2010–2019 (እ.አ.አ)
ከሁሉም ታላቅ መሪዎች ከሁሉም ታላቅ ተከታዮች ናቸው
ኤፕረል 2016


11:10

ከሁሉም ታላቅ መሪዎች ከሁሉም ታላቅ ተከታዮች ናቸው

ወደፊት ያለው መንገድ የጨለመ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል፣ ነገር ግን አዳኝን በመከተል ቀጥሉ። እርሱ መንገዱን ያውቀዋል፤ በእርግጥም፣ እርሱ መንገድ ነው

በ12 አመቴ፣ አባቴ ወደ ተራራ ለማደን ወደ ተራራዎች ወሰደኝ። በለሊት 9 ሰዓት ከእንቅልፍ ተነስተን፣ ፈረሶቻችንን ላይ ኮርቻዎችን አሰርን፣ እና በጭለማ በጫካ ወደተሸፈነው ተራራ ሄድን። ከአባቴ ጋር ለማደን ለመሄድ እንደምወደው ያህል፣ በዚያ ጊዜ ትንሽ ፈርቼ ነበር። በእነዚህ ተራራዎች ላይ ገብቼ አልነበረም፣ እና መንገድን፣ ወይም ምንም ነገሮችን፣ ለማየት አልችልም ነበር። ለማየት የምችለው አባቴ ይዞት በነበረው የእጅ ባትሪ ደካማ ብርሀን የሚታዩት በፊታችን ያሉትን ዛፎች ብቻ ነበር። ፈረሴ ቢንሸራተት እና ቢወድቅስ -- የት እንደሚሄድ ለማየት ይችላልን? ነገር ግን ይህ ሀሳብ እንድፅናና አደረገኝ። “አባዬ የት እንደሚሄድ ያውቃል። እርሱን ከተከተልኩኝ፣ ሁሉም መልካም ይሆናል።”

እና ሁሉም ነገሮች መልካም ነበሩ። በመጨረሻም ጸሀይ ወጣች፣ እናም አብረን አስደናቂ ጊዜ አሳለፍን። ወደቤት መሄድ ስንጀምር፣ አባቴ ከሌሎቹ መካከል የቆመ ታላቅ ዳገት ያለው አስገራሚ ተራራ ላይ አጠቆመ። ”ያ ንፋሳማ ጉብታ የተራራ ወዘተ ነው። ”መልካም ለማደን የሚቻልበት ቦታ ነው።” ወዲያውም ለመመለስ እና አንድ ቀን ይህን ንፋሳማ ጉብታ የተራራ ወዘተ ለመውጣት እንደምፈልግ አወቅሁኝ።

በቀጠሉት አመታት፣ አባቴ ስለንፋሳማ ጉብታ የተራራ ወዘተ በብዛት ሲያወራ እሰማ ነበር፣ ነገር ግን፣ አንድ ቀን ከ20 አመት በኋላ ለአባቴ ደውዬ ”ወደ ንፋሳማው እንሂድ” እስካልኩት ድረስ አብረን ወደዚያ እንደገና አልተመለስንም ነበር። እንደገና ፈረሶቻችንን ላይ ኮርቻዎችን አሰርን እና ወደ ተራራ መውጣት ጀመርን። አሁን ሰላሳ አመቴ የሆንኩኝ በፈረስ በመሄድ ልምድ ያለኝ ነበርኩኝ፣ ነገር ግን እንደ 12 አመት ልጅ አይነት የነበረ የፍርሀት ስሜት ሲሰማኝ ያስደንቀኝ ነበር። ነገር ግን አባቴ መንገዱን ያውቀው ነበር፣ እናም እርሱን ተከተልኩኝ።

በመጨረሻም ወደ ንፋሳማው ጫፍ ላይ ደረስን። ትእይንቱ የሚያስደንቅ ነበር፣ እናም ታላቅ የነበረኝ ስሜቴም እንደገና ተመልሼ ለመምጣት ነበር፣ በዚህም ጊዜ ለራሴ ሳይሆን ለባለቤቴ እና ለልጆቼ ነበር። እኔ ያጋጠመኝን እንዲያጋጥማቸው ፈልጌ ነበር።

በአመታትም፣ አባቴ እንደመራኝ፣ እኔም ወንድ ልጆቼን እና ሌሎች ወጣት ወንዶችን ወደ ተራራዎች ጫፍ ለመምራት ብዙ እድሎች ነበሩኝ። እነዚህ አጋጣሚዎች መምራት ምን ማለት እንደሆነ -- እናም መከተል ምን ማለት እንደሆነ እንዳሰላስል አነሳስተውኛል።

ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ከሁሉም በላይ ታላቅ መሪ እና ከሁሉም በላይ ታላቅ ተከታይ

“ከኖሩት ሁሉ በላይ ታላቅ መሪ ማን ነበር?” ብዬ ብጠይቃችሁ፣ ምን ብላችሁ ትመልሳላችሁ? መልሱም በእርግጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱም በምናብ ሊታዩ የሚቻሉትን አይነት እያንዳንዱን የመሪነት ችሎታ ምሳሌ ያሳየ ነበር።

ነገር ግን ”ከሚኖሩት ሁሉ በላይ ታላቅ ተከታይ ማን ነው?” ብዬ ብጠይቃችሁስ። እርሱ ከሁሉም በላይ ታላቅ መሪ ነው ምክንያቱም ከሁሉም በላይ ታላቅ ተከታይ ስለሆነ ነው--በሁሉም ነገሮች የአባቱን ምሳሌ ተከተለ።

መሪዎች ሀይለኛ መሆን አለባቸው በማለት አለም ያስተምራል፤ ጌታ እነርሱ ትሁት መሆን አለባቸው ብሎ ያስተምራል። አለማዊ መሪዎች በችሎታቸው፣ በጥበባቸው፣ እና በሀብታቸው ሀይል እና ተፅዕኖ ያገኛሉ። እንደ ክርስቶስ አይነት መሪዎች ሀይልን እና ተፅዕኖ የሚያገኙት፣ ”በማሳመን፣ በትእግስት፣ በደግነት፣ እና በትህትና፣ እና ግብዝነት በሌለው ፍቅር” ነው።1

በእግዚአብሔር አስተያየት፣ ከሁሉም ታላቅ የሆኑ መሪዎች ከሁሉም ታላቅ የሆኑ ተከታዮች ናቸው።

ስለለምራት እና መከተል እንድማር ስላደረጉኝ በቅርብ ከቤተክርስቲያኗ ወጣት ወንዶች ጋር ስለነበረኝ አጋጣሚ ልንገራችሁ።

ሁላችንም መሪዎች ነን

በቅርብ፣ ባለቤቴ እና እኔ ከዎርዳችን ሌላ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ተሳታፊ ነበርን። ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት፣ ወጣት ወንድ ልጅ ወደ እኔ መጣ እና ቅዱስ ቁርባንን በማሳለፍ እንድሳተፍ ጠየቀኝ። እኔም፣ ”በደስታ አደርገዋለሁ” በማለት መለስኩኝ።

ከሌሎች ዲያቆናት ጋር ተቀመጥኩኝ እናም በአጠገቤ ከተቀመጡት አንድን ”የተመደብኩበት ምንድን ነው?” ብዬ ጠየኩኝ። ከቤተክርስቲያኗ የጸሎት ቤት መጨረሻ ከመሀከል እንደምጀምር እናም እርሱም በዚያ ክፍል በሌላኛው በኩል እንደሚገኝ፣ እና አብረን ወደ ክፍሉ ፊት በመሄድ አብረን እንደምንሰራ ነገርኝ።

እንዲህ አልኩት፣ ”ለረጅም ጊዜ ይህን አላደረኩም።”

እርሱም እንዲም መለሰ፣ ”ምንም አይደለም። ደህና ኖት። እኔም ስጀምር እንዲህ ስሜት ነበረኝ።”

በኋላም በዲያቆን ቡድን ታናሽ የነበረው፣ ከሳምንት በፊት ተሹሞ የነበረው፣በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ውስጥ ንግግር አቀረበ። ከስብሰባው በኋላ ሌሎቹ ዲያቆናት በዲያቆን ቡድን አባላቸው ኩራት እንደተሰማቸው ለእርሱ ለመንገር ተሰበሰቡ።

ዛሬ ከእነርሱ ጋር ስገናኝ፣ በዚያ ዎርድ ውስጥ ያሉ እያንዳንዱ አሮናዎ ካህናት ወደ ሌሎች ወጣት ወንዶች በሄድ የቡድናቸው ክፍል እንዲሆኑ በየሳምንቱ እንደሚጋብዝ አወቅሁ።

እነዚህ ወጣቶች ታላቅ መሪዎች ነበሩ። እናም በሀላፊነታቸው የሚያሰለጥኗቸው የማይታዩ ታላቅ አስደናቂ የመልከ ጼዴቅ ካህናት፣ ወላጆች፣ እና ሌሎች እንዳሉ ግልጽ ነው። እንደነዚህ አይነት የሚንከባከቡ ጎልማሳዎች ወጣት ወንዶችን የሚያዩአቸው እንዳሉበት ብቻ ሳይሆን፣ ለመሆን በሚችሉበት አስተያየት ነው። ስለወጣት ወንዶች ሲናገሩ ወይም ሲያናግሩ፣ በጥፋታቸው ላይ አያተኩሩም። በዚህ ምትክ፣ የሚያሳዩትን የታላቅ መሪነት ጸባዮች ላይ ያተኩራሉ።

ወጣቶች፣ ጌታም እንዲህ ነው የሚመለከታችሁ። ራሳችሁን እንደዚህ እንድትመለከቱም ይጋብዛችኋል። እንድንመራ የምንጠራበት ጊዜም በህይወታችን ይኖራል። በሌሎች ጊዜዎች፣ ተከታይ እንድትሆኑም ይጠበቅባችኋል። ነገር ግን ዛሬ ለእናንተ ያለኝ መልእክት ስለ ጥሪአችሁ በሚመለከት ነው፣ እናንተ ሁሌም መሪዎች ናችሁ፣ እናም ሁሌም ተከታዮች ናችሁ። መሪነት የደቀመዛሙርትነት መግለጫ ነው--ይህም እውነተኛ ደቀመዛሙርት እንደሚያደርጉት ሌሎችን ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ የመርዳት ጉዳይ ነው። የክርስቶስ ተከታዮች ለመሆን ከጣራችሁ፣ ከዚያም ሌሎች እርሱን እንዲከተሉ ለመርዳትና መሪዎች ለመሆን ትችላላችሁ።

ነገር ግን ለመምራት ያላችሁ ችሎታ በተጫዋችነታችሁ፣ በሚያነሳሳ ችሎታችሁ፣ ወይም በሰዎች ፊት በመናገር ችሎታችሁ የሚመጣ አይደለም። ይህም የሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ባላችሁ የልብ ውሳኔ ነው። Iይህም የሚመጣው እንደ አብርሐም ቃላት ”ታላቅ የጻድቅነት ተከታዮች”2ለመሆን ፍላጎት ሲኖራችሁ ነው። ያን ለማድረግ ከቻላችሁ--ፍጹም ባትሆኑም፣ ግን የምትጥሩ ከሆናችሁ--ከዚያም እናንተ መሪ ናችሁ

የክህነት አገልግሎት መሪነት ነው

በሌላ ጊዜ፣ ሶስት ግልማሳ ልጆች ያሏትን ያላገባች አንድ እናት ቤትን በኒው ዚላንድ ውስጥ እጎበኝ ነበር። ታላቁ ወንድ ልጅ 18 አመቱ ነበር እናም ባለፈው ሳምንት እሁድ የመልከጼዴቅ ክህነትን ተቀብሎ ነበር። ይህን ክህነት ለመጠቀም ችሎ እንደነበር ጠየቅሁት። እንዲህ አለ፣ ”ይህ ምን ማለት እንደሆን እርግጠኛ አይደለሁም።”

አሁን የመፅናኛ ወይም የመፈወሻ የክህነት በረከት ለመስጠት ስልጣን እንዳለው ነገርኩት። ለብዙ አመታት የመልከጼዴቅ ክህነት ያለው በአጠገቧ ያልነበራችን እናቱን ተመለከትኩኝ። ”ለእናትን በረከት ብትሰጣት አስደናቂ እንደሚሆን አስባለሁ” አልኩኝ።

እንዲህ መለሰ፣ ”እንዴት እንደሚደረግ አላውቅም።”

እጆቹን በእናቱ ራስ ላይ በመጫን፣ ስሟን በመጥራት፣ በረከት የሚሰጣት በመልከጼዴቅ ክህነት ስልጣን እንደሆነ በመግለጽ፣ መንፈስ በአዕምሮህ እና በልብህ የሚሰጥህን ተናገር፣ እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ፈፅም።

በሚቀጥለው ቀን፣ ከእርሱ ኢሜል ደረሰኝ። በክፍልም እንዲህ ይላል፥ ”በዚህ ምሽት ለእናዬ በረከት ሰጠሁኝ!። … በጣም፣ በጣም የፍርሀት እና ብቁ ያለመሆን ስሜት ነበረኝ፣ ስለዚህ መንፈስ ከእኔ ጋር እንዲገኝ በመጸለይ ቀጠልኩኝ፣ ምክንያቱም ያለዚህ በረከት መስጠት አልችልምና። ስጀምር፣ ስለራሴና ስለደካማነቴ ረሳሁ። … የተሰማኝን ታላቅ የመንፈስ እና የስሜት ሀይል አልጠበኩትም ነበር። … ከዚያም በኋላ የፍቅር መንፈስ በጣም ነክቶኝ ስሜቴን ለመቋቋም አልቻልኩም፣ ስለዚህ እናቴን አቅፌ እንደ ህጻን አለቀስኩኝ። … አሁን ይህን ስፅፍም፣ መንፈስ በሀይል ይሰማኛል እንደገና ኃጢያት ለመፈጸም በምንም አልፈልግም። … ይህንወንጌል እወዳለሁ።”3

ምንም ልዩነት የሌለው የሚመስለው ወጣት፣ ምንም እንኳን ብቁነት ባይሰማውም፣ በክህነት አገልግሎት ታላቅ ነገሮች ለማከናወን መመልከቱ የሚያነሳሳ አይደለምን? በቅርብ ይህ ወጣት ሽማግሌ በሚስዮን የሚያገለግልበት ጥሪ እንደተቀበለና በሚቀጥለው ወር ወደሚስዮን ማሰልጠኛ ስፍራ እንደሚገባ ተምሬአለሁ። ብዙ ነፍሶችን ወደ ክርስቶስ እንደሚመራ አምናለሁ ምክንያቱም፣ በ14 አመት ወንድሙ ላይ በምሳሌው ሀይለኛ ተፅዕኖ ከሚያደርግበት ከቤቱ ጀምሮ፣ በክህነት አገልግሎቱ ክርስቶስን እንዴት እንደሚከተል ተምሯልና።

ወንድሞች፣ የምናውቀውም ይሁን ወይም አይሁን፣ ሰዎች፣ እንዲሁም ቤተሰብ አባላት፣ ጓደኞች፣ እና እንድጋዎች፣ እየተመለክቱን ነው። እንደ ክህነት ባለስልጣኖች፣ ወደ ክርስቶስ መምጣታችን ብቻ ብቁ አይደለም፣ ሀላፊነታችን “ሁሉንም ወደ ክርስቶስ እንዲመጣ መጋበዝ”4 ነው። ለራሳችን መስፈሳዊ በረከቶችን በማግኘት ብቻ መረካት አንችልም፤ የምናፈቅርቸውን ሰዎች ለእነዚያ አይነት በረከቶች መምራት ይገባናል--እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት፣ ሁሉንም ማፍቀር ይገባናል። አዳኝ ለጴጥሮስ የሰጠው ሀላፊነት ለእኛም የተሰጠ ሀላፊነት ነው፥ “አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና።”5

የጋለሊን ሰው ተከተሉ

ወደፊት ያለው መንገድ የጨለመ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል፣ ነገር ግን አዳኝን በመከተል ቀጥሉ። መንገዱን ያውቀዋል፣ በእርግጥም፣ እርሱ መንገዱ ነው6 ወደ ክርስቶስ በተጨማሪ ቅንነት ስትመጡ፣ ሌሎች እናንተ ያጋጠማችሁን እንዲያጋጥማቸው ያላችሁ ፍላጎት በጥልቅ ይሰማችኋል። ለዚህ ስሜት ያለ ሌላ ቃል ልግስና ነው፣ ይህም “በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች ሁሉ ላይ በሚያፈሰው”7ነው። ከዚያም ክርስቶስን በመከተል በኩል፣ ሌሎችን ወደ እርሱ እንደምትመሩ ታገኛላችሁ፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዳሉት፣ “የጋለሊ ሰውን--እንዲሁም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን--ስንከተል፣ ምንም ብንሆን፣ ጥሪአችን ምንም ቢሆን የግል ተፅዕኖአችን ለመልካም ነገር ስሜት ይኖረዋል።”8

ይህች የኢየሱስ ክርስቶስ እውነታዊ ቤተክርስቲያን እንደሆነች እመሰክራለሁ። በእግዚአብሔር ነቢይ፣ ታላቅ መሪ እና ደግሞም እውነተኛ የአዳኝ ተከታይ በሆኑት፣ በፕሬዘደንት ሞንሰን እንመራለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።