በትከሻው ያስቀምጣችኋል እናም ወደቤት ይሸከማችኋል
መልካሙ እረኛ የጠፋውን በግ እንዳገኘው፣ ልባችሁን ወደ አለም አዳኝ ከፍ ካደረጋችሁ፣ እርሱ ያገኛችኋል።
በልጅነቴ ከማስታውሳቸው ሁሉ የሚያስፈራኝ ከእንቅልፌ ያነቃኝ በርቃት የአየር ወራር ማስታወቂያ ነበር። ብዙ ጊዜ ሳይፈጅም፣ ሌላ ድምፅ፣ የአውሮፕላኑ ድምጽ አየሩን እንደሚያንቀጠቅጥ አይነት እስከሚመስል ድረስ በቀስታ ይጨምራል። እናታችን እንድናደርግ እንዳስተማረችን፣ እና ልጆች የተዘጋጀውን ሻንጣችንን ይዘን ወደ ቦንብ መሸሸጊያው ኮረብታ እንሮጥ ነበር። በጭለማው ውስጥ ስንሮጥ፣ አረንጓዴ እና ነጭ ብውታዎች ከሰማይ ወርደው ቦንቡ የሚመታውን ቦታ ያጠቁማሉ። በሚያስገርም ሁኔታ፣ ሁሉን እነዚህን ብውታዎች የገና ዛፍ ብለው ይጠሯቸዋል።
አራት አመቴ ነው፣ እናም ለአለም ጦርነት ምስክር ነኝ።
ድሬዝድን
ቤተሰቤ ከኖሩበት ሳይርቅ የሚገኝ የድሬዝድን ከተማ ነበር። በዚያ የሚኖሩት እኔ ካየኋቸው በአንድ ሺህ እጥፍ የሚሆን ነበር ያዩት። በብዙ ሺህ ኪሎግራም ቦብቦች ምክንያት የነበረ በጣም ትልቅ የእሳት አውሎ ንፋስ በድረዝደን ውስጥ በሙሉ አለፈ፣ 90 በመቶ ከተማውን ደመሰሰው እናም በሚያልፍበትም ከቆሻሻ እና አምድ በስተቀር ምንም አልተወም።
በአጭር ጊዜ፣ አንዴ “የጌጥ ሳንጣ” የተባለ ስም የተሰጠው ቦታ አልነበረም። የጀርመን ጸሀፊ ስለመደምሰሱ እንዲህ ጻፈ፣ “ወብቷ የተገነባወ በአንድ ሺህ አመት ነበር፣ በአንድ ምሽት ይህም በሙሉ ተደመሰሰ።”1 በልጅነቴ የራሴ ህዝብ በጀመሪት ጦርነት ምክንያት የነበረው ጥፋት እንዴት ለመታደስ እንደሚችል አይታየኝም ነበር። በአካባቢያችን ያለው አለም ተስፋ የሌለው እና ወደፊት የሚመለከቱት የሌለው ነበር።
ባለፈው አመት፣ ወደ ድሬስደን ለመመለስ እድል ነበረኝ። ከጦርነቱ ሰባ አመት በኋላ፣ ይህም እንደገና “የጌጥ ሳንጣ” ነው። የፈረሱት ነገሮች ተጠርገዋል፣ እናም ከተማው ታድሳል እናም ተሻሽሏል።
በጉብኝቴ ፍራውንኪርችህ፣ የሴት ወይዘሮ ቤተክርስቲያንን ቆንጆ የሉተር ቤተክርስቲያን አየሁ። በመጀመሪያ በ1700 (እ.አ.አ) የተገነባው፣ ይህም የድረዝደን የሚያብረቀርቅ ሀብት ነበር፣ ነገር ግን ተሰባብሮ ነበር። ለብዙ አመታት እንደዚያ ቀረ፣ በመጨረሻም ፍራውንኪርችህ እንደገና እንድሚገነባ ተወሰነ።
ከፈረሰው በተክርስቲያን ለመጠቀም የሚቻልባቸው ድንጋዮች ተሰብስበው እና ተዘርዝረው ነበር፣ እናም ብዙዎቹም እንደገና በሚገነባበት ጊዜ ተጠቅመውባቸው ነበር። ዛሬ በእሳጥ የጠቆሩትን ድንጋዮች የውጪውን ግድግዳ ላይ እንደ ምልክት ይታያሉ። እነዚህ “ጠባሶች” የዚህ ህንጻ የጦርነት ታሪኮች ማስታወሻ ብቻ ሳይሆኑ የተስፋ ሀውልት—ከአመድ አዲስ ህይወት ለመፍጠር ሰው ስላለው ችሎታ ታላቅ ምሳሌ ነው።
ስለድረዝደን ታሪክ ሳሰላስል እና በፍጹም የተደመሰሰውን እንደገና ስለገነቡት ብልህነት እና ውሳኔ ስገረምበት፣ የመንፈስ ቅዱስ አስደሳች ትፅዕኖ ተሰማኝ። በእርግጥም ሰው የተሰበረ ከተማን ውድመት፣ ፍርስራች፣ እና ድምሰሳ፣ ከወሰደ እና ወደሰማይ ከፍ ያለ የሚያነሳሳ ህንጻ ለመገንባት ከቻለ፣ ሁሉን ቻይ አባታችን የወደቁትን፣ የሚታገሉትን፣ እና የጠፉትን ልጆቹን በዳግም ለመመለስ ምን ያህል ተጨማሪ ችሎታ አለውን?
ህይወታችን እንዴን አይነት ውድመት እንዳለው ምንም ግድ የለውም። ኃጢያታችን እንዴት እንደቀላ፣ ምሬታችን እንዴት ዝልቅ እንደሆነ፣ እኛም እንዴት ብቸኛ፣ የተጣችል፣ ወይም ልባችን የተሰበረ መሆኑም ግድ የለውም። ተስፋ የሌላቸውም፣ ተስፋ ቆርጠው ያሉትም፣ እምነትን የከዱትም፣ ሀቀኝነታቸውን አሳልፈው የሰጡትም፣ ወይም እግዚአብሔርን የሰደቡትም እንደገና ለመገንባት ይችላሉ። ልዩ ከሆኑት አንዳንድ የጥፋት ልጆች በስተቀር፣ እንደገና ለመገንባት የማይችል የተሰባበረ ምንም ህይወት የለም።
የወንጌል አስደሳች ዜና ይህ ነው፥ በውድ የሰማይ አባታችን እና መጨረሻ በሌለው በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል በተሰጠው የደስታ እቅድ ምክንያት፣ ከውድቀት ለመዳን ከመቻላችን በተጨማሪ፣ ስጋዊ አስተሳሰብን ለማለፍ እና የዘለአለም ህይወት ወራሾች እና ለመግለጽ የማይቻለው የእግዚአብሔር ክብር ተካፋዮች ለመሆን እንችላለን።
የጠፋው በግ ምሳሌ
በአዳኝ አገልግሎት ጊዜ፣ የእርሱ ዘመን የሀይማኖት መሪዎች “ኃጢያተኞች” ብለው ከሚጠሯቸው ጋር ኢየሱስ ጊዜ ማሳለፉን ተቃውመው ነበር።
ምናልባት ለእነርሱ ኃጢያተኛ ጸባዮችን ተቀባይ ወይም ደጋፊ እንደሆነ ይመስላቸው ነበር። ምናልባት እነርሱ ኃጢያተኞች ንስሀ እንዲገቡ የሚያደርግ መልካም መንገድ እነርሱን መወገዝ፣ ማሳለቅ፣ እና ማሳፈር ነው ብለው ያምኑ ነበር።
ፈራሲዎች እና ጸሀፊዎች የሚያስቡትን አዳኝ ሲገነዘብ ታሪክ ነገራቸው፥
“መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?
“ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል።”2
በመቶ አመቶች በኋላ፣ ይህም ምሳሌ የጠፋውን በግ ለመመለስ እና የጠፉትን ለመርዳት በስራ እንደምንጠራበት ትርጉም ተሰጥቶታል። ይህም በእርግጥ ትክክለኛ እና ትክክለኛ ቢሆንም፣ በዚህ ላይ ተጨማሪ እንደሚኖረው አስባለው።
የኢየሱስ አላማ፣ በመጀመሪያ፣ ስለምለካሙ እረኛ ስራ ለማስተማር ለመሆን ይችላልን?
ለአስቸጋሪው ልጁ እግዚአብሔር ስላለው ፍቅር እያስተማረ መሆኑ ይችላልን?
የአዳኝ መልእክት እግዚአብሔር ስለጠፉት ያውቃል--እርሱም ያገኛቸዋል፣ ይደርስላቸዋል፣ እናም ያድናቸዋል፣ የሚል ሊሆን ይችላልን?
ይህም ከሆነ፣ በግስ ለዚህ መለኮታዊ እርዳታ ብቁ ለመሆን ምን ማድረግ አለበን?
በጉ ለመጠቀም አስቸጋሪ የሆነ ቴክኖሎጂ መጠቀም ያስፈልገዋልን? ጂ.ፕ.ሴ በመጠቀም የት እንደሚገኝ ማወቅ አለበትን? በእጅ ስልክ ለመጠቀም የሚችልበት መሳሪያ ለመፍጠር ልዩ ችሎታ ያስፈልገዋልን? መልካሙ እረኛ መጥቶ ከማዳኑ በፊት በጉ በህዝብ በሚታወቅ ሰው ደጋፊነትን ለማግኘት ያስፈልገዋልን?
አይደለም። በጉ ለመዳን ብቁ የሚሆነው ስለተወደደ ነው።
ለእኔ፣ የጠፋው በግ ምሳሌ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ከሚገኑ መልእክቶች ሁሉ በላይ ተስፋ የሚሰጥ ጥቅስ ነው።
አፍቃሪው አዳኛችን፣ መልካሙ እረኛ፣ እናንተ እና እኔን ያውቃል። እናንተ ያውቃችኋል እናምም ያፈቅራችኋል።
ስትጠፉ ያውቃል፣ እናም የት እንዳላችሁም ያውቃል። ሀዘናችሁን ያውቃል። ጸጥተኛ ልመናችሁንም። ፍርሀታችሁንም። እምባዎቻችሁንም።
በራሳችሁ መጥፎ ምርጫዎች ወይም እናንተ ለመቆጣጠር በማትችሉበት ጉዳዮች ቢሆንም፣ እንዴት እንደጠፋቹ ግዴታ የለውም።
የሚያስብበት አናንተ ልጆቹ መሆናችሁ ነው። ይወዳችኋል። ልጆቹን ያፈቅራል።
ስለሚወዳችሁ፣ ያገኛችኋል። በደስታ በትከሻው ላይ ያደርጋችኋል። ወደቤት ሲያመጣችሁ፣ ለአንድ እና ለሁሉም እንዲህ ይላል፣ “የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ።”3
ምን ማድረግ አለብን?
ነገር ግን እናንተም ምን ማድረግ አለብን? ብላችሁ ታስቡ ይሆናል። በእርግጥ ለመዳን ከመፈለግ በላይ ማድረግ አለብኝ።
አፍቃሪው አባታችን ልጆቹ በሙሉ ወደ እርሱ እንዲመለሱ ፍላጎት ቢኖረውም፣ ማንንም ወደ ሰማይ በግድ አይመልስም።4 እግዚአብሔር ያለፍቃዳችሁ አያድናችሁም።
ምን ማድረግ አለብን?
ግብዣው ቀላል ነው፥
“ወደ እኔ … ዙሩ።”5
“ወደ እኔ ኑ።”6
“ወደ እኔ ቅረቡ እና እኔም ወደ እናንተ እቀርባለሁ።”7
እኛ ለመዳን እንደምንፈልግ የምናሳየው እንዲህ ነው።
ይህም ትንሽ እምነት ያስፈልገዋል። ነገር ግን ተስፋ አትቁረጡ። አሁን እምነትን ለመሰብሰብ የማትችሉ ከሆናችሁ፣ በተስፋ ጀምሩ።
እግዚአብሄር እንዳለ አሁን ለማለት የማትችሉ ከሆነ፣ እንደሚገኝ ተስፋ በማድረግ ለመጀመር ትችላላችሁ። ለማመን መፈለግ ትችላላችሁ።8 ይህም ለመጀመሪያ ብቁ ነው።
ከዚያም፣ በዚያ ተስፋ መሰረት በመስራት፣ ወደ ሰማይ አባት ቅረቡ። እግዚአብሄር ፍቅሩን ወደ እናንተ ይዘረጋል፣ እናም የማዳን እና የመቀየር ስራው ይጀምራል።
ከጊዜ በኋላም፣ እጁን በህይወታችሁ ውስጥ ትገነዘባላችሁ። ፍቅሩ ይሰማችኋል። በእርሱ ብርሀን ለመራመድ እና የእርሱን መንገድ የመከተል ፍላጎት በእናንዳንዱ የእምነት እርምጃዎቻችሁ ያድጋል።
እነዚህን የእምነት እርምጃዎች “ታዛዥነት” ብለን እንጠራቸዋልን።
በእነዚህ ቀናት ይህ ተወዳጅ ቃል አይደለም። ነገር ግን ታዛዥነት በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ የተወደደ ሀሳብ ነው፣ ምክንያቱም “የወንጌሉን ህግጋትና ስርዓቶችን በማክበር፣ የሰው ዘር ሁሉ በክርስቶስ የኃጢአት ክፍያ አማካይነት መዳን እንደሚችሉ” እናውቃለን።9
በእምነት ስናጨምር፣ በታማኝነት ማደግም አለብን። ከዚህ በፊት የድረዝደንን መደምሰስ ስላለቀሰበት የጀርመን ደራሲ ጠቅሼ ነበር። ደግሞም ይህን ሀረግ ጻፈ “Es gibt nichts Gutes, ausser: Man tut es.” የሰለስቲያል ቋንቋን ለመናገር ለማይችሉት፣ ይህ እንዲህ ይተረጎማል “ካላደረጋችሁት በስተቀር ምንም መልካም የለም።”10
እናንተ እና እኔ ስለመንፈሳዊ ነገሮች ልብ በሚነካ መንገድ እንናገር ይሆናል። በሀይማኖት ርዕስ ባላችሁ ቅን ምሁር ትርጉም ሌሎችን ለማስገረም እንችል ይሆናል። ስለሀይማኖት እንዘምር እና “በላይ ስላለም ቤታችን እናልም” ይሆናል።11 ነገር ግን እምነታችን እንዴት እንደምንኖር ካልለወጠ--ይምነታችን በየቀኑ የምንወስንበት ላይ ተፅዕኖ ከሌለው--ሀይማኖታችን በከንቱ ነው፣ እናም እምነታችንም፣ ያልሞተም ቢሆንም፣ በእርግጥም ደህና አይደለም እና በመጨረሻም፡ለመሞት አደጋ ላይ ነ ያለው።12
ታዛዥነት የእምነት የህይወት ደም ነው። በታዛዥነት ነው ወደ ነፍሳችን ብርሀንን የምንሰብስበው።
ነገር ግን ታዛዥነትን አንዳንዴ እንደማንረዳው ሀሳብ አለን። ታዛዥነትን ወደ መጨረሻ የምንደርስበት እንደሆነ ሳይሆነ፣ በራሱ መጨረሻ እንደሆነ እንመለከተው ይሆናል። ወይም የምናፈቅራቸውን፣ በሚቀጥል ሙቀት እና በተደጋጋሚ ድብደባ፣ ወደ ተቀደሱ እና ሰማያሪ ነገሮች ለማስተካከል የምሳሌ ታዛዥነት መዶሻን በትእዛዛት የብረት ቅርፅ ማውጫ ላይ እንቀጠቅጥ ይሆናል።
ምንም ጥርጥር የለውም፣ ወደ ንስሀ መግባት በጥብቅ ሀይል መጠራት የሚያስፈልገን ጊዜዎች አሉ። በእርግጥም፣ በዚህ አይነት ብቻ መደረስ የሚችሉ አንዳንዶችም አሉ።
ነገር ግን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የምናከብርበትን ምክንያት የሚገልጽ ሌላ ምሳሌ አለ። ታዛዥነት ነፍሳችንን ወዳልሆንንበት የማጣመም፣ ወይም የመጠምዘዝ፣ እና የመቀጥቀጥ ሂደት ላይሆንም ይችላል። በዚህ ምትክ፣ በምን እንደተሰራን ለማወቅ የምንችልበት ሂደት ሊሆን ይችላል።
በሁሉም ሀይለኛ እግዚአብሔር የተፈጠርን ነን። የሰማይ አባታችን ነው። እኛም ቃል በቃል የእርሱ የመንፈስ ልጆች ነን። በጣም ውድ በሆኑ እና በጣም በተነጠሩ መለኮታዊ ነገሮች የተሰራን ነን፣ እና በዚህም በውስጣችን መለኮታዊ ነገሮች የያዝን ነን።
በዚህ ምድር ላይ ግን ሀሳባችን እና ስራዎቻችን በተበከነው፣ ቅዱስ ባልሆነውም እና ንጹህ ባልሆነው እንቅፋት ይሆንብናል። የአለም አቧራ እና ቆሻሻ የውልድ መብታችንን እና አላማችንን እንዳንረዳ እና እንዳናውቅ በማድረግ ነፍሳችን ላይ እንከን ያደርግበታል።
ነገር ግን ይህም በእውነት ማን እንደሆንን ለመቀየር አይችልም። የፍጥረታችን መሰረታዊ መልኮታዊነት ይቀራል። ልባችንን ወደ ውድ አዳኛችን ለማዞር ስንመርጥ እና በደቀመዛሙርትነት መንገድ እግራችንን ስናሳርፍ፣ ታዕምራታዊ ነገር ይደርሳል። የእግዚአብሄር ፍቅር ልባችንን ይሞላል፤ የእውነት ብርሀን አዕምሮአችንን ይሞላል፤ ኃጢያት ለመስራት ያለንን ፍላጎት እናጣለን፤ እናም በጭለማ ለመራመድ ከዚህ በኋላ አንፈልግም።13
ታዛዥነትን እንደ ቅጣት ሳይሆን ወደ መለኮታዊ እጣ ፈንታችን የሚወስድ ነጻ እንደሚያደርገን መንገድ እንመለከተዋለን። እናም ቀስ በቀስ፣ በከሉ፣ አቧራው፣ እና የዚህች አለም ገደብ እየወደቁ ይሄዳሉ። በመጨረሻም፣ በውስጣችን የሚገኘው ታላቅ ዋጋ ያለውም የሰማይ ሰው ዘለአለማዊ መንፈስ ይገለጻል፣ እናም የመልካምነት ብርሀን ፍጥረታችን ይሆናል።
ለመዳን ብቁ ናችሁ
ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ውድ ጓደኞቼ፣ እግዚአብሔር እንደሆንነው--በእውነት እንደሆንን--እንደሚያየን እናለመዳን ብቁ እንደሆንን እንደሚያየን እመሰክራለሁ።
ህይወታችሁ የተእንደተበላሸ ይሰማችሁ ይሆናል። ኃጢያት ሰርታችሁም ይሆናል። የፈራችሁ፣ የተናደዳችሁ፣ ያዘናችሁ፣ ወይም በጥርጣሬ የተሰቃያችሁ ይሆናል። ነገር ግን መልካሙ እረኛ የጠፋውን በግ እንዳገኘው፣ ልባችሁን ወደ አለም አዳኝ ከፍ ካደረጋችሁ፣ እርሱ ያገኛችኋል።
ያድናችኋል።
ከፍ ያደርጋችኋል እናም በትከሻው ያስቀምጣችኋል።
ወደቤትም ተሸክሞ ይወስዳችኋል።
ሟች እጆች የተሰባበረውን እና የተደመሰሰውን ውብት ወዳለው ማምለኪያ ቦታ ለመቀየር ከቻሉ፣ ውድ የሰማይ አባታችን እኛል ለመገንባት እንደሚችል እና እንደሚገነባ መተማን እንችላለን። እቅዱ እኛ ከነበርንበት በጣም ታላቅ--ልናስብበት ከምንችለው በላይ ታላቅ--ወደሆነ ነገር ለመገንባት ነው። በደቀመዛሙርትነት መንገድ በምንወስደው በእያንዳንዱ የእምነት እርምጃ፣ ለመሆን ወደተመደብንበት ወደ ዘለአለማዊ ክብር እና መጨረሻ ወደሌለው ሰዎች እያደግን እንሄዳለን።
ይህም ምስክሬ፣ በረከቴ፣ እና ትሁት ጸሎቴ የሆነው በመምህራችን ቅዱስ ስም፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።