ይህ ወዴት ያመራል?
አማራጮችን ከተመለከትን እና ወዴት እንደሚመሩ ካሰላሰልን የተሻሉ ውሳኔዎችን/ምርጫዎችን እንመርጣለን፡፡
የተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ስለወደፊቱ እንድናስብ ያበረታታናል፡፡ የ ስጋ ህይወትን አላማ እና ተከትሎት የሚመጣውን እውነታ ያብራራልናል፡፡ ተግባራችንን አሁን ለማስተካከል ስለወደፊቱ ታላቅ ነገሮች ያስተምረናል፡፡
በአንጻሩ ሁላችንም ስለዛሬ ብቻ የሚያስቡ ሰዎችን አናውቃለን፤ ዛሬ ገንዘብህን ተጠቀም፣ ዛሬ ተዝናና ፣ ስለነገ አታስብ ሚሉ አሉ፡፡
ሁል ጊዜ ስለወደፊቱ የምናስተውል ከሆነ ዛሬያቸንና ነገአችን የተሻለ ደስታ ይኖረዋል፡፡ ዛሬ ላይ ውሳኔን ስንወስን “ይህ ወዴት ያመራል? ” ብለን ሁል ጊዜ መጠየቅ አለብን፡፡
፩.
አንዳንድ ውሳኔዎች አንድ ነገር በመስራት አና ባለመስራት መሃል ያሉ ምርጫዎች ናቸው፡፡ ከብዙ አምታት በፊት የእንዲህ አይነት ምርጫ ምሳሌ በዩናይትድ ስቴትስ አንድ የካስማ ጉባኤ ላይ ሰማሁ፡፡
ቦታው የሚያምር የኮሌጅ ጊቢ ነበር፡፡ በዛ ብለው የተሰበሰቡ ወጣት ተማሪዎች ሳር ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ይህንን ታሪክ ሲያስረዳ የነበረው ተናጋሪ አንድ የሚያምር ባለ ትልቅና ጸጉራም ጭራ ሽኮኮ በአንድ የሚያምር ዛፍ አካባቢ ሲጫወት አየተመለከቱ እንደነበር ተናገረ፡፡ አንዳንድ ጊዜ መሬት ላይ፣ አንዴ ላይ አንዴ ታች እና በግንቡ አካባቢ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ የተለመደ እይታ ለምን ብዙ ተማሪዎችን ሳበ?
በአቅራብያው በነበረው ሳር አጠገብ አንድ ቀላ ያለ ከአዳኞች ጋር አብሮ ሚሰራውሻ በንቃት ተኝቶ ነበረ፡፡ የተማሪዎቹ ትኩረት በሱ ላይ፣ የውሻው ደግሞ በሸኮኮው ላይ ነበር፡፡ ሽኮኮው ዛፉን እየተሸከረከረ ከአይን በተሰወረ ቁጥር ውሻው በዝግታ ጥቂት ሴንቲ ሜትሮች ይጠጋል፤ ከዝያም ወደቀደመው ተመሳሳይ አቋቋም ይመለሳል፡፡ ይህ ነበር የተማሪዎችን ትኩረት የሳበው፡፡ በዝምታና ያለእንቅስቃሴ አይኖቻቸው ውጤቱ ይበልጥ ግልጽ በሆነው ትዕይንት ላይ ተተክሎ ነበር፡፡
በመጨረሻ ውሻው ሸኮኮውን ዘሎ በአፉ ውስጥ ለመያዝ በጣም ቀረበ፡፡ የፍርሃት ትንፋሽ መጣ ፤ ተማሪዎቹ በፍጥነት ወደፊት ተወርውረው ትንሹን እንስሳ ከውሻው መንጭቀው ጎተቱት፤ ነገር ግን በጣም ዘግይተው ነበር፡፡ ሸኮኮው ሞቶ ነበር፡፡
ከህዝቡ መሃል ማንኛውም ሰው በማንኛውም ሰዓት እጃቸውን በማውለብለብ ወይም በመጣራት ማስጠንቀቅ ይችሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ማንም ምንም አላደረገም፡፡ አይቀሬው ውጤት እየተቃረበ እና እየተቃረበ ሲመጣ ተቀምጠው ተመለከቱ፡፡ ማንም “ይህ ወዴት ያመራል?” ብሎ አልጠየቀም፡፡ የተጠበቀው ሲሆን ሁሉም ሊሆን ያለውን ለመከላከል ቸኮሉ፤ ነገር ግን በጣም ረፍዶ ነበር፡፡ ሁሉም መስጠት የቻሉት በእንባ የተሞላ ጸጸት ነበር፡፡
ያ እውነተኛ ታሪክ ጥሩ ያልሆኑ ውሳኔዎች ምሳሌ ነው፡፡ በራሳችን ህይወትና በአካባቢያችን ዙርያ ከምናየው ኑሮ እና ሁኔታዎች ጋር ይሄዳል፡፡ አደጋ በሰዎች ወይም በምንወደው ነገር ላይ ሲመጣ የመናገር ወይም የመተግበር ወይም ዝም የማለት ምርጫ አለን፡፡ “ይህ ወዴት ያመራል?” ብሎ ራሳችንን መጠየቅ መልካም ነው፡፡ ውጤቱ ፈጣንና ከባድ ሲሆን ምንም አለማድረግ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ በጊዜ ትክክለኛ ማስጠንቀቅያዎችን ማሰማት ወይም ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶችን መደገፍ አለብን፡፡
አሁን የገለጽኩላችሁ ውሳኔዎች አንድ እርምጃ መውሰድን ወይም ምንም አለማድረግን ያካትታል፡፡ ይበልጥ የተለመዱት በአንድ ተግባር ወይም በሌላ መሃል ያሉ ምርጫዎች ናቸው፡፡ እነዚህ በመልካም ወይም በክፉ መሃል ያሉን ምርጫዎችን ያካትታሉ፤ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ በሁለት መልካም ነገሮች መሃል ያሉ ምርጫዎች ናቸው፡፡ በነዚህም ጊዜ ወዴት ያመራል ብሎ መጠየቅ ጥሩ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ጊዜያችንን እንዴት ማሳለፍ አለብን ከሚለው ጋር ተያይዞ ፤ ከሁለት መልካም ነገሮች መሀል ምርጫ እንመርጣለን፡፡ ቪድዮ ጌሞችን መጫወት፣የስልክ የጽሁፍ መልዕክት መላክ ወይም ቴሌቭዥን ማየት ወየም ስልክ ማናገር ላይ መጥፎ ነገር የለም፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ “የእድል ዋጋ” የምንለውን ያካትታል ፤ ይህም ማለት አንድ ነገር በመስራት ጊዜ ምናሳልፍ ከሆነ ሌላውን የመስራት እድል እናጣለን፡፡ ምንም እንኳን በራሱ ፍጹም ቢሆንም በዛ ነገር ላይ ጊዜ ስናጠፋ ልናጣ የምንችለውን በጥንቃቄ የመመዘን አስፈላጊነት ማየት እንደምትችሉ እርግጠኛ ነኝ፡፡
ከተወሰነ ጊዜ በፊት “ደህና፣ የተሻለ፣ ምርጥ” በሚል ርእስ ንግግር አድርጌ ነበር፡፡ በዛ ንግግር ላይ “የአንድ ነገር ደህናመሆን ለማድረግ በቂ ምክንያት አይደለም፡፡” ብዬ ነበር፡፡ መስራት የምንችላቸው መልካም ነገሮች ቁጥር፤ ለማሳካት ካለን ጊዜ በእጅጉ ይልቃል፡፡ አንዳንድ ነገሮች ከደህና የተሻሉ ናቸው እናም እነዚህ ነገሮች በህይወታችን ቅድምያ መሰጠትንና ትኩረትን ይሻሉ፡፡ የተሸሉ ወይም ምርጥ የሆኑ ነገሮችን ለማግኘት አንዳንድ ደህና የሆኑ ነገሮችን መተው አለብን፡፡1
አርቃችሁ እዩ፡፡ አሁን ላይ የምንወስነው ውሳኔ በወደፊታችን ላይ ያለው ተጽዕኖ ምንድነው? ትምህርት የመማርን፣ ወንጌልን የማጥናት፣ ቅዱስ ቁረባንን በመካፈል ቃል ኪዳናችንን የማደስና ቤተመቅደስ የመሄድ አስፈላጊነትን አስታውሱ፡፡
፪.
ስለራሳችን ምን እንደምናስብ ወይም ራሳችንን የት አንደምንመድብ ለመምረጥ “ይህ ወዴት ይመራል?” ማለት ያስፈልጋል፡፡ ከሁሉም በላይ እያንዳንዳችን የዘላለም ህይወት እጣ ፈንታ ያለን የእግዝአብሔር ልጆች ነን፡፡ በዘላለም አይን እያንዳንዱ ምደባ እንደ ስራን፣ ዘርን፣ አካላዊ ገጽታን ወይም ክብርን እንኳን ጊዜያዊ እና ጥቂት ነው፡፡ ልትተጉለት በምትችሉት ግባችሁ ላይ ገደብ በሚያስቀምጥ መልኩ ስለራሳችሁ አታስቡ ወይም ራሳችሁን አትመድቡ፡፡
እኔ የማወራውን የምታዩ ወይም የምታነቡ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ መሪዎቻችሁ ለምን የእኛንትምህርትና ምክር እንደሚሰጡ ታውቃላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እንወዳቹሃለን፡፡ የሰማይ አባታችንና የሱ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ይወዳቹሃል፡፡ ለኛ ያላቸው ዕቅድ “ታላቅ የደስታ ዕቅድ” ነው፡፡(አልማ 42:8). ያ ዕቅድ ትዕዛዞቻቸው፣ ስርዐቶቻቸው እና ቃልኪዳኖች፣ ፣ በዚህኛውና በሚቀጥለው ህይወት ወደ ታላቁ ደስታና ሃሴት ይመራናል፡፡ እንደ አባቱና ልጁ አገልጋዮች፤ በመንፈስ ቅዱስ በመሩን መሰረት እናስተምራለን እናም እንመክራለን፡፡ እውነቱን ከመናገርና ለዘላለማዊ ህይወት “ከስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ለሆነው” ት እና ቃ 14፣7ባወጡት መንገድ እንድትሄዱ ከማበረታታት ውጪ ሌላ ፍላጎት የለንም፡፡
፫.
አሁን ላይ የተፈጸሙ ውሳኔዎች ወደፊት ስላላቸው ተጽዕኖ ሌላ ምሳሌ ልስጣችሁ፡፡ አስፈላጊ የሆነ የወደፊት ስኬት ግብ ለማግኘት ዛሬ ላይ ስለምንከፍለው መስዋዕትነት ምርጫ ይመለከታል፡፡
በካሊ ካሊፎርንያ ሲደረግ በነበረ የካስማ ጉባኤ ላይ አንዲት እህት እስዋና እጮኛዋ ወደ ቤተመቅደስ ውስጥ ለመጋባት ፍላጎት እንደነበራቸውና ሚቀርባቸው ቤተመቅደስ ርቆ ፔሩ እንደሚገኝ ተናገረች፡፡ ለባስ ክፍያ ለረጅም ጊዜ ገንዘባቸውን አጠራቀሙ፡፡ በመጨረሻም ወደ በጎታ በሚሄድ ባስ ተሳፈሩ፡፡ ነገር ግን እዛ ሲደርሱ ወደ ሊማ ፔሩ የሚሄዱ ባሶች መቀመጫዎች ሁሉ እንደተያዙ ተረዱ፡፡ ወደ ቤት ሳይጋቡ መመለስ ወይም ከቤተመቅደስ ውጪ መጋባት ይችሉ ነበር፡፡ ባጋጣሚ አንድ ሌላ አማራጭ ነበራቸው፡፡ 1ወደ ሊማ በሚሄደው ባስ ወለል ላይ ተቀምጠው ለአምስት ቀንና አምስት ለሊት ለመጓዝ ፈቃደኛ ከሆኑ መሄድ ይችላሉ፡፡ ይህን ለማድረግ መረጡ፡፡ ምንም እንኳን አንዳንድ ተሳፋሪዎችአንዳንዴ ወለሉ ላይ ዘና ለማለት ወንበር ላይ እንዲቀመጡ ቢፈቅዱላቸውም ጉዞው ከባድ ነበር አለች፡፡
በዛች እህት ንግግር ውስጥ ያስገረመኝ ነገር እሱዋና ባልዋ ቤተመቅደስ በዚህ አይነት መንገድ በመሄዳቸው አመስጋኝነትዋ ነበር፤ ምክንያቱም ስለወንጌል እና ስለቤተመቅደስ ይሰማቸው የነበረውን መንገድ ስለቀየረ ነው ብላለች፡፡ ጌታ በመስዋዕት በሚመጣ እድገት ሸለማቸው፡፡ መስዋዕት ካልነበረው ተደጋጋሚ የቤተመቅደስ ጉብኝት ይልቅ የአምስት ቀን ጉዞው የበለጠ መንፈሳዊ ግንባታ እንደነበረውም ተመለከተች፡፡
ያንን ምስክርነት ከሰማሁ በአመታቶቹ ውስጥበቤተመቅደስ ለመጋባት ከሚያስፈልገው መስዋእትነት በፊት ሌላ ምርጫ መርጠው ቢሆን የነዚህ ጥንዶች ህይወት እንዴት የተለየ ይሆን ነበር እያልኩ አስባለሁ፡፡
አንዳንድ ትልቅ ሌሎች ደግሞ ትንሽ የሚመስሉ ቁጥር አልባ ምርጫዎችን በህይወት እንመርጣለን፡፡ ወደ ሁዋላ ስንመለከት አንዳንድ ምርጫዎቻችን ምን ያህል በህይወታችን ትልቅ ልዩነት እንዳመጡ ማየት እንችላለን፡፡ አማራጮችን ከተመለከትን እና ወዴት እንደሚመሩ ካሰላሰልን የተሻሉ ውሳኔዎችን/ምርጫዎችን እንመርጣለን፡፡ ይህን ስናደርግ የፕረዝደንት ረስል ኤም ኔልሰንን መጨረሻውን በማሰብ ጀምሩ ሚለውን ምክር እየተከተልን እንሆናለን።2 ለኛ ሁልጊዜ መጨረሻው በቃልኪዳን መንገድ በቤተመቅደስ አማካኝነት ወደ ዘላለማዊ ህይወት ፣ ከእግዚአብሄር ስጦታዎች ሁሉ የላቀው ነው፡፡
ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና የሃጥያት ክፍያው እና ስለዘላለማዊው ወንጌል እውነቶች ውጤት እመሰክራለሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።