2010–2019 (እ.አ.አ)
ሸንጎ፡ የእኔነት ስፍራ
የሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ሸንጎ፡ የእኔነት ስፍራ

ጌታ ጠንካራ ሸንጎን እንድትፈጥሩ ይሻል፡፡ ልጆቹን ሲያሰባስብ የኔነትን የሚሰማቸው እና ሊያድጉበት የሚገባ ስፍራ ያስፈልጋቸዋል፡፡

በ2010 አመተ ምህረት አንድሬ ሴባኮ እውነትን ለማግኘት የሚሻ ወጣት ወንድ ነበር ፡፡ ምንም እንኩዋን ከልብ የመነጨ ጸሎትን አድርጎ ባያውቅም፤ ለመሞከር ወሰነ፡፡ ይህን ካደረገ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ሚስዮናውያንን አገኘ፡፡ የመጽሃፈ ሞርሞን ምስል ያለበትን በራሪ ወረቅት ሰጡት አንድሬ አንዳች ስሜት ስልተሰማው መጽሃፉን እንዲሸጡለት ጠየቃቸው፡፡ ወደ ቤተክርስትያን ከመጣ መጽሃፉን በነጻ ማግኘት እንደሚችል ነገሩት፡፡ 1

አንድሬ በቦትስዋና አፍሪካ ውስጥ በቅርብ በተቋቋመው ሞቹዲ ቅርንጫፍ ብቻውን በመምጣት ተካፈለ፡፡ ነገር ግን ቅርንጫፉ 40 የሚሆኑ አፍቃሪና በወዳጅነታቸው የተጣመሩ አባላት ያሉበት ነበር፡፡2 አንድሬን እጃቸውን ዘርግተው ተቀበሉት፡፡ የሚስዮናውያኑን ትምህርት ተከታትሎ ተጠመቀ በጣም ድንቅ ነበር፡፡

ከዛስ ምን የይሁን ? አንድሬ በንቁ ተሳትፎው እንዴት ሊቀጥል ይችላል? በቃል ኪዳኑ ጎዳና እንዲገፋበት ማንስ ይረዳዋል? ለነዚህ ጥያቄዎች አንዱ መልስ የእሱ የክህንት ስብስብ ሸንጎ ነው፡፡3

እያንዳንዱ የክህነት ተሸካሚ በምንም ሁኔታ ላይ ቢገኝ ጠንካራ ከሆነ ሸንጎ ተጠቃሚ ነው፡፡ የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚ የሆናችሁ ወጣት ወንድሞቼ ጌታ ጠንካራ የሆነ ሸንጎን እንድትፈጥሩ ይጠብቅባችኋል፡፡ ለያንዳንዱ ወጣት ወንድ የእኔነት እንዲሰማው የሚያደርግ ስፍራ፡ የጌታ መንፈስ የሚገኝበት ስፍራ እና እያንዳንዱ የሸንጎው አባል በእንኳን ደህና መጣህ ስሜትና ተፈላጊነቱ እንዲሰማው የሚያደርግው ስፍራ፡፡ ጌታ ልጆቹን ሲያሰባስብ ሊገኙበትና ሊያድጉበት የሚገባ ስፍራ ያስፈልጋቸዋል፡፡

እያንዳንዳቹ የሸንጎ አመራሮች በሁሉም የሰብስቡ አባላት ዘንድ ፍቅርንና ወንድማማችነትን እያሳደጋቹ መንግዱን እንድትመሩ መንፈሳዊ መነሳሳትን መሻት ይኖርባችኋል፡፡4 ለአዳዲስ አባላት ፤ ተሳትፎአቸው ለቀነሰና የተለየ እንክብካቤ የሚሹት ላይ ልዩ ትኩረት መስጠት አለባችሁ፡፡5 በክህነት ሃይል አማካኝነት ጠንካራ ሸንጎን ትፈጥራላቹ፡፡6 ጠንካራና ህብረት ያለው ሸንጎ በ አንድ ወጣት ወንድ ሕይወት ላይ ሙሉ ለውጥን ያመጣል፡፡

የቤተክርስቲያ አዲሱን ቤትን ያማከለ የወንጌል አስተምህሮ አሰራር ሲተዋውቅ አንዳንዶች እንደ አንድሬ ያሉትን አስበው “ በቤታቸው ውስጥ የወንጌል አስተምህሮ ጥናት እና ወንጌል በተግባር ከማይኖርበት የሚመጡ ወጣቶችስ እጣቸው ምንድን ነው?7 ችላ ይባላሉን?”

አይደለም! ማንም ችላ የሚባል አይኖርም! ጌታ ሁሉንም ወጣት ወንድና ወጣት ሴት ይወዳችዋል እኛ የክህነት ተሸካሚዎች የጌታ እጆች ነን። እኛ በቤተክርስትያን ጥረት የተደገፈን ቤትን ያማከለ ስርአት ደጋፊዎች ነን፡፡ እያንዳንዱ ቤተሰብ ወይም ግለሰብ በቤቱ ያለው ድጋፍ አናሳ ሲሆን የክህነት ሸንጎዎች ፤ ሌሎች አመራሮችና ጓደኞች የመደግፍና እነሱን የመንከባከብ ሃላፊነት አለባቸው፡፡

ይህ ተግባራዊ ሲሆን አይቻለሁ። ተሞክሮውም አለኝ። እኔ የስድስት አመት ልጅ ሳለሁ ቤተሰቦቼ ፍቺ ፈጽመው አባቴ እናቴን ከአምስት ልጆች ጋር ጥሏት ሄደ፡፡ እናታችን እኛን ለመንከባከብ ስራ ጀመረች፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ሁለተኛ ስራና ተጨማሪ ትምህርትም አስፈልጓት ነበር፡፡ እኛን ለመንከባከብ የነበራት ሰአት ውስን ነበር፡፡ ነገር ግን አያቶቻችን፣ አጎቶቻችን፣ አክስቶቻችን፣ ኤጲስ ቆጶሳት፣ እና የቤት ለቤት አስተማሪዎች መልአክ የሆነችውን እናቴን ለማገዝ ተረባረቡ፡፡

እኔ ደሞ ሸንጎ ነበረኝ፡፡ ለጓደኞቼና ወንድሞቼ ስለወደዱኝና ስላገዙኝ በጣም አመስጋኝ ነኝ፡፡ የእኔ ሸንጎ፡ የእኔነት የሚፈጥር ስፍራ ነበር፡፡ አንዳንዶች ከቤተሰቤ ሁኔታ የመነጨ ደካማና ውጤት አልባ እንደሆንኩ አድርገው ሊያስቡኝ ይችሉ ይሆናል፡፡ ምናልባትም ሆኜ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የክህነት ሸንጎዎች እነዚህን ጎዶሎዎች ይቀይራሉ፡፡ የእኔ ሸንጎ ዙሪያዬን ከበው ህይወቴን ከሚገመተው በላይ ባርከውታል፡፡

በዙሪያችን ብዙ ደካሞችና ውጤት አልባ የሆኑ አሉ። ምናልባትም ሁላችንም በአንድ ወይም በሌላ መንግድ እንደዛው ልንሆን እንችላለን፡፡ ነገር ግን ሁላችንም ጥንካሬን ልንሰጥበትና ልንቀበልበት የምንችልበት ስፍራ የሆነ ሸንጎ አለን፡፡ ሸንጎ ማለት “ሁሉ ለአንድ፤ አንዱ ለሁሉ” ማለት ነው፡፡8 እርስ በርሳችን የምንማማርበት፣ አገልግሎት የምንሰጥበት ፣ እና የወንድማማችነት ህብረትን እየገነባን እግዚአብሄርን የምናገለግልበት ስፍራ ነው፡፡9 ተአምራትም የሚፈጸሙበት ስፍራ ነው፡፡

በአንድሬ ሸንጎ ስለተከሰቱት ጥቂት ተአምራት ላካፍላችሁ እወዳለሁ፡፡ እነዚሀን ምሳሌዎች ስናገር እንድትመለከቱ የምፈልገው እያንዳንዱ የክህነት ሸንጎ ሲከተላቸው የሚያጠነክሩትን መርሆዎች ነው፡፡

አንድሬ ከተጠመቀ በኋላ ሚሲዮናዊያን ሌሎች አራት ወጣት ወንዶችን ሲያስተምሩ አብሮ ይሄድ ነበር፡፡ እነሱም ተጠመቁ፡፡ አሁን አምስት ወጣት ወንዶች ሆኑ፡፡ አንዳቸው ሌላውን ማጠናከር ጀመሩ እንዲሁም ቅርንጫፋቸውን፡፡

ስድስተኛ ቱሶ የተባለ ወጣት ወንድም ተጠመቀ፡፡ ቱሶ ለሌሎች ሶስት ጓደኞቹ ወንጌልን አካፍሎ ተጠመቁ ባጭር ጊዜ ዘጠኝ ሆኑ፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት ሲሰባሰቡም በዚህ መልኩ ነው ፤ ቀስ በቀስ ፣ በጓደኞቻችው ግብዣ፡፡ በጥንት ጊዜ፤ እንድሪያስ ክርስቶስን ሲያገኝ በፍጥነት ወደ ወንድሙ ስምኦን በመሄድ “ወደ ኢየሱስም አመጣው” 10 በተመሳሳይም ፊሊጶስም የክርስቶስ ተከታይ ከሆነ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ጓደኛውን ናትናኤልን “መጥተህ እይ” ብሎ ጋበዘው፡፡ 11

በሞቹዲ፤ አስረኛው ወጣት ወንድ ቤተክርስትያንን ተቀላቀለ፡፡ ሚስዮናውያኖቹ ደሞ አስራ አንድኛውን አገኙ፡፡ አስራ ሁለተኛው ወጣት ወንድ ደሞ የወንጌልን ተጽእኖ በጓደኞቹ ላይ በማየቱ ተጠመቀ፡፡

የሞቹዲ ቅርንጫፍ አባላት በጣም ተደሰቱ፡፡ እነኚህ ወጣት ወንዶች “ ወደ ጌታ ተለወጡ_ _ ፟ ወደ ቤተክርስቲያንም ተቀላቀሉ”12

መጽሃፈ ሞርሞን በመለወጣቸው ላይ ታላቅ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ 13 ቱሶ እንዲህ ሲል ያስታውሳል “መጽሃፈ ሞርሞንን ማንበብ ጀመርኩ ሁል ጊዜ ትርፍ ሰአት ሲኖረኝ፣ ቤት ስሆን፣ ትምህርት ቤት እንዲሁም በሁሉ ቦታ፡፡”14

ኦራቲሌ በጓደኞቹ መልካም ተምሳሌት ወደወንጌሉ ተሳበ እንዲህም ሲል ያብራራል “ጣትን የማጮህ ያህል ፍጥነት ባለው መልኩ የሚለወጡ ይመስላል... ለውጣቸው ትምህርት ቤት ይዘውት ከሚመጡት ትንሽ መጽሃፍ ጋር ተያያዥነት እንዳለው፡፡ ገመትኩ.... በጣሙን ጥሩ ሰዎች መሆን እንደቻሉ ተገነዘብኩ....... እኔም መለወጥን ፈለኩኝ።15

ምስል
ሞቹዲ ቅርንጫፍ

12ቱም ወጣት ወንዶች የተሰባሰቡትና የተጠመቁት በተከታታየ ሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ነበር፡፡ እያንዳንዳቸው ከቤተሰባችው ውስጥ ብቸኛ የቤተክርስቲያን አባል ነበሩ። ነገር ግን በቤተክርስትያን ቤተሰባቸው እንደ ፕሬዚዳንት ራክዌላ ቅርንጫፍ ፕሬዚዳንታቸው፣16 ሽማግሌና እህት ቴይለር ጥንድ ሚስዮናውያንና ሌሎች የቤተክርስትያን አባላት ባሉ ተደግፈዋል፡፡17

ወንድም ጁኒየር የሸንጓቸው መሪ እሁድ እሁድ ከሰአት በኋላ ወጣት ወንዶቹን በቤቱ በመጋበዝ ምክርን ይለግሳቸዋል፡፡18 ወጣት ወንዶቹ በጋራ ቅዱሳን ጽሁፎችን ያጠናሉ እንዲሁም ተከታታየ የቤተሰብ ምሽትን ያከናውናሉ፡፡

ምስል
አባላትን መጎብኘት

ወንድም ጁኒየር አባላትን እንዲጎበኙ፣ ሌሎች ሰዎች በሚስዮናውያን ሲማሩ፣ እንዲሁም ሌሎች ጉብኝት የሚያስፈልጋቸው ሲኖሩ ዪዟቸው ይሄዳል፡፡ አስራ ሁለቱም ወጣት ወንዶች በወንድም ጁኒየር መኪና ጀርባ ላይ ተጭነው ይጓዛሉ፡፡ በየተለያዩ ቤቶች ሁለት ወይም ሶስት እያደረግ ያደርሳችውና በኋላም ይሰበስባቸዋል፡፡

ምንም እንኳን ወጣቶቹ ወንጌልን ገና እየተማሩ ያሉና ብዙ እናውቃለን ብለው ባያስቡም ወንድም ጁኒየር ለሚጎበኙዋችው ሰዎች ከሚያውቁት አንድ ወይም ሁለቱን እንዲያካፍሉ ነገራቸው፡፡ እነኚህ ወጣት የክህነት ተሸካሚዎች አስተማሩ፣ ጸለዩ እናም የቤተክርስትያነ ጠባቂዎች ሆኑ፡፡19 የክህነት ሃላፊነታቸውን በመወጣት ከማገልገል የሚገኘውን ደስታ አጣጣሙ፡፡

ምስል
የወንድሞች ቡድን

አንድሬም ይህን አለ “በጋራ ተጫውተናል፣ በጋራም ሰቀናል፣ በጋራም አንብተናል፣ እንዲሁም ወንድማማቾች ሆነናል”።20 እንዲሁም እራሳቸውን “የወንድማማች ቡድን” በማለት ይጠራሉ፡፡

አንድ ላይም ሆነው የሚሲዮን አገልግሎትን ማበርከት እንዳለባቸው እቅድን ነደፉ፡፡ ከቤተሰባቸው ብቸኛ የቤተክርስትያን አባል እንደመሆናቸው ብዙ መሰናክሎች ነበሩባችው፡፡ ነገር ግን እርስ በእርስ በመረዳዳት ተወጧቸው፡፡

አንድ በአንድ የሚስዮን ጥሪያቸው ደረሳቸው፡፡ ቀድመው የሄዱት እቤት ሆነው በመዘጋጀት ላይ ላሉት ደብዳቤን በመጻፍ ልምዳቸውን ያካፍሉና እንዲያገለግሉ ያበረታቷቸው ነበር፡፡ አስራ አንዱ ወጣት ወንዶች ሚስዮናውያን ሆነው አገለገሉ፡፡

እነዚህ ወጣት ወንዶች ወንጌልን ለቤተሰቦቻቸውም አካፈሉ፡፡ እናት ፣ እህት፣ ወንድም፣ ጓደኛ፣ እንዲሁም በሚስዮን ሳሉ ያስተማሯቸው ሰዎችም ጭምር ተለውጠው ተጠመቁ፡፡ ተአምራት ተፈጠሩ እናም ስፍር ቁጥር የሌላቸው ነፍሳትም ተባረኩ፡፡

አንዳንዶቻቹ እንዲህ ያለው ተአምር ሊሆን የሚችለው የእስራኤል መሰባሰብ እየፈጠነበትና እየለመለመበት ባለው እንደ አፍሪካ ባለ ስፍራ ብቻ ነው ብላችሁ እያሰባችሁ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ቢሆንም በሙቺዲ ቅርንጫፍ የተተገበረው መርህ በሁሉም ስፍራ እውነታ እንደሆነ እመሰክራለሁ፡፡ በየትም ስፍራ ብትሆኑ የናንተ ሸንጎ በማበርታትና ወንጌልን በማካፈል ማደግ ይችላል፡፡ አንድ ደቀመዝሙር ወደ አንድ ጓደኛው በሚደርስለት ጊዜ አንዱ ሁለት ሊሆን ይችላል፡፡ ሁለትም አራት ሊሆን ይችላል፡፡ አራትም ስምንት ሊሆን ይችላል፡፡ ስምንትም አስራ ሁለት ሊሆን ይችላል፡፡ ቅርንጫፎች ዋርድ መሆን ይችላሉ፡፡

ምስል
ሞቹዲ ዋርድ

አዳኝ እንዲህ ሲል አስተማረ “ሁለት ወይም ሶስት (ከዛም በላይ) በስሜ በሚሰበሰቡበት ........ በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁ”21 የሰማይ አባት በዙሪያችን በሙላ ያሉን ሰዎች አእምሮና ልብ እያዘጋጀ ነው፡፡ እነሱ ጌታን ለማወቅ በሚጥሩበት ወቅት እንድንወዳቸውና እንድናግዛቸው ምሪቶችን መከተል እንችላለን፣ የወዳጅነት እጃችንን መዘርጋት እንችላለን፣ ሌሎችን መጽሃፈ ሞርሞንን እንዲያነቡ መጋብዝ እንችላለን፡፡

የሞቹዲ ወንድማማቾች ቡድን ጉዟቸውን በጋራ ከጀመሩ 10 አመትን አስቆጥረዋል፡፡ አሁንም ድረስ የወንድማማች ቡድን እንደሆኑ ይገኛሉ፡፡

ካትሌጎ እንዲህ አለ “ በርቀት ምክያት እንኳን አንድ ላይ ባንሆንም ነገር ግን አንዳችን ለአንዳችን ሁሌም አለን”22

እኔ ጸሎቴ ነው እኛ የጌታን ጥሪ ተቀብለን በክህነት ሸንጓችን ከርሱ ጋር በመጣመር እያንዳንዱ ሸንጎ የእኔነት ስፍራ እንዲሆን፣ የመሰባሰቢያ ስፍራ እንዲሆንና የሚያድግ ሰፍራ እንዲሆን ማድረግ እንድንችል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን ነው እናም ይህ የእርሱ ስራ ነው። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ማርክ እና ሺርሊይ ቴለር፣ ኮምፕ የወንድማማቾች ቡድን (የሞቾዲ ቅርንጫፍ የመለወጥ ታሪክና ምስርክነት, 2012–13እኤአ), 4, የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጽሃፍት, ሶልት ሌክ ሲቲ ይመልከቱ፡፡

  2. የግል መላላኮች፣ ሌታናንግ አንድሬ ሰባኮ፤ የወንድማማች ቡድን ዋና መጽሃፍ፣ የወንድማማች ቡድን ማጣቀሻ 2011-19፣ በቤተክርስትያን ታሪክ ቤተመጽሃፍ ሶልት ሌክ ሲቲ ዪታ ፡፡

  3. ፕሬዚዳንት ቦይድ ኬ ፓከር እንዲህ አሉ “ አንድ ወንድ ክህነትን ሲሸክም ከእራሱ የሚበልጥ እካል ክፍል ይሆናል፡፡ ከእራሱ ውጭ የሆነና ሙሉ ለሙሉ የሚቆምለት ነግር ይሆናል (የእህትማማችነት ማእቀፍኤንዛይን ህዳር. 1980እኤአ, 109–10). )

  4. ፕሬዚደንት ራስል ኤም ኔልሰን እንዴት አድርገን ራእይን እንደምንሻ ካበራሩ በኋላ እንዲህ አሉ “ ይህንን ሂደት እለት ተእለት፣ ወር ከወር፣ ከአመት አመት ስትደጋግሙት ወደ “ራእይ መርሆዎች ታድጋላችሁ”” (“ራእይ ለቤተክርስትያን፣ ራእይ ለሂዎታችን፣” ሊያሆና, ግንቦት 2018 እኤአ, 95; እንዲሁም የቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንቶች አስተምህሮ: ጆሴፍ ስሚዝ [2007እኤአ], 132 ን ይመልከቱ ).

  5. መመሪያ መጽሃፍ 2: ቤተክርስትያን ማስተዳድር (2010 እኤአ)፣ 8.3.2 ይመልከቱ።

  6. ሊሎች እርዳታዎች የኤጲስ ቆጶስ አባላት እና አማካሪዎች፡፡ ሽማግሌ ሮናልድ ራዝባንድ በ መጋቢት 31 2018 እኤአ የተዋወቀውን የመልከጸዲቅ ክህነት ሽንጎ መዋቅር ማሻሻያ አንዱ አስፈላጊነቱን ይህ ነው ብለዋል “ ኤጲስ ቆጶስ ለሽማግሌ ሸንጎና ለሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንቶች ተጨማሪ ሃላፊነትን መስጠት አለባቸው ይህም ኤጲስ ቆጶሱና አማካሪዎቹ ዋናው ሃላፊነታቸው ላይ ያተኩራሉ ያም ሃላፊነታቸው በወጣት ሴቶችና ወጣት ወንድ የአሮናዊ የክህነት ስልጣን ተሸካሚዎችን ማነጽ ነው፡፡ (“እዩ! ንጉሳዊውን ወታደርሊያሆና, ግንቦት 2018 እኤአ, 59). መልአክትም ይረዳሉ፡፡ አሮናዊ የክህነት ተሸካሚዎች የመላእክትን አግልግሎት ቆልፍ ተሸካሚዎች ናቸው ( ትምህርትና ቃልኪዳን 13፡1 ይመልከቱ እንዲሁም ዴል ጂ ራንላንድ እና ሩት ሊይበርት ራንላንድ የመልከጻዲቅ ክህነት (2018እኤአ) 26 ይመልከቱ ሽማግሌ ጀፍሪ አር ሆላንድ እንዲህ ብለዋል “(አገልጋይ መላእክትን) ብዙውን ጊዜ አይታዩም አንዳንዴም ይታያሉ ታዩም አልታዩም ግን ሁሌም ቅርብ ናቸው አንዳንዴ የሚሰጣቸው ትእዛዝ በጣም ግዙፍና ለአለም ሁላ ጠቃሚ ነው፡፡ አንዳንዴም መልእክታቸው ግላዊ ናቸው፡፡ በተደጋጋሚ የመልአክት ጠቀሜታ ማስጠንቀቂያን ለመስጠት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ግን ያጽናናሉ፣ ምህረት የተሞላበትን እገዛ ለማድረግ፣ በአስቸጋሪ ጊዜም ምሪትን ለመስጠት ነው፡፡” (“አገልጋይ መላዕክት,” ሊያሆና, ህዳር 2008 እኤአ, 29). የዚህ አይነት እርዳታን ስትሹ “ጠይቁ የሰጣችኋል”(ዮሃንስ 16፡24)፡፡

  7. ራስል ኤም ኔልሰን, “የመክፈቻ ንግግር,” ሊያሆና ህዳር. 2018 እኤአ, 7–8።

  8. የአሌክሳንድሬ ዱማስ ሶስቱ ነፍጠኞች ይመልከቱ

  9. መመሪያ መጽሃፍ 2፣ 8.1.2 ይመልከቱ።

  10. ዮሀንስ 1፥40-42 ይመልከቱ።

  11. ዮሀንስ 1፥43-46 ይመልከቱ።

  12. 3 ኔፊ 28:23

  13. “የመጽሃፈ ሞርሞን ሃይል” (ለአዳዲስ የሚስዮን ፕሬዝዳንቶች ሴሚናር 27 ሰኔ 2017 እኤአ) በዲ ቶድ ክርስቶፈርስን ይመልከቱ

  14. ቱሶ ሞሌፌ, ቴለር, የወንድማማች ቡድን, 22.

  15. ኦራቲሌ ሞሎሳንክዋ, ቴለር, የወንድማማች ቡድን, 31-32.

  16. ሉካስ ራክዌላ፣ ሞቹዲ ፣ ቦትስዋና፡፡

  17. ማርክና ሺርሊ ቴይለር አይዳሆ አሜሪካን

  18. ሲልቨስተር ጁኒየር ክጎሲማንግ፣ ሞቹዲ ፣ ቦትስዋና፡፡

  19. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20:46-47, 53,54 ይመልከቱ።

  20. የግል ምልልስ፣ ላታናንግ አንድሬ ሴባኮ፣ የወንድሞች ቡድን ማጣቀሻ፡

  21. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 6፥32

  22. ካትሌጎ ማኞሌ በ “የወንድማማቾች ቡድን 2ተኛ ትውልድ” (ያልታተመ ስብስብ) 21.

አትም