2010–2019 (እ.አ.አ)
ሁሌም እርሱን አስታውሱት
ኤፕረል 2016


12:6

ሁሌም እርሱን አስታውሱት

በሁሉም ጊዜ፣ በሁሉም ነገሮች፣ እና በሁሉም በምንሆንባቸው ቦታዎች ሁሉ ሁሌም እርሱን እናስታውሰው ዘንድ ትሁቱ ምስክርነቴ እና ፀሎቴ ነው።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ በኤሽያ ውስጥ ሳገልግል፣ ሰዎች አንዳንዴ እንዲህ ብለው ይጠይቃሉ፣ “ሽማግሌ ጎንግ፣ በቤተክርስቲያኑ የኤሽያ ክልል ውስጥ ምን ያህል ሰዎች ይኖራሉ?”

እኔም እንዲህ እላለሁ፣ “የአለም ግማሹ ህዝብ---3.6 ቢሊዮን ሰዎች።”

አንዱ እንዲህ ጠየቀ፣ “የሁሉንም ስሞች ማስታወስ ከባድ ነው?”

ማስታወስ--- እና መርሳት የየቀን የህይወት ክፍል ነው። ለምሳሌ፣ አንዴ፣ አዲሱ ስልኳን ሁሉም ቦታዎች ከፈለገች በኋላ፣ በስተመጨሻ በሌላ ስልክ እላዩ ላይ ለመደወል ሚስቴ ወሰነች። ስልኳ ሲጮህ ስትሰማው፣ ሚስቴ እንዲህ ብላ አሰበች፣ “የሚደውልልኝ ማን ሊሆን ይችላል? ያንን ቁጥር ለማንም አልሰጠሁም!”

ማስታወስ--እና መርሳት--የዘለአለማዊ ጉዞአችንም ክፍል ነው። ጊዜ፣ ነፃ ምርጫ፣ እና ትውስታ በእምነት እንድንማር፣ እንድናድግ፣ እናም እንድንጨምር ይረዳናል።

በተወደደ መዝሙር ቃላቶች ውስጥ፤

ሁሉንም ክብር ለኢየሱስ ስም እንዘምራለን፣

እና አድናቆት እና ክብር እንሰጣለን። …

እናንተ ቅዱሳን፣ ተካፈሉ እና መስክሩ

እርሱን አስታውሱ።1

በእያንዳንዱ ሳምንት፣ ቅዱስ ቁርባን በመካፈል ውስጥ፣ ሁልም እርሱን ለማስታወስ ቃል እንገባለን። ከ400 በላይ ከሆኑ ጥቅሶች ማስታወስ ስለሚለው ቃል በማጣቀስ፣ ሁሌም እርሱን ልናስታውሰው የምንችልባቸው ስድስት መንገዶች እነዚህ ናቸው።

መጀመሪያ፣ በእርሱ ቃልኪዳኖች እና ማረጋገጫዎች ላይ መተማመንን በማኖር ሁሌም እርሱን ማስታወስ እንችላለን።

እና ወደ ላይ ያያሉ፣ ከዛም ፂዮን ወደ ታች ትመለከታለች፣ እናም ሙሉ ሰማይ በደስታ ይናወጣል፣ እና ምጌታ ዘለአለማዊ ቃልኪዳኖቹን ያስታውሳል--ከአዳም ጊዜ ጀምሮ እስከ አዳም ትውልድ “እውነቱን እስከሚያውጁበት፣ ድር በደስታ ትንቀጠቀጣለች።”2

ጌታ ቃላኪዳኖቹን ያስታውሳል፣ በመፀሀፍ ሞርሞን፣ ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት፣ አማካኝነት የተበታተነችው እስራኤልን የመሰብሰቡንም ቃልኪዳን ጨምሮ እናም የነብስን ዋጋ ለሚያስታውሱ እያንዳንዱ አባላት እና ለሚስኦኖች የተገቡትንም ቃልኪዳኖች ያካትታል።3

ጌታ ሀገራትን እና ሰዎችን ያስታውሳል እናም ማረጋገጫን ይሰጣል። በእነዚህ የግርግር እና ሽብር ጊዜያት፣4“አንዳንዶች በሰረገላዎች፣ እና አንዳንዶች በፈረሶች ይታመናሉ፤ ነገር ግን እኛ የጌታችን የእግዚአብሔርን ስም እናስታውሳለን፣”5 እርሱም “በወደፊትም እንደ ድሮ” የሚመራውም፣6 “በአስቸጋሪው ጊዜ” 7 እኛ “የሚሰለቸው የእግዚአብሔር ስራ ሳይሆን ነገር ግን የሰዎች ስራ መሆኑን እናስታውሳለን።”8

ሁለተኛ፣ በህይወታችን በሙሉ ያለውን እጁን በምስጋና እውቅና በመስጠት ሁሌም እርሱን ማሰብ እንችላለን።

ወደኋላ ሲታይ በህይወታችን ውስጥ የጌታ እጅ በብዛት ግልፅ ነው። የክርስቲያን ፈላስፋው ሶረን ኬርኬርጋርድ እንዳለው፤ “ህይወትን መረዳት ያለብን ካለፈው ነው። ነገር ግን … መኖር ያለብን ወደፊት ነው።”9

ውዷ እናቴ በቅርቡ 90 አመቷን አከበረች። በእያንዳንዱ የህይወቷ ቅፅበት ስለነበሩት የእግዚአብሔር በረከቶች በምስጋና መሰከረች። የቤተሰብ ታሪኮች፣ የቤተሰብ ባህሎች፣እና የቤተሰብ ትስስሮች የወደፊት ሂደትን እና ተስፋን በማቅረብ፣ ያለፉትን ነገሮች በማስታወስ እንድናጣጥም ይረዱናል። የክህነት ስልጣን መስመር እና የፓትሪያርክ በረከቶች በትውልዶች መሀል ስለ የእግዚአብሔር እጅ ምስክሮች ናቸው።

ምን እና እንዴት ለማስታወስ እንደምትመርጡ የሚያንፀባርቅ፣ የራሳችሁ ህያው የማስታወሻ መፅሀፍ እንደሆናችሁ አስባችሁት ታውቃላችሁ?

ለምሳሌ፣ ወጣት ሳለሁ፣ የትምህርት ቤት ቅርጫት ኳስ መጨወት በጣም እፈልግ ነበር። ደጋግሜ ተለማመድኩ። አንድ ቀን አሰልጣኙ 1.93 ሜትር ወደሆነው የሙሉ የክልል አማካኝ እና 1.88 ሜትር ወደሆነው የሁሌም የፊት ኮከብ አመለከተኝ እናም እንዲህ አለ፣ “ቡድኑ ውስጥ ላስገባህ እችላለሁ፣ ነገር ግን መቼም የምትጫወት አይመስለኝም።” ከዛም እንዴት በቅንነት እንዳበረታታኝ አስታውሳለሁ፣ “እግር ኳስ ለምን አትሞክርም? ጥሩ ልትሆን ትችላለህ።” የመጀመሪያ ጎል ሳገባ ቤተሰቦቼ ደስታቸውን ገለፁ።

በታማኝነት፣ በደግነት፣ በታጋሽነት፣ እና በማበረታታት አንድ እድል፣ ሁለተኛ እድልን የሚሰጡንን ሰዎች ማስታወስ አለብን። እና ሌሎች በጣም እርዳታ ባስፈለጋቸው ጊዜ የሚያስታውሱት ሰው መሆን እንችላለን። የሌሎችን ድጋፍ እና የመንፈስ ቅዱስን ምሬታዊ ተፅእኖ በአመስጋኝነት ማስታወስ እርሱን የማስታወስ አንዱ መንገድ ነው። ብዙ በረከቶቻችንን የምንቆጥርበትእና እግዚአብሔር ያደረገውን የምናይበት መንገድ ነው።10

ሶስተኛ፣ “ከሀጢያቱ ንሰሀ የሚገባ፣ እርሱን ይቅር እለዋለሁ፣ እናም እኔ ጌታ አላስታውሳቸውም” በማለት ጌታ ቃል የገባውን በማመን እርሱን ሁሌም ማስታወስ እንችላለን።11

ሙሉ ለሙሉ ንስሀ ስንገባ፣ መናዘዝን እና ሀጢያታችንን መተውን ጨምሮ፣ ፀፀታችን ሲወገድ፣ ከሄኖክ ጋር እንዲህ እንጠይቃለን፣ “ጌታ ሆይ፣ እንዴት ነው የሆነው?” እናም ምላሹን እንሰማለን “በክርስቶስ ላይ ባለን እምነት”12 እናም “እኔን እንድታስታውስ” በማለት በሰጠው ግብዣ ምክንያት ነው።”13

አንዴ ንስሀ ስንገባ እናም የክህነት መሪዎች ብቁ መሆናችንን ካወጁ፣ እነዚህ ያለፉ ሀጢያቶችን በመደጋገም መናዘዝ አያስፈልገንም። ብቁ መሆን ፍፁም መሆን ማለት አይደለም። የእርሱ የደስታ እቅድ በህይወት ጉዞአችን ውስጥ አንድ ቀን በክርስቶስ ፍፁም እስክንሆን ድረስ በትህትና ሰላም ውስጥ እንድንሆን ጋብዞናል፣ 14 አሁን ፍፁም ባለመሆናችን በቀጣይነት ልንሰጋ፣ ልንሰላች ወይም ልናዝን አይገባም። አስታውሱ፣ ስለ እኛ ማንም ሰው እንዲያውቅ የማንፈልገውን ነገሮች ሁሉ እርሱ ያውቃል--እናም አሁንም ቢሆን ይወደናል።

ሌሎችን እና እራሳችንን ይቅር ስንል የእርሱ የሀጢያት ክፍያ እንዲያድነን ለመርደት አንዳንዴ በክርስቶስ ምህረት፣ ፍትህ፣ እና ፍርድ እና ነፃ በሚያወጣው ግብዣው ላይ ያለን እምነት በህይወት ይፈተናል።

በሌላ አገር ያለች አንድ ሴት እንደ ጋዜጠኛ ለመስራት ማመልከቻ አስገባች፣ ነገር ግን ስራዎችን የሚመድበው ሀላፊ ጨካኝ ነበር። እንዲህ አላት፣ “በእኔ ፊርማ፣ የቆሻሻ ጉድጓድ ትቆፍሪያለሽ እንጂ ጋዜጠኛ እንደማትሆኚ አረጋግጥልሻሉ።” በወንበዴ ወንዶች መካከል እርሷ ብቻ ነበረች ሴት የቆሻሻ ጉድጓድ ቆፋሪ።

ከአመታት በኋላ፣ እቺ ሴት ሀላፊ ሆነች። አንድ ቀን የእርሷን ፊርማ ለስራ ፈልጎ አንድ ወንድ መጣ።

እርሷም ጠየቀች፣ “ታስታውሰኛለህ?” እርሱ አላስታወሳትም።

እንዲህ አለች፣ “አንተ አታስታውሰኝም፣ ግን እኔ አስታውስሀለሁ። በአንተ ፊርማ፣ መቼም ጋዜጠኛ እንደማልሆን አረጋግጠህ ነበር። ባንተ ፊርማ፣ በወንበዴ ወንዶች መሀል ብቸኛ ሴት ሆኜ የቆሻሻ ጉድጓድ እንድቆፍር ላከኝ።”

እንዲህ ብላ ነገረችኝ፣ “ያንን ሰው እርሱ ካደረገው በተሻለ ምላሽ መስጠት እንዳለብኝ ይሰማኛል--ነገር ግን ያ ጥንካሬ የለኝም።” አንዳንዴ ያ ጥንካሬ አብሮን የለም፣ ነገር ግን የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የሀጢያት ክፍያ በማስታወስ ሊገኝ ይችላል።

እምነት ሲከዳ፣ ህልም ሲበታተን፣ ልብ ደጋግሞ ሲሰበር፣ ፍትህን ስንፈልግ እና ምህረት ሲያስፈልገን፣ ቡጢ ስንጨብጥ እና እንባችን ሲፈስ፣ መጨበጥ ያለብንን እና መልቀቅ ያለብንን ለማወቅ ስንፈልግ፣ ሁሌም እርሱን ልናስታውስ እንችላለን። ህይወት አንዳንዴ እንደሚመስለው አስጨናቂ አይደለም። የእርሱ የማያልቅ ርህራሄ መንገዳችንን፣ እውነትን እና ህይወታችንን እንድናገኝ ሊረዳን ይችላል።15

ቃላቶቹን እና ምሳሌውን ስናስታውስ፣ ሰው አናስቀይምም እኛም አንቀየምም።

የጓደኛዬ አባት የሜካኒክ ሰራተኛ ነበር። ታማኝ ልፋቱ በጥንቃቄ በታጠቡት እጆቹ ላይም እንኳ ይታያል። አንድ ቀን በቤተመቅደስ ውስጥ ለማገልገል እጁን መታጠብ እንዳለበት አንድ ሰው ለጓደኛዬ አባት ነገረው። ከመናደድ ይልቅ፣ ይሄ መልካም ሰው ቤተመቅደስ ከመሄዱ በፊት በተጨማሪ ሳሙና ያለው ውሀ የቤተሰቡን የምግብ እቃዎች ማሻሸት ጀመረ። እርሱ በጣም በነፁ እጆች እና ልቦች “ወደ ጌታ ኮረብታ የሚወጡት” እና “በቅዱስ ቦታው የሚቆሙት” ሰዎች ተምሳሌት ነው።16

መልካም ያልሆኑ ስሜቶች፣ ቂሞች፣ ወይም ቅሬታዎች ካሉን፣ ወይም ሌሎችን ይቅረታ የመጠየቅ ምክንያት ካለን፣ የማድረጊያ ጊዜው አሁን ነው።

አራተኛ፣ ወደቤቱ ሁሌም በመልካም እንደሚቀበለን እንድናስታውስ እርሱ ይጋብዘናል።

በመጠየቅ እና በመፈለግ እንማራለን። ነገር ግን እባካችሁ ፍለጋውን አታቋርጡ፣ በቲ ኤስ ኤሊዮት ቃላት ውስጥ እንዳለው፣ “ከተነሳችሁበት እና ለመጀመሪያ ጊዜ ቦታውን እስካወቃችሁበት”17 እስክትደርሱ ድረስ። ዝግጁ ስትሆኑ፣ እባካችሁ ደግማችሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ልባችሁን ወደ መፅሀፍ ቅዱስ ክፈቱ። እባካችሁ ከልባችሁ፣ እንደገና ለመጀመሪያ ጊዜ ፀልዩ።

ያንን ቀድማችሁ እመኑ ወይም ትውስታ ትደክማለች። ያ እምነታችሁን እንዲያሳድግ አድርጉ። ከእግዚአብሔር ጋር፣ ያለመመለስ ትርጉም የለውም።

የጥንት እና የዘመኑ ነብያት፣ እውነቶችን፣ ቃልኪዳኖችን፣ እና በተመለሰው ወንጌሉ ውስጥ የቤዛነት ሀይሉን እንድናጣ ምክንያት የሚሆኑ፣ የሌሎች ወይም የራሳችን፣ ሰዋዊ ስህተቶች፣ ወይም ድክመቶችን እንዳንፈቅድ ይማፀኑናል።18 ይሄ በተለይ ፍፁም ባልሆነ ተሳትፎአችን አማካኝነት እያንዳንዳችን በምናድግበት በቤተክርስቲያን ውስጥ ጠቃሚ ነው። ነብዩ ዮሴፍ እንዲህ አለ፣ “ፍፁም ነኝ ብዬ መቼም አልነገርኳችሁም፤ ነገር ግን ባስተማርኩት መገለጥ ውስጥ ምንም ስህተት የለም።”19

አምስተኛ፣ በቅዱስ ቁርባን አማካኝነት በሰንበት ሁሌም እርሱን ማስታወስ እንችላለን። በምድራዊ አገልግሎቱ መጨረሻ እና በትንሳኤው አገልግሎቱ መጀመሪያ፣ አዳኛችን ዳቦ እና ወይን ወሰደ እናም ስጋ እና ደሙን እንድናስታውስ ጠየቀ፣20 “ይህንን ባደረጋችሁ ጊዜ በዚህ ሰአት ከእናንተ ጋር እንደነበርኩ ታስታውሳላችሁ።”21

በቅዱስ ቁርባን ስርአት ውስጥ፣ የልጁን ስም በላያችን ላይ ለመውሰድ እና ሁሌም እርሱን ለማስታወስ እናም የሰጠንን ትእዛዛቱን ለመጠበቅ፣ እና መንፈሱ ሁል ጊዜም ከእኛ ጋር ይሆን ዘንድ፣ ለአባታችን ለእግዚአብሔር ምስክር እንሆናለን።22

አሙሌቅ እንዳስተማረው፣ በመስካችን፣ በከብቶቻችን፣ እና በቤታችን ላይ ስንፀልይ፣ እናም የተቸገሩትን፣ የተራቆጡተን፣የታመሙ እና የተጎዱትን ስናስብ፣ እርሱን እናስታውሳለን።23

በስተመጨረሻም፣ ስድስተኛ፣ እርሱ ሁሌም እኛን እንደሚያስታውሰን ሁሉ እኛም እርሱን ሁሌ እንድናስታውሰው አዳኛችን ይጋብዘናል።

በአዲሱ አለም፣ ትንሳኤን ያደረገው አዳኛችን የነበሩት ሰዎች አንድ በአንድ ቀርበው እጆቻቸውን በጎኑ ላይ እንዲያደርጉ እናም በእጆቹ እና እግሮቹ ላይ ያሉትን የሚስማር ምልክቶች እንዲነኩ ጋበዛቸው።24

ቅዱስ መፅሀፍት ትንሳኤውን እንዲህ ይገልፁታል፣ “ማንኛውም እጅ እ እግር እንዲሁም መገጣጠሚያ ወደ ቦታው ይመለሳል፣” እና “የራስ ፀጉርም ቢሆን አይጠፋም።”25 ያ እንዳለ ሆኖ፣ አዳኛችን ፍፁም ሆኖ፣ ትንሳኤ ያደረገው አካሉ ቁስልን በጎኑ እና የሚስማር ምልክቶችን በእጆቹ እና እግሮቹ ላይ እንዴት አሁንም ሊኖር እንደቻለ እባካችሁ አስቡበት።26

አንዳንዴ በታሪክ ውስጥ፣ ምድራዊ ሰዎች በስቅላት ሞተው ያውቃሉ። ነገር ግን አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ብቻ ነው የንፁህ ፍቅሩን ምልክቶች ተሸክሞ አሁንም እኛን የሚቀበለን። እያንዳንዳችንን፣ በስም፣ ወደ እርሱ ለማቅረብ በመስቀል ላይ የመሆኑን ትንቢት የሚያሟለው እርሱ ብቻ ነው።27

አዳኛችን እንዲህ አወጀ፤

“አዎን እነርሱ ይረሱ ይሆናል እኔ ግ አልሳሽም።”

“እነሆ እኔ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ።”28

እርሱ እንደዲህ ይመሰክራል፤ “እኔ ከፍ የተደረኩት ነኝ። እኔ የተሰቀለው ክርስቶስ ነኝ። እኔ የእግዚአብሐር ልጅ ነኝ።”29

በሁሉም ጊዜ፣ በሁሉም ነገሮች፣ እና በሁሉም በምንሆንባቸው ቦታዎች ሁሉ ሁሌም እርሱን እናስታውሰው ዘንድ ትሁቱ ምስክርነቴ እና ፀሎቴ ነው።30 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።