2010–2019 (እ.አ.አ)
አምናለሁን?
ኤፕረል 2016


11:31

አምናለሁን?

እነዚህ ነገሮች እውነት ከሆኑ፣ ከዚህ በፊት አለም አውቃ ከነበረው በላይ ታላቅ የተስፋ እና የእርዳታ መልእክት አለን።

በመጋቢት 30 ላይ፣ ልክ ከአንድ አመት በፊት፣ ከአሜሪካን ፎርክ፣ ዩታህ የሆነው ትንሹ የሁለት አመት እድሜ ያለው ኢታን ካረነሰካ፣ በሳንባ ምች በሽታ እና በሳንባው አካባቢ ባለ ውሃ መቋጠር ምክንያት ሆሰፒታል ተኝቶ ነበር። ከሁለት ቀናት በኋላ፣ በሂሊኮርተር በሶልት ሌክ ከተማ ወዳለ ዝቅተኛ ሆስፒታል መብረር እስኪኖርበት ድረስ የጤናው ሁኔታ በጣም ከባድ ደረጃ ደረሰ። የተጨነቀችው እናቱ፣ ሚሼል፣ በሂሊኮፈፍተሩ የፊት ወንበር ላይ ሆና ከወንድ ልጇ ጋር እንድትበር ተፈቅዶላት ነበር። በሂሊኮፕተር ውስጥ ካሉት ሌሎች ሰዎች ጋር እንድታወራ ማዳመጫ ተሰጥቷት ነበር። ሀኪሞቹ የታመመው ትንሹ ልጅን ሲያክሙ ትሰማ ነበር እናም እራሷ የህፃን ልጅ የጤና ተንከባካቢ በመሆኗ፣ ሚሼል ኤታን ሀይለኛ ችግር ውስጥ እንደነበር ለመረዳት በበቂ ሁኔታ ታውቃለች።

ኢታን ካረነሰካ በታመመበት ጊዜ

በዚህ አሳሳቢ ወቅት ላይ፣ ሚቼል በድራፐር ዩታህ ቤተመቅደስ አናት ላይ አየበረሩ እንደነበር ተገነዘበች፣ ከአየር ላይ ሆና፣ ከሸለቆው ማዶ ወደ ውጪ ተመለከተች እንዲሁም የጆርዳን ሪቨር ቤተመቅደስንም፣ የኦኩርህ ማውንቴን ቤተመቅደስንም፣ እናም የሶልት ሌክ ከተማ ቤተመቅደስንም በሩቁ ተመለከተች። እንዲህ የሚል ሀሳብ ወደ አእምሮዋ መጣ፤ “ታምኚዋለሽ ወይስ አታምኚውም”

ስለዚህ ተሞክሮ እንዲህ ትላለች።

“በህፃናት ክፍል ውስጥ እና በወጣት ሴቶች ክፍል ውስጥ ስለ ቤተመቅደስ በረከቶች እና ቤተሰቦች ዘላለም እንደሆኑ ተምሬአለሁ። በምሽኔ ላይ መልካም ለሆኑት የሜክሲኮ ህዝብ ስለ ቤተሰቦች መልእክቶችን አካፍያለሁ። ከዘላለም አጋሬ ጋር ለጊዜው እና ለዘላለም በቤተመቅደስ ታትሜያለሁ። እንደ ወጣት ሴቶች መሪ ስለ ቤተሰብ ትምህርቶችን አስተምሬ ነበር እናም በቤተሰብ የቤት ምሽት ላይ ለልጆቼ ስለ የዘላለም ቤተሰቦች ታሪኮች አካፍያለሁ። አውቀው ነበር፣ ነገር ግን አምነው ነበርን? መልሴ የመጣው ጥያቄው ልክ ወደ አእምሮዬ በመጣበት ፍጥነት ነበር፤ መንፈስ ለልቤ እና ለአእምሮዬ አስቀድሜ የማውቀውን “አምኜዋለሁ” የሚለውን አረጋገጠልኝ።

“በእውነት ቤተሰቦች የዘላለም እንደሆኑ ላለኝ እውቀት እና እምነት በማመስገን የሰማይ አባት ጋር ልቤን በፀሎት አፈሰስኩት። ሁሉን እንዲቻል ላደረገው ስለ ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ አመሰገንኩት። ለወንድ ልጄ አመሰገንኩት እናም ትንሹ ኢታንን ወደ ሰማያዊው ቤቱ ማምጣት ካስፈለገው፣ ችግር እንዳልነበረው ለሰማይ አባቴ አሳወኩት። ሙሉ ለሙሉ በሰማይ አባቴ ላይ ተማመንኩ፣ እናም ኤታንን በድጋሚ እንደማው አወቅሁ። በዛች አስቸኳይ ጊዜ ላይ ወንጌሉ እውነት እንደነበር እውቀት እና እምነት ስለነበረኝ በጣም አመስጋኝ ነበርኩ። ሰላም ነበረኝ።”1

ልዩ ህክምናን እያገኘ፣ ኤታን ብዙ ሳምንታትን በሆስፒታል አሳለፈ። ልዩ ህክምናን እያገኘ፣ ኤታን ብዙ ሳምንታትን በሆስፒታል አሳለፈ። ውድ የሆኑ ሰዎች ፀሎቶች፣ ፆም፣ እናም የእምነት ፍቅር፣ ከዛ እንክብካቤ ጋር በአንድ ላይ፣ ከቤተሰቡ ጋር እንዲሆን ሆሰፒታሉን ለቆ ወደ ቤት እንዲመለስ ፈቀደለት። ዛሬ ጤነኘ እና በጥሩ ነው ያለው።

የካረነሰካ ቤተሰብ
ኤታን ካረነሰካ ተሽሎት

ለሚሼል ይህ ጠቃሚ ወቅት በህይወትዋ ሙሉ የተማረችው ከቃላቶች በላይ እንደነበርነሰ፤ እውነት እንደሆነ አረጋገጠላት።

አንዳንዴ በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን ተአምር እና ማእረግ ሙሉ ለሙሉ ለመረዳት እስክንቸገር ድረስ እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልነታችን ለተሰጡን በረከቶች በጣም እንዛመዳቸዋለንን? በዚህ ህይወት ውስጥ ሊቀርብ ከሚችለው ታላቅ ስጦታ ግብዝ በመሆናችን ጥፋተኞች ሆነን እናውቃለንን? አዳኝ እራሱ ይህንን አስተማረ፣ “ትእዛዛቴን ከጠበቃችሁ እና እስከመጨረሻው ከፀናችሁ፣ ከእግዚያብሄር ስጦታዎች ሁሉ ሆነውን ታላቅ ስጦታ የዘላለም ህይወትን ይኖራችኋል።”2

እሁድ ለመሄድ እና እንዴት ጥሩ ሰው መሆን እንደምንችል ለመማር ይህ ቤተክርስቲያን ከጥሩ የበለጠ ቦታ እንደሆነ እናምናለን። መልካም የስነ ምግባር ደረጃ ካላቸው ጋር የምንጎዳኝበት ከሚያምር የክርስቲያን ማህበራዊ ክበብ የበለጠ ነው። ወላጆች ልጆቻቸውን ተጠያቂዎች፣ መልካም ህዝብ ይሆኑ ዘንድ በቤታቸው ውስጥ ማስተማር የሚችሉት ታላቅ የሀሳቦች ክምችት አይደለም። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከእነኚህ ነገሮች ሁሉ የበለጠ በጣም ጥሩ ነው።

እንደ ሀይማኖት ጥልቅ የኛ ብቻ ናቸው ስለምንላቸው እውቀቶች ለደቂታ አስቡ። እየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ሳለ ያቋቋመው ቤተክርስቲያን እራሱ በድጋሚ በእግዚያብሄር በተጠራ ነብይ በኩል በእኛ ጊዜ እንደተመለሰ እና በእግዚያብሄር ስም ለመተግበር የጥንት ሀዋሪያት የያዙትን ተመሳሳይ ኃይል እና ስልጣን የእኛ መሪዎች እንደያዙ እናምናለን። የእግዚያብሄር ክህነት ተብሎ ይጠራል። በተመለሰው ስልጣን አማካኝነት፣ እንደ ጥምቀት ያሉ የመዳን ስርዓቶችን መቀበል እንደምንችል እና የሚያፀዳው እና የሚያጣራው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ሁሌም ከእና ጋር ይሆናል ብለን እናወራለን። በክህነት ቁልፍ አማካኝነት ይህንን ቤተክርስቲያን የሚመሩ እና አቅጣጫ የሚያሲዙ ሃዋሪያት እና ነብያት አሉን፣ እናም በነዚህ ነብያቶች በኩል እግዚያብሄር ለልጆቹ እንደሚናገር እናምናለን።

አንድ ቀን ወደ እግዚያብሄር መገኛ እንድንመለስ እና ከእሱ ጋር ለዘላለም አብረን እንድንኖር የሚያስችሉንን ቤተመቅደስ ውስጥ ቃልኪዳኖች ለመግባት እና ስርዓቶችን ለመቀበል ይህ የክህነት ኃይል እንዲቻል እንዳደረገው እናምናለን። እንዲሁም፣ በዚህ ኃይል አማካኝነት፣ የእግዚያብሄር ቤቶች ናቸው ብለን በምናምነው በቅዱስ ህንፃዎች ውስጥ ጥንዶች አዲሱን እና ዘላለማዊውን የጋብቻ ቃልኪዳን ሲገቡ ቤተሰቦች ለዘላለም በአንድ ላይ ይታሰራሉ የሚለውንም የእኛ ብቻ አድርገን እናወራለን። ለእኛ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በነዚህ ጠቃሚ የማዳን ስርዓቶች ላይ ለመሳተፍ እድል ሳይገኙ በምድር ላይ ለኖሩት ለቅድመ አያቶቻችንም እነዚህን የማዳን ስርዓቶችን መቀበል እንደምንችል እናምናለን። በእነዚሁ ተመሰሳሳይ ቅዱስ ቤተመቅደሶች ውስጥ ለቅድመ አያቶቻችን ስርዓቶችን በውክልና መፈፀም እንደምንችል እናምናለን።

ኢየሱስ ክርስቶስ የአለም አዳኝ እንደሆነ መፅሀፍ ቅዱስ ስለሚያውጀው በነብይ እና በእግዚያብሄር ኃይል አማካኝነት ተጨማሪ ቅዱሳን መፅሀፍትን፣ ተጨማሪ ምስክርን እንደምንቀበል እናምናለን።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የእግዚያብሄር መንግስት እንደሆነ እና በምድር ላይ ብቸኛው ትክክለኛ ቤተክርስቲያን እንደሆነ እንናገራለን። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተብሎ ይጠራል ምክንያቱም ከአናት ላይ ይቆማልና፣ የእሱ ቤተክርስቲያን ነው፣ እናም እነዚህ ነገሮች የተቻሉት በቤዛዊ መስእዋእትነቱ ምክንያት ነው።

እነዚህ የተለዩ ሁኔታዎች በዚህ ምድር ላይ ባለ በየትኛውም ቦታ እና ድርጅት ውስጥ መገኘት እንደማይችሉ እናምናለን። ሌሎች ሀይማኖቶች እና ቤተክርስቲያኖች መልካም እና ታማኝ ሆነው ሳለ፣ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሚገኘውን የማዳን ስርዓቶችን የማቅረብ ስልጣን አንዳቸውም የላቸውም።

የእነዚህ ነገሮች እውቀት አለን፣ ነገር ግን እናምናቸዋለን? እነዚህ ነገሮች እውነት ከሆኑ፣ ከዚህ በፊት አለም አውቃ ከነበረው በላይ ታላቅ የተስፋ እና የእርዳታ መልእክት አለን። እነሱን ማመን ለእኛ እና ለምንወዳቸው የዘላለማዊ ጥቅም ጉዳይ ነው።

ለማመን፣ ወንጌልን ከጭንቅላቶቻችን ወደ ልቦቻችን መውሰድ አለብን! በቀላሉ በእንቅስቃሴዎቻችን ውስጥ ወንጌልን መኖር የሚቻል ነው ምክንያቱም ስለሚጠበቅብን ምክንያቱም ያደግንበት ባህል ስለሆነ ወይም ምክንያቱም ልምድ ስለሆነ። አንዳንዶች ምን አልባትም የንጉስ ቢኒያም አስገዳጅ ስብከትን ተከትሎ ህዝብ የተሰማቸውን እንዲህ የሚለውን ድምፅ አላጋጠማቸውም። እናም ሁሉም በአንድ ድምፅ እንዲህ በማለት ጮሁ፣ አዎን፣ ለእኛ የተናገርካቸውን ቃላት በሙሉ እናምናለን፤ እናም ደግሞ ሁሉን የሚገዛው በጌታ መንፈስ አማካኝነት እርግጠኝነታቸውን እና እውነተኝነታቸውን እናውቃለን፣ ታላቅ ለውጥ ለእኛ ወይንም በልባችን ውስጥ በመስራት ከእንግዲህ ኃጢያት ለመፈፀም ምንም ፍላጎት የለንም፣ ነገር ግን ያለማቋረጥ መልካምን መስራት እንጂ።3

ከአሁን በኋላ የአለም መንገድ የመከተል ፍላጎት እናቁም እግዚያብሄርን እንድናስደስት ዘንድ ሁላችንም ልቦቻችን እና የውስጥ ፍጥረታችንን ለመለወጥ መሻት ይገባናል። ትክክለኛ መለወጥ በጊዜ ሂደት የሚመጣ እና እምነትን ለመለማመድ ፍቃደኝነትን የሚያካትት ሂደት ነው። ከኢንተርኔት ይልቅ ቅዱሳን መፅሀፍትን ስንመረምር ይመጣል። ለእግዚያብሄር ትዕዛዛት ታዛዦች ስንሆን ይመጣል። በዙሪያችን ያሉትን ስናገለግል መለወጥ ይመጣል። ቅን ከሆነ ፀሎት፣ ቋሚ ከሆነ የቤተመቅደስ ተሳትፎ፣ እናም በእግዚአብሔር የተሰጡንን ሃላፊነቶች በእምነት ከማሟላት ይመጣል። ወጥነት እና የእለት ተእለት ጥረትን ይጠይቃል።

በብዛት እንደዚህ እጠየቃለሁ፣ “የዛሬ የእኛ ወጣቶች ከሚጋፈጡዋቸው ፈተናዎች ታላቅ የቱ ነው?” “ታላቅ እና ሰፊ ህንጻ” በህይወታቸው ውስጥ ሁሌ የሚገኝ ተፅዕኖ እንዳለው እንደማምን መልስ ሰጠኋቸው።4 መፅሀፈ ሞርሞን በተለይ ለእኛ ጊዜ የተፃፈ ከነበረ፣ ከዚያም በሌሂ የህይወት ዛፍ ራእይ ውስጥ ለሁላችንም ያለው መልእክት ጠቀሜታ እና አነኛ ጣቶቻቸውን የሚጠቁሙ ሰዎች ጉዳት እና ታላቅ እና ሰፊ ከሆነው ህንፃ ያለው ማንጓጠጥ በእርግጥም ማለፍ አንችልም።

ለእኔ በጣም አሳዛኝ የሆነው አንደኛቸውን በድቅድቅ ጨለማ በቀጥተኛው እና በጠባቧ መንገድ ውስጥ የታገሉ፣ የብረት ዘንጉን አጥብቀው የያዙ፣ ግባቸውን ያሳኩ፣ እናም ንፁውን ፍቅር እና ጣፋጩን ፍሬ መቅመስ የጀመሩት ሰዎች መገለጫ ነው። እነኛ በትልቁ እና በሰፊው ህንፃ ውስጥ ያሉ አለባበሳቸው እጅግ ያማረ ሰዎች ቅዱስ መፅሀፉ እንዲህ ይላል “ወደ ፍሬው መጥተው በተካፈሉት ላይ እጃቸውን እየጠቆሙ እና እየተሳለቁባቸው ነበር።

“እናም ስለተሳለቁባቸውም ፍሬውንም ከተካፈሉ በኋላ አፈሩ፣ ወደተከለከለው መንገድ ገቡና ጠፉ።”5

እነኚህ ጥቅሶች በህይወታችን ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ያለንን ሰዎች ይገልፃሉ። የተወለድንበት ወይም በጭለማ ጭጋግ ውስጥ በመጓዝ የደረስን ብንሆንም፣ ከሁሉም በላይ ውድ እና ተወዳጅ” የሆነውን ይህን ፊሬ ቀምሰናል6 “የእግዚአብሔር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ወደሆነው” የዘለአለም ህይወት ለመድረስ ችሎታ አለን። ሀይማኖታችንን የሚያሳልቁትን ወይም መጠራጠርን በመፍጠር የሚደሰቱትን ወይም በቤተክርስቲያኗ መሪዎች እና ትምህርት ጥፋት የሚያገኙትን ባለማዳመጥ መመገብን መቀጠል ያስፈልገናል። በየቀኑ— ከጥርጣሬ ይልቅ እምነትን ለመምረጥ የምናደርገው ምርጫ ነው። ሽመግሌ ኤም. ሩሴል ባላርድ “በጀልባው ላይ ቆዩ፣ የህይወት አድን ጃኬት ተጠቀሙ፣ እናም በሁለት እጃችሁ ጠንክራችሁ ያዙ” ብለው አጥብቀው አስገንዝበውናል።7

የጌታ እውነተኛ ቤተክርስቲያን አባል እንደመሆናችን፣ አሁንም በጀልባው ላይ ነን። በህይወት ፈተናዎች ውሰጥ በሰላም እንዲያደርሱን ምቾት፣ እርዳታ፣ እና ምሬት የሚሰጡንን እውነታን ለማግኘት የአለምን ፍልስፍናዎችን መመርመር የለብንም— አስቀድሞ አለንና! ልክ የኤታን እናት ለረጅም ጊዜ የቆየው እምነቷን እንደመረመረች እና አስቸጋሪውን ወቅት በድፍረት፣ “አምነዋለሁ” ብላ እንዳወጀችው፣ እኛም ማድረግ እንችላለን።

በጌታ መንግስት ውስጥ ያለን አባልነት መለካት የማይችል ዋጋ ያለው ስጦታ እንደሆነ መሰክርላችኋለሁ። ታዛዦች እና ታማኞች ለሆኑት ሰዎች ያዘጋጀው በረከቶች እና ሰላም የሰው አእምሮ መሸከም ከሚችላው ከማንኛውም ነገር በላይ የሆነ እንደሆን እመሰክራለሁ። ይህንን ምስልርነት የምተውላችሁ በእየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።