2010–2019 (እ.አ.አ)
ለእርሱ
ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ)


ለእርሱ

ሌሎችን ስናገለግል ማንን እናም ለምን የሚለውን ማወቅ ታላቁ የፍቅር መገለጫው ለጌታ መሰጠት እንደሆነ እንረዳለን።

በዚህ በታሪካዊው ምሽት፣ ፍቅሬን እና አድናቆቴን ለእያንዳንዶቻችሁ እገልጻላሁ፣ ውድ እህቶቼ። እድሚያችን፣ አድራሻችን፣ሁኔታዎቻችን ምንም ይሁን ምን፣ በአንድነት፣ በጥንካሬ፣ በአላማ፣ እናም በሰማይ አባት፣ በአዳኛችን በእየሱስ ክርስቶስ እናም በህያው ነብያችን ፕሬዝዳንት ራስል ኤም ኔልሰን፣ ለመወደዳችን እና ለመመራታችንን በምስክርነት ዛሬ በዚህ ምሽት ተሰብስበናል።

እንደወጣት ትዳራማዎች፣ ባለቤቴ እና እኔ ወደ ቤተክርስትያን ለብዙ ዓመታት ቤተክርስትያን መጥተው የማያውቁ ቤተሰቦችን ለመጎብኘት እና ለማገልገል በካስማችን መሪ ተጠርተን ነበር። ጥሪውንም በፍቃደኝነት ተቀብለን፣ ከተወሰኑ ቀናቶች በኃላ ወደቤታቸው ሄድን። ከቤተክርስትያን ጎብኚ እንዳልፈለጉ ወዲያውኑ ለእኛ ግልፅ ነበር።

እናም በሚቀጥለው ጉብኝታችን፣ የቾኮሌት ኩኪ ልባቸውን እንደሚያቀልጠው በመተማማን፣ በሳህን ኩኪስ ይዘን ቀረብናቸው። አልተሳካም። ጥንዶቹ፣ በተከለለ በር አናገሩን፣ ወደውስጥ እንድንገባ እንደማይፈልጉ የበለጠ ግልጽ ነበር ያደረገው። ወደቤታችን ስንነዳ ግን፣ በቾኮሌቱ ፈንታ የሩዝ ብስኩት ወስደንላቸው ቢሆን ኖሮ ውጤታሞች ልንሆን እንደምንችል ሳይበዛ እርግጠኞች ነበርን።

የመንፈሳዊ እይታ ማጣታችን በተጨማሪ ያልተሳኩት ሙከራዎቻችንን አበሳጪ ተስፋ አስቆራጭ አደረገው። ተቃውሞ ፍጹም ምቹ አይደለም። ራሳችንን እንዲህ ብለን መጠየቅ ጀመርን፣ “ከብዙ ጊዝያቶች በኋላ ለምንድን ነው ይህን የምናደርገው? እቅዳችን ምንድን ነው?”

ሽማግሌ ካርል ቢ. ኩክ አስተያየታቸውን እንዳቀረቡት፥ ”የሚያስፈራ ነገር እንድናደርግ ከተጠየቅን፣ በማገልገል ከደከምን፣ ወይም መጀመሪያ አስደሳች የማይመስለንን ነግረ ለማድረግ ከተጠራል፣ በቤተክርስቲያኗ ማገልገል አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።”1 ከእኛ የተሻለ፡ የላቀ አስተሳሰብ/ አመለካከት ያለውን ሰው ምሪት፡ መጠየቅ እንደነበረብን ስንወስን የኤልደር ኩክን ቃል እውነታ እየተለማመድን ነበር፡፡

ለምን እናም፣ ከብዙ ጥልቅ ፀሎት እና ጥናት በኋላ፣ ለምን ስለሚለው የአገልግሎት ጥያቄያችን መልስን ተቀበልን። መረዳታችን ላይ ለውጥ ነበረ፣ የልብ መለወጥ፣ በእርግጥም የመገለፅ ልምምድ ነበረን።2 ከቅዱሳን መፅሐፍት ምሪትን ስላሻን፣ ጌታም ሌሎችን የማገልገሉን ሂደት እንዴት ቀላል እና ትርጉማማ እንደምናደርግ አስተማርን። ልባችንን እና አመለካከታችንን እንድንቀይር ያደረገን ያነበብነው አንቀጽም እንዲህ ይላል፥ “እንዲህ በማለት ትእዛዛትን እሰጣቸዋለሁ፥ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም አዕምሮህ፣ እና በፍጹም ሀይልህ ውደድ፤ እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም አገልግለው።”3 ምንም እንኳን ይህን ቁጥር በደንብ አስቅድመን የምናቀው ቢሆንም፣ በአዲስ እና አስፈላጊ በሆነ ሁኔታ የሚናገረን ይመስል ነበር።

ከልብ እነዚህን ቤተሰቦች እና የኤጲስ ቆጶሳችንን ለማገልገል ስንጥር እንደነበር ተገነዘብን፣ ነገርግን በእውነት ለጌታ ካለን ፍቅር በመነጨት ነውን እያገለገልን ያለነው ብለን እራሳችንን መጠየቅ ነበረብን። ንጉስ ቢንያም ይህን በግልፅ ያለያየው እንዲህ በማለት ነው፥ “እነሆ፣ እላችኋለሁ ዘመኔን እናንተን በማገልገል አሳልፌአለሁ ስላልኳችሁ በእውነት በእግዚአብሔርም አገልግሎት ስለነበርኩ መኩራት አልፈልግም፣ በእግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ ነበር ያለሁትና።”4

እናስ ንጉስ ቢንያም ስለዕውነት ማንን ነበር ያገለግል የነበረው? የሰማይ አባትን እና አዳኝን ሌሎችን ስናገለግል ማንን እናም ለምን የሚለውን ማወቅ ታላቁ የፍቅር መገለጫው ለጌታ መሰጠት እንደሆነ እንረዳለን።

ትኩረታችን ቀስ በቅስ ሲቀየር፣ ፀሎታችንም ይቀየራል። ጌታን ከማፍቀራችን የተነሳ፣ እነዚህን ውድ ቤተሰቦች ለመጎብኘት በጉጉት መጠበቅ ጀመርን።5 ለእርሱ ነበር ስናደርግ የነበረው። ትግሉን፡ትግል መሆኑ እንዲቀር አደረገው። ከብዙ ወራቶች ቤታቸው ደጃፍ ላይ ከቆምን በኋላ፣ ቤተሰቦቹም ወደ ውስጥ ያስገቡን ጀመሩ። በመጨረሻም፣ የተለመደ የፀሎት እና የወንጌል ውይይት አንድላይ ነበረን። ለረዥም ዓመታት የሚዘልቅ ጓደኝነትም ተመሰረተ። የእርሱን ልጆች ስንወድ ፡ እርሱን እያመለክነው እና እየወደድነው ነበር።

አንድን ችግረኛን ሰው ከልባችሁ ለመርዳት በመጣር በፍቅር ስትደርሱ፣ ጥረታችሁ ሳይስተዋል ወይም ምንአልባትም ሳይደነቅ ወይም ሳይፈለግ የሄደ መስሎ ተሰምቷቹህ ስለሚያውቅ ጊዜ ወደኋላ ተመልሳችሁ ልታስቡ ትችላላችሁን? በእዚያን ወቅት፣ አገልግሎታችሁ ዋጋ እንዳለው ጠይቃችሁ ታውቃላችሁን? እንደዛ ከሆነም የንጉስ ቢንያም ቃል ጥርጣሬያችሁን እና እንዲሁም ጉዳታችሁን ይተካ፡ “እናንተ በአምላካችሁ አገልግሎት ብቻ ውስጥ ናችሁ።”6

ቅሬታን ከመገንባት ይልቅ፣ በአገልግሎት የበለጠ ፍፁም የሆነ ግንኙነትን ከሰማይ አባታችን ጋር መገንባት እንችላለን። ለእርሱ ያለን ፍቅር እና መሰጠት፣ የመደነቅን እና የመታወቅን ፍላጎትን ባዶ አድርጎ፣ እናም የእርሱ ፍቅር ወደ ውስጣችን እናም በእኛ አማካኝነት እንዲፈስ ያደርጋል።

አንዳንድ ጊዜ በመጀመሪያ ከግዴታ እና ከሃላፊነት የተነሳ ልናገለግል እንችላለን፣ ነገርግን ያም አገልግሎት ቢሆን በውስጣችን ወዳለ ከፍተኛ ነገር እንድንቀርብ ሊመራን ይችላል፣ “የበለጠ እጅግ ጥሩ በሆነ ሁኔታ”7 እንድናገለግል በመምራት፣ ልክ እንደ ፕሬዝደንት ኔልሰን “አዲስ፣ የተቀደሰ አቀራረብ ሌሎችን ለመንከባከብ እና ለማገልገል እንደጋበዙን።”8

እግዚኣብሔር ለኛ ስላደረገልን ነገር ላይ ሁሉ ስናተኩር፣ አገልግሎታችን ከአመስጋኝ ልብ ይመነጫል። አገልግሎታችን እኛን ስለማጉላቱ ማሰባችንን ስንቀንስ፤ በምትኩ የአገልግሎታችን ትኩረት እግዚአብሔርን ማስቀደም እንደሆነ እንገነዛባላን።9

ፕሬዝዳንት ኤም. ራስል ባላርድ እንዳስተማሩት፣ “እግዚአብሄርን እና ክርስቶስን በፍፁም ልባችን፣ ነፍሳችን፣ እናም አይምሮአችን ስንወድ ብቻ ነው ይህንን ፍቅር በልግስና ስራ ከጎረቤቶቻችን ጋር ልናካፍል የምንችለው።”10

ከአስሩ ትእዛዛቶች የመጀመሪያው ይህንን መለኮታዊ ጥበብ በድጋሚ ያብራራል ”እኔ አምላክህ እግዚአብሄር ነኝ። … ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አይኑራችሁ።”11 የዚህ ትእዛዝ አቀማመጥ እርሱን እንደዋና ግባችን ካስቀመጥነው፣ በመጨርሻም ሁሉም ነገር ለሌሎች አገልግሎታችንን ጨምሮ ወደቦታው እንደሚገባ እንድንረዳ ይረዳናል። ፈልገን በምርጫችን በሂወታችን ውስጥ ቋሚ ቦታ ሲወስድ፣ ድርጊታችንን ሁሉ ለእኛ እና ለሌሎች መልካም ይሆን ዘንድ ይባርካል።

ጌታም መከረ፣ “ በሁሉ ሃሳብህ ወደ እኔ እይ።”12 እናም በየሳምንቱ ያን ለማድረግ ቃል እንገባለን ”እርሱን ሁል ጊዜ ለማስታወስ።”13 እንዲዚህ ያለ መልካም ትኩረት በምናደርገው ነገር ላይ ሁሉ መተግበር ይቻላልን? ትንሽ ድርጊትን መፈፀም ለእርሱ ያለንን ፍቅርን እና መሰጠትን የመግለጫ እድል እየሆነ ሊመጣ ይችላልን? እንደሆነ እና እንዲሚሆን አምናለሁ።

እያንዳንዱን በድርጊት ዝርዝራችን ላይ ያለንን ነገር ሁሉ እርሱን ማጉያ መንገድ እየሆነ እንዲመጣ ማድረግ እንችላለን። በጥድፈት መሃል፣ ግዴታዎቻችን ስንወጣ፣ ወይም ደግሞ ሽንት ጨርቅ ስንቀይር ሳይቀር ሁሉ እያንዳንዱን ድርጊታችን ሁሉ እርሱን ለማገልገል እድል እና ክብር ሊሆን እንደሚችል ማየት እንችላለንን።

አሞን እንዳለው፣ “አዎን፣ ምንም እንዳልሆንኩ አውቃለሁ፤ ስለጥንካሬዬ ደካማ ነኝ፣ እናም በእራሴ አልጎርርም፣ ግን በአምላኬ እኮራለሁ፣ በእርሱ ጥንካሬ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ።”14

በህይወታችን ውስጥ እግዚአብሄርን ማገልገል ዋና ግባታችን እየሆነ ሲመጣ፣ እራሳችንን እናጣለን፣ ነገርግን በተገቢው ጊዜ እራሳችንን እናገኛለን።15

አዳኝ እንዲህ ሲል ይህን መርህ ቀላል እና ቀጥታ እንዳስተማረው፥ “ስለዚህ እነዚህ ሰዎች መልካም ስራዎቻችሁን ተመልክተው፣ እናም በሰማይ ያለው አባታችሁን ያከብሩ ዘንድ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ሁሉ ይብራ።”16

በካልኩታ፣ ህንድ የህፃናት ማሰደጊያ ግድግዳ ለይ ይገኝ የነበረ የጥበብ ቃል ላካፍላችሁ፡ “ለጋሽ ከሆንክ፣ ሰዎች እራስ ወዳድ፣ ስዉር ዓለማ ያለዉ ነው ብለው ሊወቅሱህ ይችላሉ፣ ለማንኛውም ለጋሽ ሁን። ስትገነባ አመታት የፈጀኅውን፣ አንድ ሰው በአንድ ለሊት ሊያፈርሰው ይችላል። ለማንኛውም ገንባው። ዛሬ የምታደርገውን ጥሩ ነገር ነገ ሰዎች ሊረሱ ይችላሉ። ለማንኛውም መልካምን አድርግ። ለዓለም ያለህን እጅግ መ ልካሙን ስጥ፣ እናም ላይበቃ ይችላል። ነገር ግን ያለህን ሁሉ ለዓለም ስጥ። ይህ፣ በመጨረሻው ግምገማ፣ ባንተና በአምላክህ መሃከል ነው… ለማንኛውም።”17

እህቶች፣ ሁልጊዜ በእኛና በአምላካችን መሃል ነው። ልክ ፕሬዝዳንት ጄምስ ኢ. ፋውስት እንዳሉት “‘ትልቁ ዓለም የሚፈልገው ነገር ምንድነው?’ … ‘በዓለም ላይ የእያንዳንዱ ሰው ሁሉ ታላቁ ፍላጎት ከክርስቶስ ጋር ግላዊ፣ ቀጣይነት ያለው የቀን በቀን ግንኙነት አይደለምን?’ እንደዚህ ያለ ግንኙነት መኖር በውስጣችን ያለውን መለኮታዊነት ይፈታዋል፣ እናም ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን መለኮታዊ ግንኙነት እያወቅን እንደመምጣት በሂወታችን ውስጥ ትልቅ ልዩነት የሚፈጥር ምንም ነገር የለም።”18

በዚህም አይነት፣ አልማ ለልጁ እንደገለጸው፣ “አዎን፣ እናም ለድጋፍህ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ጩህ፤ አዎን፣ ስራህ ሁሉ ለጌታ ይሁን፣ እናም ወደ የትኛውም ሥፍራ ብትሄድ በጌታ ይሁን፤ አዎን፣ ሀሳብህ ሁሉ በጌታ የተመራ ይሁን፤ አዎን የልብህ ዝንባሌ ለዘለዓለም በጌታ ላይ ይሁን።”19

እናም ፕሬዝዳንት ራስል ኤም ኔልሰን እንደዚህ ብሎ አስተምሮናል፣ “የእርሱን ፍቃደኛ፣ የሃጥያት ክፍያ ስንረዳ፣ በእኛ በኩል የሚደረግ መሰዋትነት እርሱን ለማገልገል ባለን እድል እጅግ በላቀ የምስጋና ስሜት የከለላል።”20

እህቶች እየሱስ ክርስቶስ በሃጣያት ክፍያው እኛ ላይ እና በእኛ ውስጥ ሲሰራ በእኛ በኩል ሌሎችን ለመባረክ እንደሚሰራ እመሰክራለሁ። እናገለግላቸዋለን፣ ነገር ግን የምናገለግለው እርሱን በመውደድ እና በማገልገል ነው። መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ብሎ እንደገለፀው እየሆንን እንመጣለን፡ “ሁሉም ወንድ (እናም ሴት) የጎረቤቱን ፍላጎት ቢሻ፣ እናም ሁሉንም ነገር ወደ እግዚአብሄር እያየ ቢያደርግ።”21

ምን አልባትም የካስማ መሪያችን ባለቤቴ እና እኔ ከእነኛ ከቀደሙት እና በእቅድ፣ ነገር ግን ፍጹም ካልሆኑት፣ ለእግዚአብሔር የተወደዱ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ከማገልገል ጥረት መማር ያለብን ትምህርት ያ እንደሆነ አውቆ ይሆናል። እርሱን ለማገልገል ስንጥር እርሱ ለእኛ ስለሚያካፍለው መልካምነት እና ፍቅር የግል እና እውነት የሆነውን ምስክርነቴን እሰጣለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።

አትም