![](https://www.churchofjesuschrist.org/imgs/https%3A%2F%2Fassets.churchofjesuschrist.org%2Fbb%2Fec%2Fbbec7294473053123f5953b920f329b58f0a2668%2Fbbec7294473053123f5953b920f329b58f0a2668.jpeg/full/!250,/0/default)
ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ
ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተመለከትን እንደ እስራኤል ሽማግሌዎች ቃለኪዳናችንን እንድንጠብቅ እና ጥሪያችንን እንድናጎላ ይረዳናል፡፡
ኢየሱስ በቅፍረናሆም አቅራቢያ በሚገኘው መንገድ ላይ በብዙ ሰዎች ተከቦ ሲራመድ፤ በጠንካራ ህመም ለ አስራ ሁለት አመት ስትሰቃይ የነበረች ሴት ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፡፡1 እሷም ወድያው ተፈወሰች፡፡2
ቅዱሳን መፀሐፍ ኢየሱስ‹‹ከእርሱ፤ ‹‹ኃይል እንደወጣ በገዛ እራሱ አውቆ››3 ‹‹በሕዝብ መካከል ዘወር ብሎ››4 ‹‹ይህንም ያደረገችውን ለማየት››5 ‹‹ሴቲቱ ግን የተደረገላትን ስላወቀች፣እየፈራች እየተንቀጠቀጠች››6 ‹‹መጥታ በፊቱ ተደፍታ እውነቱን ሁሉ ነገረችው፡፡››7
“እርሱም። ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ አላት” ።8
ኢየሱስ ክርስቶስ ሴትየዋን አዳናት አካላዊ ፈውስ አድርጎላት ነበር፤ ኢየሱስ ሊያያት ሲዞር፤ በእርሱ ላይ ያላትን እምነት አወጀች እርሱ ደግሞ ልቧን ፈወሰው፡፡ 9 በፍቅር አናገራት ፤ የእርሱን ይሁንታ አረጋገጠላት ፤እና በእርሱ ሰላም ባረካት 10
ወንድሞች እንደ ቅዱስ ክህነትን ተሸካሚነታችን፤ ሁላችንም በደህንነት ስራ ላይ ተሳታፊ ነን፡፡ በመጨረሻው አመታት ጌታ የስራውን ኃላፊነት በእስራኤል ሽማግሌዎች ትከሻ ላይ እኩል አድርጎ አስቀምጧል11 ጌታ የሚያበረታታ ሀላፊነት ሰጥቶናል- ከእህቶቻችን ጋር ስንሰራ፣ በተቀደሰ መንገድ እንድናገለግል፣ በሁለቱም መጋረጃ በኩል የእስራኤልን መሰባሰብ ማፋጠን፤ቤታችንን የእምነት መገኛ እና የወንጌል መማሪያ አድርገን ማቋቋም፤ እንዲሁም አለምን ለኢየሱስ ዳግም ምፅአት እንድናዘጋጅ፡፡ 12
አዳኛችን የሁሉ ነገር መንገድን እንደማሳየቱ መጠን፤እርሱም ወደ አባቱን ያይ እና ያገለግለው እንደነበር እኛም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መመልከት እና እርሱን ማገልገል አለብን፡፡ 13 አዳኛችን ለነብዩ ጆሴፍ በዚህ መንገድ ነበር የተናገረው፡፡
“ባሰባችሁት ነገር ሁሉ ወደ እኔ ተመልከቱ፣ አትጠራጠሩ፣ አትፍሩ፡፡
ጎኔ ላይ የተወጋሁት ቁስል፣ እናም በእጄ እና በእግሬ ላይ ያሉትን የምስማር ምልክቶች አስቧቸው፤ እናም እምነት ይኑራችሁ፣ ትእዛዛቴን ጠብቁ፣ እናም መንግስተ ሰማያትን ትወርሳላችሁ።14
በቅድመ ዓለም ግዛት ኢየሱስ ለአባቱ እንዲ ብሎ ቃልኪዳን ገብቷል፤ የአባቱን ፍቃድ ሊፈፅም ፤ አዳኛችን እና ቤዛችን ሊሆን፡፡ አባቱም ‹‹ማንን እልካለሁ? ›› ብሎ በጠየቀ ወቅት፡፡15 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤
“ይሄው እዚህ ነኝ፣እኔን ላከኝ።”16
“አባት ሆይ፣ ፈቃድህ ይፈጸም፣ እናም ክብርም ለዘለአለም ያንተ ይሁን።”17
በመላው የምድር ህይወቱ ኢየሱስ ያንን ቃልኪዳን ኖሮታል፡፡ በትህትና፤በርህራሄ እና በፍቅር አባቱ በሰጠው ኃይልና ስልጣን አማካኝነት የአባቱን ትምህርት አስተማረ የአባቱንም ስራ ሰራ፡፡ 18
ኢየሱስ ልቡን ለአባቱ አሳልፎ ሰጥቶል እንዲህም አለ፧
‹‹አብን እንድወድ››19
‹‹አብም እንዳዘዘኝ እንዲሁ አደርጋለሁ››20
‹‹ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና፡፡››21
እየተሰቃየ በጌቴስማኒ ‹‹ነገር ግን ፤የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ›› እያለ ይጸልይ ነበር፡፡22
ጌታ እስራኤል ላሉ ሽማግሌዎቹ በጠራቸው ግዜ ‹‹ወደ እኔ በሁሉም በኩል እዩ›› እና ‹‹ቁስሎቹን ›› ከሞት የተነሳውን አካሉን፤ ከሃጥያት መመለሻ ጥሪ እና ከዓለም እና ወደ እርሱ መመለስ እና እሱን መውደድ እና መታዘዝ ነው፡፡ ይህ ጥሪ ትምህርቱን በእርሱ መንገድ እንድናስተማር እና ስራውን በእርሱ መንገድ እንድንፈፅም ነው፡፡ ስለዚህ ፤ ይሄ ፤እርሱን በፍፁም እንድናምነው፤ ፍቃዳችንን ለእርሱ አሳልፈን እንድንሰጠው እና ልባችንን ለእርሱ እንድንማርክ፤ እናም በእርሱ የማዳን ኃይል እርሱን እንድንመስል ጥሪ ነው፡፡23
ወንድሞች፤ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተመለከትን በእስራኤል ውስጥ ሽማግሌዎቹ እንድንሆን ይባርከናል- ትሁት፣ሩህሩህ፣ የተሰጠን፤ የእርሱ ፍቅር የሞላን፡፡24 እናም የወንጌሉን በረከት እና ደስታ እና ቤተክርስቲያን ለቤተስባችን እና ከመጋረጃው በሁለቱም በኩል ላሉትን ለወንድምቻችን እና ለእህቶቻችንን እናመጣለን ፡፡
ፕሬዝዳንት ራስል ኤም ኔልሰን ወደ ኢየሱስ ክርሰቶስ በዚህ መልኩ እንድናይ ጠርተውናል‹‹ጠንኳራ ሀዋርያ ለመሆን ቀላል ነገር ወይም የሚያቀል ነገር የለም ››። አትኩሮታችን መሆን ያለበት በአዳኛችን እና በእርሱ ወንጌል ላይ መታስር ነው፡፡ በሁሉም አስተሳሰባችን ወደ እርሱ እንድንመለከት ማድረግ አእምሮን ማጠንከርን ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን እንደዛ ስናደርግ፤ ጥርጣሬያችን እና ፍርሀታችን ይጠፋል፡፡25
‹‹መጣበቅ›› ታላቅ ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም በጥንካሬ መታሰር፣ መሳሳብ እና በፍፁም መያዝ ማለት ነው፡፡26 ቃልኪዳናችንን በመጠበቅ አትኩሮታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ ላይ እናስራለን
ቃልኪዳችንን መጠበቅ በሁሉም ስራዎቻችን እና በንግግራችን ላይ ተፅእኖ ይኖረዋል ፡፡ የምንኖረው የቃልኪዳን ህይወት 27 በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያተኮሩ ሙሉ ቀላል የቀን በቀን የእምነት ተግባሮች፤ ከልብ የመነጨ ፀሎት በእርሱ ስም፤ የእርሱንቃል መመገብ፤ ለሃጥያታችን ንስሀ ለመግባት ወደ በእርሱመዞር፤የእርሱን ትዛዛት መጠበቅ፤ ቅዱስ ቁርባን መውሰድ እና የእርሱንቀድሶ መጠበቅ፤ በተቀደሰውየእርሱ ቤተ መቅደሱ በቻልነው መጠን ማምለክ፤ እና ቅዱሱን የእርሱን ክህነት የእግዚአብሔርን ልጆች ለማገልገል መለማማድ ነው፡፡
ቃልኪዳኖቻችን በመሰጠት ስንወጣ ልባችንን እና አእምሮአችንን ለአዳኛችን የቤዛነት ኃይል እና በመንፈስ ቅዱስ ቅድስና ተፅእኖ ስር እንሆናለን፡፡ አዳኛችን የእኛን ተፈጥሮ መስመር በመስመር ይቀይራል፤ ወደ እርሱ በጥልቅ ይለውጠናል እናም ቃልኪዳናችን በልባችን ውስጥ ህይወትን ይዘራል፡፡28
ለሰማይ አባታችን የምንገባው ቃል ጠንካራ ቆራጥነት እና፤ የውስጣችን ጥልቅ ፍላጎትን ያሳያል፡፡ የሰማይ አባታችን የገባልን ቃልኪዳኖች በምስጋና እና በደስታ ይሞሉናል፡፡29 ቃልኪዳኖቻችን የምንከተላቸው ህጎች መሆናቸው ይቀርና የምንወዳቸው የሚያነሳሱን፤ የሚመሩን እናም አትኩሮታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እንድናጣብቅ የሚረዱን መርሆች ይሆናሉ፡፡ 30
ይህ የቆራጥነት ተግባር ለሁሉም ፤ ለወጣት እና ለአዛውንት አለ፡፡ እናንት ወጣት ወንዶች ቅዱስ የሆነውን የአሮናዊውን ክህነት የተሸከማችሁ፤ በዚህ ምሽት የምለው ሁሉ በእናንተ ይተገበራል፡፡ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን አመስግናለሁ ፡፡ እናንተ ቅዱስ የሆነውን ስርዐት እና ቃልኪዳን ለሚሊዮን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በሳምንቱ ታቀርባላችሁ፡፡ ቅዱስ ቁርባኑን ስታዘጋጁ፣ስትባርኩ ወይም ስታሳልፉ፤ ስታገለግሉ፤ በቤተ መቅድስ ስታጠምቁ፤ ጓደኞቻችሁን ወደ መነቃቅያ ዝግጅቶች ስትጋብዙ ወይም የጉባኤ አባሎቻችሁን ስታድኑ፤ የደህንነተ ስራን እየፈፀማችሁ ነው፡፡ እናንተም ወደ የኢየሱስ ክርስቶስ መመልከት እና በየቀኑም ቃልኪዳኖቻችሁን መኖር ትችላላችሁ፡፡ ቃል እገባላችኋለሁ ይህን ካደረጋችሁ፣ አሁን እና በመጭው ቀናት፣ የእስራኤል ብርቱ ሽማግሌዎች፣ የጌታ ታማኝ አገልጋዮች ትሆናላችሁ፡፡
ወንድሞቼ አውቃለሁ ይህ ሁሉ ከባድ ይመስላል፡፡ ግን እባካችሁ የአዳኛችንን እነዚህን ቃላቶች አስታውሱ ‹‹አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም››፡፡31 ለእኛም ቢሆን እንዲሁ ነው። ብቻችንን አይደለንም። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እና የሰማይ አባታችን ይወዱናል፤ እና ከእኛ ጋር ናቸው፡፡32 ምክንያቱም ኢየሱስ ወደ አባቱ ተመልክቶ ታላቁን የስርየት መስዋትነት አጠናቅቆአል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚረዳን እርግጠኛ በመሆን ወደ እሱ መመልክት እንችላለን፡፡
ማንኛችንም ፍጹም አይደለንም፤ አንዳንዴ ወደ ኋላ እንቀራለን ፡፡ ተስፋ እንቆርጣለን ሀሳባችን ይበታተናል ፡፡ እንደናቀፋለን፡፡ ነገር ግን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በንስሃ ልብ ከተመለከትን እሱ ወደ ላይ ከፍ ያደርገናል፤ ከሃጥያት ያነፃናል፤ ይቅር ይለናል እና ልባችንን ይፈውሰዋል ፡፡ እርሱ ታጋሽ እና ደግ ነው፡፡ የእርሱ የማዳኛ ፍቅሩ በፍፁም አያልቅም እና በፍፁም አይወድቅም፡፡33 እንደ እስራኤል ሽማግሌዎች ቃለኪዳናችንን እንድንጠብቅ እና ጥሪያችንን እንድናጎላ ይረዳናል፡፡
አላማው አንዲሳካ ፤አብ በአስፈላጊ ነገሮች ሁሉ ይባርከናል፡፡‹‹በመሆኑም፣ ፤ በሰማይ እናም በምድር በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አብ ፈቃድ የተላኩ ነገሮች ሁሉ፣ ህይወት እና ብርሀን፣ መንፈስ እና ሀይል፣ ለእርሱ ተገዢ ናቸውና።››34
መለኮታዊው ብርሃን እና ኃይል በህይወታችን ሲወርድ ሦስት ተአምራዊ ነገሮች ይከሰታሉ፡-
በመጀመሪያ፤ማየት አንችላለን ከውጭ ባለፈ ጥልቅ ልብን ኢየሱስ ሴቲቱን እንዳያት በራዕይ አማካኝነት እኛም ማየት እንጀምራልን፡35 ኢየሱስ የእንደሚያየው ስናይ ፤ በእርሱ ፍቅር የምናገለግላቸውን እንድንወዳቸው ይባርከናል፡፡ በእርሱ እርዳታ፤ እኛ የምናገግላቸው አዳኛችንን ያዩታል እና ፍቅሩም ይስማቸዋል፡፡ 36
ሁለተኛ፤ የክህነት ኃይል አለን፡፡ ለመባረክ፤ ለመምራት፤ለመጠበቅ፤ ለማጠንከር እና ሌሎችን ለመፈወስ እና ለእነሱ ለምንወዳቸው ታምራትን ለማምጣት እና ቤተስባችንን እና ጋብቻችን በደህና ለመጠበቅ ይህንን ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለመስራት ስልጣን እና ኃይል አለን፡፡37
ሦስተኛ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ይሄዳል፤ በምንሄድበት ይሄዳል፤ ስናስተምር ያስተምራል፤ ስናፅናና ያፅናናል፡፡ ስንባርክ፤ ይባርካለ38
ወንድሞች፤ልንደሰትባቸው የሚገቡ ምክንያቶች የሉንምን? አለን; የእግሒአብሔርን ቅዱሱን ክህነት ይዘናል፡፡ ወደ ኢየሱስ ክርሰቶስ ስንመለከት፤ ቃልኪዳናችንን ስንኖር፤ እናም ትኩረታችንን እርሱ ላይ ስናጣብቅ፤ ከእህቶቻችን ጋር በጋራ እና በቅዱስ መንገድ ስናገለግል፤ በመጋረጃው በሁለቱም በኩል የተበተኑትን እስራኤል እንሰበስባለን፤ ቤተሰቦቻችንን እናጣምራለን እናም እናጠነክራለን፤ እናም አለምን ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅአት እናዘጋጃለን፡፡ ይህ ይሆናል፡፡ ስለዚህም እመሰክራለሁ።
በዚህ ከልብ የመነጨ ፀሎት እጨርሳለሁ፤ሁላችንም፤ እያንዳንዳችን; በሁሉም አመለካከታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንመልከት፡፡ አትጠራጠሩ፡፡ አትፍሩ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።