2010–2019 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ
የሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


2:3

የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ

የአዳኛችን የሃጥያት ክፍያ ወሰን የለሽ ብቻ ሳይሆን ለግለሰብ ደራሽ ነው፡፡

በዓመቱ በዚህ ወቅት የአዳኛችንን የሃጥያት ዋጋ ክፍያ በጥልቀት እናስባለን እናም ሃሴት እናደርጋለን፡፡ በርግጥም ታላቅ ሰማያዊ ፡አእምሮን የሚያሰፋ፣ ይህ ዓለም ወይም ህዋ ከቶ የማያውቀው ጥልቅ ፍቅር ያለው ትምህርት ነው፡፡ ለሕይወታችን አላማ እና ተስፋ የሚሰጠን ነገር ነው፡፡

ምንድን ነው ታዲያ የኢየሱስ ክርስቶስ የሀጥያት ክፍያ? በአንድ እይታ፤ ይህ በጌተሰማኔ በአታክልቱ ስፍራ የተጀመረ፤ በመስቀል ላይ የቀጠለ፤ እናም በአዳኛችን ከመቃብር ትንሳኤ ማድረግ የተፈጸመ ተከታታይነት ያለው መለኮታዊ ክስተት ነው:: ይሄ ለእኛ ካለው ልንረዳው ከማንችለው ፍቅር የተነሳሳ ነበር፡፡ ሃጥያት የሌለበት፤ በሞት እና በሁሉም ክፍሎች ላይ ወሰን የለሽ ኃይል ያለው ፤ ለመላው ሃጥያታችን እና በሽታዎቻችን ለመሰቃየት ገደብ የለሽ ብቃት ያለው ፤ በርግጥም ከሁሉ በታች የወረደ ፍጡር ይፈለጋል፡፡ 1 ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ ተልዕኮ ነበር ፤ ይህ የእሱ የሃጥያት ክፍያ ነበር ፡፡

ከዚያስ አላማው ምንድን ነበር ? ለእኛ ወደ እግዚአብሔር መገኛ መመለስ እንችል ዘንድ ፤ የበለጠ እሱን እንድንመስል፤ እናም ሙሉ የሆነ ደሰታ እንዲኖረን ነበር፡፡ ይህ የሆነው አራት መሰናክሎችን በማለፍ ነው፡፡

  1. ስጋዊ ሞትን

  2. በአዳም እና በእኛ ሃጥያቶች አማካኝነት የመጣ መንፈሳዊ ሞትን፡፡

  3. ስቃያችንን እና መከራችንን

  4. ደካማነታችንን እና ጉድለታችንን

ነገር ግን እንዴት ነው አዳኛችን የፍትህን ህግ ሳያፈርስ ይህን መፈጸም የሚችለው?

ከአውሮፕላን ነጻ ውድቀት

ለቅጽበት አስቡት አንድ ሰው አስደሳች የአየር ላይ ዝላይን በማሰብ የችኮላ ውሳኔን ይወስንና ወዲያው ከአንድ ትንሸ አውሮፕላን ላይ በፍጥነት ይዘላል፡፡ እንዲህ ካደረገ በኋላ፤ የተግባሩን አይረቤነት ወዲያው ይገነዘባል፡፡ በደህና መሬት ላይ ማረፍ ፈለገ፤ ነገር ግን አንድ እንቅፋት አለ—የመሬት ስበት ህግ፡፡ በድንጋጤ ፡ ለመብረር ተስፋ በማድረግ እጆቹን በፍጥነት አንቀሳቀሳቸው፤ ነገር ግን ምንም አልጠቀመውም፡፡ ሰውነቱን ለማንሳፈፍ ወይም ቀለል በማድረግ በዝግታ ለመውርድ አመቻቸ።ነገር ግን የመሬት ስበት ህግ የማይቀየር እና ምህረት የለሽ ሆነ ፡፡ ከመሰረታዊው የተፈጥሮ ሕግ ጋር ለመሟገት ሞከረ ፤ ‹‹ይሄ ስህተት ነበር ፡፡ዳግመኛ አላደርገውም ፡፡ ›› ነገር ግን ልመናው የማይሰሙ ጆሮዎች ላይ ወደቁ፡፡ የመሬት ስበት ህግ ስለ ርህራሄ አያውቅም ፤ ማንንም አይለይም፡፡ መልካም እድሉ ሆነና፤ ሰውየው በድንገት ጀርባው ላይ የሆነ ነገር ይሰማዋል፡፡ በአውሮፕላን ውስጥ የነበረው ጓደኛው፤ ያን የሞኝነት ቅጽበት ተረድቶ፤ ከመዝለሉ በፊት ፓራሹቱን አስቀምጦበት ነበር፡፡ የመገንጠያውን ገመድ አግኝቶ ሳበው፡፡ እፎይ አለ ፤ ተንሳፍፎ በደህና መሬት ደረሰ፡፡ ‹‹የመሬት ስበት ህግ ተጥሷል፣ ወይስ ያ ፓራሾት በዛ ህግ ውስጥ በደህና ለማረፍ ለማመቻቸት ሰርቷል?›› ብለን ልንጠይቅ እንችላለን።

በፓራሹት በደህና ለማረፍ መውረድ

ሃጥያት ስንሰራ ከአውሮፕላን እንደዘለለው ሞኝ ሰውዬ ነን፡፡ በእራሳችን ምንም ብናደርግ፤ መከስከስ ብቻ ነው የሚጠብቀን፡፡ ለፍትህ ህግ ተገዥዎች ነን፤ ልክ እንደ የመሬት ስበት ህግ፤ የማይወላውል እና ይቅር የማይል ነው ፡፡ መዳን ምንችለው አዳኛችን በሃጥያት ክፍያው አማካኝነት በመሃሪነት በሰጠን መንፈሳዊ ፓራሹት አማካኝነት ብቻ ነው:: በኢየሱስ ክርሰቶስ እምነት ካለን እና ንስሃ ከገባን( ማለትም እኛ የመገንጠያ ገመዱን በመሳብ ሀላፊነታችንን ስንወጣ) የአዳኛችን የጥበቃ ሀይል እኛን ወክሎ ይከፈታል፤ እናም መንፈሳዊ ጉዳት ሳይደርስብን እናርፋልን፡፡

ይህ እውን የሚሆንበት ብቸኛው ምክንያት፤ አዳኛችን እነዚህን አራት የኛን መንፈሳዊ እድገት የሚገድቡ እንቅፋቶች ስላሸነፈ ነው፡፡

1.ሞት በከበረ ትንሳኤው ሞትን ድል አድርጎአል፡፡ ሃዋርያው ጳውሎስ “ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።” ብሎ አስተምሯል፡፡”2

2.ሃጥያት፡- አዳኛችን ንስሃ ለሚገቡ ሁሉ ሀጥያታቸውን እና ጥፋተኝነታቸውን አሸንፎላቸዋል፡፡ የማንጻት ሃይሉ እጅግ ጥልቅና ሰፊ በመሆኑ ኢሳያስ “ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፡፡”ብሎ ቃል ገብቷል፡፡ 3

አንድአንዴ ራሳቸውን ይቅር ማለት ከከበዳቸው ፣ የአዳኙን የማዳን ሀይል ፤ ትክክል ባልሆነ የዋህነት የገደቡ ጥሩ ቅዱሳኖች ጋር እገናኛለሁ፡፡ ባለማወቅ ወሰን የለሹን የሃጥያት ክፍያ እንዴትም ቢሆን ለሃጥያታቸው እና ለድክመታቸው መድረስ እንደማይችል በማሰብ ገደብ ያስቀምጡለታል፡፡ ነገር ግን ዘላለማዊው የሀጥያት ክፍያ ሁሉንም ሀጥያታቸውን እና ድካማቸውን ጠቅልሎ ይከበዋል፤ እንዲሁም በሌሎች የሚድርስብንን ስቃይ እና በደል ያካትታል፡፡

ትሩማን ጂ. ማድሰን ይህን አጽናኝ ምልከታ ሰቷል

‹‹ከእናንተ አንዳንዶቻችሁ በመታለል ብዙ ርቀት እንደሄዳችሁ አምናችኋል ...በሃጥያት ተመርዛችሁ በድጋሚ መሆን የምትችሉትን የማትሆኑ የሚመስላችሁ አሁን ስሙኝ፡-

ምስክርነቴ ይህ ነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን እና ከመጠቀ እውቀቱ ፤ ከማይደርስብት አልፋችሁ ልትጠፉ አትችሉም፡፡ ምስክርነቴ ይህ ነው ንስሃን ለማነሳሳት የሚያበቃ ትንሽ ብልጭታ እስካለ ድረስ ፡፡ እርሱ በዛ ይገኛል፡፡ ወደ እናንተ ደረጃ ብቻ አይደለም የወረደው፤ ከሁሉ ነገር በታች ወረደ ፤ ‹‹እርሱም በሁሉም ነገሮች ውስጥና በሁሉም ነገሮች በኩል በመሆን፤ የእውነት ብርሃን ይሆን ዘንድ፡፡ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥6.] 4

የኢየሱስ ክርስቶስን የሀጥያት ክፍያን መረዳት አስፈላጊነቱን እና ዘላለማዊ ጥቅሙን የበለጠ መረዳት አንዱ ምክንያት ሌሎችን እና እራሳችንን ይቅር ለማለት ከፍ ያለ ፍላጎት መኖር ነው፡፡

ምንም እንኳን በክርስቶስ የማንጻት ኃይል ብናምንም፤ አልፎ አልፎ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ ‹‹እንዴት ነው ሃጥያቴን ይቅር እንደተባለኩኝ የማቀው?›› መንፈሱ ከተሰማን፤ ይቅር የመባላችን ምስክርነት ይሆናል ፤ ወይም የመንፃት ሂደቱ በስራ ላይ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ፕሬዝዳንት ሔነሪ ቢ. አይሪንግ ‹‹ የመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ ከተስማችሁ፤ የሃጥያት ዋጋ ክፍያው በህይወታችሁ እየስራ ስለመሆኑ እንደማስረጃ ውሰዱት››ብለው አስተምረዋል፡፡ 5

የመጨረሻ መንገድ

አንዳንዶች ‹‹ነገር ግን ይቅር ከተባልኩ ለምንድን ነው አሁንም ጥፋተኝነት የሚስማኝ?›› ብለው ይጠይቃሉ:: ምን አልባት የፀፀታችን ትውስታ በእግዚአብሔር ምህረት ማስጠንቀቂያ ነው፤ መንፈሳዊው ‹‹ቁም የሚለው ምልክት›› ለትንሽ ግዜ እንኳን ቢሆንም በተጨማሪ ፈተና ስንጋፈጥ ማሳያ ይሆናል ፤ “በእዛ መንገድ ተመልሰህ አትሂድ፤ ምን አይነት ስቃይ እንደሚያመጣ ታውቃለህ ››ብሎ ይጮሀል፡፡ በዚህ መልኩ፤ እንደ ቅጣት ሳይሆን እንደ ጠባቂ ያገለግለናል፡፡

ስለዚህ ሃጥያታችንን እያስታውስን ከፀፀት ግን ነፃ መሆን እንችለለን?

ንስሀ ከገባ ከአመታት በኋላም፤ አልማ ሀጥያቱን ያሰታውስ ነበር፡፡ እናም አሁን፣ እነሆ፣ ይህንን ባሰብኩ ጊዜ፣ ህመሜን ደግሞ ለማስታወስ አልቻልኩም፤ አዎን፣ ከእንግዲህም ወዲያ በኃጢአቴ ትውስታ አልተሰቃየሁም። 6

እንዴት ነው ሃጥያቱን እያስታወሰ ስቃይ ወይም ፀፀት ግን የማይሰማው? ምክንያቱም ንስሀ ስንገባ ‹‹ከእግዚአብሔር እንወለዳለን›› 7 ቅዱሳን መፅሐፍት እንደሚሉት በክርስቶስ ‹‹አዲስ ፍጡር›› እንሆናለን ።8 አሁን በፍፁም ታማኝነት ‹‹እኔ አነዛን ያለፉትን ሀጥያቶች የፈፀምኩ ወንድ ወይም ሴት አያደለሁም፤ እኔ የታደስኩ እና የተለወጥኩ ሰው ነኝ›› ማለት እንችላለን፡፡

ስቃዮች እና መከራዎች አልማ ስለ ክርሰቶስ ሲተነብይ ‹‹እናም በመከራና በሁሉም ዓይነት ህመምና ፈተናዎች በመሰቃየት ፤ ይሄዳል፤” ለምን? “ይህን ማድረጉን እናስታውሳለን በስጋ አንጀቱ በምህረት ይሞላ ዘንድ፣ ድካማችንን በራሱ ላይ አደረገ እናም በስጋ ህዝቡን ከድካሙ እንዴት እንደሚረዳ ያውቅ ዘንድ ይህንን ያደርጋል፡፡” 9

ይሄን እንዴት ነው የፈጸመው? አንዳንዴ ስቃይን ያስወግድልናል፤ አንዳንዴ እንድንፀና ሀይልን ይሰጠናል፤ እናም አንዳንዴ ነገሮች ግዜያዊ እንደሆኑ በይበልጥ እንድንረዳ ዘላለማዊ እይታን ይሰጠናል፡፡ ዮሴፍ ስሚዝ ለሁለት ወራት ያክል በሊበርቲ እስር ቤት ከማቀቀ በኋላ፤ በስተመጨረሻ “እግዚአብሔር ሆይ የት ነህ?” ብሎ ጩሆ አለቀሰ፡፡ 10 ፈጣን እፎይታን ከመስጠት ይልቅ፤ እግዚአብሔር‹‹ ልጄ ፤ ለነብስህ ሰላም ይኑርህ ፤ ጭንቀትህ እና ስቃይህ ለጥቂት ጊዜ ቢሆን ነው፤ ከዚያም በመልካም ይህን ብትፀና፤ እግዚአብሔር ወደ ላይ ዘላለማዊ ክብር ይሰጥሀል›› ብሎ መልሶለታል፡፡ 11

አሁን ጆሴፍ ፤ይህ ሁሉ መራራ ተሞክሮ በዘላለማዊ ሚዛን እንደ ነጥብ እንደሆነ ተረዳ፡፡ በዚህ ከፍ ባለ እይታ፣ ከዛች የእስር ቤት ክፍል ሆኖ ለቅዱሳኖቹ ይህን ፃፈላቸው “ስለዚህ፣ ውድ ወንድሞች፣ በሀይላችን ያሉትን ነገሮች ሁሉ በደስታ እናድርግ፤ ከዚያም በእርግጠኝነት እግዚአብሔር የሚያደርገውን ማዳን ለማየት እንቁም እና የክንዱንም መገለጥ እንጠባበቅ።” 12 በአዳኛችን የሃጥያት ክፍያ ምክንያት፤ ሁላችንም ለፈተናዎቻችን ትርጉም፤ ለእረፍታችን ተስፋ የሚሰጠንን ዘላለማዊ እይታን ማግኘት እንችላለን፡፡

4.ድክመቶች እና ጉድለቶች በሱ ሃጥያት ክፍያ ምክንያንት ፤ አዳኙ የመቻል ሃይል አንዳንድ ጊዜ ጸጋ ተብሎ ሚጠራው አለው ፤ ይህም ድክመታችንን እና ጉድለታችንን እንድናሸንፍ ይረዳናል ስለዚህ እሱን ለመምሰል በምናደርገው ጥረት ያግዘናል፡፡ 13

ሞሮኒ እንዲህ አስትማረ “አዎን ወደ ክርስቶስ ኑ፣ እናም በእርሱ ፍጹማን ሁኑ::.. በጸጋውም በክርስቶስ ፍጹም ትሆናላችሁ፡፡”14 እንድንጠራ፤ እንዲሁም ፍፁም እንድንሆን የሚያስችሉን ሀይሎች ቢያንስ ሁለት መንገዶች ወይም ዘዴዎች አሉት፡፡

መጀመሪያ፤ የመዳኛ ስርዓቶች ቅዱሳን መጻህፍት እንደሚነግሩን ፣ “በስርዓቶች... የአምላክነት ሀይል ይገለጻል።” 15 አንድአንዴ ስርዓቶችን እንደ ከፍታ ማግኛ የማረጋገጫ ዝርዝር አድርገን እናስብ ይሆናል፤ እውነታው ግን ይበልጥ ክርስቶስን እንድንመስል የሚረዳንን አምላካዊ ሀይልን ለእያንዳንዳችን የሚከፍት ነው፡፡ ለምሳሌ፥

  • ስንጠመቅ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ስንቀበል ፤ ንፁህ እንሆናለን- ስለዚህ በይበልጥ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ እንሆናለን፡፡

  • በተጨማሪም፤ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት፣ አእምሮአችን ይበራል እና ልባችን ይራራል ስለዚህ እንደሱ የበለጠ ማሰብ እና ሊሰማን እንችላለን፡፡

  • እናም እንደ ትዳር አጋር ስንታተም ‹‹ዙፋናትን፤ መንግስታትን፤ ጌቶችን፤ እና ሀይላትን›› የመውረስ መብት እንደ እግዚአብሔር ስጦታ ይሰጣቸዋል፡፡16

የመንፈስ ስጦታ ሁለተኛው የማስቻያ ሀይል መንገድ ነው ፡፡ በክርስቶስ የሀጥያት ክፍያ ምክንያት፤ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እና ተከትሎ የሚመጣውን የመንፈስ ስጦታዎች ማግኝት እንችላለን፡፡ እነዚህ ስጦታዎች አምላካአዊ የሆኑ ባህሪዎች ናቸው፣ ስለዚህ እነዚህን የመንፈስ ስጦታዎች ባገኘን ቁጥር የበለጠ እንደ እግዚአብሄር እንሆናለን፡፡ ያለጥርጥር ስለዚህ ነው ቅዱሳን መጻህፍት በተለያዩ ጊዜያት እነዚህን ስጦታዎች እንድንፈልግ የሚያበረታቱን፡፡17

ፕሬዝዳንት ጆርጅ ኪው. ካነን “ማንም ‘ይህ ተፈጥሮዬ ነውና መተው አልችልም‘ ማለት የለበትም፡፡ በዚህ አይታለፍም፤ እግዚአብሔር በገባው ቃል አማካኝነት....(ድክመታችንን) የሚያጠፋ ስጦታ ይሰጠናል፡፡ ማናችንም ፍፁማን ካልሆንን፤ ፍፁም ለሚያደርገን ስጦታ መፀለይ የኛ ሀላፊነት ነው፡፡18

በማጠቃለያ፤ የአዳኛችን የሀጥያት ክፍያ በሞት ፋንታ ህይወትን “በአመድ ፋንታ አክሊልን” በጉዳት ፋንታ ፈውስን፤ እና ለድካም ፍፁምነት ይሰጠናል፡፡19 ይሄ ለዚህ አለም እንቅፋት እና መከራ ሰማያዊ ማርከሻ መድሀኒት ነው፡፡

አዳኛችን በምድር ህይወቱ መጨረሻ ሳምንት ላይ እንዲህ ብሎአል፣ “በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዧችሁ፤ እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ።” 20 ምክንያቱም አዳኛችን የሃጥያት ክፍያን ስለከፈለልን ፤ የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት እስከጠበቅን ድረስ፤ ምንም አይነት ውጫዊ ኃይል ወይም ክስተት ወይም ሰው፤ ምንም ሀጥያት ወይም ሞት ወይም ፍቺ፤ ዘላለማዊ ሕይወትን ከማግኘት ማገድ አይችልም፡፡ ይህን በማወቅ ፤ ባለመፍራትና በዚህ ሰማያዊ ተልዕኮ እግዚአብሄር ከኛ ጋር መሆኑን በጽኑ ማረጋገጫ ወደ ፊት መገስገስ እንችላለን፡፡

የአዳኛችን የሃጥያት ክፍያ ወሰን የለሽ ብቻ ሳይሆን ለግለሰብ ደራሽ እደሆነ እመሰክራለሁ ። ወደ እግዚአብሔር እቅፍ የሚመልሰን ብቻ ሳይሆን ፤ ልክ እንደ እርሱ መሆን የሚያስችለን ነው ፤ ይህም የከበረው የክርስቶስ የሃጥያት ዋጋ ክፍያ አላማ ነው ፡፡ ስለዚህ ነገር እርግጠኛ እና አመስጋኝ የሆነውን ምስክርነቴን አካፍላችኃለሁ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።