2010–2019 (እ.አ.አ)
መልካም እረኛ፣ የእግዚያብሄር በግ
የሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


መልካም እረኛ፣ የእግዚያብሄር በግ

ኢየሱስ ክርስቶስ በጎቹን በድምጹ እና በስም ይጠራል፡፡ ይፈልገናል ይሰበስበናል፡፡ እንዴት በፍቅር ማገልገል እንደሚቻል ያስተምራል፡፡

የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች እንቅልፍ አልወስድ ብሏችሁ እና እንደ መፍትሄ ምናባዊ በጎችን ለመቁጠር ሞክራችሁ ታውቃላችሁ? ጸጉራም በግ አጥሩን ሲዘል እናንተ ትቆጥራላችሁ -1, 2, 3, … 245, 246, … 657, 658 …1

እንደእኔ፣በጎችን መቁጠር እንቅልፍ እንዲወስደኝ አያደርገኝም፡፡ አንዱን ወይ አጣዋለሁ ወይ ይጠፋብኛል ብዬ ስለምሰጋ እንቅልፍ ሳይወስደኝ ይቀራል፡፡

ለንግስና ከበቃው እረኛ ልጅ ጋር እንዲህ እናውጃለን—

«እግዚያብሄር እረኛዬ ነው አንዳች አይጎድልብኝም ፡»

«በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል በእረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል

«ነፍሴንም ይመልሳታል፡፡»2

ምስል
መልካሙ እረኛ መስተዋቱን አቀለመው፡፡

በዚህ የትንሳኤ ወቅት የእግዚያብሄር በግም የሆነውን መልካሙን እረኛ እናስታውሰዋለን፡፡ ከሁሉም መለኮታዊ ማዕረጎቹ አንዳቸውም ይበልጥ ልብ የሚነካ እና ገላጭ አይደሉም፡፡ አዳኙ እራሱን እንደ መልካም እረኛ እንዲሁም በትንቢታዊ ምስክርነቱ እንደ እግዚያብሄር በግ ብሎ ከመጥቀሱ በመነሳት ብዙ እንማራለን፡፡ እነዚህ ሚናዎችና ውከላዎች እጅጉን ተሟሟይ ናቸው፡፡እያንዳንዱን ውድ በግ ከእረኛው በተሻለ ሁኔታ ማን ይታደጋቸዋል? ከእግዚያብሄር በግስ በተሻለ ማን እረኛችን ሊሆን ይችላል?

እግዚያብሄር አንድያ ልጁን እስከመስጠት ድረስ አለምን እንዲሁ ወዷል ፣ የእግዚያብሄርም አንድያ ልጅ ለአባቱ በመታዘዝ ህይወቱን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡3 “መልካሙ እረኛ እኔ ነኝ መልካም እረኛ ህይወቱን ስለበጎቹ አሳልፎ ይሰጣል፡፡“ ሲል ኢየሱስ ይመሰክራል፡፡4 ኢየሱስ ህይወቱን አሳልፎ ሊሰጥ ስልጣን አለው ደግሞም ሊያነሳት ስልጣን አለው፡፡5 ከአባቱ ጋር በመሆን አዳኛችን እንደ መልካም እረኛችንም እንደ እግዚያብሄር በግም በተለየ ሁኔታ ይባርከናል፡፡፡፡

እንደ መልካም እረኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጎቹን በድምጹ እና በስሙ ይጠራል፡፡ ይፈልገናል ይሰበስበናል፡፡ እንዴት በፍቅር ማገልገል እንደሚቻል ያስተምራል፡፡ በድምጹ እና በስሙ ከሚጠራን ጀምረን እነዚህን ሶስት ጭብጦች እንመልከት፡፡

በመጀመሪያ መልካሙ እረኛችን «በጎቹን በስማቸው ይጠራቸዋል … ድምጹን ያውቃሉ”6 እናም በክርስቶስ ስም በሆነው በስሙ ይጠራችኋል፤.”7 ኢየሱስን በትክክለኛ ምክንያት ለመከተል ስንመርጥ መልካምን የማድረግ፣ እግዚያብሄርን የመውደድ እና የማገልገል ተነሳሽነት ይመጣል ፡፡ 8 ስናጠና ፣ ስናሰላስል እና ስንጸልይ በየወቅቱ የቅዱስ ቁርባን እና የቤተመቅደስ ቃልኪዳናትን ስናድስ እንዲሁም ሁሉንም ወደ ወንጌሉና ወደ ስርዐቶቹ እንዲመጡ ስንጋብዝ ድምጹን እየሰማን ነው፡፡

በኛ ዘመን ፕሬዚደንት ራሰል ኤም.ኔልሰን ዳግም የተመለሰችውን ቤተክርስቲያን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰጣት —የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በሚለው ስም እንድንጠራት መክሮናል፡፡ 9 ጌታም እንዲህ ብሏል «ስለዚህ፣ ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ፣ በስሜ አድርጉት፤ ስለዚህ ቤተክርስቲያኗን በስሜ ጥሯት፤ እናም ወደ አብም በስሜ ፀልዩ እርሱም ለእኔም ሲል ቤተክርስቲያኗን ይባርካታል።”10 በአለም ዙሪያ በልባችንና በቤታችን ወደ አብ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጣራለን፡፡ ቤትን ያማከለ፣በቤተክርስቲያን የታገዘ አምልኮ ፣ የወንጌል ጥናት እና ሁሉን አቀፍ የቤተሰብ ገቢሮች ለመሳሰሉት የደግነት በረከቶች አመስጋኞች ነን፡፡

ሁለተኛ መልካሙ እረኛችን ይፈልገናል ፤ እንዲሁም ወደራሱ በረት ይሰበስበናል፡፡ እንዲህ ሲል ጠየቀ “መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?”11

አዳኛችን ለአንዱ እና ለዘጠና ዘጠኙ አብዛኛውን ጊዜ በተመሳሳይ ጊዜ ይደርስላቸዋል፡፡ ስናገለግል የጠፉትን እየፈለግንም እንኳ የጸኑትን እና ያልጠፉትን ዘጠና ዘጠኙን እውቅና እንሰጣለን፡፡ ጌታችን ይፈልገናል እንዲሁም “ከተበተንባቸው ቦታዎች” 12”ከአራቱም የምድር ማዕዘናት ነጻ ያወጣናል፡፡”13 በቅዱስ ቃልኪዳኑ እና የሃጥያት ክፍያ በሆነው ደሙ ይሰበስበናል፡፡.14

አዳኛችን ለአዲስ ኪዳን ደቀመዛሙርቱ “ከዚህ በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ ” ሲል ነገሯቸዋል፡፡.”15 በአሜሪካዎች፣ የተነሳው ጌታ ለሌሂ የቃልኪዳን ልጆች “እናንተ በጎቼ ናችሁ፡፡” ሲል መስክሮላቸዋል፡፡16 እየሱስም ሌሎቹ በጎች ገና ድምጹን እንደሚሰሙ ተናግሮ ነበር፡፡17 መጽሀፈ ሞርሞን የኢየሱስ ክርስቶስን ድምጽ የሚመሰክር ሌላኛው ኪዳን መሆኑ እንዴት ያለ በረከት ነው!

ኢየሱስ ክርስቶስ ድምጹን የሚሰሙትን እና ትዕዛዛቱን የሚጠብቁትን ሁሉ እንድትቀበል ቤተክርስቲያኗን ጋብዟል18 የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት የውሃ ፣ የእሳት እና የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ያካትታል፡፡19 “እናም አሁን የእግዚአብሔር በግ፣ ቅዱስ ሆኖ፣ ፅድቅን ሁሉ ለመፈፀም በውሃ መጠመቅ ካስፈለገው፣ አቤቱ ቅዱስ ያልሆንነው፣ አዎን፣ እኛ በውሃ እንኳን መጠመቅ ምን ያህል ያስፈልገናል!“ ሲል ይጠይቃል ኔፊ20

ምስል
መጥምቁ ዮሀንስ ኢየሱስን ሲያጠምቅ

ዛሬ፣ ጌታችን ፣የምናደርገው እና እየሆንን ያለነው ማንነት ሌሎችን እንዲመጡና እንዲከተሉት የሚጋብዝ እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ ኑ ፍቅርን፣ ፈውስን፣ ግንኙነትን እና የእሱ የመሆንን ቃልኪዳን አግኙ በእግዚያብሄር ቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ የሚደረጉትን ሁሉንም የቤተሰባችሁን ትውልዶች መባረክ የሚችሉ የተቀደሱ የደህንነት ስርዐቶች ጨምሮ አግኙ በመሆኑም በመጋረጃው በሁለቱም በኩል ያለው እስራኤል ይሰሰበሰባል፡፡21

ሶስተኛ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ “እስራኤል እረኛ፣ ” 22 በእስራኤል እረኞች እንዴት በፍቅር እንደሚያገለግሉ በምሳሌ አሳይቷል፡፡ ጌታችን እንወደው እንደሆን ሲጠይቀን ለስምዖን ጴጥሮስ እንዳለው “በጎቼን መግብ …ሲል ይማጸናል፡፡ …በጎቼን መግብ።” በጎቼን መግብ።”23 እረኞቹ ጠቦቶቹን እና በጎችን በሚመግቡ ጊዜ እነዚያ በበረቱ ያሉት “እንደማይፈሩ ፣ እንደማይታወኩ የሚፈልጉትንም እንደማያጡ” ጌታ ቃል ገብቷል፡፡”24

መልካሙ እረኛችን በእስራኤል የምንገኝ እረኞች እንዳናንቀላፋ፣25 በጎቹን እንዳንበትን ወይም በጎቹ ከመስመር እንዲወጡ ምክንያት እንዳንሆንባቸው26 ለራሳችን ጥቅም የራሳችንን መንገድ እንዳንከተልም አስጠንቅቋል፡፡.27 የእግዚያብሄር የሆኑ እረኞች የሚያበረቱ ፣ የተሰበረውን የሚጠግኑ ፣ ከመንጋው የወጣውን መልሰው የሚያመጡ ፣ የጠፋውን የሚፈልጉ መሆን አለባቸው፡፡28

በተጨማሪም ጌታ “ለበጎቹ ግድ የማይሰጣቸውን”29 አገልጋይ እረኞች እና “ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ ነገርግን ውስጣቸው ነጣቂ ተኩላ ከሆኑ ሃሰተኛ ነቢያት እንድንጠበቅ አስጠንቅቋል፡፡”30

መልካሙ እረኛችን በአላማ እና በእምነት የግለሰብ የመምረጥ ነጻነታችንን ስንጠቀም ደስ ይለዋል፡፡ በእርሱ በረት ውስጥ ያሉ ት ለሃጥያት ክፍያ መስዋዕቱ በምስጋና ወደ አዳኝ ይመለከታሉ፡፡ እርሱን ለመከተል ቃልኪዳን የምንገባው ወጣ ገባ እያልን፣በጭፍን ወይም “እንደበግ” ሳይሆን እግዚያብሄርን እና ጎረቤታችንን በፍጹም ልባችን እና በፍጹም ሃሳባችን ለመውደድ በመፈለግ አንዳችን የአንዳችንን ሸክም በመሸከም እና አንዳችን ስለሌላው ደስታ በመደሰት ነው፡፡ ክርስቶስ ፍቃዱን ለአባቱ በፍቃዱ አሳልፎ እንደሰጠ እኛም ስሙን በክብር በላያችን እንወስዳለን፡፡ የእርሱን የማሰባሰብ እና ሁሉንምልጆቹን የማገልገልን ስራ በደስታ ለመቀላቀል እንሻለን፡፡

ወንድሞችና እህቶች እየሱስ ክርስቶስ ነቀፋ የሌለበት እረኛችን ነው፡፡ ስለ በጎቹ ሕይወቱን አሳልፎ ስለሰጠ እና አሁን በክብር ከሙታን ስለተነሳ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ፍጹም በግ ነው፡፡31

የእግዚያብሄር የመስዋእት በግ ከመጀመሪያውም ጀምሮ ወካይ ጥላ ነበረው፡፡ መልአኩም አዳም ያቀረበው መስዋዕት “ንስሃ እንድንገባ እና በልጁ ስም ለዘላለም ወደ እግዚያብሄር እንድንጣራ የሚጋብዘን የአብ አንድያ ልጅ መስዋእት አምሳያ ነው” ብሎ ነገረው፡፡”32

ለምድር አህዛብ ሁሉ የቃልኪዳን በረከቶችን ያቋቋመው አባታችን አብርሃም አንድያ ልጅን መሰዋት ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል ለማወቅ የሚያስችል ልምድ ወስዷል፡፡

“ይስሃቅም አባቱን አብርሃምን “አባቴ ሆይ“ አለው፡፡ አብርሃምም “እነሆኝ ልጄ“አለው፡፡ እርሱም “እሳትና እንጨቱ ይሄው ፤ ነገር ግን የሚቃጠለው መስዋእት የት አለ...? ብሎ ጠየቀ፡፡

““አብርሃምም ልጄ ሆይ ለሚቃጠል መስዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚያብሄር እራሱ ያዘጋጃል አለው፡፡”33

ሃዋርያትና ነቢያት ቀድሞ የተዘጋጀውን የእግዚያብሄር በግ ተልዕኮ አስቀድመው አይተው ተደስተዋል፡፡ ዮሃንስ ከጥንቱ አለም እና ኔፊ ከአዲሱ አለም “ስለእግዚያብሄር በግ“ መስክረዋል፤”34 “አዎ ፤ የዘላለም አባት ልጅም ስለሆነው፣ … የአለሙ አዳኝ ስለሆነው”35

”አቢናዲ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ መስዋዕት መሰከረ-”እኛ ሁላችንም እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እናም ጌታ የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።”36 አልማ ታላቁንና የመጨረሻውን የእግዚያብሄር ልጅ መስዋዕት “ከሌሎች ከሁሉም ይበልጥ አስፈላጊው አንድ ነገር“ ሲል ጠርቶታል፡፡ አልማ “በእግዚያብሄር በግ ላይ እምነት ይኑራችሁ“ ፣ “ኑ ፤ አትፍሩ፡፡“ ሲል ያበረታታል ፡፡37

አንድ ውድ ጓደኛዬ ስለ እየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ውድ ምስክርነቷን እንዴት እንዳገኘች አካፍላለች፡፡ በኛ የተፈጸመ ሃጥያት ብቻ ሁልጊዜ ታላቅ ቅጣት እንደሚያስከትል ስታምን ነው የደገችው፡፡ መለኮታዊ ይቅርባይነት ስለሚቻልበት ሁኔታ ግንዛቤ እንዲኖራት እግዚያብሄርን ለመነችው፡፡ ንስሃ የሚገቡትን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ይቅር ሊላቸው እንደሚችል ፣ይቅርታ እንዴት ፍትህን እንደሚያመጣ ለማወቅ ጸለየች፡፡

አንድ ቀን ጸሎቷ የመንፈሳዊ ለውጥ ተመክሮ ባገኘችበት ሁኔታ ተመለሰላት፡፡ አንድ ተስፋ የቆረጠ ወጣት የተሰረቁ ሁለት እሽግ ምግብ ተሸክሞ እየሮጠ ከአንድ ግሮሰሪ መጋዘን ወጣ፡፡ ግርግር ወዳለበት መንገድ ሮጠ ፤የመጋዘኑ ሃላፊም ተከታተለው እና ያዘው ከዚያም ይጮህበትና ይጣላው ጀመር፡፡ በፍርሃት ውስጥ በነበረው ወጣት ሰው ላይ ሌባ ነው ብላ ከመፍረድ ይልቅ ጓደኛዬ ሳይታሰብ ለእሱ ጥልቅ በሆነ የርህራሄ ስሜት ተሞልታ ራሷን አገኘችው፡፡ ያለምንም ፍራቻና ስለ ራሷ ድህንነት ሳትሰጋ፣ በቀጥታ ወደሚጣሉት ሁለት ሰዎች ተራመደች፡፡ እራሷንም እንዲህ ስትል አገኘችው “የምግቡን ሂሳብ እኔ እከፍላለሁ እባክህን ይሂድ ተወው እኔም ለምግቡ እንድከፍል ፍቀድልኝ”

በመንፈስ አነሰሽነት እና ተሰምቷት በማያውቅ ፍቅር ጓደኛዬ እንዲህ አለች፡፡“ላደርግ የፈለኩት ነገር ቢኖር ወጣቱን ሰው መርዳትና ማዳን ነበር፡፡“ ጓደኛዬ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም የሃጥያት ክፍያ መስዋዕቱን መረዳት እንደጀመረች ተናገረች—እንዴትና ለምን እየሱስ ክርስቶስ በንጹህና ምሉእ ፍቅሩ የእርሷ አዳኝ እና ቤዛዋ ለመሆን በፍቃደኝነት መስዋዕት እንደሚሆንላት እናም እሷም ለምን እንዲሆናት እንደፈለገች38

እንዲህ ብለን ብንዘምር አይደንቅም፡፡

እዩ መልካሙ እረኛ እየፈለገ ነዉ

የጠፋውን በግ እየፈለገ

ሲያመጣቸው በደስታ

ታላቅ ክፍያ ተከፍሎባቸው እየዳኑ39

አዳኛችን እንደእግዚያብሄር በግነቱ መቼ ብቸኝነት እንደሚሰማን.፣ እንደምንዳከም ፣በነገሮች እርግጠኛ መሆን እንደሚሳነን ወይም እንደምንሰጋ ያውቃል፡፡ ኔፊ የእግዚያብሄር በግ ሃይል “ በበጉ ቤተክርስቲያን ቅዱሳንና በጌታ የቃልኪዳን ህዝቦች ላይ ሲወርድ “ በራእይ ተመልክቷል፡፡ ምንም እንኳ በምደር ገጽ ሁሉ የተበተኑ ቢሆኑ ፤ ፅድቅንና የእግዚአብሔርን ኃይል በታላቅ ክብር የታጠቁ ነበሩ፡፡”40

ይህ የተስፋና የምቾት ቃልኪዳን የኛንም ዘመን ይጨምራል፡፡

በቤተሰባችሁ፣በትምህርት ቤታችሁ፣በስራ ቦታችሁ ወይም በአካባቢያችሁ ብቸኛ የቤተክርስቲያኗ አባል ናችሁ? አንዳንድ ጊዜ ቅርንጫፋችሁ ትንሽ የሆነ ወይም የተነጠለ እንደሆነ ይሰማችኋል? ምናልባት ያልተለመደ ቋንቋ ወይም ልማድ ወዳለበት አዲስ ቦታ ተዛውራችኋል? ምናልባት የህይወት ሁኔታዎቻችሁ ተለዋውጠዋል፤ይሆናሉ ብላችሁ ከማታስቧቸው ነገሮች ጋር ተጋፍጣችኋል? በኢሳይያስ ቃላት አማካኝነት አዳኛችን ማረጋገጫን ሰጥቶናል ፣ ማንም ሆንን ማን፣ ምንም አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ብንሆን “መንጋውን እንደእረኛ ያሰማራል፣ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፣ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል” ፡፡41

ምስል
መልካሙ እረኛ በጎቹን ሲያሰባስብ

ወንድሞችና እህቶች መልካሙ እረኛችን በድምጹ እና በስሙ ይጠራናል፡፡ ይፈልገናል ፤ ይሰበስበናል አንዲሁም ወደ ህዝቡ ይመጣል፡፡ በህያው ነብዩ እና በእኛ አማካኝነት ሁሉም ዳግም በተመለሰው ወንጌል ምልዐት እና በቃልኪዳኑ መንገድ ሰላምን ፣ አላማን ፣ ፈውስን እና ደስታን እንዲያገኙ ይጋብዛል፡፡ የእስራኤል እረኞች በእርሱ ፍቅር እንዲያገለግሉ ምሳሌ ሆኖ ያስተምራል፡፡

እንደ እግዚያብሄር በግ መለኮታዊ ተልዕኮው ቀድሞ የተዘጋጀ ነበር ፤ ሃዋርያትና ነቢያትም በተልእኮው ሃሴትን አድርገዋል፡፡ ህልቆመሳፍርት የሌለው እና ዘላለማዊ የሃጥያት ክፍያው የደስታ ዕቅዱ እና የፍጥረት ዓላማ እምብርት ነው፡፡ እንደሚራራልን ማረጋገጫ ሰጥቶናል፡፡

ውድ ወንድሞችና እህቶች “ የእግዚያብሄርና የበጉ ትሁት ተከታዮች ለመሆን“ 42 ምናልባት አንድ ቀን ስማችን በበጉ የህይወት መዝገብ ላይ እንዲጻፍ፣43 የበጉን መዝሙር ለመዘመር44 ወደ በጉ ማእድ ለመጋበዝ ፍላጎታችን ይሁን፡፡45

እንደ እረኛ እና እንደ በግ እንዲህ ሲል ይጣራል- “ወደ ቤዛችሁ ወደ ታላቁ እና እውነተኛ እረኛችሁ ትክክለኛ እውቀት…” እንደገና ኑ፡፡46 ”በጸጋው በክርስቶስንጹህ ልንሆን እንደምንችል ‘’ ቃል ገብቷል፡፡.47

በዚህ የትንሳኤ ወቅት እናመሰግነዋለን

“በጉ የተወደደ ነው!” እያልን48

“ሆሳእና ለእግዚያብሄር እና ለበጉ !“49

ሰለፍጹም መልካም እረኛችን ፍጹም የእግዚያብሄር በግምስክርነቴን እሰጣለሁ ። በስማችን ይጠራናል ፣ በስሙ— ያውም በተቀደሰው የእየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም —አሜን፡፡

አትም