2010–2019 (እ.አ.አ)
የዘላለም ቤተሰቦች
ኤፕረል 2016


15:34

የዘላለም ቤተሰቦች

የክህነት ግዴታችን ቤተሰባችንን እና በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ቤተሰቦች የአሳብ መዓከል ላይ ማስቀመጥ ነው።

በዚህ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርሰቲን አጠቃላይ የክህነት ስብሰባ ላይ ከእናንተ ጋር በመሆኔ አመስጋኝ ነኝ። ይህ በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ ታላቅ ወቅት ነው። ከአንድ መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመታት በፊት በ1834 (እ.አ.አ.) በኪርትላንድ ኦሃዮ ውስጥ ሁሉም ክህነቶች 14 በ14 ጫማ (4.2 በ4.2 ሜትር) በሆነ እረጅም መማሪያ ቤት ውስጥ እዲሰበሰቡ ተጠርተው ነበር። በዛ ስብሰባ ውስጥ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንደዚህ ብሏል ተብሎ ተዘገበ፥ “በእናቱ እግር ላይ ካለ ህፃን ይልቅ የዚህችን ቤተክርስቲያንና መንግስት እጣፈንታ ካሁን በኋላ አታውቁም። አትረዱትም። … ዛሬ ምሽት የምትመለከቱት ትንሽ እጅ የሚሆኑ ክህነቶችን ብቻ ነው፣ ነገር ግን ይህች ቤተክርስቲያን ሰሜንና ደቡብ አሜሪካን ትሞላለች—ዓለምን ትሞላለች።”1

ከ110 አገራ የሚበልጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የክህነት ተሸካሚዎች በዚህ ስብሰባ ውስጥ ተሰብስበዋል። ምናልባት ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ይሄን ሰዓት እና ከፊታችን ያለውን ክብራማ ወደ ፊት ቀድሞ አይቷል።

ዛሬ ምሽት መልዕክቴ ያንን ወደ ፊትና የሰማይ አባታችን ያዘጋጀልንን የደስታ ዕቅድ አካል ለመሆን ምን ማድረግ እንዳለብን ለመግለፅ ለመሞከር ነው። ከመወለዳችን በፊት ከተወደሰ እና ከዘላለማዊ የሰማይ አባታችን ጋር በቤተሰብ ውስጥ ኖርን። እንደእርሱ ለመሆን ማደግ እና መሻሻል የሚያስችለንን ዕቅድ አወጀ። ለእኛ ስላለው ፍቅር ብሎ አደረገው። የዕቅዱ አላማ የሰማይ አባታችን እንደሚኖረው ለዘላለም የመኖር እድልን ለመፍቀድ ነበር። ይህ የወንጌል ዕቅድ የምንፈተንበትን ሟች የሆነ ሕይወት ሰጠን። በኢየሱስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት የወንጌልን ህግጋቶችና የክህነት ሥነ-ስርዓቶችን ከጠበቅን ከስጦታዎቹ ሁሉ በላይ ታላቅ የሆነው የዘላለም ሕይወት እንደሚኖረን ቃል-ኪዳን ተሰጥቶ ነበር።

የዘላለም ሕይወት እግዚአብሔር የዘላለም አባታችን የሚኖረው ዓይነት ሕይወት ነው። እግዚአብሔር አላማው “የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት ማምጣት” (ሙሴ 1፥39) እንደሆነ ተናገረ። ስለዚህ፣ የእያንዳንዶቹ የክህነት ተሸካሚዎች ታላቅ አላማ ሰዎችን ለዘላለም ሕይወት እንዲነሱ በመርዳት ስራ ውስጥ ድጋፍ መስጠት ነው።

እያንዳንዱ የክህነት ሙከራና እያንዳንዱ የክህነት ሥነ-ስርዓት የሰማይ አባት ልጆች በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት መስዋዕትነት አማካኝነት ፍፁም የሆነ የቤተሰብ አባሎች ለመሆን እንዲለወጡ ለመርዳት የታቀደ ነው። “የእያንዳንዱ ሰው ታላቅ ስራ ወንጌልን ማመን፣ ትዕዛዛትን መጠበቅ እና የዘላለም ቤተሰብን መፍጠርና ፍፁም ማድረግ”2 እንዲሁም ሌሎችን ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ መርዳት ነው።

ያ እውነት ስለሆነ፣ የምናደርገው እያንዳንዱ ነገር የሰለስቲያል ጋብቻን ትኩረቱና አላማው ያደረገ መሆን አለበት። ያ ማለት ከዘላለም ጓደኛ ጋር በቤተ-መቅደስ ውስጥ ለመታተም መጣር አለብን ማለት ነው። ባልና ሚስትን ከቤተሰባቸውን ጋር በዚህ ሕይወትና በሚመጣው ዓለም አብሮ የሚያስር ቃል-ኪዳኖችን እንዲያደርጉና እንዲጠብቁ ሌሎችን እንዲሁ ማበረታታት አለብን።

ለምንድን ነው ይሄ ነገር ለእያንዳንዳችን—ለወጣት ወይም ለአዛውንት፣ ለዲያቆን ወይም ለሊቀ ካህን፣ ለወንድ ልጆች ወይም ለአባቶች የበለጠ ጥቅም ያለው የሚሆነው? የክህነት ግዴታችን ቤተሰባችንን እና በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ቤተሰቦችን የአሳብ መዓከል ላይ ማስቀመጥ ነው። እያንዳንዱ ዋና ውሳኔ ቤተሰብን ከሰማይ አባትና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚሆን ሕይወት ብቁ በማድረግ ላይ በሚኖረው ውጤት መሰረት ያደረገ መሆን አለበት። በክህነት አገልግሎታችን ውስጥ እደዚህ ዓይነት ጠቃሚ ነገር የለም።

ዛሬ ምሽት እንደ ቤተሰብ አባልና እንደ ምልዓተ ጉባኤ አባል እያዳመጠ ላለ ለአንድ ዲያቆን ይሄ ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል ልንገራችሁ።

በቤተሰቡ ውስጥ ተደጋጋሚ የቤተሰብ ፀሎት ወይም ተደጋጋሚ የቤተሰብ ምሽት ሊኖር ወይም ላይኖር ይችላል። አባቱ ይሄን ግዴታ ተገንዝቦ ለፀሎት ወይም ለመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ቤተሰቡን በአንድ ላይ ከጠራ፣ ዲያቆኑ ለመሳተፍ በፈገግታ ሊጣደፍ ይችላል። ወንድሞቹንና እህቶቹን እንዲሳተፉ ሊያበረታታ እንዲሁም ሲሳተፉ ሊያወድሳቸው ይችላል። ትምህርት ሲጀምር ወይም በሌላ በሚያስፈልግ ጊዜ አባቱን ቡራኬ መጠየቅ ይችላል።

እንደዚህ ዓይነት አማኝ አባት ላይኖረው ይችላል። ነገር ግን በእምነቱ ምክንያት ለእነዛ ልምዶች የልቡ ፍላጎት የሰማይን ኃይሎች በዙሪያው ላሉ ሰዎች ያመጣል። ዲያቆን በሙሉ ልቡ ለሚፈልገው ለቤተሰብ ሕይወት ይሻሉ።

በአሮናዊ ክህነት ውስጥ ያለ አስተማሪ በቤት ለቤት የማስተማር ስራ ውስጥ ጌታ የቤተሰብን ሕይወት እንዲለውጥ ለመርዳት እድልን ሊመለከት ይችላል። ጌታ በትምህርት እና ቃል-ኪዳኖች ውስጥ እንዲህ አሳብ አቀረበ፥

“የመምህሩ ሀላፊነትም ቤተክርስቲያኗን ዘወትር መጠበቅ፣ እና እነርሱን መርዳትና ማጠንከር ነው፤

““እናም ምንም ጥፋት በቤተክርስቲያኗ እንዳይኖር፣ እንዲሁም አባላቶቿ እርስ በራሳቸው እንዳይከፋፉ፣ እንዳይዋሹ፣ እንዳይተማሙ፣ ወይም ክፉ እንዳይነጋገሩ መጠበቅ” ነው” (ት. እና ቃ. 20፥53–54)።

በተመሳሳይ ሁኔታ በአሮናዊ ክህነት ውስጥ ካህኑ ይሄ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፥

“የካህን ሀላፊነት መስበክ፣ ማስተማር፣ ማብራራት፣ አጥብቆ መምከር፣ እናም ማጥመቅ፣ እናም ቅዱስ ቁርባንን መባረክ ነው፣

“እናም የእያንዳንዱን አባል ቤትን መጎብኘት፣ እናም በሚስጥር እና በድምፅ እንዲጸልዩ እና የቤተሰብ ሀላፊነታቸውን እንዲያከናውኑ በጥብቅ ማበረታት ነው” (ት. እና ቃ. 20፥46–47)።

ለእነዛ ችግሮች እንዴት መነሳት እንደምትችሉ ወጣት አስተማሪና ካህን በነበርኩበት ጊዜ እንደተገረምኩት ልትገረሙ ትችላላችሁ። አንድን ቤተሰብ ሳላስቀይም ወይም ሳልተች ወደ ዘላለማዊ ሕይወት በሚያስኬድ ሁኔታ እንዴት እንደማሳስብ እርግጠኛ አልነበርኩኝም። ልቦችን የሚቀይረው ብቸኛ ማሳሰቢያ ከመንፈስ ቅዱስ እንደሚመጣ ተማርኩኝ። ያ ብዙ ጊዜ ፍፁም የቤተሰብ አባል በነበረውና በሆነው የአዳኙን ምስክርነት ስንሰጥ ይከሰታል። ለእርሱ ባለን ፍቅር ላይ ስናተኩር፣ በምንጎበኛቸው ቤቶች ውስጥ ስምምነትና ሰላም ያድጋል። መንፈስ ቅዱስ ለቤተሰቦች በምንሰጠው አገልግሎት ውስጥ ይንከባከበናል።

ወጣቱ የክህነት ተሸካሚ በሚፀልይበት መንገድ፣ በሚናገርበት መንገድ እና የቤተሰብን አባሎች በሚያበረታታበት መንገድ የአዳኙን ተፅዕኖና ምሳሌ ወደ አእምሮአቸውና ልቦቻቸው ሊያመጣ ይችል ይሆናል።

አንድ ብልህ የክህነት መሪ ያ ነገር እንደገባው አሳየኝ። ወጣት ወንድ ልጄን በቤት ለቤት ትምህርት ጉብኝት ውስጥ እንዲመራ ጠየቀው። ቤተሰቡ የእሱን ማነሳሳት ሊቃወሙ እንደሚችሉ ተናገረ፣ ነገር ግን የአንድ ወጣት ልጅ ቀላል ትምህርትና ምስክርነት በበለጠ ሆኔታ የጠነከረ ልባቸውን እንደሚሰነጠቅ አሰበ።

አንድ ወጣት የመልከጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ የዘላለም ቤተሰቦችን በመፍጠር ላይ ለመርዳት ምን ማድረግ ይችላል? ወደ ሚስዮን ለመሄድ ተዘጋጅቶ ይሆናል። በሙሉ ልቡ ቤተሰቦችን ማግኘት፣ ማስተማርና ማጥመቅ እንዲችል መፀለይ ይችላል። አንድ ቀን መልከ መልካም ወጣት ከተወዳጅ ሙሽራውና ከሁለት ውብ ትናንሽ ልጃ ገረዳቸው ጋር ከእኔና ከሚስዮን ጓደኛዬ ጋር መቀመጣቸውን አሁንም ድረስ አስታውሳለሁ። መንፈስ ቅዱስ መጣና የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንደተመለሰ መሰከረላቸው። በአንድ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ውስጥ እንደተመለከቱት ለሁለት ትናንሽ ልጃ ገረዳቸው በረከት እንዲሰጧቸው እስከመጠየቅ ድረስ አመኑ። ልጆቻቸው እንዲባረኩ ፍላጎት ነበራቸው፣ ነገር ግን እውነተኛ በረከቶች እውን የሚሆኑት ቃል-ኪዳን ከገቡ በኋላ በእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ ውስጥ ብቻ እንደሆነ አልገባቸውም ነበር።

እነዛን ጥንዶችና ትናንሽ ልጃ ገረዶች ምናልባት አሁን ካለ ዘላለማዊ ቤተሰብ ቃል-ኪዳን አድገው ሳስብ አሁንም ድረስ ህመም ይሰማኛል። ወላጆቻቸው ቢያንስ ለእነሱ ዝግጁ የነበሩትን በረከቶች ትንሽዬ እውቀት ነበራቸው። በሆነ ሁኔታ፣ በሆነ ቦታ የዘላለም ቤተሰብ ለመሆን ብቁ እንዲሆኑ እድሉን እንዲያገኙ ተስፋዬ ነው።

ወደ ሚስዮን የሚሄዱ ሌሎች የመልከጸዲክ ክህነት ተሸካሚዎች ወንድ ልጄ ማቲው የነበረውን ልምድ ይኖራቸዋል። እሱና ጓደኛው ከስምንት ልጆቿ ጋር የምትኖር ባሏ የሞተባትን አንዲት ሴት አገኙ። የዘላለም ቤተሰብ እንዲኖራችሁ የምትፈልጉትን ነገር እነሱም እንዲኖራቸው ፈለገ። ለልጄ በዛ ሰዓት ይህ የማይቻል ወይም ቢያንስ ለመሆን የሚከብድ መስሎ ታየው።

ልጄ ባሏ የሞተባትን ሴት ካጠመቃት ከዓመታት በኋላ ያችን ትንሽዬ ከተማ ጎበኘሁ እና ከቤተሰቧ ጋር በቤተክርስቲያን እንድገናኝ ጋበዘችኝ። ልጆቿ ከብዙ የልጅ ልጆቿ ጋር በአካባቢው ውስጥ ከተለያዩ የቤተክርስቲያን ቅርንጫፎች እስኪመጡ ድረስ ትንሽ ጊዜ መጠበቅ ነበረብኝ። አንድ ወንድ ልጇ በኤጲስ ቆጶስ አመራር ውስጥ በአማኝነት እያገለገለ ነበር፣ እናም እያንዳንዳቸው ልጆቿ በቤተ-መቅደስ ቃል-ኪዳኖች ተባርከው ነበር፣ እንዲሁም በዘላለም ቤተሰብ ውስጥ ታትመው ነበር። ከዚህች ውድ እህት ተለይቼ ስሄድ እጆቿን ወገቤ ላይ አድርጋ (በጣም አጭር ነበረች፣ ስለዚህ እስከ ወገቤን ብቻ ነበር ለመድረስ የምትችለው) እንዲህ አለችኝ፣ “እባክህን ማቴኦን ከመሞቴ በፊት እንዲመጣ ንገረው።” በእነዛ አማኝ ሽማግሌዎች አማካኝነት ከእግዚአብሔር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ የሆነውን ስጦታ በደስታ መጠባበቅ ተሰጥቷታል።

አንድ ሽማግሌዎች ከሚስዮን ሲመለስ የዘላለም ሕይወትን ለእሱና ለሚወዳቸው ሰዎች ለመሻት ለዝግጁነቱ ታማኝ ለመሆን ማድረግ ያለበት ነገሮች አሉ። ለአጭር ጊዜ ወይም ለዘላለም ከጋብቻ ውጪ የበለጠ አስፈላጊ ዝግጁነት የለም። ከሚስዮን በኋላ ላሉ ዕቅዶች ጋብቻን ቅድሚያ የማድረግ ብልህ ምክሮችን ሰምታችኋል። አማኝ የክህነት አገልጋይ በብልሃት ያደርገዋል።

ጋብቻን በማሰብ የልጆቹን ወላጆችና የሚኖራቸውን ውርስ እየመረጠ እንዳለ ይመለከታል። ከልብ በመፈለግና ፀሎታማ ምልከታ ጋር ምርጫውን ያደርጋል። የሚያገባት ሴት የቤተሰብ ምናቡን፣ የጌታን የጋብቻ አላማ የፀና እምነቶችን የምትካፈል መሆኑን እንዲሁም ለልጆቹ ደስታ ማግኘት እምነት የሚጥልባት ሴት መሆኗን ያረጋግጣል።

ፕሬዘደንት ኤን ኤልደን ታነር ብልህ ምክርን ሰጡ፥ “ከሌሎች የበለጠ ማክበር የሚገባችሁ ወላጆች የልጆቻችሁ ወላጆች ሊሆኑ ያሉት ናቸው። እነዛ ልጆች ልትሰጧቸው የምትችሉት ጥሩ ወላጅነት---ንፁህ ወላጅነት ይገባቸዋል።”3 ንፅህና የእናንተ እና የልጆቻችሁ መከላከያ ይሆናል። ለእነሱ የዛ በረከት ዕዳ አለባችሁ።

ዛሬ ምሽት በማዳመጥ ላይ ያሉ አንዳንድ ባሎችና አባቶች አሉ። ምን ልታደርጉ ትችላላችሁ? የሆነ ቀን በሰለስቲያ የክብር ደረጃ ውስጥ ለመኖር ለእናንተና ለቤተሰባችሁ አስፈላጊ የሆነውን መለወጥ ለማድረግ ፍላጎታችሁ እንዲጨምር ተስፋዬ ነው። እንደ አንድ የክህነት አባት፣ ባለቤትህ ከጎንህ ሆና፣ ያቺን ቀን በጉጉት ለመጠባበቅ እንዲበረታቱ የእያንዳንዶቹን የቤተሰብ አባል ልቦች መንካት ትችላለህ። የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎችህን ከቤተሰብህ ጋር ትካፈላለህ፣ መንፈስ ቅዱስ የተጋበዘበት የቤተሰብ ምሽት ታደርጋለህ፣ ከሚስትህና ከቤተሰብህ ጋር ትፀልያለህ እንዲሁም ቤተሰብህን ወደ ቤተ-መቅደስ ለመውስድ እራስህን ታዘጋጃለህ። ወደ የዘላለም ቤተሰብ ቤት በሚያመራው መንገድ ላይ አብረሃቸው ትጓዛለህ።

ሚስትህንና ልጆችህን የሰማይ አባት እንደተንከባከበህ ትንከባከባቸዋለህ። ቤተሰብህን በእርሱ መንገድ ለመምራት የአዳኙን ምሳሌና አቅጣጫ ትከተላለህ።

“በማሳመን፣ በትእግስት፣ በደግነት፣ እና በትህትና፣ እና ግብዝነት በሌለው ፍቅር ካልሆነ በስተቀር፣ ምንም ሀይል ወይም ተጽዕኖ በክህነት ስልጣን ዘዴ ሊደገፍ አይቻልም ወይም አይገባውም፤

“ይህም በርህራሄ፣ እና ያለግብዝነትና ያለተንኮል መንፈስን በታላቅ በሚያሳድግ ንጹህ እውቀት ብቻ ነው ሊደገፍ የሚችለው፤—

“መንፈስ ቅዱስ በሚነሳሳበት በትክክለኛው ጊዜ በሀያልነት በመቆጣት፤ ከዚያም በኋላ እንደጠላት እንዳያይህ፣ ለተቆጣኸውም ተጨማሪ ፍቅር አሳይ” (ት. እና ቃ. 121፥41–43).

ጌታ የክህነት አባቶችን ምን ዓይነት ባሎች መሆን እንዳለባቸው ነገራቸው። እንዲህ አለ፣ “ሚስትህን በፍጹም ልብህ ውደዳት፣ እናም ከሚስትህም በስተቀር ከማንም ጋር አትጣመር” (ት. እና ቃ. 42፥22)። ጌታ ለባልና ሚስት በአንድ ላይ ሲናገር እንዲህ አዘዘ፣ “… አታመንዝር፣ … ወይም እንደዚህ አይነት ነገሮችን አታድርግ” (ት. እና ቃ. 59፥6).

ለወጣቶች ጌታ ደረጃውን አስቀምጧል። “ልጆች ሆይ፣ ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉም ለወላጆቻችሁ ታዘዙ” (ቆላስይስ 3፥20)፣ እና “አባትህንና እናትህን አክብር” (ዘጸአት 20፥12)።

ጌታ በቤተሰብ ውስጥ ላሉ በሙሉ ሲናገር፣ ምክሩ እርስ በእርስ እንዲዋደዱና እንዲደጋገፉ ነው።

የቤተሰብ “የእያንዳንዱን አባል ሕይወት ለማነፅ ጣሩ”፣ “ደካሞችን ለማጠንከር፤ የጠፉትን ተወዳጆች መልሶ ለማግኘት እና በታደሰው መንፈሳዊ ጥንካሬአቸው ተደሰቱ” 4 ብሎ እርሱ ጠየቀን።

ጌታ እንዲሁም የሞቱ ዘመዶቻችን በዘላለም ቤታችን ውስጥ አብረውን እንዲሆኑ ለመርዳት የምንችለውን በሙሉ እንድናደርግ ይጠይቃል።

ሰዎች ቅድመ ዓያቶቻቸውን እንዲያገኙና ስሞችን ወደ ቤተ-መቅደስ እንዲወስዱ ለመርዳት በታታሪነት የሰራ የሊቀ ካህናት የቡድን መሪ ከዚህ የሄዱትን ሰዎች እያዳነ ነው። ለእነዛ ሊቀ ካህናትና ሥነ-ስርዓቶቹን ላከናወኑ ሰዎች በሚመጣው ዓለም ውስጥ ምስጋና ይኖራል፣ ምክንያቱም በመንፈስ ዓለም ውስጥ የሚጠብቁትን ቤተሰባቸውን አልረሷቸውምና።

ነቢያት እንዲህ ብለዋል፥ “ከምታደርጉት የጌታችን ስራ በጣም ጠቃሚ የሆነው በራሳችሁ ቤት ግድግዳ ውስጥ የምታደርጉት ስራ ይሆናል። የቤት ለቤት ትምህርት፣ የኤጲስ ቆጶስ ስራ እና ሌላ የቤተክርስቲያን ኃፊነቶች በሙሉ ጠቃሚዎች ናቸው፣ ነገር ግን በጣም ጠቃሚ የሆነው ስራ በራሳችሁ ቤት ግድግዳ ውስጥ ያለው ነው።”5

በቤታችሁና በክህነት አገልግሎታችሁ ውስጥ ታላቅ ጥቅም ያለው ነገር እኛንና የምንወዳቸውን ሰዎች ወደ ዘላለም ሕይወት እንዲሰሩ ለመርዳት በምናደርገው ትንሽዬ ተግባሮች ውስጥ ይሆናል። እነዛ ተግባራት በዚህ ሕይወት ውስጥ ትንሽ ሊመስሉ ይችሉ ይሆናል፣ ነገር ግን ዘላቂ የሆኑ በረከቶችን ለዘላለም ያመጣሉ።

የሰማይ አባት ልጆችን ወደ እርሱ ቤት እንዲሄዱ ለመርዳት በአገልግሎታችን ውስጥ አማኞች ስንሆን፣ ምድራዊ አገልግሎታችንን ስንጨርስ ሁላችንም በጣም መስማት ለምንፈልገው ሰላምታ ብቁ እንሆናለን። ቃሎቹ እነዚህ ናቸው፥ “መልካም፣ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፥ በጥቂቱ ታምነሃል፣ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ”(ማቴዎስ 25፥21)።

ከእነዛ መካከል “ብዙ ነገሮች” መጨረሻ የሌለው የልጅ ልጅ ዝርያ ቃል-ኪዳን ነው። በአባታችንና በውድ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤት ውስጥ ለዛ መለኮታዊ በረከት ሁላችንም ብቁ እንድንሆን እንዲሁም ሌሎችን ብቁ እንድናደርግ ፀሎቴ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith (2007), 137.

  2. ብሩስ አር መካንኬ፣ in Conference Report, ሚያዝያ 1970 (እ.አ.አ.)፣ 27።

  3. ኤን ኤልደን ታነር፣ Church News፣ ሚያዝያ 19፣ 1969 (እ.አ.አ.)፣ 2።

  4. ብሩስ አር መካንኬ፣ in Conference Report, ሚያዝያ 1970 (እ.አ.አ.)፣ 27።

  5. ሃሮልድ ቢ ሊ፣ Decisions for Successful Living (1973) (እ.አ.አ.)፣ 248–49።