2010–2019 (እ.አ.አ)
የእግዚአብሔር አፋጣኝ ቸርነት
የሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


የእግዚአብሔር አፋጣኝ ቸርነት

ነገር ግን የዛሬው መልእክቴ ጌታን በትዕግሥት እየጠበቅን ሳለ እንኳን ወደ እኛ በፍጥነት የሚመጡ በረከቶች አሉ፡፡

ከበርካታ አመታት በፊት፣ የአምስት አመቱ ወንድ ልጃችን ወደኔ በመምጣት እንዲህ ሲል አስታወቀ “ አባዬ አንድ ነገርን ተረድቻለሁ፡፡ የተረዳሁትም ነገር ላንተ በቅርቡ ማለት ለኔ በጣም ረጅም ጊዜ እንደሆነ ነው።”

ጌታ ወይም አገልጋዮቹ “ከዚህም ብዙ ቀናት አይደለም” ወይም “ጊዜው ሩቅ አይደለም” ብለው ሲናገሩ፣ በቀጥተኛ አባባል የህይወት ዘመን ወይም ከዚያ በላይ ሊሆን ይችላል።1 የርሱ ጊዜ፣ እና ብዙውን ጊዜ የሱ ጊዜ አቆጣጠር ከኛ የተለየ ነዉ፡፡ ትአግስት ቁልፍ ናት። ያለሷም፣ ለህይወትና ለመዳን በእግዚኣብሄር እምነትን ማደግም ሆነ ማሳየትም አንችልም። ነገር ግን የዛሬው መልእክቴ ጌታን በትዕግሥት እየጠበቅን ሳለን እንኳን ወደእኛ በፍጥነት የሚመጡ በረከቶች አሉ፡፡

አልማና ህዝቡ በላማናውያን ተይዘው በነበረበት ወቅት ለነጻነታቸው ጸልየው ነበር፡፡ ምንም እንኳን በፍጥነት ነጻ ባይወጡም በትዕግስት ነጻነታቸውን ሲጠባበቁ ጌታ በተወሰኑ በረከቶቹን በቸርነቱን አሳይቷቸዋል፡፡ በፍጥነትም የላማናውያንን ልብ አራርቶ እንዳይገሏቸው አደረገ፡፡ የአልማንም ህዝቦች አጠንክሮ ሸክማቸውን አቀለለ፡፡2 ነጻ ከወጡ በኋላ ፣ ወደ ዛራሄምላ ተጓዙ እናም በመገረም ለሚሰሙ አድማጮቻቸው ተሞክሮዋቸውን አካፈሉ። የዛራሄምላ ህዝብም ተደነቁ፣ “እናም … ፈጣን የእግዚአብሔርን ቸርነት እናም አልማንና ወንድሞቹን … ከባርነት ማውጣቱን ባሰቡ ጊዜ፣ ድምፃቸውን ከፍ አደረጉና ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀረቡ።”3

የእግዚአብሔር አፋጣኝ ቸርነት በእውነተኛ ሃሳብ እና ከልብ በመነጨ ሙሉ ዓላማ ለሚጠሩት ሁሉ ይመጣል። ይህም ማለት በተስፋ መቁረጥ ከልባቸው የሚጮሁትን ነፃ መውጣት በረጅም ርቀት ላይ ያለ እና መከራም የተራዘመ እንዲሁም የበረታ በሚመስል ሁኔታ ውስጥ፡ ያሉትን ያካትታል።

እንድዚሁም አንድ ወጣት ነብይ በጉድጓድ አፋፍ ላይ በመሰቃየት ላይ ሆኖ በመጨረሻ ላይ “ እነሆ እግዜአብሄር ሆይ፣ ወዴትስ ነህ” በማለት ጮኸ። እጅህስ ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል ... ? አዎ ጌታ ሆይ፣ እስከመቼስ ...?”4 በምላሹም፣ ጌታ ዮሴፍን ወዲያውኑ ነጻ አላወጣውም፣ ነገር ግን ወዲያውኑ ሰላምን ለገሰው፡፡5

በተጨማሪም ለሚመጣ መዳን እግዚያብሄር አፋጣኝ ተስፋን ይሰጣል።6 ምንም ይሁን ምን፣ በየትኛውም ቦታ ቢሆን፣ በክርስቶስ ውስጥ እና በክርስቶስ አማካኝነት ሁልጊዜ ተስፋ ከብሩህ ፈገግታ ጋር ከፊታችን አለ፡፡። 7 ወዲያውኑ በፊታችን።

በተጨማሪም ፣ እንዲህ ሲል ቃል ገብቷል “የኔ ቸርነት ካንተ አይርቅም፡፡”8

ከሁሉም በላይ የእግዚአብሔር ፍቅር ፈጣን ነው። ከጳውሎስ ጋር በመሆን ይህንን እመሰክራለሁ፣ ምንም ነገር “በክርስቶስ ኢየሱስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።”9 ኃጢያቶቻችን እንኳን ቢሆኑ፣ ለጊዜው ከመንፈሱ እኛን ቢያርቁንም፣ ከዘላቂው እና ከፈጣኑ እና አባታዊ ፍቅሩ ሊለየን አይችልም።

“እኛን ወዲያውኑ የሚባርክባቸው“ አንዳንድ መንገዶች እና ዘዴዎች እነዚህ ናቸው፡፡10 አሁን፣ እነዚህን መርሆች ለማቅረብ፣ ህይወታቸው የእግዚአብሔር አፋጣኝ ቸርነት ምስክር ስለሆኑ የሁለት ሰዎች አጋጣሚዎችን ለእናንተ አካፍላለሁ።

ኤሚሊ ገና ከአስራዎቹ ዕድሜጀምሮ ከአደገኛ ዕፅ ጋር በተያያዘ ትግል ታደርግ ነበር። ለሙከራ የተጀመረ ወደ ልምድ አመራ፣ ልምድም፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ምንም እንኳን መሻሻልን ብታሳይም፣ ይህም ​​ለብዙ አመታት በምርኮ ይዟት ሱስ ሆነ። ኤሚሊ ችግሯን በጥንቃቄ ደበቀች። በተለይም ሚስትና እናት ከሆነች በኋላ፡፡

የእሷ መዳን አጀማመር በፍጹም ነጻ መውጣት አልመስል ብሏት ነበር፡፡። አንድ ደቂቃ፣ የኤሚሊ መደበኛ የሕክምና ምርመራ ስታደርግ የነበረ ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ በአምቡላንስ ወደ ተኝቶ ታካሚዎች ተቋም ትወሰድ ነበር። ከልጆቿ፣ ከባለቤቷና ከቤቷ መለየትን ስታስብ መሸበር ጀመረች።

በዚያ ምሽት ብቻዋን በቀዝቃዛው እና በጨለማው ክፍል ውስጥ ኤሚሊ በአልጋዋ ላይ ጥቅልል ብላ አነባች። በእዚያ ክፍል ውስጥ እና በነፍሷ ውስጥ በተፈጠረው ጭንቀት፣ ፍራቻ እና በክፍሉ በነበረ ጨቋኝ ጨለማ በመሸነፍ ኤሚሊ በዚያ ምሽት እንደምትሞት አስባ ነበር፡፡ የማገናዘብ ችሎታዋም ጠፍቶ ነበር። በስተመጨረሻም ብቻዋን።

በዝያ በጣም ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ ውስጥ ኤሚሊ ከመኝታ ላይ በመንከባለል በጉልበቷ ለመንበርከክ ጥንካሬን ሰበሰበች። ምንም ከዚህ ቀደም ስታደርግ እንደነበረው ጸሎት አቀማመጧን ሳታስተካክል፣ እራሷን በሙሉ ሁኔታ ወደ ጌታ ሰጠች፤ “ውድ አምላክ ሆይ፣ እፈልግሃለሁ፡፡ እባክህ እርዳኝ። ብቻዬን መሆን አልፈልግም። እባክህ ምሽቱን እንዳሳልፍ እርዳኝ።”

ለጥንቱ ጴጥሮስ እንዳደረገው ወዲያውኑ፣ ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ በመስመጥ ላይ የነበረውን ነፍሷን አዳነ።11 በዚያም በኤሚሊ ላይ አስደናቂ ሰላም፣ ድፍረትት፣ ማረጋገጫ፣ እና ፍቅር መጣባት። ክፍሉ ከዛ በኋላ ቅዝቃዛ አልነበረም፣ ብቻዋን እንዳልሆነች አወቀች፣ እና 14 አመት ከሞላት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ኤሚሊ ሁሉም ነገር መልካም እንደሚሆን አወቀች። ኤሚሊ “በእግዚአብሄር አንደ ነቃች”12 እናም በሰላም አንቀላፋች። እናም እንደምናየው፣ “ስለዚህ ንስሃ የምትገቡ ከሆነና፣ ልባችሁን የማታጠጥሩ ከሆነ፣ ታላቁ የቤዛነት ዕቅድ በፍጥነት በእናንተ ላይ ይሆናል።”13

ምስል
ቤተሰብ በቤተመቅደስ

የኤሚሊ ፈውስ እና የመጨረሻው ነጻነት ረጅም ጊዜ ወስዷል፣ የወራት የክትትል ህክምና፣ ስልጠና እና የምክር አገልግሎት ወስዳለች፣ በዚህም ሂደት ውስጥ ቸርነቱ ደግፏታል እና አንዳንዴም ተሸክሟታል። ቸርነቱ ከባለቤቷና ከልጆቿ ጋር ወደ ቤተመቅደስ ገብታ ስትጣመር ከእርሷ ጋር ቀጥሏል። እንደ ዘረሔምላ ህዝቦች፣ ኤሚሊ በፈጣኑ የእግዚአብሔር ቸርነት እና የእርሷን ከባርነት ለማዳን ያለውን ኃይል ስታሰላስል ምስጋና ትሰጣለች።

አሁን፣ ከሌላ ህይወት ወደ ጀግና አማኝነት ተለወጠች። እ.ኤ.አ. በታኅሣሥ 27፣ 2013፣ አሊሺያ ሽሮደር ውድ ጓደኞቿን ሻን እና ሻርላ ቺልኮቴ የተባሉ በድንገት በሯ ላይ ሲገኙ በደስታ ተቀበለቻቸው። ሻን፣ የአሊሺያ ኤጲስ ቆጶስ የነበረ፣ የሞባይል ስልኩን በማቀበል በትህትና “አሊሺያ፣ እንወድሻለን፣ አላት፡፡ ይህንን የስልክ ጥሪ መመለስ አለብሽ።”

የአሊሺያ ባል፣ ማሪዮ በስልክ ላይ ነበር። ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ ከነበረ የበረዶ መኪና ጉዞ ላይ ከተወሰኑት ልጆቹ ጋር በራቀ አካባቢ ላይ ነበር። በጣም አሰቃቂ አደጋ ተከስቶ ነበር። ማሪዮ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን የ 10 ዓመቱ ልጃቸው ካሌብ ግን ሞተ፡፡ ማሪዮ የካሌብን መሞት ለአሊሺያ እያለቀሰ ሲነግራት ጥቂቶቻችን በምንረዳው መልኩ በጣም ደነገጠች እና እጅግ በጣም አዘነች። ወደታች አወረዳት። አሊሺያ በቃላት መናገር በማይቻል ሃዘን ምክንያት፣ መናገርም ሆነ መንቀሳቀስ አልቻለችም።

ኤጲስ ቆጶስ እና እህት ቺልቺኮት ወደ ፊት በፍጥነት በመሄድ ከፍ አደረጓት እና ያዟት። ለተወሰነ ጊዜ ያህል አለቀሱ እና እጅግም አዘኑ፡፡ ከዚያም ኤጲስ ቆጶስ ቺልኮቴ ለአሊሺያ በረከት ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነ፡፡

ከዚያ ቀጥሎ የተከናወነው ነገር ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እና ስለ እግዚአብሔር ፈጣን ቸርነት ምንም ካልገባን ልንረዳው አንችልም። ኤጲስ ቆጶስ ቻልኮቴ እጆቹን በአሊስያ ጭንቅላት ላይ በማስቀመጥ ቀስ ባለ ድምጽ መናገር ጀመረ። አሊሺያ ሁለት ነገሮችን ሰማች፣ እግዚአብሔር ራሱ የተናገረ ያህል ነበር። በመጀመሪያ፣ ስሟን አሊሺያ ሱዛን ሽሮደር የሚለውን። ከዛም ኤጲስ ቆጶስ የሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር ስልጣን ሲጠራ ሰማች። በዚህ ቅጽበት - ስሟን እና የእግዚአብሔርን ኃይል ብቻ በመጥቀስ - አሊሺያ ሊገለጽ በማይችል ሰላም፣ ፍቅር፣ መፅናናት እና ደስታ ስሜት ተሞላች። እናም ከእርሷ ጋር ቀጠለ።

አሁን አሊሺያ፣ ማሪዮ እና ቤተሰቦቻቸው ስለ ካሌብ ያዝናሉ እናም ይናፍቁታል። ይህ ከባድ ነዉ! ከነሱ ጋር አብሬ ሳወራ አሊሺያ ትንሹን ልጇን ምን ያህል እንደምትወደውና እንደምትናፍቀው ስትናገር ዓይኖቿ በእንባ ይሞላሉ። በጥልቅ ተስፋ መቁረጧ ወቅት ከደረሳት አፋጣኝ ቸርነቱ ጀምሮ እናም አሁንም ከቀጠለው አሰደሳች “ብዙ ቀናት ካልቀሩት “ዳግም የመገናኘት ብሩህ ተስፋ ጋር ታላቁ ነጻ አውጪ እንዴት በእያንዳንዱ አስቸጋሪው ጉዞዋ እንደረዳት ስትናገር አይኖችዋ እንደረጠቡ ነዉ፡፡

የህይወት ተሞክሮዎች አንዳንዴ ወደ ኤሚሊ እና ኦሊሺያ የደረሰውን ዓይነት እፎይታ ለመገንዘብ ወይም ለመቀበል አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እና ግራ መጋባትን እንደሚያመጡ አውቃለሁ። እኔም እንደዚህ አይነት ጊዜዎችን አሳልፊያለሁ፡፡ እንደነዚህ ባሉት ጊዜያት እኛን የሚያቆየን ሃያሉ የእግዚአብሔር አፋጣኝ ቸርነት መገለጥ መሆኑን እመሰክራለሁ። የጥንቷ እስራኤል በመጨረሻ “ባቆያቸው በዚያው አምላክ” ቀን በቀን መትረፋቸውን አስታውሱ14

ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቁ አዳኝ መሆኑን እመሰክራለሁ፣ እናም በእውነተኛ እና ከልብ በመነጨ ፍላጎት ወደ እሱ ስትመጡ፣ ሕይወታችሁን ወይም ደስታችሁን ለማጥፋት ከሚችሉ ነገሮች ሁሉ እንደሚያድናችሁ በእሱ ስም ቃል እገባላችኋለሁ። ይህ መዳን ከምትወዱት በላይ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፣ ምናልባትም ዕድሜ ልክ ወይም ከዚያ በላይ። እስከመጨረሻው የመዳን ቀን ለመደገፍ እና ለማጠናከር፣ ለእናንተ ማጽናኛ፣ ማበረታቻ፣ እና ተስፋን፣ ምስጋናዬን እሰጣለሁ እናም ስለ ፈጣኑ የእግዚአብሔር ቸርነት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ምስክርነቴን እሰጣለሁ፣ አሜን።

አትም