2010–2019 (እ.አ.አ)
የክህነት የጨዋታ መጽሃፋችሁ
የሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


የክህነት የጨዋታ መጽሃፋችሁ

የክርስቶስ ደቀመዝሙር መሆናችሁን የምታረጋግጡበት የራሳችሁን የጨዋታ መጽሃፍ አዘጋጁ፡፡

ባለፈው ታህሳስ የተቀዳሚ ፐሬዚደንት “12 ተኛ አመታቸውን በሚይዙበት በአመቱ የጥር ወር መጀመሪያ የ 11 አመት ወንዶች የአሮናዊ ክህነት ቡድንን መቀላቀል እንደሚጀምሩ…“ የሚያስተዋወቅ መግለጫ ሰጥተዋል1

በውጤቱም በአመቱ የመጀመሪያ ክፍል እስከሚቀጥለው የልደት ቀናቸው በፕራይመሪ እንደሚቆዮ የገመቱ በጣም ጥቂት የተጨነቁ 11 አመት የሞላቸው ነበሩ ነገር ግን ዛሬ እንደ አዲስ ተሽዋሚ የቤተክርስቲኗ ዲያቆናት በየእሁዱ ቅዱስ ቁርበቀንን እያሳለፉ ነው፡፡

ማን ይሆን በለውጡ ይበልጥ የተደነቀው—ዲያቆናቱ ወይስ ወላጆቻቸው ከነዚህ ብዙዎቹ —ወደ 80,000 —የሚጠጉት አዳዲስ ዲያቆናት በዚህ ታላቅ የጉባኤ ማእከል ከኛ ጋር ናቸው ወይም በቴክኖሎጂ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ ወደ ታላቁ የክህነት ወንድማማችነት እንኳን ደህና መጣችሁ!

ይህ ለውጥ ይህንን ስብሰባ ታሪካዊ ያደርገዋል—በአጠቃላይ ጉባኤ የካህናት አጠቃላይ ስብሰባ ተሳትፈው ከሚያውቁ እጅግ ትልቁ የአሮናዊክህነት ተሸካሚዎች ቡድን ሳይሆን አየቀርም፡፡ ይህን ልዩ ዝግጅት በማስመልከት ማብራሪያዬ በአሮናዊ ክህነት ተሸካሚ ወጣት ወንዶች ላይ እንዲያተኩር አደርጋለሁ፡፡

ከስፖርት የተቀሰሙ ትምህርቶች

እንደ ተማሪነታችሁ ብዙዎቻችሁ ተሰጥኦዎቻችሁን ፣ፍላጎቶቻችሁን እና በትርፍ ጊዜያችሁ የምትሰሯቸውን ነገሮች ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ ተሳትፎዎች ስፖርትን ጨምሮ ከትምህርት ቤት ውጪ በሚካሄዱ ይሄውም በትምህርት ቤት ወይም በግል ጥናት፣ በቡድን እና በግሩፕ እያሳደጋችሁ ነው፡፡

እድሜ ልኬን በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የተዝናናሁ እንደመሆኔ የአትሌቲክ ችሎታዎቻቸውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ተሳትፎ የሚያሳድጉትን ሁልጊዜ አደንቃለሁ፡፡ ለማኛውም ሰው በትክክልም በማኛውም ነገር ጥሩ ለመሆን፣ ከተፈጥሯዊ ተሰጥኦ በተጨማሪ ግብረገብ፣ መስዋእትነት ፣ እና በሰአታት የማይገደብ ስልጠናና ልምምድን ይጠይቃል፡፡ እንዲህ ያሉ አትሌቶች አንዳንድ ጊዜ ከባድ ትችቶች ከአሰልጣኞቻቸው ይሰነዘርባቸዋል ስለዚህም አሁን የሚፈልጉትን ነገር ወደፊት ለሚፈልጉት ትልቅ ነገር ሲሉ ወደጎን ያደርጓቸዋል፡፡

እጅግ ላቅ ባለ ፕሮፌሽናል አትሌቲክስ ለከፍተኛ ደረጃ ስኬት የበቁ የቤተክርስቲያን አባላት እና የክህነት ስልጣን ተሸካሚዎች እናውቃለን፡፡ አጅግ ብዙ ጥሩ ምሳሌዎች አሉ ነገር ግን ከጊዜ አንጻር ጥቂቶቹን ብቻ ነው መዘርዘር የምንችለው፡፡ ከነዚህ አትሌቶች አንዳንዶቹን ልታውቁ ትችሉ ይሆናል፤በቤዝቦል—ጀረሚ ጉትሪ እና ብራይስ ሃርፐር፣በቅርጫት ኳስ ጃባሪ ፓርከር እና ጂመር ፍሬዴት፤በእግር ኳስ —ታይሰም ሂል፣ዳኒኤል ሶሬንሰን እና ኤሪክ ዌድል፤በራግቢ—ዊልያም ሆፖቴ፤በሶከር ሪካርዶ ሮሃስ፡፡ እያንዳንዳቸው ለስፖርቱ ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

በስፖርቱ እጅግ በላቀ ደረጃ የተሳካላቸው ቢሆኑም ፣እነዚህ ወንድሞች ፍጹም አትሌት ወይም ፍጹም ሰው እንዳልሆኑ ለመቀበል የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ፡፡ በሚሳተፉበት ስፖርት ምርጥ እንዲሆኑ ጠንክረው ይሰራሉ፡፡—እና ወንጌሉን ይኖራሉ፡፡ ቢወድቁ ይነሳሉ እና ለመስተካከል ይጥራሉ፡፡

የጨዋታውን ህግ መጽሃፍ ተከተሉ

በቡድን ስፖርቶች ጨዋታዎች በተወሰኑ የግጥሚያ ሁኔታዎች ይዘጋጁና በጨዋታ ህግ መጽሃፍ ይሰባሰባሉ፡፡ አትሌቶች ሚናቸውንና ለየጨዋታው በግል የሚሰጣቸውን ሃላፊነት ይማራሉ፡፡ ውጤታማ ተጫዋቾች የጨዋታውን ህግ መጽሃፍ በጥልቀት ያጠኑታል፤ ጨዋታ ሲኖርም የት እንደሚሄዱ ምን እንደሚያደርጉ በደመነፍስ ያህል በትክክል ያውቃሉ፡፡

ምስል
የጨዋታ መጽሃፍ ያለው አሰልጣኝ፡፡

ፎቶግራፍ በ ዴቭ ካዉፕ /ሬውተርስ/stock.adobe.com

ምስል
የመጫወቻ መጽሃፍ

በተመሳሳይ መንገድ አኛ የክህነት ስልጣን ተሸካሚዎችም ቡድን አለን—ሸንጎ—አና የጨዋታ ህግ መጽሃፍ—ቅዱሳን መጻህፍት እና የዚህ ዘመን ነቢያት ቃላት፡፡

የቡድናችሁን አባላት ታጠናክራችኋላችሁ?

የጨዋታውን ህግ መጽሃፋችሁን ምን ያህል አጥንታችሁታል?

የተሰጣችህን የስራ ድርሻ ሙሉ ለሙሉ ትረዳላችሁ?

ምስል
የክህነት ሸንጎ

ተቃውሞን መጋፈጥ

ምሳሌውን ይበልጥ ሰፋ አድርጎ ለማየት ያህል፣ምርጥ አሰልጣኞች የራሳቸውን እና የተቃራኒ ቡድኑን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ያውቃሉ፡፡ ሰፋ ያለ የማሸነፍ እድል የሚፈጥርላቸውን የጨዋታ እቅድ ያዘጋጃሉ፡፡ እናንተስ?

ለምን አይነት ፈተናዎች ይበልጥ ተጋላጭ እንደሆናችሁ ታውቃላችሁ እንዲሁም ጠላት እንዴት ሊያጠፋችህ እና ሊያሳዝናችሁ እንደሚሞክር መተንበይ ትችላላችሁ፡፡ ተቃውሞ ሲገጥማችሁ እንዴት ምላሽ እንደምትሰጡ ታውቁ ዘንድ የራሳችሁን የጨዋታ እቅድ እና የጨዋታ መጽሃፍ አዘጋጅታችኋል?

የተለያዩ የስነምግባር ፈተናዎች ሲያጋጥሟችሁ—ከጓደኞቻችሁ ጋር ሆናችሁም ሆነ ኮምፒዩተሮቻችሁ ላይ ሆናችሁ—የጨዋታ እቅዳችሁን ታውቃላችሁ፡፡ አንድ ጓደኛችሁ አልኮል እንድትጠጡ ወይም አደንዛዥ እጽ እንድትጠቀሙ ቢያግባባችሁ ጨዋታውን ታውቁታላችችሁ፡፡ ልምምድ አድርጋችኋል ስለዚህም እንዴት ቀድማችሁ ምላሽ እንደምትሰጡ ታውቃላችሁ፡፡

ከጨዋታ እቅድ፣የጨዋታ ህግ እና ሚናችሁን ለመወጣት ካላችሁ ጠንካራ ውሳኔ ጋር ፈተና በናንተ ላይ አነስተኛ ተጽዕኖ ያለው ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ እንዴት ምላሽ እንደምትሰጡ እና ምን እንደምታደርጉ አሰቀድማችሁ ወስናችኋል፡፡ ፈተና በገጠማችሁ ቁጥርም ለጉዳዩ እንዳዲስ ውሳኔ መስጠት አያስፈልጋችሁም፡፡

ከአስራ ሁለቱ አንዱ ይህንን መርህ የሚያብራራ ታሪክ አካፍሏል፡፡ እንደ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ካህን ከጓደኞቹ ጋር እየተዝናና ነበር፡፡ ምግብ ቀማመሰው አብቅተው በመኪናቸው እየተዘዋወሩ ሳለ አንዳቸው ወደ አንድ ፊልም ቤት እንዲሄዱ ሃሳብ አቀረበ፡፡ ችግሩ ሊያየው የማይገባ ፊልም መሆኑን አውቋል፡፡ ምንም እንኳ በሁኔታው በዚያ ቅጽበት ግፊትና ጭንቀት ቢሰማውም ለዚህ የተዘጋጀ እቅድ ነበረው፡፡ ቀጥታ ከክህነት የጨዋታ መጽሃፉ የወጣ አንድ ገጽ ነበር፡፡

በጥልቁ ከተነፈሰና ድፍረቱን ካሰባሰበ በኋላ “ያንን ፊልም ለማየት ፍላጎት የለኝም እኔን በሬ ላይ አውርዱኝ“ ሲል አወረዱት፡፡ ወደድል የሚያመራ ቀላል ጨዋታ! ከዓመታት በኋላ በዚያኛው ምሽት ከእዚያ ከነበሩት ጓደኞቹ አንዱ እንዴት ይህ ምሳሌ በሕይወቱ ውስጥ ተመሳሳይ ሁኔታዎችን በድፍረት ለመጋፈጥ ትልቅ ጥንካሬ እንዳጎናጸፈው ገልጿል.፡፡

ከጨዋታ መጽሃፉ ገጾች

የተወሰኑ ወንድሞችን በጨዋታ መጽሃፋችሁ ውስጥ ልታካትቷቸው ስለምትችሏቸው ጨዋታዎች ጠይቄያቸው ነበር፡፡ የሚቀጥሉት አንዳንድ ጥቆማዎቻቸው ናቸው፥

  • ለታላቅ ብርሃን እና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት በየቀኑ ጸልዩ፡፡

  • የወላጆችዎን ፣ወጣት ወንዶችን እና የሸንጎ መሪዎችንና የኤጲስ ቆጶሳትን ትምህርቶች በጥንቃቄ አዳምጡ፡፡

  • ወሲባዊ ሥዕሎችን እና የብልግና ማህበራዊ ድረገጾች ይዘትን አስወግዱ፡፡

  • ለእግዚአብሔር የገባችሁትን ቃልኪዳኖች አስታውሱእንዲሁም ልትጠብቋቸው ትጉ ፡፡

  • ከቅዱሳን መጻህፍት አጥኑ ስለ ታላላቅ ነብያት ታሪኮች መልካም ባሕርያቸውን ምሰሉ፡፡

  • የሰማይ አባት ልጆችን በማገልገል ባርኩአቸው፡፡

  • ልትሆኑ የምትፈልጉትን ሰው መሆን ትችሉ ዘንድ የሚረዲችሁ ጥሩ ጓደኞች ይኑሯችሁ፡፡

  • በ FamilySearch መተግበሪያ አጠቃቀም ብቃት ያላችሁ ባለሙያዎች ሁኑ እንዲሁም የራሳችሁን የቤተሰብ ታሪክ መርምሩ፡፡

  • ከክፉ ተጽዕኖዎች መራቅ የሚችሉባቸው የማፈግፈጊያ ቦታዎችን አቅዱ፡፡.

  • የክህነት ሸንጎ አባላትን ውደዱ እንዲሁም እንዲጠነክሩ እርዷቸው፡፡

ቀደም ብለን ፎቶግራፋቸውን ስናይ ከነበሩት አትሌቶች ጋር አውርቼ ነበር ራሳቸውን በፕሮፌሽናል አትሌትነት በሚሰሩት ስራ ፕሮፌሽናል አትሌትነት አይገልፁም ይልቁንም እንደ አፍቃሪ የሰማይ አባት ልጆች እና የእግዚአብሔርን ክህነት ተሸካሚ መሆኑ አስደናቂ ሆኖ አገኘሁት፡፡

አሁን እነሱን ሐሳብ እናዳምጥ፡፡

  • ጂመር ፌሬዴት እዚህ ላይ እንደ ዲያቆን ከረባት ለማሰር በመማር ላይ እያለ “ በወንጌል እውነተኝነት ላይ ባለኝ እምነት እና እውቀት አጥብቄ መደገፍን ተምሪያለሁ፡፡ ይህ ብቁ የክህነት ስልጣን ተሸካሚ እና ከሁሉም በላይ መልካም ምሳሌ ወደመሆን መርቶኛል” ብሏል፡፡

    ምስል
    ጂመር ፍሬዲት እንደ ዲያቆን
  • ብራይስ ሃርፐር እንደ ባል ሲጽፍ “ዝና፣ሃብት እና የኤም ቪ ፒ ሽልማት ያስደስቱኛል ብዬ አስቤ ነበር፡፡ አንድ የጎደለ ነገር ነበር፡፡ ስለዚህም ተዘጋጀሁና ወደ ቤተመቅደስ አቀናሁ፡፡ አሁን እኔ ወደሰማያዊ አባቴ ለመመለስ እና በአለም እጅግ አስደሳች የሆነውን ዘላለማዊ ቤተሰብ ለማግኘት በመንገድ ላይ እገኛለሁ፡፡

    ምስል
    ብርያስ ሃርፐር ከባለቤቱ ጋር
  • ዳንኤል ሶረንሴን እዚህ ጋ እንደ ሚሲዮናዊ “ ጥሩ የጨዋታ መጽሃፍ የያንዳንዱን የቡድን አባላት ችሎታና ጥንካሬ የሚጠቀም ነው፡፡“ ይላል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል አስተምህሮቶች ባጠናሁኝ እና በተለማመድኩኝ ቁጥር ጥንካሬዎቼን እንዴት በክህነት ውስጥ መጠቀም እንደምችል አውቃለሁ፡፡

    ምስል
    ዳንኤል ሶረንሰን እንደ ሚስዮናዊ
  • ጀረሚ ጉትሬ እዚህ ላይ እንደ ሚሲዮን ፕሬዚደንት እያገለገለ ያለ እንዲህ ሲለ አካፍሏል “ እንደ 12 አለት ዲያቆን.. መንፈስ ለእኔ “ይህ ህይወት እግዚአብሄርን ለመገናኘት እራሳችንን የምናዘጋጅበት ጊዜ” እንደሆነ ሲመሰክርልኝ ተሰማኝ 2 የጨዋታው መመሪያ እምነት በእግዚአብሄር ከተግባር ጋር እና ንስሃ በ አዳኙ ነው.... የመጫወቻው መጽሃፍ ደግሞ የሚገኘው በቅዱሳን መጽሃፍት እና በህያዋን ነብያት ነዉ፡፡”

    ምስል
    ጀረሚ ጉትራይ እንደ ሚስዮን ፕሬዚደንት
  • ጃባሪ ፓርከር እዚህ ጋር እንደ አዲስ ሽማግሌ ሆኖ ሲሾም “የመጠመቅ ውሳኔ አድርጌ ባይሆን ኖሮ ምን አይነት ሰው ይወጣኝ እንደሆነ መገመት አልችልም“ ይላል፡፡ በህይወቴ በየቀኑ የሚመራኝ እግዚያብሄር ስላለኝ በጣም አመስጋኝ ነኝ፡፡”

    ምስል
    ጃባር ፓርከር ክህነትን ቅበላ
  • ሪካርዶ ሮጃስ አሁን በዚህ ሰአት እንደ ቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት በማግልገል ላይ ያለ እንዲህ አለ “በእግዚአብሄር ክህነት አማካኝነት የእርሱን ስራ ማገዝ እንችላለን፡፡ እኛ የተጠራነው እውነትን በመጠበቅ3“እንድንጸናና እንዳንደነግጥ ነው፡፡” ይህን ማድረጉ በሜዳም ላይ ሆነ እንደ ክህነት አመራር ውጤታማ እንዲሆን ረድቶታል፡፡

    ምስል
    ሪካርዶ ሮሃስ እንደ ቅርንጫፍ ፕሬዚደንት
  • ታይሰን ሂል እዚህ ላይ እንደ ሚሽነሪ የእየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለህይወቱ እንደ ጨዋታ መጽሃፍ እንዳገለገለው ይሰማዋል፡፡ “ በእግዚያብሄር ወንጌል በማመን እና በሱ ውስጥ ያለኝን ሚና ለመወጣት የአቅሜን መጣሬ በህይወት ታላቅ ሰላም እና ደስታ አምጥቶልኛል ይህም እግዚያብሄር ጥረቶቼን እንደሚረዳ በማወቄ ነው፡፡

    ምስል
    ታይሶም ሂል እንደ ሚስዮናዊ
  • ዊልያም ሆፖት በልጁ አራት ትውልድ አባል የልጅነት በረከት ስርዐት ላይ ወንጌል እንዴት እንደረዳው ሲናገር ” የተቃዋሚን ስትራቴጂዎች ለመለየት እና የሚወረወሩ የእሳት ፍላጻዎችን ለመቋቋም እና ሌሎችን የተሸለ ለማገልገል መንፈሳዊ ብቃት ይሰጣል፡፡”

    ምስል
    ዊሊያም ሆፖአት በህጻን ቡራኬ ወቅት

እናንተስ? እንደ እግዚያብሄር ልጅነታችሁ ፣እንደ ቅዱስ ክህነቱ ተሸካሚነታችሁ ከፍተኛውን እና ቅዱሱን ማንነታችሁን እውቅና ትሰጡታላችሁ? ይህንን ዘላለማዊ ማንነታችሁን በአእምሯችሁ ይዛችሁ በፈተና እና በመከራ ጊዜ የሚመራችሁ የጨዋታ እና የክህነት እቅዳችሁን አዘጋጁ፡፡ የማጥቃትንም የመከላከልንም ስልቶች ግምት ውስጥ አስገቡ፡፡

የመከላከል ስልቶች ምስክርነታችንን ለማጠናከር እንዲሁም በቀጥተኛው እና በጠባቧ መንገድ ለመቆየት የሚያስችሉ መፍትሄዎችን ይሰጣሉ፡፡ የዚህ ምሳሌዎች እንደ የዘወትር ጸሎት፣የቅዱሳን ጽሁፎች ጥናት፣ቤተክርስቲያን መሄድ፣አስራት መክፈል እና በ ለወጣቶች ጥንካሬ ፓምፍሌት ውስጥ የሚገኙትን ምክሮች መከተልን ያካትታሉ፡፡

የመከላከል ስልቶች ፈተናዎችን እንዴት እንደምንጋፈጥ ቀድሞ ማቀድን ያካትታል፡፡ መስፈርቶቻችሁን ለድርድር እንድታቀርቡስትፈተኑ ምን ማድረግ እንደሚገባችሁ ቀድማችሁ ታውቃላችሁ፡፡

ለዚያ የጨዋታ መጽሃፍ ያስፈልጋችኋል፡፡

ዛሬ የመጸለይ ስሜት አይሰማችሁም? አስቀድማችሁ በጨዋታ እቅዱ ያዘጋጃችሁትን ጨዋታ ለመጫወት ሰአቱ አሁን ነው ፡፡

ምስክርነታችሁ ሲቀዘቅዝ ይሰማችኋል? ለዚያም የምትጫወቱት ጨዋታ አላችሁ፡፡ ምን ማድረግ እንደሚገባችሁ ታውቃላችሁ፡፡

በእግዚያብሄር አይን አእጀጅገግ በብቀቃተት የያለላቸችሀሁ ኮከቦች፡፡

እናንተ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ክህነት ተሸካሚዎች ናችሁ፡፡ የብረት ዘንጉን አጥብቃችሁ ለመያዝ የምታሳዩት ቁርጠኝነት መጀመሪያ ስትፈጠሩ እንድትሆኑ ወደተፈለገው ዘላለማዊ ፍጡርነታችሁ እንድትለወጡ ያስችላችኋል፡፡

እግዚአብሄር ያውቃችኋል እናም ያፈቅራችኋል። እሱ ይባርካችኋል እንዲሁም እርምጃችሁን ይመራችኋል፡፡

ምንም ልዩ አይደለሁም ብለህ ታስብ ይሆናል ታዋቂ ኮከብ እንዳልሆንክ፡፡ ነገር ግን ያ እውነት አየይደለም። ”የአለም ደካማ ነገሮች ወደፊትም ይወጣሉ ብርቱን እና ጠንካራውን ይሰብራሉ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳን 1፧19)4ብሎ እግዚያብሄር እንዳወጀ አታውቁም?

ስለዚህ የደካማነት ስሜት ይሰማችኋል? አላስፈላጊነትስ? እንኳን ደስ አላችሁ! ሰልፉን ተቀላቅላችኋል፡፡

ጠቃሚ እንዳልሆናችሁ ይሰማችኋል? የበታችነትስ? እግዚአብሄር የሚፈልገውን ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡

ምስል
ዳዊት እና ጎልያድን

ከአስፈሪ ባላጋራው ጎሊያድ ጋር ለመግጠም ወደ ጦርሜዳ ከገባው ዳዊት የተሻለ ምን ምሳሌ አለ፡፡ በጌታ ላይ ታመኑ፣ ዳዊት እራሱን ብቻ ሳይሆን የእስራኤልን ሰራዊት አድኗል፡፡5 ከጌታ ጎን ለመሆን ድፍረትህን ስታሰባስብ እርሱ ከአንተ ጋር እንደሚሆን እወቅ:: “እግዚያብሄር ከኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?”6

እንደነበሩን የማናውቃቸው ጥንካሬዎችና ችሎታዎች እንድናገኝ ሊረዳንና በሮች ሊከፍትልን ይችላል፡፡7

የታመኑ አሰልጣኞቻችሁን አድምጡ—እንደ ወላጆቻችሁ፣ኤጲስ ቆጶሳት እና ወጣት ወንዶች መሪዎች ያሉትን የጨዋታውን መጽሃፍ ተማሩት፡፡ ቅዱሳን መጻህፍትን አንብቡ። የዘመናችን ነቢያትን ቃላት አጥኑ፡፡. የክርስቶስ ደቀመዝሙር መሆናችሁን የምታረጋግጡበት የራሳችሁን የጨዋታ እቅድን አዘጋጁ፡፡

መንፈሳችሁን ለማጠንከር አና የጠላትን ወጥመዶች ለማራቅ የምትተገብሯቸውን ጨዋታዎች ቀድማችሁ እወቁ ፡፡

ይህን ብታደርጉ እግዚያብሄር ያለ ጥርጥር ይጠቀምባችኋል፡፡

አሁን ራሳቸውን ከወንጌል ነጥለው የሚባዝኑ አንዳንዶች አሉ፡፡ አንዳንዶች በደጋፊ መቀመጫ ላይ ተቀምጠው ጨዋታውን ከሩቅ ሊያዩ ይችላሉ፡፡ አሰልጣኙ ወደ ጨዋታው ሊያስገባቸው ቢሞክርም አንዳንዶች የተቀያሪ ተጫዋቾች አግዳሚ ላይ መቀመጥን ይመርጣሉ፡፡እንድታድኑ፣ እንድታግዙ፣ እና እንደ ቡድን አባልነታቸው እንድትወዷቸው እጋብዛችኋለው፡፡

ሌሎች ወደጨዋታው መግባት ይፈልጋሉ—እናም ያደርጉታል፡፡ ከሁሉም በላይ አሰፈላጊው ነገር ምን ያህል ተሰጥኦ አላቸው የሚለው ሳይሆን ራሳቸውን ወደሜዳው ለማስገባት ምንያህል ፍቃደኞች ናቸው የሚለው ነው፡፡ “እግዚአብሔርን ለማገልገል ፈቃድ ካላችሁ ወደስራው ተጠርታችኋል” የሚለውን ቅዱስ ጽሁፍ ስለሚያውቁ ቁጥራቸው እስከሚጠራ አይጠብቁም፡፡8

ራሳችሁን ወደ ሰልፉ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡

ይህን የምታደርጉት የክህነት የጨዋታ መጽሃፋችሁን በማጥናትና በተግባር ላይ በማዋል ነው፡፡።

በሂደቱ ልትደናቀፉ እና ልትወድቁ ትችላላችሁ—ምናልባትም ብዙ ብዙ ጊዜ፡፡ ፍጹም አይደላችሁም፤ መውደቅ ባህርያችሁን የሚያስተካክልላችሁ እና በርህራሄ እንድታገለግሉ የሚያስችላችሁ የመብቃቱ ሂደት አካል ነው፡፡ ጌታ እና ዘላለማዊ የሆነው የሃጥያት ክፍያው ህተቶቻችንን ልባዊ በሆነ ንስሃ የምናሸንፍበት መንገድ አመቻችቷል፡፡

ታላላቅ አትሌቶች የአንድ ትንሽ የጨዋታቸውን ክፍል እንከንየለሽ ለማድረግ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰአታትን ያጠፋሉ፡፡ እንደ ክህነት ተሸካሚነታችሁ እንዲህ ያለ አእምሯዊ ዝግጁነት ያስፈልጋችኋል፡፡ ከወደቃችሁ፣ ንስሃ ግቡና ተማሩበት፡፡ በሚቀጥለዉ ጊዜ የተሻላችሁ እንድትሆኑ ተለማመዱ፡፡ በመጨረሻም የራሳችሁ ውሳኔ ነው፡፡ ከመጫወቻው መጽሃፍ ትማራላችሁን? ፡፡

በጌታ እንድትመኩ አበረታታችኋለሁ፡፡ የእግዚያብሄርን እቃ ጦር ሁሉ ልበሱ 9እና ወደ ጨዋታው ግቡ፡፡

ስፖርት በረቀቀ እና በከፍተኛ ደረጃ የሚጫወቱ ብዙ የሉም ነገርግን፣ ነገር ግን ደቀመዝሙር ለመሆን ብዙዎች ክርስቶስን ይከተላሉ፡፡

ያ በርግጥ የዚህ ህይወት ተልዕኳችሁ ነው—የጌታን መንገድ ለመማር፣ወደ ደቀመዝሙርነት መንገድ ለመግባት፣ እና በእግዚያብሄር እቅድ ውስጥ ለመኖር የተቻለንን ለማድረግ፡፡ ወደ እርሱ ስትዞሩ እግዚያብሄር ይደግፋችኋል እንዲሁም ይባርካችኋል፡፡ እናንተ በእርሱ አይን ሁሌም ኮኮቦች ስለሆናችሁ ይሄንን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

ለቅዱስ ክህነቱ ብቁ ሆናችሁ ክህነቱን እንድትሸከሙና እንድትኖሩ እንዲሁም የተቀደሰ ሚናችሁን ለመወጣት በየቀኑ እንድትጥሩ ቁርጥ ውሳኔ እንድታደርጉ እጸልያለሁ፡፡ ያን ማድረግ ትችሉ ዘንድ በችሎታ እና በፍላጎት እባርካችኋለሁ ፡፡ ስለያዛችሁት የክህነት ሃይል፣ስለ ህያው ነቢያት እና ስለእየሱስ ክርሰቶስ እና ስለአዳኝነቱና ቤዛነቱ ሚናው ምስክርነቴን አክላለሁ በእየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

አትም