2010–2019 (እ.አ.አ)
ለአባታችን ልጆች ታላቅ ፍቅር
የሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


2:3

ለአባታችን ልጆች ታላቅ ፍቅር

ፍቅር በምንወደው ነብያችን ፕሬዘዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንድንወስድ ለታዘዝንው መንፈሳዊ አላማ ዋና ባህሪ እናም አነሳሽ ነው፡፡

የኔ ዉድ ወንድሞች እና እህቶች ፤ ይህ በታሪክ ዉስጥ ልዩ እና ቁልፍ ጊዜ ነዉ፡፡ ከአዳኙ ዳግም ምጻት በፊት በመጨረሻው ዘመን ላይ በመኖራችን ተባርከናል፡፡ በዚ ዘመን መጀመሪያ ላይ ፤ ቤተክርስቲያኑ በስርአት ከመቋቋሙ በፊት በ1829 ዉስጥ “ድንቅ ስራ” ሊመጣ እንደሆነ የሚያዉጅ የተወደደ ራእይ ተቀብለን ነበር፡፡ ይህ ራእይ እግዚአብሔርን ለማገልገል ያሹት ለዚህ ስራ የሚበቁት በ “እምነት ፣ በተስፋ ፣ ልግስና እና ፍቅር እናም ሙሉ አይንን ለእግዚአብሔር ክብር በማድረግ እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡”1 ልግስና ማለትም ንፁህ የክርስቶስ ፍቅር ፤2 እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለዉን ዘላለማዊ ፍቅርን ያካትታል፡፡3

በዚ ጠዋት የኔ አላማ የዛን አይነት ፍቅር በሚስኦናዊ አገልግሎት ፣ በቤተ-መቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ስራ ፣ እናም ቤትን ማእከል ያደረገ በቤተክርስቲያን የተደገፈ ሃይማኖታዊ አከባበር ዉስጥ ያለውን አስፈላጊ ሚና ላይ ማተኮር ነው፡፡ የአዳኙ ፍቅር እና የኛ እኛን መሰል ወንዶች እና ሴቶች ፍቅር 4 ፤ ለማገልገል ፣ እንዲሁም በ 2018 (እ.ኤ.አ) በተገለጹት ማስተካከያዎች ውስጥ በምንወደው ነብያችን ፕሬዘዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንድንወስድ ለታዘዝንው መንፈሳዊ አላማ 5 ዋና ባህሪ እንዲሁም አነሳሽ ነው፡፡

የተበታተነውን እስራኤል ለመሰብሰብ የሚስዮናዊ ጥረት

በህይወቴ ቀደም ብዪ ነበር በሚሲዮናዊ ስራ እና ፍቅር መሀከል ላለው ግኑኝነት የተጋለጥኩት፡፡ 11 አመት እያለሁ ፤ አያቴ ከሆነው አቡነ የአቡነ በረከትን ተቀበልኩ፡፡6 ያ በረከት በግማሹ “ነፍሶችን ወደ ክርስቶስ ለማሸነፍ… ወንጌሉን ለአለም ለመሸከም ስለምትጠራ ፤ለመሰልህ ሰዎች ታላቅ ፍቅር እዲኖርህ እባርክሀለው” ይል ነበር፡፡“7

በዛ የልጅነት እድሜ ላይ እንኳን ወንጌሉን ማካፍል የተመሰረተው ለሁሉም የሰማይ አባታችን ልጆች ታላቅ ፍቅር ላይ እንደሆነ ገብቶኛል፡፡

እንደ አጠቃላይ መሪነታቸችን “ወንግሉን ስበኩ ”ላይ እንድንሰራ ከ15 አምታት በፊት ስንጠራ ፤ ሁሌም እንደነበረው የፍቅር ባህሪ በኛም ጊዜ ላይ እንደሚያስፈልግ ደመደምን፡፡ ምእራፍ 6 በክርስቶሳው ፍቅር፤ላይ ልግስና እና ፍቅርን አጠቃሎ በምስኦነናዊዎቹ ዘንድ በተከታታይነት ይበልጥ ታዋቂ ምእራፍ ሆኖአል፡፡

እንደ አዳኙ መልክተኝነታቸው አብዛኛዎቹ ምስዮናዊዎች የዚህን አይነት ፍቅር ይሰማቸዋል እና ሲስማቸው ደግሞ ጥረታቸው ይባረካል፡፡ አባሎች ጌታን አላማው ላይ ለማገዝ አስፈላጊ የሆነዉን የዚህን አይነት ፍቅር እይታ ሲያገኙ የጌታ ስራ ይከናውናል፡፡

አር. ዌይን ሹት

የዚህን አይነት ፍቅር ግሩም ምሳሌ ውስጥ ትንሽ ድርሻ እንዲኖረኝ ታድዪ ነበር፡፡ እንደ ፓስፊክ ደሴቶች አካባቢ ፕሬዘዳንት እያገልግልኩ ከፕሬዘዳንት አር. ዌይን ስልክ ተደወለልኝ፡፡ ወጣት እያለ በሳሞአ ውስጥ ሚስዮን አገልግሏል፡፡ በኋላም እንደ ሚስዮን ፕሬዘዳንት ወደ ሳሞአ ተመለሰ፡፡8 ሲደውልልኝ የአፒያ ሳሞአ ቤተመቅደስ ፕሬዘዳንት ነበር፡፡ የሚስኦን ፕሬዘዳንት በነበረበት ጊዜ ከእሱ ወጣት ሚስዮናዊዎች አንዱ ፤ አሁን በፓሲፊክ የአካባቢ ፕሬዘዳንት የሆነው ፤ ሽማግሌ ቪንስ ሃሌክ ነበር፡፡ ፕሬዘዳንት ሹት ለቪንስ እና ለመላው የሀሌክ ቤተሰብ ታላቅ ፍቅር እና አክብሮት ነበረው፡፡ አብዛኛው ቤተሰቡ የቤተክርስቲያኑ አባላት ነበሩ ፤ ነገር ግን የቪንስ አባት ፤ የቤተሰቡ አባት ኦቶ ሃሌክ (የጀርመን እና ሳሞአዊ ዘር የሆኑት) አባል አልነበሩም፡፡ ፕሬዘደንት ሹት የካስማ ጉባኤ እና ሌሎች ስብሰባዎችን በአሜሪካ ሳሞአ እንደምካፍል ስላወቀ በኦቶ ሃልክስ መኖሪያ ወንጌሉን ፤ ለሱ በማካፈል በሚል ሀሳብ መቆየት ካሰብኩ ጠየቀኝ፡፡

ሽማግሌ ኦ ቪንሰንት ሀሌክ እንደ ሚስዮናዊ አገልጋይ

ሚስቴ ሜሪ እና እኔ ከኦቶ እና ከሚስቱ ዶሮቲ ጋር በሚያምርው ቤታቸው ውስጥ ቆየን፡፡ ቁርስ ላይ የወንጌል መልእክት አካፈልኩና ኦቶን ከሚስዮናዊዎች ጋር እንዲገናኝ ጋበዝኩት፡፡ ግብዣዬን እንቢ ሲል ደግ ፤ ነገር ግን ፅኑ ነበር፡፡ ብዙ የቤተሰቡ አባሎች የኀለኛው ቀን ቅዱሳን በመሆናቸው እንደሚደሰት ተናገረ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የእሱ እናት፣ ሳሞአዊ ቅድመ አያቶች በሳሞአ ውስጥ ቀደምት የክርሲቲያን ሚንስተሮች እንደነበሩና ለነሱ ባህላዊ የክርስትና እምነት ታላቅ ታማኝነት እንደሚሰማው አበክሮ አሳወቀን፡፡9 ቢሆንም ግን እንደ ጥሩ ጓደኞች ተለያየን፡፡

በኋላም ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ የሱቫ ፊጂ ቤተ-መቅደስን ለመመረቅ እየተዘጋጀ እያለ ነገሮችን በኒውዝላንድ እንዳመቻች በኒውዝላንድ ውስጥ ሆኜ የግል ጸሀፊው፤ ወንድም ዶን ኤች. ስታህሊ እንዲደውልልኝ አስደረገ አስደወለ፡፡10 ፕሬዘዳንት ሂንክሊ ቅዱሳኖቹን ለማግኘት ከፊጂ ወደ ሳሞአ አሜሪካኖች መብረር ፈልጎ ነበር፡፡ በቀድሞ ጉብኝት ላይ አንድ የተጠቀምነው ሆቴል ታስቦ ነበር፡፡ የተለየ ማስተካከያ ማድረግ ከቻልኩ ግን ጠየኳቸው፡፡ ወንድም ስታሂሊ “አንተ የአካባቢው ፕሬዘዳንት ነህ ፤ ጥሩ ይሆናል “አለኝ፡፡

በፍጥነት ለፕሬዘዳንት ሹት ደወልኩና ጓደኛችንን ኦቶ ሃሌክ በመንፈሳዊ መልኩ ለመባረክ ምናልባት ሁለተኛ እድል እንዳለን ነገርኩት፡፡ ይህኛው ጊዜ ሚስዮናዊ የሚሆነው ፕሬዘዳንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ ነው፡፡ በፕሬዘዳንት ሂንክሊ የጉዞ ቡድን ውስጥ ላለነው ለሁላችንም ፤ሀሌኮች፤ እንግዳ ተቀባያችን ቢሆኑ አግባብ አለው ብሎ ካሰበ ጠየኩት፡፡ 11 ፕሬዘዳንት እና እህት ሂንክሊ ልጃቸው ጄን እና ሽማግሌና እህት ጄፍሪ አር. ሆላንድም የዚህ ጉዞ ቡድን ነበሩ፡፡ ከዛ ፕሬዘዳንት ሹት ከቤተሰቡ ጋር በመስራት ሁሉንም ነገር አመቻችቶ ጨረሰ፡፡12

ከቤተመቅደሱ ምረቃ በኀላ ከፊጂ ስንደርስ ፤ ሞቅ ያለ ሰላምታ አደረጉልን፡፡13 በዛ ምሽት ወደ ሺህ የሚቆጠሩ የሳሞአዊ አባላቶችን አነጋገርን ፤ ከዛም ወደ ሃሌክ ቤተሰብ ግቢ አመራን፡፡ በቀጣዩ ጠዋት ለቁርስ ስንሰበሰብ ፤ ፕሬዘዳንት ሂንክሊ እና ኦቶ ሃሌክ አስቀድመው ጥሩ ጓደኞች ሆነው ነበር፡፡ ለእኔ ከአመት በፊት ከኦቶ ጋር ያወራዉትን ተመሳሳይ ወሬ እያወሩ መሆናቸው የሚስብ ነበር፡፡ ኦቶ ለቤተክርስቲናችን ያለውን አድናቆት ገልጾ ነገር ግን አሁን ላለው ቤተክርስቲያኑ ያለውን ታማኝነት ድጋሚ ሲያረጋግጥልን ፤ ፕሬዘዳንት ሂንክሊ እጁን በኦቶ ትከሻ ላይ አደረገና “ኦቶ ይህ በቂ አይደለም ፤ የቤተክርስያኑ አባል መሆን ይገባሃል” አለው፡፡ ይህ የጌታ ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ፕሬዘዳንት ሂንክሊ በተናገረው ነገር ፤ ከኦቶ ላይ መከላከያው ጋሻ በግልጽ ሲወድቅ ማየት ትችሉ ነበር፡፡

ኦቶ ሃሌክ ከአንድ አመት እና ከተጨማሪ ትንሽ ጊዜ ቆይቶ በኋላ እንዲጠመቅ ያስጠመቀው እና ማረጋገጫ እንዲያገኝ የፈቀደለት ይህ የተጨማሪ የሚስዮናዊ ትምህርት እና መንፈሳዊ ትህትና መጀመር ነው፡፡ ከዛ ከአመት በሁዋላ የሃሌክ ቤተሰብ በቤተ-መቅደስ እንደ ዘላለማዊ ቤተሰብ ታተሙ፡፡14

ሀሌክ ቤተሰብ በቤተመቅደስ ታተሙ

በዚህ ግሩም ልምድ ውስጥ ልቤን የነካው ነገር ፕሬዘዳንት ዌይን ሹት ለበፊት ሚስዮናዊው ፤ ሽማግሌ ቪንስ ሃሌክ ፣ እና የሃሌክ መላ ቤተሰብን እንደ ዘላለማዊ ቤተሰብ ለማየት ባለው ፍላጎት ያሳየው ፤ ጥልቅ የሆነ የአገልግሎት ፍቅር ነው፡፡15

እስራኤልን ስለመሰብሰብ ሲሆን ልባችንን ከዚህ አይነት ፍቅር ጋር እንዲሄድ ማድረግ እና ከዝም ብሎ ሀላፊነት ስሜት 16ወይም ከፍቅር ስሜቶች ፀፀት መራቅ እናም በመለኮታዊ ባልደረባነት የአዳኙን መልእክት በማካፈል ፣ በማገልገል ፣ ካለም ጋር ሚስዮን ውስጥ መሳተፍ አለብን፡፡ 17

እንደ አባልነታችን ለአዳኛችን እና ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን ያለንን ፍቅር በአለም ላይ ሁሉ ቀላል ግብዣዎችን በማድረግ ማሳየት እንችላለን፡፡ አዲሱ የእሁድ ስብሰባ ፕሮግራም በተሳካ ሁኔታ ፤ እና በፍቅር ጓደኞቻችንን እናም የምናውቃቸውን ሰዎች መተው እንዲያዩ እናም የቤተክርስቲያን ልምድ እንዲሰማቸው ለመጋበዝ የተለየ እድልን ያመለክታል፡፡18 በአዳኙ ላይ የሚያተኩረው መንፈሳዊ ቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ፣ በ 50 ደቂቃ በአዲስ ኪዳንና በአዳኙ ወይም በአዳኙና በአስተምሮው ላይ ባተኮሩ ተዛማጅ ጉባኤ መልእክቶች እንደሚከተል እናውቃለን፡፡

አንዳንድ የሴቶች መረዳጃ እህቶች ፣ ከክህነት ስልጣን ጉበኤ አባላት ጋር ለምን “የመሰብሰብ ሃላፊነት እንደተሰጣቸው“ አስበዋል ፡፡ ለዚህ ምክንያቶች አሉት ፤ እናም ደግሞ አብዛኛዎቹን ፕሬዘዳንት ኔልሰን በባለፈው አጠቃላይ ጉባኤ ላይ አስቀምጠዋል፡፡ “እስራኤልን ካለእናንተ ለመሰብሰብ አንችልም” ብለው አጠቃለዋል።19 በኛ ጊዜ ላይ ወደ 30 መቶኛ በሚጠጉ የሴት ሚስዮናዊያኖች ተባርከናል፡፡ ይህ የሴቶች መረዳጃ እህቶች በፍቅር ወንጌሉን እንዲያካፍሉ ተጨማሪ ፍላጎት እና ቅስቀሳ ይሰጣል፡፡ የእየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማካፈል ከያንዳንዳችን የሚፈለገው ፤ ከወንድ ፣ ከሴት ፣ ወጣት እና ህጻናት ፤ የሚያፈቅር ፣ ቸር ፣ መንፈሳዊ ውሳኔ ነው ፡፡ ፍቅርን ፣ ደግነትን እና ትህትናን ካሳየን ብዙዎች የኛን ግብዣ ይቀበላሉ፡፡ ግብዣችንን ላለመቀበል የሚመርጡት ደግሞ ጓደኞቻችን ሆነው ይቀጥላሉ፡፡

እስራኤልን ለመሰብሰብ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ጥረት

ፍቅር በሌላው ጫፍ ላይ ያሉትን እስራኤል ለመሰብሰብ በቤተመቅደሳችን እና ቤተሰብ ታሪክ ጥረታችን ላይ ማእከል ነው ፡፡ ቅድመ አያቶቻችን ያጋጠሙአቸውን ችግሮችና መከራዎች ስንማር ለነሱ ያለን ፍቅር እና ምስጋና ይጎላል፡፡ በሁለቱም በእሁድ ስብሰባ ፕሮግራም እና በወጣቶች የክፍሎች እና የጉባኤዎች እድገት ላይ በተደረገው አዲስ ማስተካከያ የቤተመቅደሳችን እና የቤተሰብ ታሪክ ጥረት በትልቅ ዲግሪ ጠንክሯል፡፡ እኚህ ለውጦች ስለ ቅድመ አያቶቻችንን ለመማር እና በሌላው ጫፍ ያሉትን እስራኤል ለመሰብሰብ ቀዳሚ እና ይበልጥ ሀይለኛ አትኩሮት ይሰጡናል፡፡ ሁለቱም የቤተ-መቅደስም እና የቤተሰብ ታሪክም ስራ በእጅጉ አድገዋል፡፡

የመረጃ መረብ አሁን ሀይለኛ መሳሪያ ነው ፤ ቤታችን አሁን ዋነኛ የቤተሰብ ታሪክ ማዕከል ነው፡፡ ወጣት አባሎቻችን በቤተሰብ ታሪክ ፍለጋ ውስጥ ተለይተው የሰለጠኑ ናቸው ፤ እናም ለመውደድ እና ለማመስግን የተማሩትን ፤ ቅድመ አያቶቻቸውን ጥምቀት ለማካሄድ በመንፈስ የተነሳሱ ናቸው፡፡ የ11 አመት ልጆች የሙታን ጥምቀት እንዲያካሂዱ ከተፈቀደበት ለውጥ ጀምሮ ፤ በአለም ዙሪያ ያሉ የቤተመቅደስ ፕሬዘዳንቶች የሰው ብዛት በእጅጉ እንደጨመረ ያመለክታሉ፡፡ አንድ የቤተመቅደስ ፕሬዘዳንት “በተጠማቂዎች ላይ አስገራሚ እድገት አለ... የ11 አመት ልጆች መጨመር ብዙ ቤተሰቦችን ያመጣል...” ብሎ አሳውቆናል፡፡ በትንሽ እድሜያቸው እንኳን ፤ እያከናወኑት ላለው ስነ-ስርአት አክብሮት እና አላማ የተሰማቸው ይመስላሉ፡፡ ለመመልከት ያምራል!20

የህጻናት እና የወጣቶች መሪዎች የቤተሰብ ታሪክን እና የቤተመቅደስ ስራን ዋና ጥረት እያረጉት እንደሆነ እና ማረጋቸውንም እንደሚቀጥሉ አውቃለው፡፡ የሴቶች መረዳጃ እህቶች እና የክህነት ወንድሞች የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ሀላፊነታቸውን ፤ በግል እና በሌላው ጫፍ ያሉትን እስራኤል ለመሰብሰብ ልጆችን እናም ወጣቶችን በማገዝና በማነሳሳት ፤ መወጣት ይችላሉ፡፡ ይህ በተለይ በቤት ውስጥ እና በሰንበት ላይ አስፈላጊ ነው ፡፡ ለቅድመ-አያቶቻችን በፍቅር ስነ-ስርአቶችን ማካሄድ ፤ ወጣቶችን እናም ቤተሰቦችን ከዚ ይበልጥ እርኩስ እየሆነ እየሄደ ካለው አለም እንደሚየጠነክራቸው እንዲሁም እንደሚጠብቃቸው ቃል እገባለው፡፡ እንዲሁም በግል ፕሬዘዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ከቤተ-መቅደሶች እና ከቤተ-መቅደስ ስራ ጋር የተዛመዱ እጅግ አስፈላጊ ራእዮችን እንደተቀበለ መሰክራለው፡፡

ዘላለማዊ ቤተሰቦችንና ግለሰቦችን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲኖሩ አዘጋጁ

ቤትን ማእከል ያደረገ የወንግል ጥናትና ኑሮ ላይ አዲስ አትኩሮ እናም በቤተክርሲትያኗ የቀረቡ ምንጮች ዘላለማዊ ቤተሰቦችን እና ግለሰቦችን ከሱ ጋር ለማገናኘት እና ከሱ ጋር ለመኖር በፍቅር ለማዘጋጀት ታላቅ እድሎች ናቸው፡፡21

አንድ ወንድ እና ሴት በቤተ-መቅደስ ሲታተሙ በክህነት ትዕዛዝ በአዲሱና ዘላለማዊ ቃልኪዳን ውስጥ የተቀደሰ የጋብቻ ሰርአት ውስጥ ይገባሉ፡፡22 የቤተሰባቸውን ጉዳይ ለመምራት አንድ ላይ የክህነት በረከቶችን እና ሀይልን ይቀበላሉ፡፡ ሴቶች እና ወንዶች “በቤተሰብ; ለአለም አዋጅ” 23ላይ እንደተቀመጠው ልዩ ሃላፊነቶች አሏቸው ፤ ነገር ግን የነሱ ሀላፊነቶች በዋጋና በጥቅም እኩል ናቸ24 ለቤተሰባቸው ራዕይን ለመቀበል እኩል ሀይል አላቸው፡፡ በፍቅርና በፅድቅ አንድ ላይ ሲሰሩ ፤ ዉሳኔዎቻቸው በሰማይ የተባረኩ ናቸው፡፡

የጌታን ፈቃድ ለግል እናም ለቤተሰቦቻቸው ማወቅ የሚሹ ለጽድቅ ፣ ራስን ዝቅ ለማድረግ ፣ ለደግነት እና ለፍቅር ሊጥሩ ይገባቸዋል፡፡ ትህትና እና ፍቅር ፤ የጌታን ፈቃድ ፣ በተለይ ለቤተሰቦቻቸው ለሚሹ መለያ ናቸው፡፡

ራሳችንን ወደ ፍጹምነት ማምጣት ፣ ለቃልኪዳኖቹ በረከት ራሳችንን ማብቃት እና እግዚአብሔርን ለመገናኘት መዘጋጀት የግል ሀላፊነቶች ናቸው፡፡ ቤታችንን ከከበበን ወጀብ ፤ መሸሸጊያ 25እና የእምነት ቦታ በማረግ ዉስጥ ራሳችንን የቻልን እና በትጋት የተሳተፍን መሆን አለብን፡፡26 ቤተሰቦች በፍቅር ልጆቻቸውን ለማስተማር ሀላፊነት አላቸው፡፡ በፍቅር የተሞሉ ቤቶች ሀሴት ፣ ደስታ ፤ እናየምድር ላይ ገነት ናቸው፡፡27

የእናቴ ተወዳጅ መዝሙር “ፍቅር በቤት” ነበር ፡፡28 በዙሪያችን ዉበት አለ ፍቅር በቤት ካለ የሚለውን የመጀመሪያዉን መስመር በሰማች ጊዜ ሁሉ በግልፅ ትነካለች እናም እንባ ታቀራለች፡፡ እንደ ልጅ በዚህን አይነት ቤት ውስጥ እንደምንኖር እናዉቅ ነበር ፤ ከትልቅ ግቦችዋም አንዱ ነበር፡፡ 29

በቤት ውስጥ ከፍቅር ድባብ በተጨማሪ ፕሬዘዳንት ኔልሰን የኛን ዋና አላማ የሚያስቱ የመገናኛ ብዙኀን አጠቃቀምን መመጠን ላይ አተኩረዋል፡፡ 30 የትኛዉንም ቤተሰብ ሊጠቅም የሚችል ማስተካከያ ፤ መረጃ መረብን ፣ የማህበረሰብ ገጽ እና ቴሌቭዥንን ሀሳብ መስረቂያ ወይም የባሰውን አለቃችን ከማድረግ ይልቅ ፤ ባሪያችን ማድረግ ነው፡፡ የሁሉም ነፍሶች ጦርነት ፤ በተለይ ደግሞ የህጻናት ፤ አብዛኛውን ጊዜ በቤት ውስጥ ነው ፡፡ እንደ ቤተሰቦች የመገናኛ ብዙኀንን ይዘት ፤ መልካም የሆነ ፣ እድሜን ያመካለ እና እኛ ለመፍጠር እየሞከርን ካለነው የፍቅር ድባብ ጋር የሚሄድ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡

በቤቶቻችን ውስጥ ትምህርቶች ግልጽ እና የሚገፋፉ31 እንዲሁም ደግሞ መንፈሳዊ ፣ ሀሴታዊ አና በፍቅር የተሞሉ ሊሆኑ ይገባል፡፡

እኛ ለአዳኙ ያለን ፍቅር ላይ እናም ቤዛነቱ ላይ ስናተኩር ፤ በሁለቱም ጫፍ ላይ ያሉትን እስራኤልን የመሰብሰብ ጥረታችን ላይ ማእከል ስናደርገው ፣ እናም ለሌሎች ስናገለግል ፤ እናም በግል እግዚአብሔርን ለመገናኘት ስንዘጋጅ የጠላት ተጽዕኖ እንደሚጠፋና በክርስቶሳዊ ፍቅር ፤ ሀሴቱ ፣ ደስታው እና የወንጌሉ ሰላም ቤታችንን እንደሚያጎላ ቃል እገባለዉ፡፡32 ስለነዚህ የአስተምሯዊ ቃልኪዳኖች መሰክራለው እናም የእየሱስ ክርስቶስን እርግጥ የሆነ ምስክር እና የሱን ቤዛነት በኛ ስም እሰጣለው በየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን፡፡

ማስታወሻዎች

  1. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4፥1 ፣ 5

  2. ሞሮኒ 7፣47

  3. ልግስና እና ፍቅር፣” ወንጌሌን ስበኩ ፤ ለሚስዮን አገልግሎት አጋዥ ፣ አርኢቪ. ኢዲ (2019) እ.ኤ.አ, 124 ተመልከቱ፡፡

  4. ዘፀአት 6:5; ማቴዎስ 22:36-40 ተመልከቱ።

  5. “የሽማግሌዎች ጉባኤ እና የሴቶች መረዳጃ አመራሮች በአባል ሚስዮናዊ እና ቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራ ዉስጥ ያላቸው ሀላፊነቶች ፣” ማሳሰቢያ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2018 እ.ኤ.አ ይመልከቱ፡፡

  6. አያቴ በተለያዩ ካስማዎች ለሚኖሩ የልጅ ልጆች የፓትሪያርካል በረከትን ለመስጠት ስልጣን ነበረው፡፡ ታሞ ስለነበር እና ይሞታል ተብሎ ስለታሰበ ለኔ የተሰጠኝ በ11 አመቴ ነበር ፡፡

  7. ክዊንተን ኤል ኩክ፣ የአቡን በረከት ከአቡነ ክሮዚየር ኪምበል ፣ ጥቅምት 13 ፣ 1951፣ ድሬፐር ፣ ዩታ ተሰጠ፡፡

  8. ፕሬዘዳንት አር. ዋይን ሹት ከሚስቱ ሎርና ጋር በተለያዩ ሚስዮኖች ላይም በሻንጋይ -ቻይና ፣ አርሜንያ ፣ ሲንጋፖር እና ግሪክ ውስጥ አገልግለዋል፡፡ ሎርና ካረፈች በኋላ ፣ ሮዝቫልን አገባና ፣ ቢሪስባን አውስትራሊያ ሚስዮን አገለገሉ፡፡ ከዘጠኝ ልጆቹ ሰባቱ ሙሉ ጊዜ ሚስዮንን አገልግለዋል፡፡ እንደ ሚስዮን ፕሬዘዳንት በሳሞአ ባገለገለበት በ2 አመቶች ውስጥ ፣ ሽማግሌ ጆን ኤች. ግሮበርግ በቶንጋ እንደ ሚስዮን ፕሬዘዳንት እያገለገለ ነበር ፡፡ ሁለቱም ያገኙአቸው ልምዶች ታሪካዊ ናቸው ፡፡

  9. ኦቶ ሀሌክ በሳሞአ ከለንደኑ የሚስዮን ማህበር ስረ መሰረት ያለው የክርስቲያን ቤተክርስቲያን መሪ ነበር ፡፡ አባቱ ከዴሳኡ ጀርመን ፣ የጀርመን የዘር ሀረግ ውስጥ ነበር ፡፡

  10. ፕሬዘዳንት ዶን ኤች. ስታህሊ አሁን እንደ ባውንቲፉል ዩታ ቤተመቅደስ ፕሬዘዳንት እያገለገለ ነው ፡፡

  11. ፕሬዘዳንት እና እህት ሂንክሊ እና ልጃቸው ጄን ሂንክሊ ዱድሌይ ፣ ሽማግሌ ጄፍሪ አር.ሆላንድ እና እህት ፓትርሺያ ቲ. ሆላንድ ፣ ሽማግሌ ክዊንተን ኤል. እና እህት ሜሪ ጂ.ኩክ ፣ እና ወንድም ዶን ኤች.ስታሂሊ ሁሉም ተገኝተዋል፡፡

  12. ሽማግሌ ኦ. ቪንሰት ሀሌክ አባቱ ቪንስ እና ወንድሙን ዴቪድ ከባህር ማዶ ተመልሰው ለፕሬዘዳንት ሂንክሊ ጉብኝት ቤቱን እንዲመለከቱ እና ለጉብኝቱ እዛው እንዲሆኑ እንደጋበዛቸው አሳውቆናል፡፡ ሽማግሌ ሀሌክ አባቱ “ታቃለህ እኚህ መላእክቶች ሊሆኑ ይችላሉ” ብሎ አውጇል ብሏል፡፡ ለልጆቹ ፤ ነቢይን የሚቀበሉ ከሆነ ፣ ቤቱ ፍጹም እንዲሆን እንደሚፈልጉ ነግሯቸዋል፡፡

  13. ፕሬዘዳንት ሂንክሊ ፣ በአሜሪካን ሳሞአ በብሄራዊ አመራር እና በብዙ ሺህ ሳሞአኖች በእግር ኳስ ስታዲየሙ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

  14. ቤተሰቦችን በትጉ ሚስዮናዊ ስራ ማሰባሰብ ፤ በሁለቱም በሳሞአን እና ሌሎች የፖሊኔዥያ ህዝቦች ዘንድ ትልቅ መገለጫቸው ሆኗል፡፡

  15. ፕሬዘዳንት ሹት በ2016 እ.ኤ.አ ፣ በኦቶ ሀሌክ ቀብር ላይ በጣም ከመወደዳቸውና ከመመስገናቸው የተነሳ ፤ እንዲናገሩ ተጋብዘው ነበር፡፡

  16. “አንዳንዴ በመጀመሪያ በግዴታ ወይም በሀላፊነት ስሜት ልናገለግል እንችላለን ፣ ግን ይሄው አገልግሎት እንኳን ወደ አንድ ከፍተኛ ነገር እንድንሳብ …በይበልጥ ምርጥ መንገድ እንድናገለግል” ይመራናል [”1 ቆሮንቶስ 12፡31]”(ጆይ ዲ. ጆንስ “ለሱ” ፣” ወይም ሊያሆና ፣ ህዳር 2018 እ.ኤ.አ ፣50)፡፡

  17. ታድ አር. ካሊስተር የማያልቀው ቤዛነት (2000)እ.ኤ.አ ፣ 5-8 ይመልከቱ፡፡

  18. የቤተክርስቲያን አባሎች ግብዣዎች በሚያደርጉበት ማንኛውም ሰአት ከሚስዮናዊያኖች ጋር መተባበር አለባቸው፡፡

  19. ረስል ኤም. ኔልሰን “እስራኤልን በመሰብሰብ ውስጥ የእህቶች ተሳትፎሊያሆና ፣ህዳር 2018 እ.ኤ.አ ፣ 70 ተመልከቱ ፡፡

  20. ፕሬዘደንት ቢ. ጃክሰን እና እህት ሮዝመሪ ኤም.ዊክሶም ፤ የሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ፤ ለህፃናት ክፍል አጠቃላይ አመራር ፣ መጋቢት 2019 እ.ኤ.አ፡፡ “ፍላጎቱን ለሟሟላት ብዙ ተጨማሪ በጣም በጣም በጣም ትንሸ የጥምቀት ልብሶች እያዘዝን ነው !” ብለው አሳውቀዋል፡፡

  21. ራስል ኤም ኔልሰን “የመክፈቻ ንግግር,” ሊያሆና ህዳር 2018 እኤአ, 6–8 ይመልከቱ፡፡

  22. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 131፥1-4 ተመልከቱ።

  23. ቤተሰብ፧ ለአለም የተላለፈ አዋጅሊያሆና፣ ጥቅምት 2017, 145 ተመልከቱ።

  24. “ባላቸው ግልፅ የወላጅነት ሀላፊነት ውስጥ ሁሉም አባት ለቤተሰቡ ፓትሪያርክ እና ሁሉም እናት ማትሪያርክ ነው” (ጄምስ ኢ.ፋውስት “የነብያዊ ድምፅ” ፣ ኢንሳይን፤ ግንቦት 1996፣6)፡፡

  25. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45:26-27; 88:91.ተመልከቱ።

  26. ረስል ኤም. ኔልሰን ፣ “አርአያ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መሆንሊያሆና፣ ህዳር 2018 ፣ 113 ይመልከቱ፡፡

  27. “ቤት በምድር ላይ ገነት ሊሆን ይችላል” መዝሙር ቁጥር ፡ 298 ፣ይመልከቱ፡፡

  28. ( “ፍቅር በቤት፣” መዝሙር፣ ቁጥር.294)

  29. የዚህ አይነት ፍቅር እንዲገኝ ከሆነ ፤ በትምህርት እና ቃልኪዳን 121፡41-42 ውስጥ ያለው መመሪያ ግቡ ሊሆን ይገባል፡፡

    “በማሳመን፣ በትእግስት፣ በደግነት፣ እና በትህትና፣ እና ግብዝነት በሌለው ፍቅር ካልሆነ በስተቀር፣ ምንም ሀይል ወይም ተጽዕኖ በክህነት ስልጣን ዘዴ ሊደገፍ አይቻልም ወይም አይገባውም ፤

    መንፈስን ካለግብዝነት እና ተንኮል በትልቁ በሚያሳድግ ፤ በደግነት ፣ እና ንፁህ እውነት፡፡

    የልጆች የማይገባ ወቀሳ ሊቆም ይገባል፡፡ ስህተቶችን እና የጥበብ እጥረትን ማሸነፍ ወቀሳ ሳይሆን ፤ መመሪያ ይፈልጋል፡፡ ሀጢአት መቀጣትን ይፈልጋል (ትምህርት እና ቃልኪዳን 1፡25-27 ይመልከቱ)፡፡

  30. ረስል ኤም.ኔልሰን “እስራኤልን በመሰብሰብ ውስጥ የእህቶች ተሳትፎ ” ፣ 69 ፤ እንዲሁም ረስል ኤም.ኔልሰን ፣ የእስራኤል ተስፋ (አለም አቀፍ ወጣቶች አምልኮ ፣ ሰኔ 3፣2018 ) የእስራኤልተስፋ፡፡

  31. ስንገልጸው በቤት ውስጥ ትምህርት ፤ ለሁሉም እድሜ ልጆች እንደ አንድ ክፍል ትምህርት ቤት ነው፡፡ የ11 አመቱን ልጅ ስናስተምር የ3 አመቱን ልጅ መተው አንችልም፡፡

  32. ዮሀንስ 17፡32 ኔፊ 31፥20ሞሮኒ 7፥47 ተመልከቱ።