2010–2019 (እ.አ.አ)
መፅሐፈ ሞርሞን በመቀየር ውስጥ ያለው ሀላፊነት
ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ)


መፅሐፈ ሞርሞን በመቀየር ውስጥ ያለው ሀላፊነት

እስራኤልን ለመጨረሻ ጊዜ እየሰበሰብን ነው እናም ያንንም የምናደርገው፣ የመለወጥ ህይል ባለው መሳሪያ፣ በመጽሐፈ ሞርሞን ነው።

ዛሬ ብዙ ሰዎች ስለ እግዘአብሔር እውነታነት እና ከእርሱ ጋር ስላለን ግንኙነት በጥርጥሬ ያስባሉ። አብዛኞቹ ስለ ታታቁ የደስታ እቅድ በጥቂቱ ወይም እንደውም ምንም አያቁም። ከ30 በላይ አመታት በፊት፣ ፕሬዘዳንት ቤንሰን እንዲህ አስተዋሉ “አብዛኛው አለም ዛሬ የአዳኝን መለኮታዊነት ይቃወማል። ተአምራዊ ውልደቱን፣ ፍፁም ህይወቱን፣ እና ክቡሩን የትንሳኤውን እውነታ ይጠራጠራሉ።”1

በእኛ ጊዜ፣ ጥያቄዎች በአዳኝ ላይ ብቻ ሳይሆኑ በቤተክርስቲያኗ—የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን—በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ዳግም የመለሰው፤ ላይም ያተኮሩ ናቸው። እነዚህ ጥያቄዎች በአብዛኛው በአዳኙ ቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ትምህርቶች፣ ወይም ተግባራት ላይ ያተኮሩ ናቸው።

መጽሐፈ ሞርሞን በምስክርነት እንድናድግ ይረዳናል

ከወንጌሌን አውጁ{4}፣ ላይ እዲህ እናነባለን፤ “[የሰማይ አባታችን እና የእርሱ የደስታ እቅድ] መረዳታችን የሚመታው ከእግዚአብሔር ቀጥታ መገለጥን ከሚቀበሉት የወቅቱ ነብያት፤ ከጆሴፍ ስሚዝ እና ተከታዮቹ ነው። ስለዚህ፤ አንድ ሰው መመለስ ያለበት የመጀመሪያ ጥያቄ ጆሴፍ ስሚዝ ነብይ መሆኑን ነው፤ እና እርሱ ወይም እርሷ መጽሐፈ ሞረሞንን በማንበብ እና ስለሱም በመፀለይ ያንን መልስ መመለስ ይችላሉ።”2

በጆሴፍ ስሚዝ መለኮታዊ የነብይነት ጥሪ ላይ ያለኝ ምስክርነት የጠነከረው ልላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት የሆነውን መጽሐፈ ሞረሞን በፀሎት መንፈስ በማንበቤ ነው። የመጽሐፈ ሞርሞንን እውነታነት ለማወቅ ሞሮኒ “በክርስቶስ ስም፣ የዘለአለም አባት፤ እግዚአብሔርን ጠይቁ” ብሎ የጋበዘውን ተግብሬያለሁ።3 እውነት እንደሆነ እንደማውቅ ምስክርነቴን እሰጣለሁ። ለእናንተ እንደመጣው ሁሉ ለእኔም እውቀቱ “በመንፈስ ቅዱስ ሀይል” መጥቷል።4

የመጽሐፈ ሞርሞን መግቢያ እንዲህ ይላል፤ “ይህንን መለኮታዊ ምስክርነት[የመጽሐፈ ሞረሞንን] ከመንፈስ ቅዱስ የተቀበሉ በዚህ ሀይል ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም አዳኝ እንደሆነ፤ ጆሴፈ ስሚዝ የእርሱ ገላጭ እና በእነዚህ በኋለኛው ዘመናት ነቢይ እደሆነ፤ እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የጌታ መንግስት እንደገና ለአንዴ በምድር ላይ የተቋቋመበት ለዳግም ለመሲሁ ምፅአት መዘጋጃዎች እንደሆነ ያውቃሉ።”5

እንደ ወጣት ሚስኦናዊ ወረደ ቺሊ ስሄድ፣ ስለ መጽሐፈ ሞረሞን የመቀየር ሀይል ህይወትን የሚቀይር ትምህርት ተማርኩ። አቶ ጎንዛሌዝ በእርሱ ቤተከርስቲያን ውስጥ በተከበረ ስልጣን ላይ አገልግሏል። በሀይማኖት ትምህር ድግሪን ጨምሮ ጥልቅ ስልጠናዎችን ወስዷል። በእርሱ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ይኮራ ነበር። የሐይማኖት ምሁር እንደነበረ ለእኛ ግልፅ ነበር።

በእርሱ መኖሪያ ከተማ ሊማ፣ ፔሩ ውስጥ ስለሚመላለሱት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ወንጌል ሰባኪዎችን በደምብ ያውቅ ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ እውቀቱ ሊያስገርማቸው ሁሌም ከእነርሱ ጋር ለመገናኘት ይፈልግ ነበር።

አንድ ቀን፣ ከሰማይ የተሰጠ ስጦታ ነው ብሎ ባሰበው መልኩ፣ ሁለት ሚስኦናዊያን በመንገድ ላይ አስቆሙት ቅዱስ መጽሐፍትን ለማካፈል ወደ ቤቱ መምጣት እንደሚችሉ ጠየቁት። ይሄ ህልሙ እውን እንደሆነ ነው! ፀሎቶቹ ምላሽ አገኙ። በስተመጨረሻ፣ እነዚህን የተሳሳቱ ወጣት ወንዶችን ማስተካከል የሚችልበት ሆነ። መጽሐፍ ቅዱሳትን ለመወያየት ወደቤቱ ቢመጡ ደስታው እንደሆነ ነገራቸው።

ቀጠሮው እስኪደርስ በጠም ቸኩሎ ነበር። እምነታቸው ውሸት እንደሆነ ለማሳየት መጽሐፍ ቅዱሳን ለመጠቀም ተዘጋጅቶ ነበር። የእነርሱን የስህተት መንገዶች መጽሐፍ ቅዱስ በግልፅ ያሳያል ብሎ ይተማመን ነበር። የቀጠሮው ምሽት ደረሰ፣ እናም ሚስኦናዊያኑ በሩን አንኳኩ። ደስተኛ ነበር። የእረሱ ጊዜ በስተመጨረሻ ደረሰ።

በሩን ከፈተ እና ሚስኦናዊያኑን ወደ ቤቱ ጋበዘ። አንዱ ወንጌል ሰባኪ ሰማያዊ መጽሐፍ ሰጠው እና መጽሐፉ የእግዚአብሔርን ቃል እንደያዘ ንፁህ ምስክርነቱን አካፈለው። ሁለተኛው ወንጌል ሰባኪ ስለ መጽሐፉ፣ በወቅቱ የእግዚአብሔር ነብይ፣ ጆሴፍ ስሚዝ በሚባል፣ እንደተተረጎመ እና ስለ ክርስቶስ እንደሚያስተምር ጠንካራ ምስክርነቱን ጨመረ። ወንጌል ሰባኬዎቹ ተሰናበቱት እና ከቤቱ ሄዱ።

አቶ ጎንዛሌዝ በጣም ተበሳጭቶ ነበር። ነገር ግን መጽሐፉን ከፈተ እና ገልፆቹን ማገላበጥ ጀመረ። የመጀመሪያውን ገልጽ አነበበ። ገልጽ በገልጽ አነበበ እና እስከሚቀጥለው ቀን ከሰአት ድረስ አላቆመም። መጽሐፉን በሞላ አነበበ እና እውነት እንደነበር አወቀ። ምን ማድረግ እንደነበረበት አወቀ። ለሚስኦናውያኑ ደወለ፣ ትምህርቶችን ወሰደ፣ እናም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ለመሆን የነበረውን ህይወት ተወ።

ያ መልካም ሰው በፕሮቮ ዩታህ የኤምቲሲ መምህሬ ነበር። የወንድም ጎንዛሌዝ የመለወጥ ታሪክ እና የመጽሐፈ ሞርሞን ሀይል ታላቅ አድናቆት በእኔ ላይ እንዲሆን አደረገ።

በቺሊ ስደርስ፣ የሚስኦናዊ ፕሬዘዳንቴ፤ ፕሬዘዳንት ሮይደን ጄ. ግሌድ፣ በየሳምነቱ በጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ ላይ የተመዘገበውን የጆሴፍ ስሚዝን ምስክርነት እንድናነብ ጋበዘን። የመጀመሪያ ራዕይ ምስክርነተ እኛ ካለን የወንጌል ምስክርነት እና ከመጽሐፈ ሞርሞን ምስክርነት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው አስተማረን።

የእርሱን ግብዣ በአትኩሮት ተቀበልኩት። የመጀመሪያውን ራዕይ ዘገባ አንብቤያለሁ፤ መጽሐፈ ሞርሞንን አንብቤያለሁ። እንደ ሞሮኒ ምሬት ፀልያለሁ እና መጽሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ “በክርስቶስ ስም፣ የዘለአለማዊ አባት፣ እግዚአብሔርን”6 ጠይቄያለሁ። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዳለው መፅሐፈ ሞርሞን፣ “በምድር ካሉ መጽሐፍት በሙሉ የበለጠ ትክክል እንደሆነ፣ እናም የኃይማኖታችን የማዕዘን ድንጋይ እንደሆነና ከማንኛውም ሌላ መጽሐፍ በበለጠ በውስጡ ባሉት አስተያየቶች በመኖር ሰው ወደ እግዚአብሄር ሊቀርብ እንደሚችል” እመሰክራለሁ።7 ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንደዚህም አውጇል፤ “መጽሐፈ ሞርሞን እና መገለጦች ባይኖሩ፣ ሀይማኖተታችን የት ይሆን ነበር? ምንም የለንም።”8

የግል መለወጥ

እኛ ማን እንደሆንን እና የመጽሐፈ ሞርሞን አላማ በተሻለ ስንረዳ፣ መለወጣችን ጥልቀት ያለው እና በይበልጥ እውነታማ ይሆናል። ከእግዚአብሔር ጋር የገባናቸውን ቃልኪዳኖች ለመጠበቅ ያለን መሰጠት ይጠነክራል።

የመጽሐፈ ሞርሞን ዋና አላማ የተበተነውን እስራኤል መሰብሰብ ነው። ይሄ መሰባሰብ ለሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች ወደ ቃለኪዳኑ መንገድ እንዲገቡ እድል ይሰጣል እና፣ በእነዚያ ቃልኪዳኖች፣ ወደ እግዚአብሔር እይታ እንዲመለሱ ማድረግ። ንሰሀን ስናስተምር እና የተለወጡትን ስናጠምቅ፣ የተበታተነችን እስራኤል እንሰበስባለን።

መጽሐፈ ሞርሞን ስለ እስራኤል ቤት 108 ቦታ ይጠቅሳል። በመጽሐፈ ሞርሞን መጀመሪያ ላይ ኔፊ እንዲህ አስተማረ፣ “ለእኔ ዓላማ መሟላት ሰዎችን ወደ አብርሃም አምላክ፣ ወደ ይስሀቅ አምላክና፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ እንዲመጡና እንዲድኑ ለማሳመን ነው።”9 የአብረሃም፣ የይስሀቅ፣ እና የያቆብ አምላክ፣ የብሉ ኪዳን አምላክ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ወንጌሉን በመኖርን ወደ ክርስቶስ ስንመጣ እንድናለን።

ቀጥሎም፣ ኔፊ እንዲህ ጻፈ፤

“አዎን፣ አባቴ ስለአህዛቦችና ስለእስራኤል ቤትም ብዙ ተናገረ፣ እነርሱንም ልክ ቅርንጫፎቹ እንደወደበቁት ወይራ ዛፍ እንደሚመሰሉና በምድር ላይ ሁሉ እንደሚበታተኑ አነፃፀረ።

እናም የእስራኤል ቤቶች ከተበተኑ በኋላ እንደገና በአንድ ላይ መሰብሰብ አለባቸው፤ ወይም አህዛብ የወንጌልን ሙሉነት ከተቀበሉ በኋላ፣ የወይራው ዛፍ ተፈጥሮአዊ ቅርንጫፎች፣ ወይም በአጠቃላይ የእስራኤል ቤት ቅሪት ይጣበቃሉ፣ ወይም የእነርሱ መድሐኒትና ጌታ ከሆነው እውነተኛ መሲህ ጋር ይጣበቃሉ።”10

በተመሳሳይ፣ በመጽሐፈ ሞርሞን መጨረሻ፣ ነብዩ ሞሮኒ ስለቃልኪዳናችን እንዲህ በማለት ያስታውሰናል፤ “እናም ከዚህም በኋላ እንዳትቀላቀሊ፣ የዘለዓለማዊ አባት ለአንቺ፣ አቤቱ የእስራኤል ቤት፣ የገባው ቃል ኪዳን ይሟላም ዘንድ ካስማዎችሽን አጥብቂ እናም ወሰንሽንም ለዘለዓለም አስፊ፤ ከእንግዲህም አታፍሪም።”11

የዘለአለማዊ አባት ቃልኪዳኖች

በሞሮኒ “የዘለአለማዊ አባት ቃልኪዳኖች” የተባሉት ምንድናቸው? ከአብረሃም መጽሐፍ እንዲህ እናነባለን፥

“ስሜ ህዋዌ ነው፣ እና መጨረሻውን ከጅማሬው አቃለሁ፤ ስለሆነም እጄ ከእናነተ ጋር ነው።

“እና ታላቅ ህዝብ አደርችኋለሁ፣ እናም ከመጠን በላይ እባርካችኋለሁ እና ስማችሁን በህዝቦች ውስጥ ታላቅ አደርገዋለሁ፤ እናም ከእናንተ በኋላ ለሚኖሩት ዛራችሁ በረከት ትሆናላችሁ፣ ያም በእጆቻቸው ይህን አገልግሎት እና ክህነት ለሁሉም ህዝቦች ያካፍሉ ዘንድ።”12

ፕሬዘዳንት ሩሴል ኤም ኔልሰን በቅርብ በነበረው አለማቀፍ ስርጭት እንዳስተማሩት “እነዚህ በእርግጠም የኋለኛው ቀን ናቸው{28}፣ እናም እስራኤልን ለመሰብሰብ ጌታ ስራውን እያፋጠነ ነው። ያ መሰባሰብ አሁን በምድር ላይ እየሆኑ ካሉት እጅግ አስፈላጊው ነገር ነው። ምንም ነገር በትልቅነት አይወዳደረውም፣ ምንም ነገር በአስፈላጊነቱ አይወዳደርም፣ ምንም ነገር በግርማዊነት አይወዳደረውም። ምርጫቹ ከሆነ፣ የምትፈልጉ ከሆነ፣ የዛ ታላቅ ክፍል መሆን ትችላላችሁ። ትልቅ የሆነው፣ ግዙፍ የሆነው፣ ግርማዊ የሆነው ትልቅ አካል መሆን ትችላላችሁ።

“ስለ መሰብሰብ፣ ስናወራ እያልን ያለነው ይህን ቀላል እውነታ ነው፤ እያንዳንዱ የሰማይ አባት ልጆች፣ በሁለቱም ማጋረጃ ጀርባ ያሉት፣ የኢየሱስ ክርስቶስን የተመለሰው ወንጌል መልእክትን መስማት ይገባቸዋል። የበለጠ ማወቅ ይፈልጉ እንደሆነ እራሳቸው ይወስናሉ።”13

እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልነታችን እያደረግን ያለነው ይሄን ነው፤ አለምን ወደ መረዳት—እናም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መለወጥ ለማምጣት መሻታችን ነው። “እኛ የኋለኛው ቀን ሰብሳቢዎች ነን።”14 ተልዕኮአችን ግልጽ ነው። ወንድሞች እና እህቶች፣ የሞሮኒን ቃል በልባችን እንደወሰድን የምንታወቅ ሰዎች እንሁን፣ እንደ ጸለይን እና መጽሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ መልስ ያገኘን፣ እናም ከዛ ለሌሎች በቃል እንዲሁም ከዛ በተሻለ በድርጊት ያንን እውቀት ያካፈልን እንሁን።

በመቀየር ውስጥ የመጽሐፈ ሞርሞን ድርሻ

መፅሐፈ ሞርሞን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙሉነትን ይዟል።15 ከተጠበቀ የእርሱን ስጦታ፣ እንዲሁም የዘለአለም ህይወትን ወደሚያረጋግጥልን ወደ አብ ቃል ኪዳኖች ይመራናል።16 መጽሐፈ ሞርሞን የሁሉም የሰማይ አባት ወንዶች እና ሴት ልጆች የመለወጥ የማእዘን ድንገይ ነው።

ከፕሬዘዳንት ኔልሰን እንደገና ልጥቀስ: “ከመጽሐፈ ሞርሞን በየቀኑ ስታነቡ፣ የመሰብሰቡን ትምህርት፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነታዎች፣ የሀጢያት ክፍያው፣ እና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኙ የእርሱ ወንጌል ሙሉነትን፣ ትማራላችሁ። መጽሐፈ ሞርሞን ለእስራኤል መሰባሰብ መእከላዊ አካል ነው። በእርግጥም፣ መጽሐፈ ሞርሞን ባይኖር ኖሮ፣ ቃል የተገባው የእስራኤል መሰባሰብ አይከናወንም ነበር።”17

ቃል የተገቡትን በረከቶች ለኔፋውያን ሲያስተምር አዳኝ በተጠቀማቸው ቃላት ላጠናቅ፥ “እናንተ የነቢያት ልጆች ናችሁ፤ እናም የእስራኤል ቤት ናችሁ፣ እናም እግዚአብሔር ለአብርሃም በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ከአባቶቻችሁ ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ።”18

እኛ የእግዚአብሔር ወንዶች እና ሴቶች ልጆች፣ የእስራኤል ቤት፣ የአብረሃም ዘር እንደሆንን እመሰክራለሁ። እስራኤልን ለመጨረሻ ጊዜ እየሰበሰብን ነው እና ያንንም ከጌታ መንፈስ ጋር በማጣመር፣ የመለወጥ ታላቅ ሀይል ያለው መሳሪያ በሆነው መጽሐፍ በመጽሐፈ ሞርሞን እያደርግን ነው። በእኛ ጊዜ የእስራኤልን መሰባሰብ በሚመሩት የእግዚአብሔር ነብይ፣ ፕሬዘዳንት ሩሰል ኤም ኔልሰን፣ እንመራለን። መጽሐፈ ሞርሞን እውነት ነው። ህይወቴን ቀይሮታል። መሮኒ እና በእድሜዎች ሁሉ በነበሩ ነቢያት እንደተባሉት፣ ይህ እናንተን ሊቀይር እንደሚችል ቃል እገባላችኋለሁ።19 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

አትም