2010–2019 (እ.አ.አ)
ምን እናድርግ?
ኤፕረል 2016


11:52

ምን እናድርግ?

እህቶች፣ መንግስቱን የምንገነባው ሌሎችን ስንንከባከብ ነው። ስለ እውነት ስንናገር እና ስንመሰክርም ጭምር መንግስቱን እንገነባለን።

ከኢየሱስ ትንሳኤና ማረግ በኋላ፣ሐዋሪያው ጴጥሮስ እንዳስተማረው፣ “እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን፣ እግዚአብሔር ጌታ ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።” ሲያደምጡ የነበሩት ልባቸው ተነካ እናም ጴጥሮስ እና ሌሎችን እንዲህ ብለው ጠየቁ፣ “ወንድሞች ሆይ፣ ምን እናድርግ?”1 እናም የኋላ ኋላ ለጴጥሮስ ትምህርቶች በደስታ ታዘዙ።

ነገ የፋሲካ እሁድ ነው፣ አዳኝን ለማሰብ፣ ንስሀ ለመግባት፣ እና በደስታ ለመታዘዝ እኛም ልባችን እንደተነካ ተስፋ አደርጋለሁ።

በዚህ አጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ፣ በቤተክርስቲያን መሪዎች፣ ከወንድም እና ከሴትም፣ የሚሰጡ የተነሳሱ ምሬቶችን እናዳምጣለን። በእነርሱ ቃላት ልቦቻችን እንደሚነኩ በማወቅ፣እንዲህ ብዬ እጠይቃችኋለሁ፣ “ሴቶች እና እህቶች፣ እኛ ምን እናድርግ?”

Tእንደ አጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ ፕሬዘዳንትንቷ፣ ኤሊዛ አር ስኖው ከ150 አመታት በፊት ለእህቶች እንዲህ ብላ አወጀች፣ “ጌታ በእኛ ላይ ከፍተኛ ሀላፊነቶችን ጥሎብናል።”2 የእርሷ አዋጅ አሁንም እውነት እንደሆነ እመሰክራለሁ።

የጌታ ቤተክርስቲያን ልዩ ተሰጥኦቸውን ለመንከባከብ እና ድምጻቸውን ከፍ የሚያደርጉ እናም ለወንጌልን እውነትነት ቋሚ የሆኑ በመንፈስ የሚመሩ ሴቶች ያስፈልጉታል። የምንነሳሳበት እና ስሜታችን የእግዚአብሄርን መንግስት ለመገንባት አስፈላጊ ክፍሎች ናቸው፣ይህም ማለት ለእግዚያብሄር ልጆች ደህንነት ለማምጣት የበኩላችንን ማድረግ ነው።

በመንከባከብ መንግስቱን መገንባት

እህቶች፣ መንግስቱን የምንገነባው ሌሎችን ስንንከባከብ ነው። ሆኖም፣ በተመለሰው ወንጌል ውስጥ መገንባት ያለብን የመጀመሪያው የእግዚያብሄር ልጅ እራሳችን ነው። ኤማ ስሚዝ እንዲህ አለች፣ “ራሴን ለማወቅ እና ለመረዳት፣ ከፍ ማለቴን የማይረዳውን ማንኛውንም ባህል ወይም ፍጥረት ለማሸነፍ እችል ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን መንፈስ እሻለሁ።”3 በአዳኝ ወንጌል ውስጥ የእምነት መሰረት መገንባት እና በቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖች ሀይል በማግኘት ወደዘለአለማዊነት ከፍ ለመደረግ መግፋት አለብ።

ባህሎቻችን በዳግም በተመለሰው ወንጌል ውስጥ ቦታ ባይኖራቸውስ? እነዚህን ለመተው የስሜት ድጋፌ እና የሌሎች መንከባከብ፣ እኔ ያስፈልገኝ እንደነበር፣ ያስፈልጋቸውም ይሆናል።

በቅድመ አባቶቼ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚዘጋጀውን፣ የእኔ ሰርግ ክብረ በአል ላይ የማግኖሊያ ዛፎች ይኖሩ ዘንድ፣ በተወለድኩ ጊዜ ወላጆቼ የማግኖሊያ ዛፍን ተከሉ። ነገር ግን በጋብቻዬ ቀን፣ በአጠገቤ ምንም ወላጆች አልነበሩም እና ምንም ማግኖሊያ አልነበረም፣ ምክንያቱም ወደ ቤተክርስቲያኗ ከተቀየርኩ አንድ አመት እንደሞላኝ፣ የቤተመቅደስ ቡራኬን ለመቀበል እና ከእጮኛዬ ዴቪድ ጋር ለመታተም ወደ ሶልት ሌክ ሲቲ፣ ዩታህ፣ ተጓዝኩኝ።

ሉዚያንን ለቅቄ ወደ ዩታህ ስቃረብ፣ የቤት አልባነት ስሜት ወደ እኔ መጣ። ከሰርጉ በፊት፣ በፍቅር አክስት ካሮል በመባል ከምትታወቀው፣ የዴቪድ የእንጀራ እናት እናት ጋር ነበር የምቆየው።

በደምብም ከማላቃቸው ቤተሰቦች ጋር ለዘለአለም ከመታተሜ በፊት በእንግዳ ቤት ውስጥ ለመቆየት፣ ይኸው ለዩታህ እንግዳ ሆኜ ተገኘሁ። (ጥሩው ነገር የወደፊት ባለቤቴን እና ጌታን አፍቅር እና አምን ነበር!)

በአክስት ካሮል ቤት የፊት በር ስቀርብ፣ ፈርቼ ነበር። በሩ ተከፈተ፣ እንደፈራች ጥንቸል እዚያው ቆምኩ--እናም አክስት ካሮል፣ ያለ ምንም ቃል፣ ወደ እኔ ደረሰች እና ወደ ክንዶቿ አስገባችኝ። እርሷ፣ የራሷ ልጆች ስላልነበራት፣በተንከባካቢ ልቧ እኔ የራሴ የሆነ ያህል የሚሰማኝ ቦታ እንደሚያስፈልገኝ ታውቅ ነበር። ኦ፣ የዛ ወቅት ምቾት እና ጣፋጭነት! ፍራቻዬ ቀለጠ፣ እና ደህንነት ወዳለበት መንፈሳዊ ቦታ እየተሳብኩ እንደሆነ ስሜት ወደ እኔ መጣ።

አክስት ካሮል ለእኔ እንዳደረገችው፣ በህይወታችሁ ውስጥ ፍቅር ለሌላ ሰው ቦታን ያዘጋጃል።

እናቶች ያልተወለዱ ልጆችን ለመንከባከብ በሰውነታቸው ውስጥ---እና ሲያሳድጓቸውም በተስፋ በልባቸውም ውስጥ---ክፍል ያዘጋጃሉ፣ ነገር ግን መንከባከብ ልጆችን በመውለድ ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። ሔዋን ልጆች ከመውለዷ በፊት “እናት” ተብላ ተጠርታለች።4 “እናት መሆን” ማለት “ህይወት መስጠት” ማለት ነው ብዬ አምናለሁ። ህይወት የምትሰጡበት ብዙ መንገዶችን አስቡባቸው። ይህም ማለት ተስፋ ለሌለው ስሜታዊ ህይወት መስጠት ወይም ለተጠራጣሪ ሰው መንፈሳዊ ህይወትን መስጠት ሊሆን ይችላል። በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ጋር፣ ለተገደቡት፣ ለተወገዱት፣ እና እንግዳ ለሆኑት በስሜት የሚፈውስ ቦታ ለመፍጠር ትችላላችሁ። በዚህ ረጋ ብለው ግን ሀይለኛ በሆኑት መንገዶች፣ የእግዚአብሔርን መንግስት እንገነባለን። እህቶች፣ ሁላችንም ወደ ምድር የመጣነው ህይወት ከሚሰጡ፣ የእናትነት ስጦታዎች ጋር ነው፣ ምክንያቱም ያ የእግዚአብሔር እቅድ ነውና።

የእርሱን እቅድ መከተልና የመንግስት ገንቢዎች መሆን ራስ ወዳጅ ያልሆነ መስዋዕት ያስፈልገዋል። ኦርሰን ኤፍ. ዊትኒይ እንዲህ ፃፈ፤ “የምንሰቃየው እና የምንፀናበት ነገሮች በሙሉ፣ በተለይ በትግስት ስንፀና፣ … ልቦቻችንን ያነፃል … እና ይበልጥ የተረጋጋን እና ለጋስ እንድንሆን ያደርገናል። … በችግር እና መከራ ውስ ጥ ነው፣ በሰማይ እንዳሉት አባታቸን እና እናታችን እንድንሆን የሚያደርገንን ትምህርት እናገኛለን።”5 እየተበደልንም ቢሆን በሚያነፁን መከራዎች ውስጥ በትግስት በመስራት ማለፍ አለብን፣ የምንሰቃየውን ሁሉ ክርስቶስ ይረዳል እናም በእርሱ ስራ ውስጥ እኛ እንድንጠቅም ያደርገናል ብለን እናምናለን።

በንግግር እና በምስክርነት አማካኝነት መንግስቱን መገንባት

ስለ እውነት ስንናገር እና ስንመሰክርም ጭምር መንግስቱን እንገነባለን። የጌታን ንድፍ እንከተላለን። እርሱ በእግዚአብሔር ሀይል እና ስልጣን ይናገራል እናም ያስተምራል። እህቶች፣ እኛም ያንን ማድረግ እንችላለን። ሴቶች መነጋገር እና መሰብሰብ ይወዳሉ። በአደራ በተሰጠን የክህነት ስልጣን ስንሰራ፣ ንግግራችን እና መሰብሰባችን ወረ ወንጌል ማስተማር እና መምራት ያድጋል።

እህት ጁሊያ ቢ ቤክ፣ የቀድሞ አጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ ፕሬዘዳንት፣ እንዲህ አስተማረች፤ “ለግል መገለጥ ብቁ መሆን፣ መቀበል እና በዛ ላይ ለመተገበር መቻል በዚህ ህይወት ውስጥ ሊገኝ የሚችል ብቸኛው በጣም አስፈላጊው ክህሎት ነው። … ንቁ ጥረትን ይጠይቃል።”6

ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጣ የግል መገለጥ ሁሌም እንድንማር፣ እንድንናገር፣ እና በዘለአለማዊ እውነታ፟፣ የአዳኝ እውነታ፣ ላይ እንድንተገብር ያነሳሳል። ይበልጥ ክርስቶስን ስንከተል፣ የበለጠ የእርሱ ፍቅር እና ምሬት ይሰማናል፤ የበለጠ የእርሱ ፍቅር እና ምሬት ሲሰማን፣ እርሱ እንዳደረገው እውነተን ለመናገር እና ለማስተማር፣ ተቃርኖ ቢኖርም እንኳ፣ በይበልጥ እንፈልጋለን።

ከጥቂት አመታት በፊት፣ የስልክ ጥሪን በተቀበልኩበት ጊዜ እናትነትን ለመጠበቅ መገለጥ እንዲኖረኝ ፀለይኩ።

ደዋይዋ እንዲህ ጠየቀች፣ “ኔይል ማሪዮት ነሽ፣ ትልቅ ቤተሰብ ያላት እናት?”

በደስታ እንዲህ መለስኩ፣ “አዎ!”፣ “መልካም፣ ጥሩ ነው!” የሚል አይነት ምላሽ ከእርሷ በመጠበቅ ነበር።

ነገር ግን አይደለም! ድምፅዋ በስልክ ውስጥ እየጮኸ የሰጠችኝን ምላሽ መቼም አልረሳውም፤ “ወደ እዚህ በጣም ወደተጨናነቀ ፕላኔት ልጆችን በማምጣትሽ በጣም ተናድጃለሁ!”

“ኦ፣” ተንተባተብኩ፣ “እንዴት እንደምታስቢ ገባኝ።”

በንዴት ጮኸች፣ “አይ--አልገባሽም”

እኔም በማጉረምረም፣ “መልካም፣ ምናልባት አልገባኝ ይሆናል።”

በጩኸት እናት ለመሆን ስላደረኩት የሞኝ ምርጫ ማውራት ጀመረች። እየቀጠለች እያለ፣ ለእርዳታ መፀለይ ጀመርኩኝ እና ረጋ ያለ ሀሳብ ወደ እኔ መጣ፤ “ጌታ ለእርሷ ምን ይል ይሆን?” ከዚያም በፅኑ ቦታ ላይ የቆምኩ እና በኢየሱስ ክርስቶስ እሳቤ ብርታት እንዳገኘሁ ተሰማኝ።

እንዲህ ስል እመለስኩኝ፣ “የትልቅ ቤተሰብ እናት በመሆኔ ደስተኛ ነኝ፣ እናም አለምን የተሻለ ቦታ ሊያደርጉ እንዲችሉ አድርጌ ለመንከባከብ የተቻለኝን ሁሉ እንደማደርግ ቃል እገባልሻለሁ።”

እንዲህ ብላ መለሰች፣ “መልካም፣ እንደዛ እንደምታደርጊ ተስፋ አደርጋለሁ!” እና ዘጋችው።

ትልቅ ነገር አልነበረም--- ሆኖም በእራሴ ኩሽና ውስጥ በደህንነት ቆሜ ነበር! ነገር ግን በራሴ ትንሽ መንገድ፣ ቤተሰብ፣ እናቶች፣ እና የሚንከባከቡን የሚያጠቃ ለመከላከል የቻልኩት በሁለት ነገሮች ምክንያት ነው። (1) የእግዚአብሔር የቤተሰብ አስተምሮትን ተረድቼዋለሁ እና አምንበታሉ፣ እናም (2) የዚህን እውነታ ቃላት እንዲመሰክሩ ፀልዬ ነበር።

ከአለም ወጣ እና ለየት ማለት ጥቂት ትችቶችን ያመጣል፣ ነገር ግን የአለም ምላሽ ምንም ቢሆን፣ እኛ እራሳችንን ከዘለአለማዊ መርሆዎች ጋር ማጣመር እና ከፍ አድርገን መመስከር አለብን።

እራሳችንን ስንጠይቅ፣ “ምን እናድርግ?” ይሄን ጥያቄ እናሰላስለው፤ “አዳኝ በቀጣይነት ምን ያደርጋል?” እርሱ ይንከባከባል። እርሱ ይፈጥራል። እድገትን እና መልካምነትን ያበረታታል። ሴቶች እና እህቶች፣ እነዚህን ነገሮች ማድረግ እንችላለን! የመጀመሪያ ክፍል ልጃገረዶች፣ የእናንተን ፍቅር እና ደግነት የሚያስፈልገው የቤተሰብ አባል አንድ ይገኛልን? ሌሎችን በመንከባከብ መንግስቱን ትገነባላችሁ።

በአባቱ ምሬት ስር ሆኖ፣ የአዳኝ የምድር ፍጥረት፣ የመንከባከብ ታላቅ ድርጊት ነበር። እንድናድግበት እና በእርሱ የሀጢያት ክፍያ ላይ እምነትን እንድናዳብር ቦታን አዘጋጀለን። እምነት በኢየሱስ ክርስቶስ እና በሀጢያት ክፍያው ላይ የመዳን እና የተስፋ፣ የእድገት እና የአላማ ወሳኙ ቦታ ነው። ሁላችንም ክፍሉ ለመሆን የምንችልበት መንፈሳዊ እና ሰውነታዊ ቦታ ያስፈልገናል። እኛ በሁሉም እድሜ ያለን እህቶች፣ ይህንን ቦታ ለመፍጠር እንችላለን፤ ቅዱስ የሆነ ቦታም ጭምር ነው።

ታላቁ ሀላፊነታችን አዳኝን የሚከተሉ፣ በማነሳሻ የሚንከባከቡ፣ እና እውነትን ያለፍርሀት የሚኖሩበት ሴቶች መሆንከፍተኛው ሀላፊነታችን ነው። የሰማይ አባት የመንግስቱ ገንቢዎች እንድንሆን ስንጠይቅ፣ ሀይሉ ወደ እኛ ይፈሳል እናም እንዴት ለመንከባከብ እንደምንችል እናውቃለን፣ በመጨረሻም እንደ ሰማይ ወላጆቻችን እንሆናለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ሐዋርያት 2:36–37.

  2. እላይዛ አር. ስኖው፣ በDaughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society (2011), ውስጥ 42።

  3. ኤማ ስሚዝ፣ በDaughters in My Kingdom, ውስጥ 12።

  4. ዘፍጥረት 3፥20 ተመልከቱ።

  5. ኦርሰን ኤፍ. ውትኒ፣ በSpencer W. Kimball, Faith Precedes the Miracle (1972), ውስጥ 98።

  6. ጁሊ ቢ ቤክ፣ “And upon the Handmaids in Those Days Will I Pour Out My Spirit,” Liahona, ግንቦት 2010, 11።