2010–2019 (እ.አ.አ)
የክህነት ሀይል ዋጋ
ኤፕረል 2016


15:41

የክህነት ሀይል ዋጋ

እንደ እግዚአብሔር ወንድ የክህነት ሀይል ይኖረን ዘንድ ለመጸለይ፣ ለመጾም፣ ለማጥናት፣ ለመፈለግ፣ ለማምለክ፣ እና ለማገልገል ፈቃደኞች ነን?

ከስድስት ወር በፊት በጥቅምት 2015 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ውስጥ፣ እንደ እግዚአብሔር ሴትነት መለኮታዊ ሀላፊነታቸው ለቤተክርስቲያኗ ሴቶች ተናግሬ ነበር። አሁን ለእናንተ ወንድሞች እንደ እግዚአብሔር ወንዶች ስላላችሁ መለክታዊ ሀላፊነት ላነጋግራችሁ እፈልጋለሁ። በአለም ስጓዝ፣ በቤተክርስቲያኗ ወንዶች እና ወንድ ልጆች ጥንካሬ እና መልካምነት ተደንቄአለሁ። የፈወሳችኋቸውን ልቦች እና ከፍ ያደጋችኋቸውን ህይወቶች ለምቁጠር ምንም መንገድ የለም። አመሰግናችኋለሁ።

ባለፈው ጉባኤ መልእክት፣ ከብዙ አመት በፊት እንደ ልብ ቀዶ ጠጋኝ ሀኪም ሁለት ትትንሽ እህቶችን ለማዳን ባለመቻሌ ስለነበረኝ አሳዛኝ አጋጣሚ ተናግሬ ነበር። በአባታቸው ፍቃድ፣ ስለቤተሰቡ ተጨማሪ ለማለት እፈልጋለው።

የልብ በሽታ በሩዝ እና ጂሚ ሃትፊልድ የተወለዱ ሶስት ልጆችን ያሰቃይ ነበር። የመጀመሪያ ልጃቸው፣ ጅሚ፣ ዳግማዊ፣ በሽታው ምን እንደሆነ ባልታወቀበት ምክንያት ሞተ። ወላጆቹ ለሁለት ሴት ልጆቻቸው፣ ለሎራል አን እና ለታናሽ እህቷ ጊአይ ልን፣ እርዳታ በሚፈልጉበት ጊዜ ነበር እኔ በዚህ የተሳተፍኩት። Iከቀዶ ጥገናቸው በኋላ ሁለቱም ሴቶች በመሞታቸው ልቤ ተሰብሮ ነበር።1 በሚረዳ ሁኔታም፣ ሩዝ እና ጂሚ በመንፈስ ተሰባብረው ነበር።

ከጊዜም በኋላ፣ እነርሱ በእኔ እና በቤተክርስቲያኗ ላይ ቂም ይዘው እንደነበር አወቅኩኝ። ለስልሳ አመት ያህል እኔ በዚህ ሁኔታ ተጨንቄ ነበር እናም ለሃትፊልድ ቤተሰብም አዝን ነበር። ያለ ስኬታማ ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ለመመስረት ሞክሮ ነበር።

ከዚያም ባለፈ ግንቦት ምሽት፣ ከእንቅልፍ በነዚያ ሁለት ሴቶች ከመጋረጃው በሌላ በኩል በመምጣት አስነሱኝ። በበአካላዊ ስሜት አላየኋቸውም ወይም አልሰማዋቸውም፣ የተሰማኝ በቅርብ እንዳሉ ነው። በመንፈስም፣ ልመናቸው ተሰማኝ። ምልእክታቸው አጭር እና ግልፅ ነበር። “ወንድም፣ ኔልሰን፣ ከማንም ግጋር አልተሳሰርንም! ልትረዳን ትችላለህን?” ከዚያ ጊዜ በኋላም፣ እናታቸው ሞተው እንደነበር አወቅሁኝ፣ ነገር ግን አባታቸው እና ተናሽ ወንድማቸው በህይወት ነበሩ።በሎራል አን እና ጌይ ልን ልመና በመደፋፈር፣ ከአባታቸው ጋር ለመገናኘት ሞከርኩኝ።

በሎራል አን እና ጌይ ልን ልመና በመደፋፈር፣ ከልጁ ሿን ጋር ከሚኖር ከአባታቸው ጋር ለመገናኘት ሞከርኩኝ። በዚህ ጊዜ ከእኔ ጋር ለመገናኘት ፈቃደኛ ነበሩ።

በሰኔ፣ አሁን 88 አመታቸው በነበሩት በጅሚ ፊት ተንበረከኩኝ እና ከእርሳቸው ጋር በዝልቅ ተነጋገርን። ስለሴት ልጆቻቸው ልመና ተናገርኩኝ እና ለቤተሰባቸው የመተሳሰር ስርዓትን ለማከናወን ለእኔ ክብር እንደሚሆን ነገርኳቸው። ሁለቱም የቤተመቅደስ መንፈሳዊ ስጦታን ስላልተቀበሉ፣ ለመዘጋጀት እና ወደ ቤተመቅደስ ለመግባት በእርሳቸው እና በሿን በኩል ብዙ ጊዜ እና ጥረት እንደሚያስፈልግ ገለጽኩላቸው።

በግንኙነታችን ጊዜ በሙሉ፣ የመንፈስ ስሜት በደንብ ይሰማን ነበር። እና እያንዳንዳቸውም ጅሚ እና ሿን ግብዣየን ተቀበሉ፣ በጣም ተደስቼ ንበር! ከካስማ ፕሬዘደንታቸው ፣ ከኤጲስ ቆጶሳቸው፣ ከቤት ለቤት አስተማሪዎቻቸው፣ እና ከዎርድ የሚስዮን መሪያቸው ፣ እንዲሁም ከወጣት ሚስዮኖች እና ከጎልማሳ ባልና ሚስት ሚስዮኖች ጋር በትጋት ሰሩ። ከዚያም፣ በቅርብ በፔይሰን ዩታ ቤተመቅደስ ውስጥ፣ ሩት እና ጂሚን እና አራት ልጆቻቸውን ለእነርሱ ለማስተሳሰር ታላቅ እድል ነበረኝ። ወንዲ እና እኔ በዚህ ስሜት በተሞላ አጋጣሚ ስንሳተፍ አልቅሰን ነበር። በዚያ ቀን ብዙ ልብ ተፈውሰው ነበር።

ሽማግሌ እና እህት ኔልሰን ከሀትፊልድ ቤተሰብ ጋር በቤተመቅደስ እያሉ

ሳስብበት፣ በጅሚ እና ሿን እና ለማድረግ ፈቃደኙ ስለሆኑት እገረም ነበር። ለእኔ ጀግና ሆነዋል! የልቤ ምኞትን ለማግኘት የምችል ቢሆን፣ ይህም በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ እያንዳንዱ ወንድ እና ወጣት ሰው የዚህ አባት እና ወንድ ልጅ ብርታት፣ ጥንካሬ፣ እና ትህትና እንዲያሳዩ ነው። ይቅርታ ለማድረግ እና የድሮ ጉዳትን እና ጸባይን ለመተው ፈቃደኛ ነበሩ። የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እንዲያጸዳቸው እና እንዲያጎላቸው ከክህነት መሪዎቻቸው የሚመጣውን መመሪያ ለመቀበል ፈቃደኛ ነበሩ። እያንዳንዱም “በቅዱሱ የእግዚአብሔር ስርዓት በኩል የሆነው”2 ክህነት በብቁነት የተሸከመ ሰው ለመሆን ፈቃደኛ ነበሩ።

መሸከም ማለት የተያዘውን ነገር ክብደት መደገፍ ነው። የእግዚአብሔር ብርቱ ሀይል እና ስልጣን የሆነውን ክህነት መሸከም ቅዱስ ታማኝነት ነው። ለዚህ አስቡበት፥ ለእኛ የተሰጠው ክህነት እግዚአብሔር ይህችን እና መቆጠር የማይችሉ አለማትን የፈጠረበት፣ ሰማይኛ፡ምድርን የሚገዛበት፣ እና ታዛዥ ልጆቹን ከፍ የሚያደርግበት አንድ አይነት ሀይል እና ስልጣን ነው።3

በቅርብ፣ ዌንዲ እና እኔ ኦርጋን የሚጫወቱት የመክፈቻ መዝሙርን ለመጫወት በተዘጋጁበት ስብሰባ ውስጥ ነበርን። አይኑ በሙዚቃው ላይ ነበር፣ ጣቶቹም በኦርጋኑ ናይ። ቅልፎችን መንካት ጀመረ፣ ነገር ግን ምንም ድምጽ አይወጣም። ለዊንዲ እንዲህ አልኳት፣ “ምንም ሀይል የለውም።” ለዚያ ኦርጋን ይመጣ የነበረውን የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያቆም አንድ ነገር ነበር ብዮእ አሰብኩኝ።

ወንድሞች፣ በዚህ አይነት፣ የክህነት ስልጣን ቢሰጣቸም ግን በሰፈንነት፣ ታማኝ ባለመሆን፣ በኩራት፣ ስነ ምግባር የለሽነት፣ ወይም በአለም ነገሮች ዝንባሌ አይነት ኃጢያቶች የሀይል ፍሰት የተገደበባቸው የክህነት ሀይል ያልነበራቸው በጣም ብዙ ወንዶች እንዳሉ ይሰማኛል።

የሰማይ ሀይልን ለማግኘት ያላቸውን ችሎታ ለማሳደግ ትንሽ ወይም ምንም ያላደረጉ በጣም ብዙ የክህነት ተሸካሚዎች እንዳሉም ፍርሀቴ ነው። በሀሳባቸው፣ በስሜታቸው፣ ወይም በስራቸው ንጹህ ስላልሆኑት ወይም ባለቤቶቻቸውን እና ልጆቻቸውን ዝቅ በማድረግ የክህነት ሀይልን ስለሚዘጉም በሙሉ እጨነቃለሁ።

Iበጣም ብዙ የሆኑ ነጻ ምርጫቸውን ለጠላት በሚያሳሽን ሁኔታ አሳልፈው በመስጠታቸው እና በሚያደርጉትም፣ “የሌሎችን ለመባረክ ከምሸከመው የአዳኝ ሀይል በላይ የራሴን ፍላጎት ለማሟላት ብቻ ነው የማስበው” በማለታቸው ፍርሀት አለኝ።

ወንድሞች፣ በእኛ መካከል አንዳንዶች የክህነት ሀይል ምን እንደሆነ አንድ ቀን ተነስተው ይገነዘቡ እና የእግዚአብሔርኝ፡ሙሉ ኀይል ለመጠቀም፡ከመራር በላይ በሌሎች ላይ ሀይል ወይም በስራ ሀይል ለማግኘት በጣሩ ዝልቅ ጸጸት እንደሚሰማቸው ፍርሀት አለኝ።4 ፕሬዘደንት ጆርጅ አልበት ስሚዝ እንዳስተማሩት “የዚህን ህይወት ሰዓቶች በችላ ለማጥፋት እና ከዚያም ወደ ዘለአለማዊ አለም ላማለፍ በዚህ የምንገኝ፡አይደለኝም፡ ነገር ግን ቀን በቀን የሰማይ አባታችን ከዚህ በኋላ እንድንሞላ የሚጠብቀንን፡ቦታ ለሞምላት ራሳችንን ብቁ ለማድረግ ነው በዚህ ያለነው።”5

ለምን ሰው ቀኑን አጥፍቶ በኤሳው የምስር ወጥ የሚረካው6 የአብርሀምን በረከቶች ለመቀበል በሚያስችለው በታመነበር ዘንድ?7

እያንዳንዳችን በክህነት ተሸካሚዎች ባሉን እድሎች እንድንኖር በአስቸኳል እለምናችኋለሁ። በሚመጡት ቀናት፣ ክህነትን በማተስኮር የሚመለከቱት ወንዶች ብቻ፣ በትጋት በጌታ በራሱ ለመማር የሚፈልጉ ብቻ ናቸው ሌሎችን ለመባረክ፣ ለመምራት፣ ለመጠበቅ፣ ለማጠናከር፣ እና ለመፈቀስ የሚችሉት። ለክህነት ሀይል ዋጋው የከፈለ ሰው ብቻ ነው ለሚያፈቅራቸው ታዕምራትን ለማምጣት እና ጋብቻውን እና ቤተሰቡን፣ በአሁን እነ በዘለአለም በሙሉ፣ በደህንነት ለመጠበቅ የሚችለው።

እንደዚህ አይነት ሀይል ለማግኘት የሚከፈለው ዋጋ ምንድን ነው? የአዳኝ ሐዋርያ፣ ጴጥሮስ--ከያዕቆብ ጋር የመልከጼዴቅ ክህነትን ለጆሴፍ ስሚዝ እና ለኦሊቨር ካውደሪ የሰጠው ያ ጴጥሮስ8—“ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች”9 ለመሆን የሚያስፈልጉንን ጸባዮች አውጇል።

ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሀንስ የመለከ ጼዴቅ ክህነትን በሹመት ሰጡ።

እምነት፣ በጎነት፣ እውቀት፣ ራስን መግዛት፣ መፅናት፣ እግዚአብሔርን መምሰል፣ ወንድማማች መዋደድ ፍቅር፣ ልግስና እና ትጋትን ጥቅሷል።10 እናም ትህትናን አትርሱ!11 ስለዚህ እንዲህ እጠይቃችኋለሁ፣ የቤተሰብ አባላቶቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ እና አብረናቸው የምነሰራው ሰዎች እናንተ እና እኔ እነዚህን እና ሌሎች መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለማሳደግ እንዴት እያደረግን ነን ይሉ ይሆን?12 ተጨማሪ እነዚያ ጸባዮች የሚያድጉ ከሆኑ፣ የክህንት ሀይላችን ከፍተኛ ይሆናሉ።

በክህነት ያለንን ሀይል እንዴት ለመጨመር እንችላለን? ከልባችን መጸለይ ያስፈልገናል። የድሮ እና የሚመጡ ድርጊቶችን በትህትና መናገርና ለአንዳንድ በረከቶች በመጠየቅ መፈጸም፣ የሚጸና ሀይል ከእግዚአብሔር የሚያመጣ አይነት ንግግን አይደለም። ለተጨማሪ ሀይል እንዴት ለመጸለይ ለማወቅ ለመጸለይ ፈቃደኛ ናችሁ? ጌታ ያስተምራችኋል።

ቅዱሳት መጻህፍት ለመፈተሽ እና በክርስቶስ ቃላት ለመመገብ13—ተጨማሪ ሀይል ለማግኘት በትጋት ለማጥናት ፈቃደኛ ናችሁን? የሚስትህ ልብ ሲመልጥ ለማየት ከፈልግህ፣ የክርስቶስን ትምህርት በኢንተርኔት ላይ ስታጠና 14 ወይም ቅዱስ መጻህፍትን ስታነብ ታግኝህ!

በቤተመቅደስ በየጊዜም ለማምለክ ፈቃደኝ ነህን? ጌታ የሚያስተምረውን በቅዱስ ቤቱ ውስጥ፡ማድረግኝ፡ይወዳል። የመልከጼዴቅ የክህነት ስርዓቶችን በቤተመቅደስ ውስጥ ስትለማመድ ስለክህነት ቁልፎች፣ ሳልጣን፣ እና ሀይል እንዲያስተምራችሁ ስትጠይቁን እንዴት እንደሚደሰት አስቡበት። 15 የእናንተ የሚሆነውን ተጨማሪ የክህነት ሀይል አስቡበት።

ሌሎችን የማገልገል የሆነውን የፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰንን ምሳሌ ለመከተል ፈቃደኛ ናችሁን? በአንድ ሰው በር ላይ ለመድረስ በመንፈስ የሚነሳሱበትን በመከተል፣ እና ከዚያም “የሴት ልጃችን ሙት ማስታወሻ እንደሆነ እንዴት አወቁ?” ወይም “ልደቴ እንደነበር እንዴት አወቁ” የሚሉ ቃላትን በሚሰሙበት፣ ለብዙ አመቶችን ወደ ቤት የረዘመ መንገድን ይዘው ሄደዋል። ተጨማሪ የክህነት ሀይል ከፈለክ፣ እርሷን እና ምክሯን በማቀፍ ባለቤትህን ትንከባከባለህ እናም ከፍ አድርገህ ትመለከታለህ።

አሁን፣ ይህ ሁሉ በጣም ብዙ እንደሆነ ቢመስል፣እኛ በስራችን ለማደግ ወይም የባንክ ገንዘብ ቁጥራችንን ለመጨመር እንደ ምናስብበት የክህነት ሀይልን ለማግኘት ብናስብበት እንዴት ከባለቤታችን፣ ከልጆቻችን፣ እና አብረናቸው ከምንሰራው ጋር ያለን ግንኙነት ልዩ እንደሚሆን አስቡበት። በጌታ ፊት ራሳችንን ብናቀርብ እና እንዲያስተምረን ብንጠይ፣ የእርሱ ሀይል ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን ያሳየናል።

በእነዚህ በኋለኛው ቀናት፣ በተለያዩ ቦታዎች የምድር መንቀጥቀጥ እንደሚኖር እናውቃለን።16 ምናልባት ከእነዚህ የተለያዩ ቦታዎች አንዱ፣ የስሜት፣ የገንዘብ፣ ወይም የመንፈስ “ምድር መንቀጥቀጥ” የሚደርስበት፣ የእኛ ቤት ሊሆን ይችላል። የክህነት ሀይል ባህርን ጸጥ ለማድረግ እና የተሰባበረውን መሬት ለመፈወስ ይችላል። የክህነት ሀይል አዕምሮን ጸጥ ለማድረግ እና የተሰባበረውን ልብ ለመፈወስ ይችላል።

እንደ እግዚአብሔር ወንድ እንደዚያ አይነት የክህነት ሀይል ይኖረን ዘንድ ለመጸለይ፣ ለመጾም፣ ለማጥናት፣ ለመፈለግ፣ ለማምለክ፣ እና ለማገልገል ፈቃደኞች ነን? ሁለት ትትንሽ ሴት ልጆች ከቤተሰባቸው ጋር ለመተሳሰር ጉጉት ስለነበራቸው፣ አባታቸው እና ወንድማቸው ቅዱስ የመልከጼዴቅ ክህነትን ለመሸከም ዋጋን ለመክፈል ፈቃደኛ ነበሩ።

ውድ ወንድሞች፣ ቅዱስ ታማኝነት—ሌሎችን ለመባረክ የእግዚአብሔር ስልጣን ተሰጥቶናል። እያንዳንዳችን የእግዚአብሔር ወንድ ሰው እንዲሆን በቀድሞ የተመደበበት—የእግዚአብሔርን ክህነት በጀግንነት ለመሸከም፣ በክህነት ውስጥ ያለውን ሀይል ለመጨመር፡የሚያስፈልገውን ያህል ዋጋ ለመክፈል ጉጉ ያለው አይነት ሰው እንሁን። በዛም ሀይል፣ እኛ አለምን ለአዳኛችን፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ለማዘጋጀት እንችላለን። ይህች፣ በልብ በምወዳቸው እና በምደግፋቸው፣ በነቢዩ በፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን የምትመራ፣ ቤተክርስቲያኑ ናት። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።