አባቶች
በወንዶች ታላቅ ሀላፊነቶች፣ እንዲሁም በባልነት እና በአባትነት፣ ውስጥ ወንዶች መልካም ለማድረግ በሚችሉበት ላይ ነው ዛሬ ለማተኮር ነው የምፈልገው።
ዛሬ ስለአባቶች እናገራለሁ። አባቶች በመለኮታዊ የደህንነት እቅድ ውስጥ መሰረታዊ መርሆ ነው፣ እናም ይህን ጥሪ ለማሟላት ለሚጥሩት የሚያበረታታ ድምጽን ከፍ ለማድረግ እፈልጋለሁ። አባትነትን እና አባቶችን ማሞገስ እና ማበረታታት ሌሎችን ማሳፈር ወይም ችላ ማለት አይደለም። በወንዶች ታላቅ ሀላፊነቶች፣ እንዲሁም በባልነት እና በአባትነት፣ ውስጥ ወንዶች መልካም ለማድረግ በሚችሉበት ላይ ነው ዛሬ ለማተኮር ነው የምፈልገው።
አባት የሌለው አሜሪካ የሚለውን መፅሐፍ የጻፈው ዴቪድ ብላክንሆርን እንደተመለከተው፥ “ዛሬ፣ የአምሪካዊ ህብረተሰብ የተከፋፈለ እና ስለአባትነት ሀሳብ የሚያመነታ ነው። አንዳንድ ሰዎች ይህንንም አያስታውሱትም። ሌሎች በዚህ ይናደዳሉ። ሌሎች፣ በተጨማሪም ብዙዎቹ ስለቤተሰብ የተማሩ ሰዎች፣ ችላ ይሉታል ወይም ይንቁታል። ብዙ ሌሎችም ይህን የሚቃወሙ አይደሉም፣ ወይም ይህ የልብ ውሳኔ ያደረጉበት አይደለም። ብዙ ሰዎች በዚህ ለማከናወን የምንችልበት እንዲሆን ፍላጎት አላቸው፣ ነገር ግን ህብረተሰባችን ይህን ለማድረግ እንደማይችሉ ወይም እንደማያደርጉ ያምናሉ።”1
እንደ ቤተክርስቲያን፣ በአባቶች እናምናለን። “ቤተሰቡን መጀመሪያ ባደረገ ሰው” ሁሳብ እናምናለን።2 “በመለኮታዊ እቅድ፣ አባቶች በፍቅር እና በጻድቅነት ቤተሰቦቻቸውን ያስተዳድራሉ እና ለቤተሰቦቻቸው የህይወት መሰረታዊ ፍላጎት የሟሟላት እና ጥበቃ ሀላፊነት አለባቸው። እናቶች በቀደምትነት ልጆቻቸውን የመንከባከብ ሀላፊነት” ባለባቸው እናምናለን።3 በሚስማማው የቤተሰብ ሀላፊነት “አባቶች እና እናቶች በእኩል አጋርነታቸው የመረዳዳት ሀላፊነት” እንዳላቸው እናምናለን።4 ከሚፈለገው በላይ ከመሆን በመራቅ፣ አባቶች ልዩ እና ለመተካት የማይችሉ እንደሆኑም እናምናለን።
አንዳንዶች የአባትነት መልካምነትን በሀብረተሰብ አስተሳሰብ የሚመለከቱት፣ ወንዶች ለልጆቻቸው ሀላፊነት እንዳለባቸው፣ መልካም ዜጋ እንዲሆኑና የሌሎችን ፍላጎቶን እንዲያሟሉ የሚገፋፋቸው ፣ እንዲሁም “የእናት ለልጆች የምታወጣውን አባቶች በልጆች የሚያወጡትን በተጨማሪ እንደሚያደርጉ ነው። … በአጭር፣ ለወንዶች ዋናው አባት መሆን ነው። ለልጆች ዋናው ነገር አባት እንዲኖራቸው ነው። ለህብረተሰብ ዋናው ነገር አባቶችን መፍጠር ነው።”5 እነዚህ አስተሳሰቦች አስፈላጊ እና እውነት ቢሆኑም፣ አባትነት ከህብረተሰብ ግንባት ወይም የዝግመተ ለውጥ ውጤት በላይ እንደሆነ እናውቃለን። የአባት ሀላፊነት ከሰማይ አባት ጋር እናም፣ በዚህ ሟች ቦታ፣ ከአባት አዳም ጋር፣ የመለኮታዊ መጀመሪያ አለው።
የአባትነት ፍጹም እና መለኮታዊ ምሳሌ የሰማይ አባታችን ነው። የእርሱ ጸባይ እና ባህርይ በተጨማሪም መልካምነትን እና ፍጹም ፍቅርን የያዘ ነው። የእርሱ ስራ እና ክብር ደስታዎችን ማሳደግ፣ እና የልጆቹ ዘለአለም ህይወት ናቸው።6 አባቶች በዚህች በወደቀች አለም ውስጥ ከበላይ ግርማ ጋር የሚመሳሰል ምንም ነገር አለን ለማለት አይችሉም፣ ነገር ግን እርሱን ለመምሰል ይጥራሉ፣ እናም በእርግጥም በስራው ያገለግላሉ። በሚያስደንቅ እና ረጋ ባለ እምነት የተከበሩ ናቸው።
ለወንዶች፣ አባትነት ለራሳችን ደካማነት እና ለመሻሻል በሚያስፈልገን እንድንጋፈጥ ያደርገናል። አባትነት መስዋዕት ያስፈልገዋል፣ ነገር ግን ለመረዳት የማይቻል እርካታ፣ እንዲሁም ደስታ፣ ምንጭ ነው። እንደገናም፣ ከሁሉም የሚዛለው ሞዴል፣ እኛ የመንፈስ ልጆቹን የሚያፈቅረን፣ አንድያ ልጁን ለደህንነታችን እና ለዘለአለማዊነታችን የሰጠው የሰማይ አባት ነው።7 ኢየሱስ እንዳለው፣ “ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።”8 አባቶች ያን ፍቅር የሚያሳዩት፣ ለቤተሰቦቻቸው አገልግሎት እና ድገፋ በመስራት ህይወታቸውን ቀን በቀን በመስዋዕት ሲያቀርቡ ነው።.
ምናልባት የአባት በጣም አስፈላጊ ስራ ቢኖር የልጆቹን ልብ ወደ ሰማይ አብት ማዞር ነው። በምሳሌው እና በቃላቱ አባት በቀን በቀን ህይወቱ ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን ምን እንደሚመስል ለማሳየት የሚችል ከሆነ፣ ያም አባት ለልጆቹ በዚህ ህይወት ሰላም እና በሚመጣው አለም የዘለአለም ህይወት ቁልፍ ይሰጣቸዋል።9 ቅዱሳት መጻህፍትን በብቻቸው እና ከልጆቹ ጋር የሚያነቡ አባቶች፣ የጌታን ድምጽ እንዲያውቁ ያደርጋሉ።10
በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ወላጆች ልጆቻቸውን ለማስተማር ያላቸውን ሀላፊነት በተደጋጋሚ ትኩረት ተሰጥቶበታል፥
“እና ደግሞም፣ ወላጆች በፅዮን፣ ወይም በተደራጁት ካስማዎቿ፣ ውስጥ ልጆች ኖሯቸው፣ ስምንት አመት ሲሆናቸው፣ ስለ ንስሀ፣ በህያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እምነት፣ እናም ስለ ጥምቀት እና እጆችን በመጫን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ስለመቀበል ትምህርትን ባያስተማሯቸው፣ ኃጢአቱ በወላጆች ራስ ላይ ይሆናል። …
“እናም ልጆቻቸውን እንዲጸልዩም፣ እናም በጌታ ፊት በቅንነት እንዲራመዱም ያስተምሩ።”11
በ1833 (እ፣አ፣አ)፣ ጌታ የቀዳሚ አመራር ልጆቻቸውን ለማስተማር ያላቸውን ሀላፊነታቸው ችላ በማለታቸው ገስጿቸው ነበር። ለአንዱ በግልፅ እንዲህ አለ፣ “በትእዛዛትም በኩል ልጆችህን ብርሀን እና እውነት አላስተማርክም፤ እና ክፉውም በአንተ ላይ ሀይል አለው፣ እና ይህም የስቃይህ ምክንያት ነው።”12
አባቶች የእግዚአብሔርን ህግ እና ስራዎች ለእያንዳንዱ ትውልዶች እንደ አዲስ ያስተምሩ። ዘማሪው እንዳወጀው፣
“ለልጆቻቸው ያስታውቅ ዘንድ ለአባቶቻችን ያዘዘውን ምስክር በያዕቆብ አቆመ፥ በእስራኤልም ሕግን ሠራ፤
“የሚመጣ፥ ትውልድ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ [ከዚያም] ተነሥተው ለልጆቻቸው ይነግራሉ፥
“ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እንዳይረሱ፥ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ።”13
በእርግጥም ወንጌልን ማስተማር በአባቶች እና በእናቶች መካከል የተካፈለ ሀላፊነት ነው፣ ነገር ግን ጌታ አባቶች ይህን ታላቅ አስፈላጊነት በመስጠት መሪ እንዲሆኑ እንደሚጠብቅባቸው ግልጽ ነው። (እናም ያን ንግግር፣ አብሮ መጫወት እና መስራት፣ እና ማዳመጥ የማስተማር ዋና ክፍሎች እንደሆኑ እናስታውስ።) ጌታ አባቶች ልጆቻቸውን ለማስተማር እንዲረዱ ይጠብቅባቸዋል፣ እናም ልጆች ሞዴል ይፈልጋሉ እና ያስፈልጋቸዋል።
እኔ ራሴም መልካም ምሳሌ በሆነ አባት ተባርኬ ነበር። የ12 አመት ልጅ በነበርኩበት ጊዜ፣ አባቴ ለትንሽ ከተማችን ሸንጎ አባል በመሆን ለመመረጥ ፈለገ። የሚመረጥበትን ውድድር በጣም አልጣረበትም ነበር--የማስታውሰው ቢኖር አባቴ ወንድሞቼ እና እኔ ሰዎች ፖል ክርስቶፈርሰንን እንዲመርጡ የሚያበረታታ በራሪ ወረቀቶችን በር በበር እንድናሳልፍ እንዳደረገን ነበር። ፖል መልካም እና ታማኝ ሰው ነው እና እርሱን ለመምረጥ ምንም ችግር አይኖራቸውን ያሉ በራሪ ወረቀቱን የሰጠኋቸው ብዙ ሰዎች ነበሩ። የትንሽ ልጅ ልቤ በአባቱ ኩራት ተሞልቶ ነበር። ብርታት ተጠኝ እና በእርሱ እርምጃ ለመከተል ፍላጎት ሰጠኝ። ፍጹም አልነበረም--ማንም አይደለም--ነገር ግን እርሱ ቅን እና መልካም እናም ለወንድ ልጁ የሚያነሳሳ ምሳሌ ነበር።
ቅጣት እና ማስተካከል የማስተማር ክፍል ናቸው። ጳውሎስ እንዳለው፣ “የሚወዳቸውን ጌታ ይገስጻል።”14 ነገር ግን በቅጣት ውስጥ አባት በልዩ መጠንቀቅ ይገባዋል፣ አለበለዚያም ማጎሳቀል ሊሂን ይችላልና፣ ይህም ተቀባይ አየደለም። አባት ሲያስተካክል፣ የሚያነሳሳው ፍቅር እና መሪው መንፈስ ቅዱስ መሆን ይገባዋል።
“መንፈስ ቅዱስ በሚነሳሳበት በትክክለኛው ጊዜ በሀያልነት በመቆጣት፤ ከዚያም በኋላ እንደጠላት እንዳያይህ፣ ለተቆጣኸውም ተጨማሪ ፍቅር አሳይ፤
“በእዚህም እምነትህ ከሞት ሀይል በላይ እንደሆነ ይወቅ።”15
በመለኮታዊ ምሳሌ በኩል መግሰጽ ስለመቅጣት አይደለም ግን የሚፈቀሩትን ራሳቸውን በመቻል መንገድ ላይ መርዳት ነው።
ጌታ እንዳለው “በእድሜ እስኪደርሱ ድረስ ሁሉም ልጆች በወላጆቻቸው ላይ የመደገፍ መብት አላቸው።”16 አባወራነት የተቀደሰ ስራ ነው። ለቤተሰም የሚያስፈልጋቸውን ማቅረብ፣ ከቤተሰብ የሚለዩበት ጊዜ ቢያስፈልገውም፣ ከአባትነት ጋር ያልተያያዘ አይደለም--ይህም መልካም አባት ለመሆን አስፈላጊ ነው። “ስራ እና ቤተሰብ የተደራረቡ ናቸው።”17 ይህም ቤተሰቡን በስራው ምክንያት ችላ የሚለውን ወይም፣ በሌላውም አመለካከት፣ እራሱን ለማራዘም የማይጥር እና ሀላፊነቱል በሌሎች ላይ በመጣል የሚረካውን ማረጋገጫ አይሰጠውም። በንጉስ ቢንያም ቃላት ውስጥ፥
“እናም ልጆቻችሁ ተርበው አለበለዚያም ተራቁተው እንዲሄዱ አትፈቅዱም፤ የእግዚአብሔርንም ህግ እንዲተላለፉ፣ እርስ በርሳቸውም እንዲጣሉ … አትፈቅዱም፣ .
“ነገር ግን በእውነትና በጥሞና መንገድ እንዲራመዱ ታስተምሯቸዋላችሁ፣ እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱ እንዲሁም አንደኛው ሌላኛውን እንዲያገለግል ታስተምሯቸዋላችሁ።”18
ቤተሰቦቻቸውን በብቁ ለመደገፍ መንገድ እና ገንዘብ ለማግኘት የማይችሉት ሰዎች ስቃይንም እናውቃለን። በምንም ጊዜ በሚችሉት ጥረት ሁሉ የአባቶችን ሀላፊነት እና ስራ ለማሟላት በማይችሉት ምንም እፍረት የለም። “በአካል ጉዳት፣ በሞት፣ ወይም በሌሎች ሁኔታዎች ምክንያትም እነዚህን ሀላፊነቶችን ማመጣጠን ያስፈልጋል። ለቅርብዘመዶችና ቤተሰቦችም አስፈላጊ ሲሆን እርዳታ መስጠት ይገባቸዋል።”19
የልጆቹን እናት ማፍቀር--እና ይህን ፍቅር ማሳየት--አባቶች ለልጆቻቸው ለማድረግ የሚችሉት ሁለት ከሁሉም የሚሻሉ ነገሮች ናቸው። ይህም የቤተሰብ ህይወታቸው እና ደህንነታቸው መሰረት የሆነውን ጋብቻ ያረጋግጣሉ እናም ያጠናክራሉ።
አንዳንድ ወንዶች የማደጎ አባት እና እንጀራ አባት ናቸው። ብዙዎቹ በጣም ይጥራሉ እናም በሚያስቸግር ሀላፊነትም ከሚችሉት በላይ ይጥራሉ። በፍቅር ለመደረግ የሚቻለውን በሙሉ ያደረጉትን፣ እና የግል እና የቤተሰብ ፍላጎቶችን ለማሟላት መስዋዕት ያደረጉትን እናከብራለን። እግዚአብሔር ራሱ አንድያ ልጁን ለማደጎ አባት በአደራ ሰጥቶ እንደነበር መጠቆም ይገባዋል። በእርግጥ ኢየሱስ ሲያድግ፣ እርሱ “በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት”20የማደጉ አንዳንዱ ሀላፊነት ለጆሴፍም ምክንያት ነው።
በሚያሳዝን ሁኔታ፣ በሞት፣ ችላ በማለት፣ ወይም በመፋታት ምክንያት አንዳንድ ልጆች ከአባቶች ጋር አይኖሩም። አንዳንዶች በአካል የሚገኙ ግን በስሜት ያምይኖሩ ወይም በሌላ መንገዶች ችላ የሚሉ ወይም የማይደግፉ አባቶች ሊሎሯቸው ይችላሉ። አባቶች በሙሉ የተሻለ እንዲያደርጉ እና የተሳለ እንዲሆኑ ጥሪ እናደርግላቸዋለን። በማስተላለፊያዎች እና በመዝናኛዎች፣ ምናልባት አንዳንድ ጊዜ፣ አባቶች ሁልጊዜ እንደሚታዩት ቀላደኛ እና ሞኝ ወይም “ችግር የሚፈጥር ሰው” ምትክ ባለቤታቸውን የሚያፈቅሩ እና ልጆቻቸውን በእውቀት የሚመሩ ታማኝ እና ችሎታ ያላቸው አባቶችን እንዲያሳዩ እንጠይቃቸዋለን።
የቤተሰብ ጉዝዳያቸው ችግረኝ አለሆነ ልጆች፣ እናንተ ራሳችሁ በዚህ የቀነሳችሁ አይደላችሁም። ፈተናዎች አንዳንዴም ጌታ በእናንተ ላይ ያለውን እምነት የሚያሳዩ ናቸው። እርሱ፣ በቀጥታ እና በሌሎች በኩል፣ የሚያጋጥማችሁን እንድትቋቋሙ ይረዳችኋል። እናንተም እግዚአብሄር ለቤተሰቦች የሾመውን ደስታ እና መለኮታዊ ንድፍ በእውነት የሚሰራበት እና ከኋላችሁ የሚመቱትን ትውልዶች በሙሉ የምትባርኩ ትውልዶች፣ ወይም ከቤተሰባችሁ መጀመሪያ ለመሆን ትችላላችሁ።
ለወጣት ወንዶች፣ እንደ አቅራቢ እና ጠባቂ የመሆን ያላችሁን ሚና በመገንዘብ፣ በትምህርት ቤት ትጉ በመሆን እና ከሁለተኛ ደረጃ በኋላ ለመሰልጠን በማለም ተዘጋጁ እንላለችኋለን። በዩንቨርስቲም፣ በማሰልጠኛ ትምህርት ቤት፣ በስራ መለማመጃ፣ ወይም በተመሳሳይ ፕሮግራም ቢሆንም፣ ትምህርት የሚያስፈልጋችሁን ችሎታ እና አቅም ለማሳደቅ አስፈላጊ ነው። ከሁሉም እድሜ ሰዎች፣ በተጨማሪም ከልጆች፣ጋር ለመገናኘት እና ጤናማ እና ችልማት የሚሰጥ ግንኑነቶችን ለመመስረት እድላችሁን ተጠቀሙበት። ይህም በስልክ መልእክት የመላካችሁን ችሎታ ፍጹም ከማድረግ በላይ ከሰዎች ጋር ፊት ለፊት መነጋገር እና አንዳንዴም ነገሮች አብራችሁ ማድረግ ማለት ነው። እንደ ወንድ ሰው ወደ ጋብቻችሁ እና ልጆቻችሁ ንጹህነት የምታመጡ ለመሆን ህይወታችሁን ኑሩ።
ለሚያድጉት ትውልዶች፣ አባታችሁን ከመልካም እስከ ከሁሉብ የተሻለ በሚል መዘን ላይ የተም ብትመዝኗቸውም (እና ይህም መዘን ስታድጉ እና ጥበባዊ ስትሆኑ ከፍ እንደሚል እገምታለሁ)፣ እርሱንና እናታችሁን በራሳችሁ ይህወት ለማክበር ውሳኔ አድርጉ። በዮሀን የተገለጸውን የአባት ዝልቅ የተስፋ ፍላጎትን አስታውሱ፥ በዮሀንስ የተገለጸውን የአባትን ታላቅ ፍላጎት አስታውሱ፣ “ልጆቼ በእውነት እንዲሄዱ ከመስማት ይልቅ የሚበልጥ ደስታ የለኝም።”21 የእናንተ ጻድቅነት ማንም አባት ከሚቀበለው ብር ሁሉ በላይ ታላቅ ነው።
ለወንድሞቼ፣ ለቤተክርስቲያኗ አባቶች፣ እናንተ የተሻለ ፍጹም አባቶች ለመሆን ፍላጎት እንዳላችሁ አውቃለሁ እላችኋለሁ። እኔም እንዲህ ብሆን እንደምመኝም አውቃለሁ። ይህም ቢሆን፣ የተገደብንበት ቢኖረንም፣ ወደፊት እንግፋ። የዛሬ ባህል የሆነውን ግልነት እና ራስ ገዢነት ወደጎን ተዉት እናም መጀመሪያ ስለሌሎች ደስታ እና ደህንነት አስቡ። በእርግጥም ብቁነት ባይኖረንም፣ የሰማይ አባታችን ያጎላናል እናም ተራ ጥረታችንን ፍሬ እንዲኖረው ያደራል። በNew Era ውስጥ የአጠቃላይ ባለስልጣን በሆንኩበት አመት ውስጥ በነበረው ታሪክ ተበረታትቼን ነበር። ጸሀፊው የሚቀጥለውን ታሪክ ነገረ፥
“በትንሽነቴ፣ ትንሹ ቤተሰባችን አንድ መኝታ ቤት በነበረው ቤት ውስጥ በሁለተኛው ደረጃ ላይ እንኖር ነበር። እኔም በሳሎች በሶፋ ላይ እተኛ ነበር። …
“በብረት የሚሰርውው አባቴ በየቀኑ ወደስራ በለሊት ይሄድ ነበር። በየጠዋት … በምንጣፍ ይሸፍነኝ እና ለደቂቃም ይቆም ነበር። አባቴ በሶፋው አጠገብ ቆመ እንደሚመለከተኝ ሲሰማኝ በህልም እንዳለሁ ነበር። በቀስታ ስነሳም፣ እርሱ በዚያ መሆኑ ያሳፍረኛል። የተኛሁ ለመምሰል ሞከርኩኝ… በመኝታዬ አጠገብ ቆሞ እያለ በትኩረቱ እና በሀይሉ በሙሉ—ለእኔ--ይጸልይ እንደነበረ አወቅሁኝ።
“በየጠዋት አባቴ በእኔ ላይ ይጸልይ ነበር። መልካም ቀን እንዲኖረኝ፣ ደህና እንድሆን፣ እንድማር እና ለወደፊት እንድዘጋጅ ጸለየ። እና እስከ ምሽት ድረስ ከእኔ ጋር ለመሆን ስለማይችል፣ በዚያ ቀን ከእኔጋ ለሚገኑት ለአስተማሪዎችና ለኋደኞቼም ጸለየ።
“በመጀመሪያ፣ አባቴ በእነዚያ ጠዋቶም ለእኔ በሚጸልይበት ጊዜ ምን እያደረገ እንደነበረ አላወቅኩም ነበር። ነገር ግን ሳድግ፣ ፍቅሩን እና በእኔና በማደርጋቸው ነገሮች በሙሉ ያለው ፍላጎት ይሰማኝ ነበር። ይህም ከሁሉም በላይ የምወደው ትዝታዎች አንዱ ነበር። ካገባሁ፣ የራሴ ልጆች ካገኘሁ አመታ በኋላ፣ እና ተኝተው እያሉ ወደ ክፍላቸው ገብቼና ስጸልይላቸው ነበር አባቴ ለእኔ ምን አይነት ስሜት እንደነበረው ለመረዳት የቻልኩትኝ።”22
አልማ ለወንድ ልጁ እንዳመሰከረው፥
“እናም አሁን ልጄ፣ ስለክርስቶስ መምጣት በመጠኑ እነግርሃለሁ። እነሆ፣ እርሱ ነው በእርግጥ የዓለምን ኃጥያት ሊወስድ የሚመጣው፤ አዎን፣ ለዚህ ህዝብ የደህንነትን የምስራች ዜና ለማወጅ ይመጣል።
“እናም እንግዲህ ልጄ፣ ለዚህ አገልግሎት የተጠራኸው አዕምሮአቸውን ለማዘጋጀት፣ ወይም ደህንነት ይመጣለት ዘንድ፣ በሚመጣበት ጊዜም ቃሉን እንዲሰሙ የልጆቻቸውን አዕምሮ እንዲያዘጋጁ ለህዝቡ የምስራቹን ዜና እንድትናገር ነበር።”23
ያም በዛሬ የአባቶች አገልግሎት ነው። እግዚአብሔር ይባርካቸው እና ለዚህም እኩል ያድርጋቸው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።