2010–2019 (እ.አ.አ)
የተቀደሰ ታማኝነት
ኤፕረል 2016


3:56

የተቀደሰ ታማኝነት

ይህ ውድ የክህነት ሀይል ስጦታ ከእርሱ ጋር ቅዱስ ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን ደግሞም ለእኛ ና ለሌሎች ልዩ በረከቶችን ያመጣል።

ውድ ወንድሞቼ፣ በዚህ ምሽት መንፈስ ንግግሬን እንዲመራልኝ እጸልያለሁ። ለሁላችንም አንድ የሆነ ቅድመ ተከተል አብሮ ያያይዘናል። የእግዚአብሔርን ክህነት ለመሸከም እና በስሙ ለመስራት ታምነናል። የቅዱስ ታማኝነት ተቀባዮች ነን። ብዙ ይጠበቅብናል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች፣ ክፍል 121፣ ቁጥር 36፣ ውስጥ እንደምናነበው፣ “የክህነት መብቶች እና የሰማይ ሀይላት የማይነጣጠሉ ናቸው።” ምን አይነት አስደናቂ ስጦታ ነው የተሰጠን። ክህነትን ወጠበቅ እና ለእኛ—እናም በእኛ በኩል ለሌሎች—የሰማይ አባታችን የከማሸልንን ግርማዊ በረከቶች ብቁ ለመሆን ሀላፊነቱ የእኛ ነው።

የትም ብትሄዱ፣ ክህነት ከእናንተ ጋር ይሄዳል። በቅዱስ ቦታዎች እየቆማችሁ ናችሁ? ለእናንተ ወይም ለክህነት ብቁ ባልሆኑ ቦታዎች ወይም ነገሮች በመሳተፋችሁ ራሳችሁን እና ክህነታችሁን በአደጋ ላይ ከማድረሳችሁ በፊት፣ ውጤቱን ምን እንደሚሆን ለማሰብ ቁሙ። እናንተ ማን እንደሆናችሁ እና እግዚአብሔር እንድትሆኑ የሚጠብቃችሁ ምን እንደሆነ አስታውሱ። እናንተ የቃል ኪዳን ልጆች ናችሁ። እናንተ የሀይል ሰዎች ናችሁ። እናንተ የእግዚአብሔር ልጅ ናችሁ።

ይህ ውድ የክህነት ሀይል ስጦታ ከእርሱ ጋር ቅዱስ ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን ደግሞም ለእኛ ና ለሌሎች ልዩ በረከቶችን ያመጣል። በማንኛውብ ቦታ ራሳችንን በምናገኝበት፣ ይህን ሀይል ለመጠቀም ሁልጊዜም ብቁ እንሁን፣ ምክንያቱም ይህን ለማድረግ ፍላጎታችን እና እድላችን መቼ እንደሚመጣ አናውቅምና።

በሁለተኛ አለም ጦርነት፣ አንዱ ጓደኛዬ በደቡብ ፓስፊክ ውስጥ እያገለገለ እያለ አውሮፕላኑ በባህር ላይ ተመትቶ ወድቆ ነበር። እርሱ እና አብረውት የሚኖሩት በውጤታማነት ከሚነደው አውሮፕላን በመዝለያ ጃንጥላ ወረዱ፣ ታንኳቸውን ነፉ፣ እናም ይህን ታንኳ ለሶስት ቀን ይዘው ቆዩ።

በሶስተኛው ቀን የሚያድናቸው እንደሆነ የሚያውቁትን መርከብ ተመለከቱ። አልፏቸው ሄደ። በሚቀጥለው ጠዋት እንደገና አለፋቸው። የሚያድናቸው መርከብ በአካባቢው የሚገኝበት የመጨረሻ ቀን እንደሆነ በማወቃቸው ተስፋ መቁረጥ ጀመሩ።

መንፈስ ቅዱስ ለጓደኛዬ እንዲህ ተናገረ፥ “ክህነት አለህ። የሚያድኑት መጥተው እንዲያነሷችሁ እዘዝ።”

እንደተነሳሳበት አደረገ። “በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እና በክህነት ሀይል በኩል፣ ዙር በሉ እና አንሱን።”

በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ መርከቡ በአጠገባቸው ተገኘ፣ ወደ መድረኩ እንዲወጡ ረዷቸው። ታማኝ እና ብዉ የክህነት ተሸካሚ፣ በመጨረሻ ደረጃው፣ ህይወቱን እና የሌሎችን ህይወት ለመባረክ ክህነቱን ተጠቀመ።

ለሚያስፈልግ ጊዜአችን፣ ለአገልግሎት ጊዜአችን፣ እና ለበረከት ጊዜአችን በዚህ እና አሁን ለመዘጋጀት እንወስን።

ይህን የክህነት ስብሰባ ስንዘጋ፣ እናንተ “የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት” ናችሁ እላችኋለሁ (1 ጴጥሮስ 2፥9)። ለእነዚህ መለኮታዊ አክብሮት ለማግኘት ብቁ እንድንሆን በሙሉ ልቤ የምጸልየው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።