር እንከተል “በሀይላችን ያሉትን ነገሮች ሁሉ በደስታ እናድርግ፤ ከዚያም በእርግጠኝነት እግዚአብሔር የሚያደርገውን ማዳን ለማየት እንቁም እና የክንዱንም መገለጥ እንጠባበቅ።” 25 አንዳንድ በረከቶች ለበኋላ የተቀመጡ ናቸው ፤ ለጎበዝ የእግዚአብሄር ልጆች ጭምር፡፡ 26

ከስድስት ወራት በፊት ቤትን ያማከለ በቤተክርስትያን የተደገፈ እቅድ ወንጌልን ለመማር ፣ እምነትን ለማጠንከር፣ እና ግለሰቦችንና ቤተሰቦችን ለማነጽ እንዲረዳ ተዋውቋል፡፡ ፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን ቃል ሲገቡ ይህ ለውጥ መንፈሳዊነትን እንድናጠነክር፣ የወንጌል ደስታችን እንዲጨምር እና በሰማያዊ አባታችንንና በኢየሱስ ክርስቶስ ያለን መለወጥ ጥልቅ እንዲሆን ይረዳናል፡፡ 27 ነገር ግን እነዚህን በረከቶች መሻት የኛ ሃላፊነት ነው፡፡ እያንዳንዳችን ሃላፊነት አለብንኑ ተከተሉኝ፟---- ለግለሰቦችና ለቤተሰብ የሚለውን ለመክፈትና ለማጥናት ከቅዱሳን መጻህፍትና ኑ ተከተሉኝ ሌሎች ማጣቀሻዎች ጋር በጋራ ለማጥናት፡፡28 እነዚህን ከቤተሰብና ከጓደኞቻችን ጋር ልንወያይባቸውና ሰንበታችንን ዘይቤአዊ በሆነ መልኩ እሳትን እንዲያበራ ልናደርግ ይገባል፡፡ ወይም እነዚህን ሃብቶች በቤታችን ከምረን የሚቻል ሃይላቸውን ቀብረን ልናስቀምጣቸው እንችላለን፡፡

እኔ በእምነት የሰማይ ሃይልን በማንቀሳቀስ ከእግዚአብሄር በረከቶችን እንድትቀበሉ እጋብዛችኋለሁ፡፡ እምነታችሁን በመለማመድ ክብሪቱን ጭራችሁ እሳቱን አቀጣጥሉ፡፡ ጌታን በትዕግስት ስትጠባበቁ አስፈላጊውን ኦክስጅን ማቅረባችሁን ቀጠሉ፡፡ ከዚህ ግብዣ ጋር ጸሎቴ ነው መንፈስ ቅዱስ እንዲያግዛችሁ እና እንዲመራችሁ፣ ያም ሲሆን ልክ በመጽሃፈ ምሳሌ ላይ እንዳለዉ “የታመነ ሰዉ” “ባለጠጋ ለመሆን” እንድትችሉ፡፡29 አባት እግዚአብሔርና ተወዳጁ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው እንደሆኑና ሰለኛ ግድ እንደሚላቸውና ሊባርኩንም እንደሚወዱ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ትምህርት እና ቅል ኪዳኖች 41፥178፥17104፥33

  2. ለምሳሌም፣ ክሪግ ሃርሊን፣ ተምቦግቧጊው አለም: የማርቲን ሉተር አነሳስና የለውጡ ውልደት (2017), 20 የሚለውን ይመልከቱ፡፡ የዚህ አይነት ክርክር በኦገስቲን (354- 430 ከክርስቶስ ልደት በፊት እ.ኤ.አ) እና ተቀናቃኙ ፔላጂየስ (354- 420 ከክርስቶስ ልደት በፊት እ.ኤ.አ) መሃከል ተካሂዶ ነበር፡፡ ፔላጂየስ አቁዋሙን እንዲህ ነበር “ሰዎች በጎ ማድረግ በውስጣቸው (አለ) እናም የእግዚአብሄርን ጸጋ ያገኙት በዚህ ጥሩነት እና የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት በሙሉ በመጠበቅ ነዉ፡፡” ኦገስቲን በሃይለኛው ይቃወማል፡፡ እንዲሁም የኤሪክ መታካስማርቲን ሉተር፡ እግዚአብሄርን በድጋሚ ያገኘው ሰውና አለምን የለወጠው(2017)እ.ኤ.አ 296 ይመልከቱ ሉተር ስራ ወደ እግዚአብሄር ጸጋ እንደማያደርስ ያስብ ነበር፣ እምነት ወደ ጸጋ ይመራል ስራም ይከተላል “ሰራን ከእምነት መነጠል ፈጽሞ የማይቻል ነዉ፣ ልክ ሙቀትና ብርሃንን ከእሳት መለየት እንደማይቻለው፡፡”

  3. ትምህርት እና ቃል ኪዳን 82፥10ን ይመልከቱ።

  4. ይህ የጊዜያዊ ሰፈር ክብሪት ነው, “በማንኛውም ቦታ የሚጫር” ክብሪት፡፡ ዘመናዊ ክብሪቶች ልክ እንደ ኩሽና ክብሪቶች ፎስፈረሳቸው ያለው በክብሪት ቀፎው ላይ እንጂ በክብሪቱ ጫፍ ላይ አይደለም፡፡

  5. እነዚህ ድርጊቶች ለነበልባሉ የሚሆኑ “የማነቃቂያ ሃይል” ያካትታሉ ፡፡ “የማነቃቂያ ሃይል” የሚለው አባባል በሲዊድናዊው ሳይንቲስት ስቫንቴ አርሄኒዩስ የተዋወቀው በ 1889 እ.ኤ.አ ነበር፡፡

  6. የእምነት ትምህርት (1985 እኤአ), 3።

  7. ዴቪድ ኤ ቤድናር “በእምነት ጠይቁ,” ሊያሆና ግንቦት 2008 እኤአ, 94 ይመልከቱ.

  8. ሞዛያ 2፥24–25ን ይመልከቱ

  9. ዘኋልቁ 21፥6–9ን ይመልከቱ

  10. 1 ኔፊ 17:41ን ይመልከቱ

  11. 1 ኔፊ 17:42ን ይመልከቱ

  12. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥20፟-21

  13. 2 ኔፊ 10፥24; 25፥23 ይመልከቱ

  14. አልማ 60:11, 21; ዳለን ኤች ኦክስ “ጥቃቅን እና ቀላል ነገሮች,” ሊያሆና ግንቦት 2018 እ.ኤአ, 89–92; ኤም ራስል ባላርድ “በጽናት ተሳተፉ,” ሊያሆና ህዳር 2012 እ.ኤ.አ, 29–31 ይመልከቱ፡፡

  15. የመጽሃፍ ቅዱስ መፍቻ“ጸሎት” ይመልከቱ እንዲሁም ሞሮናይ 7፥48ን ይመልከቱ፡፡

  16. አልማ 36፥18–21; ይመልከቱ እንዲሁም ኢኖስ 1፥5–8ን ይመልከቱ፡፡

  17. ዳኔል ደብሊው ጆንስ40 አመት በህንዶች መሃከል(1960)፣ 222፡፡

  18. 1 ኔፊ 16፥23 ተመልከቱ።

  19. 1 ኔፊ 17፥9ን ይመልከቱ።

  20. 1 ነገሥት 17፥10-16

  21. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥16።

  22. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥20-21 ን ይመልከቱ።

  23. ዕብራውያን 11፥16 ን ይመልከቱ።

  24. ዕብራውያን 11፡13

  25. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 123፥17።

  26. ጀፍሪ አር ሆላንድ “የጥሩ ነገሮች መምጫ ሊቀ ካህን,” ሊያሆና ህዳር1999 እኤአ, 42-45 ይመልከቱ፡፡ ሽማግሌ ሆላንድ እንዳሉት “ አንዳንድ በረከቶች በቶሎ ይመጣሉ፣ አንዳንዶች ዘግይተው፣ አንዳንዶች ከመንግስተ ሰማያት በፊት አይመጡም፣ ነገር ግን የኢየሱስ ከርስቶስን ወንጌልን ተቀብለው ለሚታቀፉ በረከቶቹይመጣሉ.”

  27. ራስል ኤም ኔልሰን “የመክፈቻ ንግግር,” ሊያሆና ህዳር 2018 እኤአ, 6–8 ይመልከቱ፡፡

  28. ኩዊንተን ኤል ኩክ, “ለሰማያዊ አባታችንና ለኢየሱስ ክርስቶስ ትልቅና ዘላቂ መለወጥ,” ሊያሆና ህዳር 2018 እኤአ, 8–12 ይመልከቱ፡፡

  29. ምሳሌ 28፥20

አትም