እጆቹ እንድንሆን ይጠይቀናል
እውነተኛ ክርስቶስ መሰል አገልግሎት እራስ የማይወድና ሌሎች ላይ የሚያተኩር ነው።
“እኔ እንደወደድኳችሁ እርስ በእርስ ተዋደዱ።”1 በእነዚህ ድንቅ መዘምራን የተዘመሩት እነኚህ ቃሎች ከታላቁ የሃጢያት ክፍያ መስዋዕቱ ሽማግሌ ጀፍሪ አር ሆላንድ “በዚህ ዓለም ታሪክ ውስጥ ከታዩት እጅግ ግዙፍ የንፁህ ፍቅር መገለጫ”2ብለው በሚጠሩት መስዋዕትነት ከዓታት በፊት በኢየሱስ ተነግረው ነበር።2
ኢየሱስ እንድናፈቅር ብቻ አይደለም ያስተማረን፣ ነገር ግን ያስተማረውን ኖሮት ነበር። በመላ በአገልግሎቱ ላይ ኢየሱስ “መልካም ነገሮችን አደረገ”3 እናም “ሁሉንም ምሳሌውን እዲከተሉ ለመነ።”4 “ሕይወቱን የሚያድን ያጣታል፤ ገር ግን ለኔ ብሎ ሕይወቱን የሚያጣ ሁሉ ያድናታል”ብሎ አስተማረ።5
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ማፍቀርን የተረዱትና የኖሩት እዲህ አሉ፤ “አዳኝ ሌሎችን በማገልገል ስራ ውሰጥ እራሳችንን አሳልፈን ካልሰጠን በስተቀር፣ ለሕይወቶቻችን ጥቂት አላማ እንዳለ እየነገረን እንደሆነ አምናለሁ። ሌሎችን በማገልገል ስራ ውስጥ እራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ ሲያድጉና ሲበለፅጉ — እናም በውጤቱ ህይወታቸውን ሲያድኑ፤ ለራሳቸው ብቻ የሚኖሩ ቀስ በቀስ ይጠወልጋሉ እናም ህይወታቸውን ያጣሉ።”6
እውነተኛ ክርስቶስ መሰል አገልግሎት እራስ የማይወድና ሌሎች ላይ የሚያተኩር ነው። አካለ ጎዶሎ ባሏን የምትንከባከብ አንዲት ሴት እንዲህ አስረዳች፣ “ስራችሁን እንደ ሸክም አትቁጠሩት፤ ፍቅር በእውነት ምን እንደሆነ ለመረዳት ለማወቅ እንደ እድል ቁጠሩት።”7
በቢ.ዋይ. ዩ መንፈሳዊ ፐሮግራም ላይ ስትናገር እህት ሶንድራ ዲ ሂስቶነ እንዲህ ጠየቀች፤ “በእውነት ወደ እርስ በእርሳችን ልቦች ውስጥ መተያየት ብንችልስ? እርስ በእርሳችን የበለጠ እንግባባ ነበርን? ሌሎች የሚሰማቸውን ስሜት በመሰማት፣ ሌሎች የሚያዩትን በማየት እና ሌሎች የሚሰሙትን በመስማት ሌሎችን ለማገልገል ጊዜ እናገኛለን፣ እንወስዳለን እንዲሁም በተለየ መልኩ እናያቸዋለን? በበለጠ ትግስት፣ በበለጠ ደግነትና በበለጠ መቻቻል እናያቸዋለን?”
እህት ሂስተን በወጣት ሴቶች ካምፕ ውስጥ ስታገለግል የገጠማትን ልምድን አካፈለች። እንደዚህ አለች፤
“አንዷ የመንፈስ አስተማሪያችን ስለ መሆን አስተማረችን። ከዓረፍተ ነገሮቿ መካከል አንዱ ሌሎችን ሰዎች የሚያወቅና የሚረዳ ሰው ሁኑ---መስታወቶቹን ወርውሩና በመስኮት አሻግራችሁ ተመልከቱ የሚል ነበር።
“ይህን ለማሳየት፣ አንዷን ወጣት ሴት ጠራቻትና ወደ እሷ ዞራ እድትቆም ጠየቀቻት። ከዛ መስታወት አወጣችና በወጣት ሴቷና በእሷ መካከል አስቀመጠችውና ከዛ መስታወቱን እየተመለከተች ከወጣት ሴቷ ጋር ታወራ ነበር። ብዙም ሳያስደንቅ ውጤታማና ከልብ የሆነ ንግግር ለመሆን ሁላ አልቻለም። ይህ ስለራሳችን ብቻ በጣም የምንጨነቅ ከሆነና እራሳችንና ፍላጎታችንን ብቻ የምንመለከት ከሆነ ከሌሎች ጋ ለመነጋገርና ለመርዳት እንዴት ከባድ እንደሆነ ያስረዳ በጣም ኃይለኛ በምስል የተደገፈ ትምህርት ነበር። ከዛ መስታወቱን ዞር አደረገችው፣ ከዛ የመስኮት ፍሬም አወጣችና በእሷና በወጣት ሴቷ ፊት መካከል አደረገችው። … ወጣት ሴቷ አትኩሮቷ እንደነበረችና እውነተኛ አገልግሎት በሌሎች ሰዎች ፍላጎት ላይና ስሜት ላይ ማተኮር እንደሚያስፈልገው ለማየት ችለን ነበር። ብዙ ጊዜ ስለራሳችንና ስለተጨናነቀው ሕይወታችን እንጨነቃለን---ሌሎችን ለማገልገል እድል በመፈለግ ላይ እያለን መስኮቶች ውስጥ ስንመለከት---በአገልግሎት መስኮት አሻግረን በግልፅ መመልከት አንችልም።”8
“የቤተሰብ አባል፣ ጓደኞች፣ የምናውቃቸው ሰዎች፣ ወይም እንግዶችም ይሁኑ የእኛን ትኩረት፣ የኛን ማበረታታት፣ የኛን እርዳታ፣ የኛን ማፅናናት፣ የኛን ደግነት በሚፈልጉ ሰዎች ተከበናል” ብለው ፕሬዘደንት ሞንሰን ብዙ ጊዜ አስታውሰዉናል። እንዲህ አሉ፣ “በዚህ ምድር ላይ እኛ ልጆቹን የማገልገል እና የማንሳት ጭምር አደራ ያለን የጌታ እጆች ነን። በእያንዳንዳችን ላይ ጥገኛ ነው።”9
ባለፈው አመት በጥር ወር ላይ Friend and Liahona መጽሔቶች በመላ ዓለም ላይ ያሉትን ልጆች የፕሬዘደንት ሞንሰንን---የጌታ እጆች የመሆን ምክር እንዲከተሉ ጋበዙ። ልጆች ትልቅና ትንሽ የአገልግሎት ተግባሮችን እንዲያደርጉ ተጋብዘው ነበር። ከዛ እጃቸውን በወረቀት ላይ እንዲስሉ፣ ወረቀቱን እንዲቀዱት፣ የሰሩትን አገልግሎት እንዲፅፉበትና ወደ መጽሔቶቹ እንዲልኩት ተበረታተው ነበር። ዛሬ ማታ ከምታዳምጡት ምናባት ብዙዎቻችሁ የሚወደድ አገልግሎት ከሰሩትና ከላኩት ሺዎች ልጆች መካከል ልትሆኑ ትችላላችሁ።10
ልጆች ወጣት ሲሆኑ ሌሎችን እንዴት መውደድና ማገልገል እንደሚቻል ሲማሩ ለመላ ሕይወታቸው የአገልግሎት መስመር ያበጃሉ ። ብዙን ጊዜ ሌሎቻችንን ፍቅር ማሳየትና ማገልገል ትርጉም ያለውና ለውጥ የሚያመጣ እንዲሆን ትልቅና አብይ መሆን እንደሌለበት ያስተምሩናል።
አንድ የመጀመሪያ ክፍል አስተማሪ የሚቀጥለውን ምሳሌ አካፈለች። “ዛሬ” አለች “የአምስትና የስድስት አመት ልጆች የፍቅር የአንገት ሃብል ሰሩ። እያንዳንቸው ልጆች ከወረቀት ብጥስጣሽ የእራሳቸውን፣ የኢየሱስን እና የተወሰኑ የቤተሰብ አባሎቻቸውንና የጓኛቸውን ስዕሎችን ሳሉ። ቁርጥራጮቹን በክብ አጣበቅናቸውና ትልቅ የፍቅር የአንገት ሃብል ሰንሰለት እንዲሰሩ እንዲሆን በአንገታቸው ላይ ጠላለፍለነው። ሲስሉ ልጆቹ ስለቤተሰቦቻቸው አወሩ።
“ሔዘር እንዲህ አለች፣ ‘እህቴ የምትወደኝ አይመስለኝም። ሁሌ እንጣላለን። … እራሴን እራሱ እጠላለው። መጥፎ ሕይወት ነው ያለኝ።’ እናም እራሷን በእጆቿ ውስጥ አደረገች።
“ስለቤተሰቧ ሁኔታ አሰብኩኝና ምናልባት ከባድ ሕይወት እንዳላት ተሰማኝ። ነገር ግን ሔዘር ይህን ካለች በኋላ በጠረጴዛው ሌላኛው ጫፍ ላይ አና እንዲህ ብላ መለሰች፣ ‘ሔዘር፣ በአንገት ሃብሌ ላይ በእኔ እና በኢየሱስ መካከል አስቀምጥሻለው ምክንያቱም ይወድሻል እኔም እወድሻለሁ።’
“አና ያንን ስትል ሔዘር በጠረጴዛው ስር ወደ አና ሄደችና አቀፈቻት።
“በክፍለ ጊዜው መጨረሻ ላይ አያቷ ልትወስዳት ስትመጣ ሔዘር እንዲህ አለች፣ አያቴ ምን እንደተፈጠረ ገምቺ? ኢየሱስ ይወደኛል።’”
በትንሹ መንገድ በፍቅርና በአገልግሎት እራሳችንን ስናሳልፍ ሌሎች የጌታ ፍቅር ሲሰማቸው ልቦች ይቀየራሉ እንዲሁም ይሳሳሉ።
ይሁን እንጂ፣ አንዳንድ ጊዜ በዙሪያችን ያሉ ካሉበት ቀንበር እርዳታና እረፍት የሚፈልጉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች ምክንያት ብዙ ፍላጎቶችን ማሟላት ከባድ ሊሆን ይችላል ።
እህቶች፣ አንዳንዶቻችሁ እያዳመጣችሁ ያላችሁ ለቤተሰብ አባሎች ፍላጎቶች አገልግሎት መስጠት ከባድ ሆኖ ሊሰማችሁ ይችላል ። አስታውሱ በእነዛ ድግግሞሽና ብዙን ጊዜ ተራ ስራዎች ውስጥ “እግዚአብሔርን እያገለገላችሁ” ነው።11
ሌሎቻችሁ የሌላ ሰው ሸክም እንዲቀል ለማገዝ እድሎችን ለማግኘት ጎረቤታችሁን ወይም ማህበረሰባችሁን ስትመለከቱ ሊሞላ የሚችል ባዶነት ሊሰማችሁ ይችላል።
ሁላችንም የተወሰነ አገልግሎት በቀን ተቀን ሕይወታችን ውስጥ ማዛመድ እንችላለን ። ቀጣይነት ባለው ዓለም ውስጥ ነው የምንኖረው። ሳንነቅፍ ስንቀር፣ ለሐሜት አምቢ ስንል፣ ሰውን መፍረድ ስናቆም፣ ፈገግ ስንል፣ አመሰግናለሁ ስንል እና ታጋሽና ደግ ስንሆን አገልግሎት እንሰጣለን ።
ሌላ አይነት አገልግሎቶች ጊዜ፣ አላማ ያለው ዕቅድ እና ተጨማሪ ጉልበት ይወስዳሉ። ነገር ግን ሁሉን ሙከራችን ይገባቸዋል። ምናልባት እራሳችንን እነዚን ጥያቄዎች በመጠየቅ መጀመር እችላለን፤
-
በተፅዕኖ ክልሌ ውስጥ ማንን ልርዳ?
-
ምን አይነት ጊዜና ግብአት አለኝ?
-
ችሎታዬንና ክህሎቴን ሌሎችን ለመባረክ በምን አይነት መንገድ መጠቀም እችላለው?
-
እንደ ቤተሰብ ምን ማድረግ እንችላለን?
ፕሬዘደንት ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ አስተማሩ፤
“በእያንዳዱ ክፍለ ዘመን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እዳደረጉት ማድረግ አለባችሁ፤ በጋራ መማከር፣ የተገኘውን ግብአት በሙሉ መጠቀም፣ የመንፈስ ቅዱስን አመራር መሻት፣ ጌታን ለእርሱ ማረጋገጫ መጠየቅ እና ከዛ ሸሚዛችሁን ወደ ላይ ሰብስባችሁ ወደ ስራ መሄድ ።
“ቃል እገባላችኋለው” አሉ። “ይህን መንገድ ከተከተላችሁ በጌታ መንገድ ማንን፣ ምን፣ መቼና፣ እና የት እደምትለግሱ የተለየ አመራር ትቀበላላችሁ።”12
አዳኝ ተመልሶ ሲመጣ እንዴት ሊሆን እደሚችል ሳስብ በኔፋውያን ጉብኝቱ ጊዜ የጠየቀውን አስባለው።
“ከእናንተ መካከል በሽተኞች አሉን? ወደዚህ ስፍራ አመምጧቸው። ከእናንተ መካከል ድውይ፣ ወይም አይነ ስውር፣ ወይም ሽባ፣ ወይም ለምፃም፣ ወይም ሰውነታቸው የሰለለ፣ ወይም ደንቆሮ፣ ወይ በተመሳሳይ የታመሙ አሉን? ወደ እዚህ ስፍራ አምጧቸው እና ለእነርሱ ከአንጀቴ ርህራሄ ስላለኝ እፈውሳቸዋለሁ፤ ውስጤም በምህረት የተሞላ ነው። …
“… “[አዳኝ] ሁሉንም ፈወሳቸው።”13
ለአሁን እጆቹ እንድንሆን ይጠይቀናል።
ለሕይወት ትረጉም የሚሰጠው የእግዚአብሔርና የጎረቤት ፍቅር እንደሆነ ለማወቅ ችያለው። የአዳኛችንን ምሳሌና ለሌሎች በፍቅር እንድንደርስ የሰጠንን ምክር እንከተል።
ስጦታችንን ሌላ ሰው ለማገልገል ብንጠቀም ጌታ ለዛ ሰው ያለውን ፍቅር ይሰማናል ያሉትን የፕሬዘደንት ሔነሪ ቢ. አይሪንግ ቃል-ኪዳን እውነተኛነት እመሰክራለሁ። [ለእኛ] ያለውን ፍቅር እራሱ [ይሰማናል]።”14 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።
ማስታወሻ፥ በሚያዝያ 2፣ 2016፣ እህት ኤስፒን ከመጀመሪያ ክፍል አጠቃላይ አመራር እንደ መጀመሪያ አማካሪ ሀላፊነት ተለቅቀው ነበር።