የአምላካዊነት ሀይል
እያንዳንዱ ቤተ-መቅደስ የእግዚአብሔር ቅዱስ፣ የተቀደሰ ቤት እና እዛ ውስጥ እያንዳንዳችን የእግዚአብሔርነትን ኃይል መማርና ማወቅ እንችላለን።
ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ከመሞቱ ከጥቂት ወሮች በፊት፣ በዚያ አስቸጋሪ ጊዜ ቤተክርስቲያኗን ስለሚያጋጥማት ታላቅ ፍላጎቶች ለመነጋገር ከአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ጋር ተገናኘ። እንዲህም ነገራቸው፣ “ከማንኛውመም ነገር በላይ ቤተመቅደስ ያስፈልገናል።”1በእርግጥም፣ ዛሬ በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜዎች፣ እያንዳንዳችን እና ቤተሰቦቻችን ከማንኛውመም ነገር በላይ ቤተመቅደስ ያስፈልገናል።
በቅርብ በነበረው የቤተመቅደስ ቅደሳ ጊዜ፣ በሁሉም አጋጣሚ በጣም ተደስቼ ነበር። በጉብኝቱ፣ ቤተመቅደስን ለማየት የመጡትን ብዙ ጎበኚዎችን ሰላም ማለትን፤ በወጣቱቹ ቅኑነት እና ደስታ የባህል በዓልን፤ ቀጥሎም የነበረውን አስደናቂ የቅደሳ ስብሰባ ወድጄው ነበር። መንፈሱ አስደሳች ነበር። ብዙ ሰዎች ተባርከው ነበር። ከዚያም በሚቀጥለው ጠዋት፣ ባለቤቴ እና እኔ ለቅድመ አያቶቼ በመጠመቅ ለመሳተፍ ወደ ማጥመቂያው ገንዳ ውስጥ ገባን። ስርዓቱን ለመጀመር ክንዴን ሳነሳ፣ በመንፈስ ሀይል ተሸንፌ ነበር። እንደገናም የቤተመቅደስ እውነተኛ ሀይል በስርዓቶች ላይ እንደሆነ ተረዳሁ።
ጌታ እንደገለጸው፣ የመልከጼዴቅ ክህነት ሙሉነት የተመሰረተው በቤተመቅደስ ውስጥ እና በዚህ ስርዓቶች ነው፣ “ክብር እና ግርማ ትቀበሉ ዘንድ፣ ለቅዱስ ክህነት ስልጣን ቁልፎች የሚሾሙት በዚህም ውስጥ ነውና።”2 “ስለዚህ፣ በዚህም ስርዓት ውስጥ፣ የአምላክ አይነት ሀይል ይታያል።”3 ይህም ቃል ኪዳን ለእናንተ እና ለቤተሰባችሁ ነው።
የእኛ ሃላፊነት አባታችን የሚሰጠውን “መቀበል” ነው4 “ለሚቀበለው ኃይልን የበለጠ ይሰጠዋል”፥5 አሁንና ለዘላለም የሚችለውንና የሚሰጠንን ሁሉለመቀበል ኃይል፤6 የእግዚአብሔር ወንድና ሴት ልጆች የመሆን ኃይል፣7 “የሰማይ ኃይሎች ” ለማወቅ፤8 በስሙ የመናገር ኃይል 9 እና “የመንፈሱን ኃይል” ለመቀበለል።10 እነዚህ ኃይሎች ለእያንዳንዳችን እንደ ግለሰብ በቤተ-መቅደስ ስነ-ስርዓቶችና ቃል-ኪዳኖች አማካኝነት የሚገኙ ይሆናሉ።
ኔፊ በታላቅ ራዕዩ የእኛን ቀን አይቷል፥ “እኔ ኔፊ በበጉ ቤተክርስቲያን ቅዱሳንና በምድር ገፅ ላይ ሁሉ በተበተኑት የጌታ የቃልኪዳን ህዝቦች ላይ የእግዚአብሔር በግ ኃይል ሲወርድ ተመለከትኩ፤ እነርሱም ፅድቅንና የእግዚአብሔርን ኃይል በታላቅ ክብር የታጠቁ ነበሩ።”11
በቅርብ ጊዜ ቤተሰባቸውን የመተሳሰሪያ መሰዊያን ከብበው በቤተክርስቲያኗ የምናደርጋቸው ሁሉም ነገሮች፣ እያንዳንድ ስብሰባ፣ መሳተፊያ፣ ትምህርት፣ እና አገልግሎት፣ እያንዳንዳችን ወደ ቤተመቅደስ እንድንመጣ እና በመሰዊያው ተንበርክከን አብ በቃል ኪዳን የገባልንን በረከቶች ለዘለአለም ለመቀበል እንደሚያዘጋጁን በሚያስተምሩበት ጊዜ ከፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እና ቤተሰባቸው ጋር በቤተመቅደስ መጎብኘት ላይ ተገኝቼ ነበር።12
በህይወታችን የቤተመቅደስ በረከቶ ሲሰሙን፣ ልባችን፣ ወደ ህያው እና ሙታን ቤተሰቦቻችን ይዞራሉ።
በቅርብ፣ የሶስት የቤተሰብ ትውልዶች ለቅድመ አያቶቻቸው በመተመቅ ሲሳተፉ በምስክር አይቻለሁ። ምንም እንኳን በውሀው ውስጥ ለመጥለቅ አስፈርቷቸው ቢሆንም፣ በዚህ አያታቸውም ተሳትፈው ነበር። ከውሀው ሲወጡና ባለቤታቸውን ሲያቅፉ፣ የደስታ እምባ ነበራቸው። ወንድ አያት እና አባትም እርስ በራስ እና ብዙ የልጅ ልጆችን ጠመቁ። ምን አይነት ታላቅ ደስታ ቤተሰቦች መካፈል ይችላሉ? እያንዳንዱ ቤተመቅደስ እናንተ እንደ ቤተሰብ በመጥመቂያው ውስጥ በቀጠሮ ጊዜ እንድታገኙ ለማድረግ ለቤተሰብ ቀደምነት ይሰጣል።
ከመሞታቸው ጥቂት ጊዜ በፊት፣ ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ ስለሙታን ቤዛነት ራዕይ ተቀበሉ። በመንፈስ አለም ውስጥ ያሉት በእነርሱ ምትክ በምንቀበለው ስርዓቶች ላይ በሙሉ እንደሚመኩ አስተማሩ። ቅዱሳት መጻህፍት እንደሚያነበው፣ “ንስሀ የገቡ ሙታንም የእግዚአብሔር ቤት ስርዓቶችን በማክበር ይድናሉ።”13 ስርዓቶችን በእነርሱ ምትክ እንቀበላለን፣ ነገር ግን ከእያንዳንዱ ስራአት ጋር የተያያዘውን ቃል ኪዳን ይገቡበታል እና ለዚህም ሀላፊነት አላቸው። በእርግጥ፣ ለእኛ መጋረጫው ስስ ነው እና ለእነርሱ በቤተመቅደስ ውስጥ በሙሉ ይከፈታል።
በዚህ ስራ ለመሳተፍ፣ እንደ ደጋፊም ሆነ እንደ ሰራተኛ፣ የግል ሀላፊነታችን ምንድን ነው? ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ቅዱሳንን በ1840 (እ.አ.አ) እንዳስተማረው፣ “ታላቅ ጥረት መደረግ አለበት፣ እናም የሚቻልበትም ያስፈልገዋል--እናም [ቤተመቅደስን የመገንባት] ስራ በጻድቅነት መፋጠን እንዳለበት፣ ቅዱሳን የእነዚህን ነገሮች አስፈላጊነት ማሰላሰል ይገባቸውል፣ …እና ከዚያም እነርሱን ለማከናወን የሚያስፈልገው ነገር ለማድረግ እርምጃ ይውሰዱ፤ እናም ራሳቸውን በብርቱነት በማስታጠቅ፣ ለማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ መወሰን፣ እናም ስራው በሙሉ በእነርሱ ላይ የሚመካ እንደሆነ አይነት ትጋታዊ ጥረት ማድረግ ይሰማቸው።”14
በመፅሐፈ ራዕይ ውስጥ እንደምናነበው፥
“እነዚህ ነጩን ልብስ የለበሱ እነማን ናቸው? ከወዴትስ መጡ?
“…እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፣ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።
“ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፥ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል፥ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል።”15
በአዕምሮ አይኖቻችሁ ዛሬ በቤተመቅደስ የሚያገለግሉትን ለማየት አትችሉምን?
በአለው ውስጥ በተከፈቱት 150 ቤተመቅደሶች ውስጥ 120 ሺህ የስርዓት ሰራተኞች አሉ። ነገር ግን ተጨማሪዎች ይህን አስደሳች እድል የሚያገኙበት አለ። ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ ሒንክሊ በአለም በሙሉ ስለሚገኙ የብዙ ትትንሽ ቤተመቅደሶች ሀሳብን ሲያቀርቡ፣ “ሁሉም የስርዓት ሰራተኞች በዎርዶቻቸው እና በካስማዎቻቸው በሌላ መጠን ለማገልገል በሚችሉ በአካባቢው በሚገኙ ሰዎች ይሞላል” በማለት አስተምረዋል።16 በብዛት፣ ሰራተኞች፣ ከዚያም በላይ ለማራዘም እድል እያለ፣ ለሁለት ሶስት አመታት ለማገልገል ይጠራሉ። እንደተጠራችሁ፣ እስከምትችሉ ያህል ድረስ ትቆያላችሁ ተብሎ የታሰበበት አይደለም። ብዙ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሰራተኞች ከሀላፊነታቸው ሲለቀቁና ሌሎች፣ አዲስ ሰራተኞች እንዲያገለግሉ ሲፈቅዱ፣ ለቤተመቅደስ ያላቸውን ፍቅር ይዘው ነው የየሚሄዱት።
ወደ 100 አመት አካባቢ፣ ሐዋርያው ጆን ኤ ውድሶው እንዳስተማሩት፥ “[ይህን] አስደናቂ ስራ ለማከናወን ተጨማሪ ሰራተኞች ያስፈልጉናል። … ከሁሉም እድሜዎች የሚመጡ፣ ብዙ ወደ ቤተመቅደስ ስራ የተቀየሩም ያስፈልጉናል። … በዚህ በአዲስ የቤተመቅደስ እንቅስቃሴ፣ ሁሉንም ሰዎች፣ ምንም በእድሜአቸው፣ ወደ ተሳታፊ አገልግሎት የማምጣት ጊዜ መጥቷል… ። … የቤተመቅደስ ስራ ለወጣት እና ተንቀሳቃሹም፣ በኋላቸው የህይወትን ፈተና ትተው ለሄዱት፣ ላረጁትም አንድ አይነት ጥቅም አለው። ወጣት ሰው፣ በህይወት አጋጣሚዎች ከተደገፉት ከአባቱ እና ከአያቱ በላይ በቤተመቅደስ ውስጥ ቦታ ማግኘቱ አስፈላጊ ነው፤ እናም ወደ ህይወት ገና የገባችው ወጣት ሴትም፣ በቤተመቅደስ ስርዓቶች በመሳተፍ የሚመጡትን መንፈስ፣ ተፅዕኖ፣ እና መመሪያ ያስፈልጋታል።”17
በብዙ ቤተመቅደሶች ውስጥ፣ የቤተመቅደስ ፕሬዘደንቶች በአዲስ ለተጠሩት እና የቤተመቅደስ በረከቶችን የተቀበሉትን ወጣት ወንዶች እና ሴቶችን ወደ ሚስዮን ማሰልጠኛ ከመግባታቸው በፊት ለአጭር ጊዜ እንደ ስርዓት ሰራተኛ እንዲያገለግሉ ይቀበሏቸዋል። እነዚህ ወጣቶች ለማገልገል በረከት ከማግኘታቸው በተጨማሪ፣ “በቤተመቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉትን በሙሉ በወብት እና በመንፈስ ያሳድጋሉ።”18
ከሚስዮናቸው በፊት እና በኋላ እንደ ቤተመቅደስ ሰራተኞች ያገለገሉ ወጣት ወንዶች እና ሴቶችን ስሜታቸውን እንዲካፈሉ ጠይቄ ነበር። እንደሚቀጥሉት አይነት ቃላትን በመጠቀም በቤተመቅደስ የነበራቸውን አጋጣሚ ገልጸዋል፥
በቤተመቅደስ ውስጥ ሳገለግል፣ ...
-
“ወደአብ እና አዳኝ የመቅረብ ስሜት” ይሰማኛል፤
-
“ሙሉ ሰላም እና ደስታ” ይሰማኛል፤
-
“በቤት” እንደመሆን ስሜት አለኝ፤
-
“ቅድስና፣ ሀይል፣ እና ጥንካሬ” ተቀብያለሁ፤
-
የቅዱስ ቃል ኪዳኖቼ አስፈላጊነት” ይሰማኛል፤
-
“ቤተመቅደስ የእኔ ክፍል ሆኗል”፤
-
“የምናገለግላቸው በስርዓቶች ጊዜ የቀረቡ ናቸው”፤
-
“ፈተናዎችን ለማሸነፍ ጥንካሬ ይሰጠኛል”፤ እና
-
“ቤተመቅደስ ህይወቴን ለዘለአለም ቀይሯል።”19
በቤተመቅደስ ውስጥ ማገልገል ምንም እድሜ ላላቸው ሰዎች በሙሉ ሙሉ እና ሀይለኛ አጋጣሚ ይሰጣቸዋል። አዲስ የተጋቡ ሰዎችም አብረው ያገለግላሉ። ፕሬዘደንት ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “በቤተመቅደስ ውስጥ ማገልገል … ልብ የሚማርክ የቤተሰብ መሳተፊያ ነው።”20 እንደ ስራአቶች ሰራተኛ፣ ለቅድመ አያቶቻችሁ ስርዓቶችን ከመቀበል በተጨማሪ፣ ለእነርሱም ስራአቶችን ለማከናወን ትችላላችሁ።
ፕሬዘደንት ዊልፈርድ ዎድረፍ እንዳሉት፥
“በእጁ [ወይም በእጇ] ለመሄድ እና የደህንነት ስርዓቶችን ለማስተዳደር ሀይል እና ስልጣን ከመያሽ በላይ ማንም ወንድ [ወይም ሴት] በምድር ላይ የሚያገኘው [የምታገኘው ታላቅ ጥሪ ምን አለ? …
“… በዚያ ነፍስ ደህንነት በኩል በእግዚአብሔር እጅ መሳሪያ ትሆናላችሁ። ከዚህ ጋር እኩል የሆነ ለሰው ልጆች የተሰጠም ምንም የለው።”21
እንዲህም ቀጠሉ፥
“የመንፈስ ቅዱስ አስደሳች መንሾካሸክ [ለእናንተ] ይሰጣል እናም ከጊዜ ወደ ጊዜ የሰማይ ሀብቶች፣ የመላእክቶች ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ይጨመራሉ።”22
“በስጋ በምናሳልፈው ትንሽ አመታት ለዚህ እኔ እና እናንተ የምንችለውን ያህል መስዋዕት ማድረግ ያስፈልገናል።”23
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን በቅርብ እንድናስታውስ እንዳደረጉን፣ “የቤተመቅደስ በረከቶች ታላቅ ዋጋ ያላቸው ናቸው።”24 “ምንም መስዋዕት ታላቅ አይደለም።”25
ወደ ቤተመቅደስ ኑ። በየጊዜው ኑ። ከቤተሰባችሁ እና ለቤተሰባችሁ ኑ። ኑ እናም ሌሎች እንዲመጡም እርዳታ ስጡ።
“እነዚህ ነጩን ልብስ የለበሱ እነማን ናቸው?” ወንድሞቼና እህቶቼ፣ እናንተ የቤተመቅደስ ስርዓቶችን የተቀበላችሁት፣ በመስዋዕትም ቃል ኪዳናችሁን የጠበቃችሁ፤ ቤተሰባችሁ የቤተመቅደስ አገልግሎት በረከቶችን እንዲያገኙ የረዳችሁ እና ሌሎችን በመንገድ የረዳችሁ ናችሁ። ለአገልግሎታችሁ አመሰግናለሁ። እያንዳንዱ ቤተመቅደስ የእግዚአብሔር ቅዱስ ቤት እንደሆነ እና በዚህም ውስጥ እያንዳንዳችን የአምላክነትን ሀይል የምንማርበት እና የምናውቅበት እንደሆነ እመሰክራለሁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።