2010–2019 (እ.አ.አ)
ለጌታ መመለስ መዘጋጀት
የሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


2:3

ለጌታ መመለስ መዘጋጀት

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቅዱሳኖች ለጌታ ዳግም ምፅአት አስፈላጊ ዝግጅቶችን ለሟሟላት ተለይቶ የተፈቀደለት እና ስልጣን የተሰጠው ነው፡፡

በሁለት ሳምነት ዉስጥ ፋሲካን እናከብራለን፡፡ ትንሳኤው የእየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊነት እና የእግዚብሔር አባትን እውነታ ያረጋግጣል፡፡ ሀሳባችን ወደ አዳኙ ይዞራል እናም “የሱን ተዛማጅ የሌለውን ህይወት እና ማለቂያ የሌለውን የሱን ታላቅነት የሚክስ መስዋትነት ፀጋን እናሰላስላለን፡፡”1 እንዲሁም “እንደ ነገስታት ንጉስ እና... እንደ ጌቶች ጌታ የሚነግስበትን ” የሱን የሚጠበቅ መመለስ እናስባለን ብዪ ተስፋ አረጋለዉ፡፡2

ከተወሰነ ጊዜ በፊት በቡዌኖስ ኤሪስ አርጀንቲና ከብዙ ከተለያዩ የሀይማኖት መሪዎች ጋር ስብሰባ ውስጥ ተሳትፌ ነበር፡፡ ለሰዎች ያላቸዉ ፍቅር የሀሰት አልነበረም፡፡ ሀሳባቸው ስቃይን በማቅለል እና ሰዎች ከጭቆናና ድህነት ላይ እንዲነሱ በመርዳት ላይ ነበር። የዚህን ቤተክርስቲያን ብዙ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ፤ ስብሰባው ውስጥ ካሉት ብዙ የእምነት ቡድኖች ጋር በትብብር የሚሰሩ ስራዎችም ጭምር ፤ ላይ አተኮርኩ፡፡ ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባሎች ፤ ይህን አይነት የክርስቶሳዊ አገልግሎት እንዲቻል በሚያደርግ ቸርነታቸው ጥልቅ ምስጋና ተሰማኝ፡፡

በዛች አፍታ መንፈስ ቅዱስ ሁለት ነገር አረጋገጠልኝ ፡፡ አንደኛ ፤ ለጊዜያዊ ፍላጎቶች የአገልግሎት ስራ ወሳኝ እንደሆነ እና ሊቀጥል እንደሚገባው፡ ሁለተኛው ያልተጠበቀ ግን ደግሞ ሀይለኛ እና ግልፅ ነበር፡፡ ይህ ነበር፡ ከራስ ወዳድነት ከነፃ አገልግሎት ፤ ባሻገር አለምን ለጌታ እየሱስ ክርስቶሰ ዳግም ምፅአት ማዘጋጀት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

እሱ ሲመጣ ጭቆና እና ኢ-ፍትሀዊነት መጥፋት ብቻ ሳይሆን ያቆማል፡፡

ተኩላውም ደግሞ ከበጉ ጋር ይኖራል ፣ አቦሸማኔው ደግሞ ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል ፣ ጥጃውም የአንበሳ ደቦልም ፣ ፍሪዳውም በአንድነት ይሆናሉ ፤ ታናሽ ልጅም ይመራቸዋል።

በተቀደሰው ተራራዬ ላይ ሁሉ አይጎዱም ፣ አይጠፉምም ፤ ውሃ ባህርን እንደሚሸፍን ሁሉ ምድር በጌታ እውቀትም ትሞላለችና።3

ድህነት እና ስቃይ መቀነስ ብቻ ሳይሆን ይጠፋሉ፡፡

“ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፡ ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሙም ፡ፀሀይ ትኩሳትም ሁሉ ከቶ አይወርድባቸውም፡፡

“በዙፋኑ መካካል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና ፡ወደ ህይወትም ምንጭ ይመራቸዋልና፡ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፡፡4

የሞት ህመም እና ጣር እንኳን ይወገዳሉ፡፡

በዚያም ቀን ህጻን አርጅቶ ካልሆነ በቀር አይሞትም ፤ እናም ህይወቱም የዛፏን እድሜ ያህል ይሆናል፤

እና ሲሞትም አያንቀላፋም፣ ያም በምድር ውስጥ አይቆይም፣ ነገር ግን በቅጽበት ዓይን ይለወጣል፣ እና ይነጠቃል፣ እና ማረፊያውም የከበረ ይሆናል።5

ስለዚህ አዎ ፤ ስቃይን እና ሀዘንን ለማቅለል አሁን የቻልነውን እናድርግ እናም ህመም እና ክፋት በአንድ ላይ ለሚያበቁበት ቀን ፣ ክርስቶስ እራሱ በምድር ላይ ሲነግስ ፤ እና ምድርም ታድሳ ገነታዊ ክብሯን ስትቀበል ፤ ለሚያስፈልጉት ዝግጅቶች ራሳችንን ይበልጥ በትጋት እንስጥ፡፡ 6 የቤዛነት እና የፍርድ ቀን ይሆናል፡፡ የአንጀሊካን ዱርሀም ጳጳስ ፤ ዶክተር. ኤን. ቲ. ራይት የክርስቶስን ቤዛነት ፣ ዳግም ምፅአት ፣ ፍርድ ፤ ኢ-ፍትሀዊነትን በማሸነፍ እና ሁሉንም በማስተካከል ውስጥ ያለውን አስፈላጊነት በደንብ ገልፆአል፡፡

እግዚአብሔር ምድር ፤ በትክክል በመረጠው ሰው የሚፈረድባትን ቀን ወስኗል እናም ይህን ደግሞ ይህን ሰው ከሞት በማስነሳት ማረጋገጫ ሰጥቶአል፡፡ ምድር የዘፈቀደ እንዳልሆነ ፤ የናዝሬቱ እየሱስ እውነታዎች ፣ በተለይ ስለሞት ትንሳኤው ፤ የማረጋገጫችን መሠረት ናቸው፡፡ መጨረሻው ፤ አሁን ፍትህን ስንሰራ ፤ መጨረሻ ላይ መውደቁ የማይቀርን ህንፃ ለመጠገን እየሞከርን ፣ወይም ለቆሻሻ መጣያ የሚገባን መኪና ለመጠገን እየሞከርን ፤ በጭለማ ውስጥ እያፏጨን የሚሆንበት ትርምስምስ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር እየሱስን ከሞት ያስነሳበት ምሳሌያዊ ኩነት ፤ የመጨረሻው ፍርድ ተጠቃሎ እንደ መጨረሻ ተስፋ ፍሬ በውስጡ የተያዘበት ነበር፡፡ እግዚአብሔር ልናስብ በምንችለው መጠን ፤ በጣም በሀይለኛ መልኩ ፣ የናዝሬቱ እየሱስ የእውነት መሲህ እንደሆነ አውጇል ፡፡ የሁሉንም የታሪክ ጭካኔዎች እና ኢ-ፍታዊነቶችን በገለፀ እና ባስቀመጠ ቦታ በመምጣት ፤ ይህን ቀውስ ፣ ጨለማ ፣ ጭካኔ ፣ ኢ-ፍትሀዊነት ፣ በውስጡ ለመሸከም እና ሀይሉን በማድከም በታላቁ የምፀት ታሪክ ውስጥ እየሱስ እራሱ በጭካኔና ኢ-ፍትሀዊ በሆነ ፍርድ ውስጥ አልፏል ፡፡ 7

ቅድም በገለፅኩት ቡኤኖስ ኤሪስ ስብሰባ ላይ መንፈስ ፤ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ለጌታ ዳግም ምጻት አስፈላጊውን ዝግጅቶች ለመፈጸም ተለይቶ ስልጣን እንደተሰጠውና እንደተወከለ ፣ ለዚህ አላማም እንደተመለሰ ፣ ግልጽ አደረገልኝ፡፡ ያሁኑን ዘመን ፤ እንደ ትንቢቱ “ሁሉንም ነገሮች በክርስቶስ በአንድ እድንሰበስብ” ፣ እግዚአብሔር ላዘጋጀው “የሙላት ጊዜ ዘመን” የተቀበሉ ሰዎች ሌላ ቦታ ልታገኙ ትችላላችሁ?8 እዚህ ለሁለቱም ለሚኖሩትም ለሞቱትም ለዛ ቀን ሊደረግ የሚያስፈልገውን ለማድረግ ፍላጎት ያለው ማህበረሰብ ካላገኛችሁ ፣ እዚህ ጌታን ለመቀበል ዝግጁ የሆኑ፤ የቃልኪዳን ሰዎችን ለመሰብሰብ እና ለማዘጋጀት ሰፊ ሰአትን እና ድጎማን ለመስጠት ዝግጁ የሆነ ተቋም ካላገኛችሁ ፤ የትም አታገኙትም፡፡

ለቤተክርስቲያኑ በ1831 እ.ኤ.አ ጌታ ሲናገር እንዲህ አወጀ፡

በምድርም ለሰው የእግዚአብሔር መንግስት ቁልፎችም ተሰጥተዋል ፣ እናም ከዚህም ወንጌሉ ፣ ወደ ምድር ዳርቻም ይንከባለላል፡፡

“በዚህ ኗሪዎችዋም እንዲቀበሉት፣ መንግስቱም በምድር ላይ እንዲሄድ፣ ጌታን ጥሩ፣ እናም የሰው ልጅ የክብሩን ብርሀን ለብሶ ከሰማይ በምድር ከተሰራችው የእግዚአብሔር መንግስት ጋር ለመገናኘት በሚገለጥበት ወደ ፊት ለሚመጡት ቀናትም ተዘጋጁ።9

ለዛ ቀን ለመዘጋጀት አሁን ምን ማድረግ እንችላለን? እንደ ህዝብ ራሳችንን ማዘጋጀት እንችላለን ፣ የጌታን የቃልኪዳን ህዝቦች መሰብሰብ እንችላለን ፣ እና ለአባቶቻችን ፤ ቅድመ አያቶቻችን የተገባውን የመዳን ቃልኪዳን ለመፈጸም መርዳት እንችላለን፡፡10 ይህ ሁሉ ጌታ ድጋሚ ከመመለሱ በፊት በተወሰነ ትልቅ ድግሪ መፈፀም አለበት፡፡

ለጌታ መመለስ ወሳኙ ፤ በምድር ላይ እሱን ሲመጣ ለመቀበል ዝግጁ የሆኑ ህዝቦች መኖር ነው፡፡ ምድርም ላይ የሚቀሩት ፣ እንዲሁም ከታናሹ ጀምሮ እስከታላቁ .... በጌታ እውቀትም ይሞላሉ ፣ እናም ዓይን ለዓይን ይተያያሉ ፣ እናም ድምፃቸውንም ያነሣሉ፥ እናም በአንድነትም ይህን አዲስ መዝሙር እንዲህ በማለት ይዘምራሉ፥ ጌታ መለሰ ፅዮንን...ብሎ ገልፆአል፡፡ ጌታ ሁሉንም ነገሮች በአንድ ጠቅልሏል። ጌታ ፅዮንን ከላይ መልሶ አምጥቷል። ጌታ ፅዮንንም ከታችም መልሶ አምጥቷል።11

በድሮ ጊዜ እግዚአብሔር የፅዮንን ፃድቅ ከተማ ለራሱ ወስዷታል፡፡12 በንፅፅርም በመጨረሻው ቀናቶች አዲስ ፅዮን ጌታን በመመለሻው ትቀበለዋለች፡፡13 ፅዮን ፤ በልባቸው ንፁህ የሆኑ፣ የአንድ ልብ እና የአንድ ሀሳብ ህዝቦች ፣ በመሃላቸው ያለምንም ደሀ በፅድቅ ውስጥ የሚኖሩ ነው፡፡14 ነቢዩ ዮሴፍ ስሚዝ “የፅዮንን ግንባታ እንደ ታላቅ አላማችን ልንይዘው ይገባል” ብሎ ገልፆአል፡፡15 ፅዮንን በቤቶቻችን ፣ በአጥቢያችን ፣ በቅርንጫፎቻችን ፣ እና በካስማዎቻችን ውስጥ በአንድነት ፣ በራስን መግዛት ፣ እና ልግስና እንገነባለን፡፡16

የፅዮን ግንባታ በተሸበሩ ጊዜዎች ውስጥ እንደሚከወን ማወቅ ይገባናል---“እነሆ፣ በቀል፣ የቁጣ ቀን፣ የንዳድ ቀን፣ የጥፋት ቀን፣ የለቅሶ ቀን፣ የሀዘን ቀን በምድር ነዋሪዎች ላይ በፍጥነት መጥቷል፤ እና እንደ አውሎ ንፋስም በምድር ፊት ሁሉ ይመጣል፣ ይላል ጌታ።”17 እና በካስማዎች ላይ አብሮ መሰብሰቡ ከአውሎ ነፋስ፣ እና ሳይቀላቀል በምድር ሁሉ ላይ ከሚፈሰው ቁጣም መጠበቂያ እና መሸሸጊያ ይሆናል ፡፡ 18

እናም ልክ እንደ በፊት ጊዜያት ለመፆም እናም ለመፀለይ፣ እናም እያንዳንዳቸው ለነፍሳቸው ደህንነት እርስ በርሳቸው እንዲነጋገሩ ዘንድ ሁል ጊዜ ይገናኛሉ(እንገናኛለን)። እናም ጌታ ኢየሱስን ለማስታወስ ዳቦውን እና ዉሀውን ልንካፈል፡፡19 ፕሬዘዳንት ረስል ኤም. ኔልሰን በባለፈው ጥቅምት አጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ እንደ አስረዱት የቤተክርስቲያኗ የረጅም ጊዜ አቋም ፤ አባሎች በጌታችን እየሱስ ክርስቶሰ እና ቤዛነቱ ላይ እምነታቸውን እንዲያሳድጉ ለማገዝ ፣ እነሱን ቃልኪዳንን በመግባት እና በመጠበቅ ውስጥ ለመርዳት ፣ እና ቤተሰባቸውን ለማጠንከርና ለማተም ነው፡፡20 በዚህ መሰረትም የቤተመቅደስ ቃልኪዳኖች ፣ የሰንበት ቀን ፣ በየቀኑ በቤት ውስጥ ፣ በቤት ላይ ማእከል ያደረገ ፣ በቤተክርስቲኑ በተቀነባበረ ስርአተ-ትምህርት ላይ በመደገፍ እና ፤ ወንጌሉን የመመገብ አስፈላጊነት ላይ አተኩሯል ፡፡ ስለ ጌታ ማወቅ እንፈልጋለን ፤ እናም ጌታን ማወቅ እንፈልጋለን፡፡21

ፅዮንን በመገንባት ውስጥ መሰረታዊው ጥረት ፤ የጌታን ለብዙ ጊዜ የተበተኑትን የቃልኪዳን ህዝቦች መሰብሰብ ነው፡፡ 22 በእስራኤል መሰብሰብ እና በአስሩ ነገዶች መመለስ እናምናለን፡፡23 ሁሉም ንስሀ የሚገቡ ፣ በክርስቶስ ላይ የሚያምኑ ፣ እና የሚጠመቁ ፣ የሱ የቃልኪዳን ህዝቦች ናቸው፡፡24 ጌታ እራሱ ከመመለሱ በፊት ፤ ወንጌሉ በሁሉም አለም25 “የእስራኤል ቤት የሆኑትን ህዝቡን እንዲመለሱ” ለማድረግ እንደሚሰበክ እናም 26፣ “ከዛም በኋላ መጨረሻው ይመጣል” ብሎ ተንብዪአል ፡፡27 የኤርምያስ ትንቢት እየተፈፀመ ነው፡፡

ስለዚህ እነሆ የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ምድር ያወጣ ህያው እግዚአብሔርን ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር፤

ነገር ግን የእስራኤልን ልጆች ከሰሜን ምድር ፣ ካሳደዳቸውም ምድር ሁሉ ፤ ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን ይኖራል ፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ፡፡ 28

ፕረዘዳንት ኔልሰን እስራኤልን መሰብሰብ ዛሬ በምድር ላይ እየተካሄዱ ካሉ በጣም አስፈላጊ ነገሮች ውስጥ አንዱ እንደሆነ በተደጋጋሚ አሳስቧል፡፡ ምንም ነገር በትልቅነት አይወዳደረውም፣ ምንም ነገር በአስፈላጊነቱ አይወዳደርም፣ ምንም ነገር በግርማዊነት አይወዳደረውም። ምርጫቹ ከሆነ፣... የዛ ትልቅ ክፍል መሆን ትችላላችሁ።29 የኋለኛው ቀን ቅዱሳኖች ሁልጊዜም የሚስዮን ሰዎች ናቸው፡፡ ከወንጌሉ መመለስ ጀምሮ ወደ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ለሚስዮን ጥሪ ምላሽ ሰተዋል ፤ አሁን ወደ አስር ሺህ የሚያህሉ እያገለገሉ ነው፡፡ እናም ሽማግሌ ክዊንተን ኤል. ኩክ አሁን እንዳስተማሩት፤ሁላችንምበቀላልና በተፈጥሮአዊ መንገዶች ፤ በፍቅር ፣ ሌሎችን ቤተክርስቲያን እንዲቀላቀሉን በመጋበዝ ፣ ቤታችንን እንዲጎበኙ የኛ ቡድን አካል እንዲሆኑ በመጋበዝ መሳተፍ እንችላለን፡፡ የመፅሀፈ ሞርሞን መታተም ፤ መሰብሰቡ እንደጀመረ ምልክት ነበር፡፡30 መፅሀፈ ሞርሞን እራሱ ፤ ለመሰብሰብ እና ለመለወጥ መሳሪያ ነው፡፡

ለዳግም ምፅአቱ ፤ ሌላ እንዲሁ አስፈላጊ የሆነ ነገር ለቅድመ አያቶቻችን መዳን ትልቅ ጥረት ነው፡፡ ጌታ ከዳግም ምፅአቱ በፊት ኤልያስን ለመላክ ቃል ገብቷል ፤ “የጌታ ታላቁና የሚያስፈራው ቀን”31፣ክህነቱን… ለመግለጥ”እና “ለአባቶች የተገባውን የተስፋ ቃል በልጆች ልብ ይተክላል፡፡”32 ቃል እንደተገባው ኤልያስ መቷል:: ቀኑ ሚያዝያ 3፣1836 ላይ ነበር ፤ ቦታው ደግሞ ኪርትላንድ ቤተ-መቅደስ ነበር፡፡ በዛች ቦታ ፣ በዛች ግዜ እሱ ቃል የተገባለትን ክህነት ፤ ለሞቱት ደህንነት እና ለባሎች ፣ ለሚስቶች ፣ እና ለቤተሰቦች በሁሉም የጊዜ ትውልድ ወስጥ አና እስከ ዘላለም የመሰብሰብ ቁልፍ በእርግጥም እሱ ሰጥቷል፡፡33 ያለዚህ የፍጥረት አላማ ይከሽፋል እና በዛ መልኩ፤ ምድር “ትረገማለች” ወይም “ትጠፋለች”::34

የሮም ጣልያን ቤተ-መቅደስ ምረቃን አስከትሎ በወጣቶች ስብሰባ ላይ ተሳታፊ የሆኑት፤ ወደ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች ፤ ለቅድመ-አያቶቻቸው ስም ያዘጋጁትን ካርድ ለፕሬዘዳንት ኔልሰን አሳዩ፡፡ ቤተ-መቅደሱ ልክ እንደተከፈተ ለነዚህ ቅድመ-አያቶቻቸው ፤ ቤተ-መቅደስ ገብተው የውክልና ጥምቀቶች ለመፈፀም ዝግጁ ነበሩ፡፡ ታላቅ አስደሳች ጊዜ ነበር ፤ ሆኖም ግን በፊት ላለፉት ትውልዶች ፅዮንን ለመመስረት የፈጣን ጥረት አንድ ምሳሌ ነው፡፡

ፅዮንን በመገንባት ውስጥ ትጉህ ለመሆን ስንጥር ፤ የጌታን ተመራጮችን በመሰብሰብ ውሰጥ አና ለሞቱት ቤዛነት ውስጥ ያለንን ድርሻ አካቶ ፤ ቆም ብለን ይህ የጌታ ስራ እንደሆነ እና እሱ እየሰራው እንደሆነ ማሰታወስ አለብን፡፡ እሱ የወይን እርሻው ጌታ ነው እና እኛ አገልጋዮቹ ነን፡፡ በወይን እርሻው ላይ በዚህ የመጨረሻ ሰአት እንድንሰራ ይጠይቀናል አናም እሱ ከእኛ ጋር ይሰራል፡፡35 ምንአልባት ከሱ ጋር እንድንሰራ ይፈቅድልናል ብል ይበልጥ ትክክል ይሆናል፡፡ ፓውሎስ እንዳለው “እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፡፡”36 እሱ ነው በዚህ ጊዜ የሱን ስራ እያፋጠነ ያለው፡፡37 የእኛን የምንቀበለውን ፍፁም ያልሆኑ ጥረቶች ፣ የኛን “ትንሽ ነገሮች” ስራ ላይ ስናውል ጌታ ታላቅ ነገሮችን ያመጣል ፡፡38

ይህ ትልቅ እና የመጨረሻው ዘመን ፤ ገነት በምድር ላይ ፤ በአዳኙ የተከበረ መመለስ ጊዜ ከላይኛው ፅዮን ጋር በመቀላቀል ፣ በቀስታ ወደ መጨረሻው ደረጃ እየተገነባ ነው፡፡ የእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አለምን ለዛ ቀን ለማዘጋጀት--- እያዘጋጀም ነው---ስልጣን ተሰቶታል፡፡ ስለዚህም በዚህ ፋሲካ የእውነት የእየሱስ ክርስቶስን ትንሳኤ እናም ትንሳኤው የሚወክለውን ነገሮች ሁሉ የእውነት እናክብር ፤ ሚወክለውም ፡ የእሱን በሰላም አንድ ሺህ አመታት ለመንገስ መመለስ ፣ ለሁሉም የጽድቅ ፍርድ እና ፍጹማዊ ፍትህን ፣ ማንኛውም በዚህ ምድር የኖረ አለሟች መሆንን ፣ እናም የዘላለም ህይወት ቃልኪዳንን ነው፡፡ የክርስቶስ ትንሳኤ ሁሉም መልካም እንደሚደረግ የመጨረሻው ማረጋገጫ ነው፡፡ ያንን ቀን ለማፋጠን ፅዮንን መገንባት ላይ እንሁን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።