2010–2019 (እ.አ.አ)
ጊዜው አሁን ነው
ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ)


11:9

ጊዜው አሁን ነው

በህይወታችሁ ውስጥ ለማሰብ የሚያስፈልጋችሁ ማንኛውም ነገር ካለ፣ ጊዜው አሁን ነው።

ከብዙ አመታት በፊት፣ ለንግድ ስራ ጉዞ በምዘጋጅበት ወቅት፣ የደረት ሕመም ይሰማኝ ጀመር። አሳስቧት፣ ባለቤቴ ከእኔ ጋር ለመጓዝ ወሰነች። በአውሮፕላን በምንጓዝበት በመጀመሪያው ጉዞ ላይ፣ ህመሙ ሀይለኛ ሆኖ መተንፈስም ያስቸግረኝ ነበር። አውሮፕላኑ ሲያርፍም፣ ከአውሮፕላን ማረፊያ ወጥተን ወደ አካባቢያችን ሆስፒታል ሄድን፣ በዚያም ከብዙ ምርመራዎች በኋላ፣ ዶክተሩ ጉዟችንን ለመቀጠል ደህና ናችሁ አለን።

ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ተመለስንና ወደ መጨረሻው መድረሻችን በረረ ላይ ተሳፈርን። እየወረድን እያለን፣ አብራሪው በራዲዮ እኔ ማን እንደሆንኩኝ በማስታወቅ እንድገልጽ ጠየቀኝ። የበረራ አስተናባሪው ወደ እኛ ቀረበች፣ የአደጋ ጊዜ ጥሪ እንደደረሰላቸው ነገረችን፣ እናም በአውሮፕላን ማረፊያው ወደ ሆስፒታል የሚወስደኝ አምቡላንስ እንደሚጠብቀኝ ነገረችን።

አምቡላንስ ላይ ተጭነን ወደ አካባቢው ድንገተኛ ክፍል ተወሰድን። በዚያም ሁለት የተጨነቁ ሀኪሞች ተገናኙን፣ እና ትክክለኛ ያልሆነ የምርመራ ውጤት እንደተሰጠኝ እና ወዲያም መታከም የሚያስፈልገው አደገኛ የሆነ ከባድ የሳንባ እጢ፣ ወይም የደም መቋጠር፣ እንዳለብኝ ነገሩኝ። ሐኪሞቹ ብዙ ሕመምተኞች ከዚህ በሽታ ለመዳን እንደማይችሉ ነገሩን። እኛ ከቤት የራቅን እንደሆንን እና ለንደዚህ ዓይነት ሕይወት-ተለዋዋጭ ክስተቶች ዝግጁ እንዳልሆንን በማወቅ፣ ሀኪሞቹም በህይወታችን ውስጥ ልናስብበት ከሚገባን አንዳች ነገር ካሉ፣ አሁን ጊዜው ነው አሉን።

በዚያ ጭንቀት በተሞላበት ቅጽበት በፍፁም በአዕምሮዬ ውስጥ የነበረው አጠቃላይ እይታዬ እንደተቀየረ አስታውሳለሁ። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በጣም አስፈላጊ የሚመስሉ ነገሮች ብዙም ተፈላጊነት አልነበራቸውም። የዚህን ሕይወት ምቾትና ስጋቶች ከአዕምሮዬ ጠፍተው ወደ ዘለአለማዊ እይታ—ወደ ቤተሰቦች፣ ልጆች፣ ባለቤቴ ሀሳብ፣ እና በመጨረሻም የራሴን ህይወት ወደማመዛዘን፣ ተለወጠ።

በቤተሰብ እና በግላችን እንዴት እያደረግን ነበርን? እኛ ከገባናቸው ቃል ኪዳኖች እና ጌታ ከሚጠብቀው ነገር ጋር በሚስማማ ሁኔታ ኖረናልን፣ ወይም ምናልባትም የዓለማችን አሳሳቢነት በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ነገሮች ትኩረታችንን ሊሰርቅ እንዲችል ፈቅደናልን?

ከዚህ ተሞክሮ ለመማር የምትችሉትን አንድ ጠቃሚ ትምህርት እንድታስቡበት እጋብዛችኋለሁ፥ ከዓለም ውጡ እና ህይወታችሁን ገምግሙ። ወይም በዶክተሩ ቃላቶች፣ በህይወትዎ ውስጥ የሆነ ማንኛውም ነገር ካለ ማሰብ ያለባችሁ፣ አሁን ጊዜው ነው።

ህይወታችንን መገምገም

መረጃዎች በሚበዙበት፣ ከመጠን በላይ ጫና በሚፈጥሩ ሁኔታዎች ውስጥ እና በዚህች ፍይወት ሁከታ ለመመርመር አስቸጋሪ በሚያደርጉ እየጨመረ የሚሄድ ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮች በሚበዙበት እና ዘለአለማዊ ነገሮች ላይ ትኩረት ለማድረግ በሚያስቸግርበት አለም ውስጥ እንኖራለን። የዕለት ተዕለት ህይወታችን በፍጥነት በሚቀይሩ ቴክኖሎጂዎች በሚመጡት ትኩረትን በሚስቡ ርእሶች ይደበደባሉ።

ለማሰላሰል ጊዜ ካልወሰድን፣ የዚህ ፈጣን አካባቢን ተፅእኖ በዕለት ተዕለት ህይወታችን እና በምናደርጋቸው ምርጫዎች ላይ ያለውን ትኩረት ላንገነዘብ እንችላለን። ህይወታችን በቃላት፣ በቪዲዮዎች እና በጋዜጣ አርዕስተ ዜናዎች ተውጠው እናገኛቸዋለን። ምንም እንኳን አስደሳች እና አዝናኝ ቢሆኑም፣ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ከዘለአለማዊ እድገታችን ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም፣ ግን የእኛን የሟች ልምዳችንን የምንመለከትበትን መንገድ ይቀይራሉ።

እነዚህ ትኩረትን የሚስቡ ከሌሂ ህልም ጋር ለማመሳሰል ይችላሉ። እጆቻችን የብረት በትሩን ይዘው በቃል ኪዳን መንገድ ስንጓዝ፣ ከታላቅ እና ሰፊ ህንጻዎች “የሚያሳልቁትን እና በጣቶቻቸው የሚጠቁሙትን” እንሰማለን እናም እናዳምጣለን (1 ኔፊ 8፥27)። ሆን ብለን አናደርጋቸውም ይሆናል፣ ነገር ግን ኣንዳንድ ጊዜ ቆም ብለን ሁካታው ምን እንደሆነ ለማየት እንዞር ይሆናል። አንዳንዶቻችን የብረት በትርን ለቅቀን የተሻለ እይታ ለማግኘት እንሄድ ይሆናል። ሌሎችም “በሚያሳልቋቸው ምክንያት” በሙሉም ይወድቃሉ (1 ኔፊ 8፥28)።

አዳኝ እንዳስጠናቀቀን “ልባችሁ … [ለዚህ ህይወት] በማሰብ እንዳይከብድ፥ … ለራሳችሁ ተጠንቀቁ” (ሉቃስ 21፥34)። የዚህ ዘመን ራዕይም ብዙዎች እንደሚጠሩ፣ ግን ትንሽ እንደሚመረጡ እንድናስታውስ አድርገውናል። የተመረጡት “ልባቸውን በአለም ነገሮች ላይ ስለሚያደርጉ እና በሰዎች ይሞገሱ ዘንድ ስለሚነሳሱ” አይደለም (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥35{8}፤ ደግሞም ቁጥር 34 ይመልከቱ)።ህይወታችንን መመርመር ከዓለም ራሳችንን ለማውጣት፣ በቃል ኪዳን መንገድ ውስጥ የት እንዳለን ለማሰላሰል፣ እናም አስፈላጊ ከሆነም፣ ጠንከር ያለ አያያዝን እና ወደፊት ለመመልከት ማስተካከያን ለማድረግ እድልን ይሰጠናል።

በቅርብ፣ በአለም አቀፍ ወጣቶች ስብሰባ ውስጥ፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ወጣቶች በሰባት ቀናት ጾም ከአለም ራሳቸውን እንዲያስወጡ፣ ከማህበራዊ ሚዲያ እንዲለያዩ ጋብዘው ነበር። እናም ባለፈው ምሽት፣ በአጠቃላይ የሴቶች ስብሰባ ውስጥ እንደዚህ አይነት ግብዣም ዘጥተዋል። ከዚያም ወጣቶቹን በሚሰማቸው ስሜት፣ በሚያስቡበት፣ ወይም እንዴት እንደሚያስቡ እንዲገነዘቡ ጠየቋቸው። ከዚያም “ከጌታ ጋር ህይወትን በሙሉ እንዲመረምሩ … እግሮቻችሁ በቃል ኪዳን መንገድ ላይ በእርግጠኛነት እንደሚተከሉ” እንዲያረጋግጡ ጋበዟቸው። በህይወታችሁ ውስጥ ለመቀየር የሚያስፈልገው ማንኛውም ነገር ካለ፣ “ዛሬ ለመቀየር ፍጹም የሆነ ጊዜ ነው”1 ብለው አበረታቷቸው።

መቀየር ስላለባቸው ነገሮች ህይወትን ስንመረምር፣ ራሳችንን አንድ ተግባራዊ ጥያቄ ልንጠይቅ እንችላለን፥ በዚህ ዓለም ትኩረት ከሚያጠፋው በላይ ከፍ ለማድረግ እና ከፊታችን በሚገኘው ዘላለም እይታ ላይ ትኩረት ለማድረግ እንዴት እንችላለን?

በ2007 (እ.አ.አ) “መልካም፣ የተሻለ፣ ምርጥ” የሚል ርዕስ ባለው በጉባኤ ንግግራቸው ውስጥ፣ ፕሬዘደንት ዳለን ኤች. ኦክስ በአብዛኛው እርስበርስ ከሚጋጩት ዓለማዊ ፍላጎቶቻችን መካከል ምርጫዎችን እንዴት ቅድሚያ መስጠት እንዳለብን አስተምረዋል። “የተሻለ ነገሮችን ለመምረጥ አንዳንድ ጥሩ የሆኑ ነገሮችን ማለፍ አለብን ምክንያቱም እነዚህ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን ያሳድጋሉ እናም ቤተሰቦችን ያጠናክራሉ።”2

በዚህ ህይወት ውስጥ ያሉ ምርጥ ነገሮች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያተኮሩ እና የእርሱን ማንነት እና ከእሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ዘለአለማዊ እውነቶች መረዳት እንደሆነ ሀሳብ አቀርባለሁ።

እውነትን ፈልጉ

አዳኝን ለማወቅ ስንሞክር፣ ማን እንደሆንን እና ለምን እዚህ እንዳለን የሚገልጸውን መሠረታዊ እውነት ችላ ማለት አይገባንም። አሙሌቅ እንደሚያስታውሰን “ይህ ጊዜ ለሰዎች እግዚአብሔርን ለመገናኘት የዝግጅት ወቅት ነው፣” ጊዜውም “ለዘለዓለማዊው … እንድንዘጋጅ የተሰጠን” ነው (አልማ 34፥32–33)። በደንብ የሚታወቀው አባባል እንድናስታውስ እንደሚያደርገን፣ “እኛ መንፈሳዊ ልምምድ ያለን ሰዎች አይደለንም። እኛ የሰው ተሞክሮዎች ያለን መንፈሳዊ ፍጥረቶች ነን።”3

መለኮታዊ ማንነታችንን መረዳት ለዘለአለማዊ መሻሻላችን ወሳኝ ነው እናም ከዚህ ህይወት መደናበርም ነጻ ሊያወጣን ይችላል። አዳኝ እንዳስተማረው፥

“እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤

“እውነትንም ታውቃላችሁ፣ እውነትም አርነት ያወጣችኋል” (ዮሀንስ 8:31–32)።

ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ እንዳወጁትም፥ “በዚህ አለም ውስጥ የሰው ዘር ሊያገኘው የሚችለው ታላቅ ውጤት ቢኖር፣ በአለም የሚገኝ የማንም ፍጥረት ስራ ወይም ምሳሌ ካገኙት እውቀት ሊያዞራቸው በማይችልበት መንገድ፣ ራሳቸውን ከመለኮታዊ እውነት ጋር በደንብ፣ በሙሉ፣ በፍጹም መተዋወቃቸው ነው።”4

በአለም ውስጥ አሁን፣ ስለእውነት ያለው ክርክር ከባድ ሆኗል፣ ሁሉም ይህ ለእያንዳንዱ ግለሰብ ትርጓሜ አንጻራዊ የሆነ ጽንሰ-ሐሳብ ይመስል ዘንድ እውነት እንዳላቸው ይናገራሉ። ወጣቱ ጆሴፍ በህይወቱ “ክርክሩ እና ጠቡ ታላቅ ስለነበረ” “የትኛው ትክክለኛ እና የትኛው ስህተተኛ እንደሆነ በምንም በእርግጠኝነት የምወስንበት መንገድ አልነበረም” (የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥8)። “በዚህ የቃላት ጦርነት እና በአስተያየት ሁካታ መካከል” መለኮታዊ መመሪያን እውነትን በመሻት ፈለገ (የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥10)።

በሚያዝያ ጉባኤ፣ ፕሬዘደንት ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “በከፍተኛ ቁጥር የሚቆጠሩ ድምፆች እና እውነትን የሚያጠቁ የሰዎችን ፍልስፍናዎች የመለወጥ ተስፋን የምንፈልግ ከሆነ፣ ራዕይን ለመቀበል መማር አለብን።”5 በእውነት መንፈስ መመካት ይገባናል፣ ይህም “ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው” ነው (ዮሀንስ 14፥17)።

ይህ ዓለም ወደ ተለዋጭ እውነታዎች በፍጥነት ሲጓዝ፣ የያዕቆብን ቃል ማስታወስ አለብን “መንፈስ እውነቱን ይናገራል እንጂ አይዋሽምና። ስለሆነም፣ እርሱ ነገሮች በእርግጥ እንዳሉ ይናገራል፣ እናም ነገሮች በእርግጥ እንደሚሆኑ፤ ስለሆነም፣ እነዚህ ነገሮች ለነፍሳችን ደህንነት በግልፅ ተገልጠውልናልና” (ያዕቆብ 4፥13)።

ከዓለም ዞር ስንል እና ህይወታችንን ስንገመግም፣ አሁን ምን ዓይነት ለውጦች ማድረግ እንዳለብን የምንመረምርበት ጊዜ አሁን ነው። ምሳሌያችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደገና መንገዱን እንደመራን በማወቅ ትልቅ ተስፋ ሊኖረን ይችላል። ከመሞቱ እና ከትንሳኤው በኋላ፣ በዙሪያው የሚገኙትን ሰዎች የእርሱን የመለኮታዊ ስራ እንዲረዱ ለመርዳት በሚሰራበት ጊዜ፣ እንዲያስታውሱ አደረገ፣ “በእኔ ሳላችሁ ሰላም [ይሁንላችሁ ዘንድ] በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ” (ዮሐንስ 16፥33)። ስለእርሱም የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።