በዚህ ቀን ምረጡ
የዘለአለም ደስታችን ታላቅነት የሚመካው ህያው የሆነውን እግዚአብሔርን በመምረጥ እና በእርሱ ስራዎች በመሳተፍ ላይ ነው።
የልብ ወለድ ገጸ-ባህሪይ የሆነችው ሜሪ ፓፐን የተለመደ የህጻናት ጠባቂ የሆነች፤ እንዲሁም አስማታዊ ነበረች።1 በኤደዋርዲየን ለንደን ውስጥ በቼሪ ትሪ መንገድ ላይ በአስራ ሰባተኛው ቁጥር ላሉ ስለተቸገሩት የባንክን ቤተሰብ ለመርዳት በምስራቅ ንፋስ ላይ ትንፋሽዋን ትነፋለች። ጄን እና ማይክል የተባሉትን ልጆች እንድትጠብቅ ሃላፊነት ተሰጣት። ጥብቅ ሆኖም ደግነት በተሞላበት መንገድ ጠቃሚ ትምህርቶችን በሚያስደስት መልኩ ማስተማር ጀመረች።
ጄን እና ማይክል ከፍተኛ ለውጥን አመጡ፣ ነገር ግን ሜሪ ስርዋን ለመልቀቅ እና ወደሌላ ለመሸጋገር ጌዜዋ እንደሆነ ወሰነች። በድርሰቱ መድረክ ላይ፣ የሜሪ የልብ ጓደኛ የነበረው በርት፣ እንዳትሄድ ለማሳመን ይሞክራል። “ሜሪ፣ እነርሱ መልካም ልጆች ናቸው።”ብሎ ተከራከረ።
“መልካም ባይሆኑ ኖሮ ከነርሱ ጋር እቸገር ነበርን? ነገር ግን እነርሱ እንድሄድ ካልፈቀዱልኝ ልረዳቸው አልችልም፣ እናም ሁሉን የሚያውቅን ልጅ እንደማስተማር የሚከብድ ነገር የለም።“ ብላ መለሰች።
በርትም “ከዚያስ?” ብሎ ጠየቀ።
ሜሪም እንዲ መለሰች፣ “ከዚያማ የሚቀጥለውን ድርሻ በራሳቸው መስራት አለባቸው”2
ወንድሞችና እህቶች፣ እንደ ጄን እና እንደ ማይክል ባንክስ፣ ሊቸገርልን የሚገባን መልካም ልጆች ነን። የሰማዩ አባታችን እኛን ሊረዳንና ሊባርከን ይሻል፣ ነገር ግን እኛ ሁልጊዜ አንፈቅድለትም። አንዳንዴም፣ ሁሉን እንደሚያውቅ ሆነን እንተገብራለን። እኛም የሚቀጥለውን ድርሻ በራሳችን መስራት አለብን። ከቅድመ ህይወት ከሰማዩ ቤታችን ወደ ምድር የመጣንበትም ምክንያት ይሄው ነው። የኛ ፋንታ ምርጫዎችን ማድረግን ያካትታል።
የሰማዩ አባታችን የወላጅነቱ አላማ ልጆቹ ትክክለኛውን እንዲያደርጉ ማስገደድ አይደለም፤ ይልቁንስ የሱ ልጆች መልካሙን ነገሮች እንዲያደርጉ እንዲመርጡ በመጨረሻም እሱን እንዲመስሉ ነው። ታዛዥ እንድንሆን ብቻ የፈለገ ከሆነ፣ ባህሪያችንን ለመለወጥ አፋጣኝ ሽልማቶችን እና ቅጣቶችን ይጠቀም ነበር።
ነገር ግን እግዚአብሄር ልጆቹ ስልጠና የወሰዱና በሴሌስሺያል መኖሪያ ቤት ውስጥ ነጠላ ጫማውን የማይዘነጣጥሉ ታዛዥ የሆኑ የቤት እንሰሳ እንዲሆኑ አይደለም የሚፈልገው።3 አይደለም፣ ነገር ግን እግዚአብሄር ልጆቹ እንዲያድጉና በቤተሰብ ንግድ እንዲተባበሩት ነው የሚፈልገው።
እግዚአብሄር በመንግስቱ ውስጥ ወራሽ እንድንሆን፣ እሱን እንድንመስል የሚመራንን የቃልኪዳን መንገድን፣ እሱ ያለውን ህይወት የሚመስል ህይወት እንዲኖረን፣ እና በሱም ዘንድ ለዘላለም እንድንኖር እቅድን አዘጋጀልን፣ 4 የግል ምርጫን ማድረግ አስፈላጊ ነበር፣ አሁንም አስፈላጊ ነው፤ ይህንንም በቅድመ ህይወታችን ዘመን ተምረናል። እቅዱንም ተቀብለን ወደምድር ለመምጣት መረጥን።
በትክክል እምነትን እንድንለማመድና ምርጫን መምረጥ መማራችንን ለማረጋገጥ፣ የእግዚአብሄርን እቅድ እንዳናስታውስ የመርሳት መጋረጃ በአምሮአችን ላይ ተሸፈነ። ያለዚያ መጋረጃ፣ የእግዚያብሄር አላማ አይሳካም ምክንያቱም መሻሻል አንችልም እናም እሱ እንድንሆን የታመንን ወራሾች መሆን አንችልም።
ነብዩ ሌሂ እንዳለው “ስለዚህ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሰው በራሱ እንዲያደርግ ነፃ ምርጫን ሰጠው።” ስለዚህ፣ ሰው በአንዱ ወይም በሌላኛው ካልተፈተነ በስተቀር ለራሱ ማድረግ አይቻለውም።”5 በመሰረታዊ ደረጃ፣ አንደኛ ሃሳብ በአባት በበኩር ልጁ በእየሱስ ክርስቶስ ቀረበ። ሌላኛው ሃሳብ ደግሞ በሉሲፈር፣ ምርጫን አስወግዶ ሃይልን ለመቀማት በፈለገው በሰይጣን ቀረበ።6
በኢየሱስ ክርስቶስ፣ “ ከአባት ጋር የሚማፀንልን ጠበቃ አለን።”7 የሃጢያት ክፍያውን መስዋት ካደረገ በኋላ እየሱስ “ … እናም አብን በሰዎች ልጆች ላይ ያለውን የምህረት መብቶች ለመጠየቅ ወደ ሰማይ አረገ። የምህረት መብቶች በማግኘቱ “ስለሆነም እርሱም ለሰው ልጆች ጉዳይ ጠበቃ ይሆናል፤”8
እኛን ወክሎ የክርስቶስ በእግዚአብሄር ፊት ያለው ጠበቃነት የመቃረን አይነት አይደለም። እየሱስ ክርስቶስ፣ የራሱን ፍቃድ በአብ ፍቃድ እንዲጥለቀለቅ የፈቀደው፣ 9 የአብን መሻት እንጂ ለሌላ ነገር አይወዳደርም። የሰማይ አባት ስለውጤታማነታችን ያለምንም ጥርጥር ይደግፈናል እናም ያበረታታናል።
የክርስቶስ ተሟጋችነት፣ ቢያንስ በከፊሉ፣ ስለሃጢያታችን ስለመክፈሉ እናም ከእግዚአብሄርም የምህረት ስንዝር ማንም አለመለየቱን ያሳያል10 ወደ እርቅ የሚወስደን አካሄድ፣ በእየሱስ ክርስቶስ ለሚያምኑት ሁሉ፣ ንስሃ ለገቡ፣ ለተጠመቁ፣ እናም እስከመጨረሻው ለጸኑ፣ 11—አዳኛችን ይቅር ይላል፣ ይፈውሳል እናም ጠበቃ ይሆንልናል። ከእግዚአብሄር ጋር ላለን መታረቅ የሚደግፍና የሚያበረታታ እሱ ረዳታችን ነው፣ አስታራቂ ነው፣ ጠበቃችን ነው፣ 12
በተቃራኒው፣ ሉሲፈር ከሳሽ ነው። የሉሲፈርን የመጨረሻ ሽንፈት ባለ ራእዩ ዮሃንስ እንዲህ ገለጸው፣ “ታላቅ ድምጽም በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፣ አሁን የአምላክ ማዳንና ሃይል መንግስትም የክርስቶስም ስልጣን ሆነ።” ለምን? ምክንያቱም “በቀንና በለሊት በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና። እነርሱም ከበጉ ደም የተነሳ ከምስክራቸውም ቃልየተነሳ ድል ነሱት።”13
ሉሲፈር ከሳሽ ነው። በቅድመ ምድራዊ ህይወት እኛን በመቃረን ተናገረ እናም በዚህም ህይወት ይወግዘናል። እኛን ወደ ታች ለማድረግ ይሻል። መጨረሻ ወደሌለው ዋይታ እንዲያጋጥመን ይፈልገናል። ብቁ አይደላችሁም የሚለን እሱ ነው፣ መልካም አይደለንም የሚለን፣ከስህተትም ማገገም የለም ብሎ የሚነግረን እሱ ነው። እሱ የመጨረሻ ተሳላቂ ነው፣ ዝቅ ስንልም ይጎስቀናል።
ሉሲፈር አንድ ልጅን መራመድ እያስተማረ ካለና ልጁም ተንበል ቢል፣ በልጁ ላይ ይጮሃል፣ ይቀጣዋል፣ እናም ሙከራውን እንዲያቆም ይነግረዋል። የሉስፈር መንገዶች ተስፋ መቁረጥን እና ስቃይን—በመጨረሻ እናም ሁልጊዜም። ይህ የውሸት አባት የመጨረሻ የሃሰት አቅራቢ ነው14 እናም በጥበብ እኛን ለማሳት እና ለማዘናጋት ይሰራል፣ ”ሁሉም ሰዎች እንደሱ እንዲሰቃዩ ይፈልጋል።”15
እየሱስ አንድ ልጅን መራመድ እያስተማረ ካለና ልጁም ተንበል ቢል፣ እንዲነሳ ይረዳዋል እናም ለሚቀጥሉትም ደረጃዎች ያግዘዋል።16 እናም ክርስቶስ ረዳት እና አጽናኝ ነው። የእርሱም መንገዶች ሁልጊዜም ደስታንና ተስፋን ያመጣሉ።
የእግዚአብሄር እቅድ ለኛ ምሪትን መስጠት ነው፣ ይህንንም ምሪት ቅዱሳት መጻህፍት ትእዛዛት ይሉታል። እነዚህ ትእዛዛት እንደድንገተኛ የተሰጡ ወይም ዝም ብሎ እንዳጋጣሚ የተሰባሰቡ እኛን ታዛዥ ብቻ አድርጎ ለማሰልጠን ያሉ አይደሉም። እኛ መልካም ባህሪያትን አጎልብተን ወደ ሰማይ አባታችን እንድንመለስ እና ዘላቂ የሆነውን ደስታ እንድንቀበልነው። ለሱ ትእዛዛቶች መታዘዝ መታወር አይደለም፤ እኛ በማወቅ እግዛብሄርን እና ወደ ቤትየሚወስደንን መንገድ እንመርጣለን። ለኛ የተሰጠው መንገድ ለአዳምና ሄዋን ከተሰጠው ጋር ተመሳሳይ ነው፤ “ስለዚህ እግዚአብሔር የቤዛነት እቅድ ማዘጋጀቱን እንዲያውቁ ካደረገ በኋላ፣ ትእዛዛትን ሰጣቸው።”17 በቃልኪዳን መንገድ ላይ እንድንጓዝ ቢፈልግም፣ የመምረጡን መብት ለኛ ሰጠን።
በእርግጥ፣ እያንዳንዱ ልጆቹ ለራሱ እና ለራሷ እንዲመርጡ እግዚአብሄር ይሻል፣ይጠብቃል እናም ይመራል። አያስገድደንም። በምርጫ ስጦታ፣ እግዚአብሄር ልጆቹ “በራሳቸው እንዲያደርጉ እንጂ እንዲደረግባቸው” አይፈቅድም።18 ምርጫ በመንገዱ ላይ ለመግባት ወይም ላለመግባት እንድንመርጥ ያስችለናል። ምርጫ መንገዱን እንድንስት ወይም እንዳንስት ያስችለናል። እንድንታዘዝ እንደማንገደድ ሁሉ፣ እንዳንታዘዝ አንገደድም። ማንም ያለኛ ፈቃድ ከመንገዱ ሊያወጣን አይችልም፣ (አሁን፣ ይህም ነጻ ምርጫቸው ከተላለፉባቸው ጋር እንዲምታቱ አይገባም። በመንገዱ ላይ አይደሉም፤ እነርሱ የአደጋ ሰለባ ናቸው። እነርሱ የእግዚአብሔርን መረዳጃ፣ ፍቅር፣ እና ርህራሄ ተቀብለዋል።)
ነገር ግን ከመንገዱ ስንወጣ፣ እግዚአብሄር ያዝናል፣ ምክንያቱምይህ በመጨረሻ፣ በማይወገድ መልኩ፣ ላነሰ ደስታ እና በረከቶችን እንድናጣ ያደርገናል። በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ፣ ከመንገዱ መውጣት ሃጢያት ብለው ይጠሩታል፣ እናም ያነሰን ደስታን እና በረከቶችን ማጣት ቅጣት ብለው ይጠሩታል። በዚህ አመለካከት፣ እግዚአብሄር እየቀጣን አይደለም፤ ቅጣት የሱ ሳይሆን፣ የኛ የምርጫችን ውጤት ነው፣
ከመንገዱ መሳታችንን ስናስተውል፣ እንደሳትን መቆየት እንችላለን ወይም በእየሱስ በክርስቶስ ቤዛነት አማካኝነት፣ አረማመዳችንን ቀይረን ወደመንገዱመመለስ እንችላለን። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ፣ ለመለወጥ መወሰን እና ወደመንገዱ መመለስ ንስሃ ተብሎ ይጠራል። ንስሃ አለመግባት ማለት እራሳችንን እግዚአብሄር ለመስጠት ከሚፈልገው በረከቶች መካከል እራሳችንን መሰረዝ ማለት ነው። “ስለ ተሰጠንን ለመደሰት ፍቃደኞች ካልሆንን፣ [እኛ] ወደ ራሳችኑ ቦታ ለመቀበል ፈቃደኛ የሆንባቸውን ነገሮች ለማግኘት እንመለሳለን”19—ይህም የኛ እንጂ የእግዚአብሄር ምርጫ አይደለም።
ከመንገዱ የወጣንበት ቅይታ ምንም ያህል ቢሆን ወይም ምንም ያህል ከመንገዱ የራቅን ቢሆንም፣ ለመመለስ ውሳኔ ስናደርግ፣ እግዚአብሄር እንድንመለስ ይረዳናል።20 በእግዚአብሄር እይታ፣ በእውነተኛ ንስሃ እና በክርስቶስ ላይ ባለን ጽናት ወደፊት በመቀጠል፣ አንዴ ወደ መንገዱ ስንገባ፣ መጀመሪያውኑ እንዳልወጣን ሆኖ ይቆጠራል።21 አዳኝ ለሃጢያታችን ይከፍላል እና እየቀነሱ ላሉት ደስታዎችን እና በረከቶች ነጻ ያወጣናል። ይህም በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ ይቅርታ መደረግ ይባላል። ከጥምቀት በኋላ፣ ሁሉም አባላት ከመንገዱ ይወጣሉ—አንዳንድም ዘልለው ይወድቃሉ። ስለሆነም፣ እምነትን በክርስቶስ መለማመድ፣ ንስሃ መግባት ከሱ እርዳታን መቀበል፣ እና ይቅር መባል፣ የአንድ ጊዜ ተግባር ሳይሆን የህይወት ሙሉ ተደጋጋሚ እና ተቀያያሪ ሂደት ነው። በዚህ መንገድ ነው፣ “እስከመጨረሻው የምንጸናው።”22
ማንን እንደምናገለግል መምረጥ ይኖርብናል።23 የዘለአለም ደስታችን ታላቅነት የሚመካው ህያው የሆነውን እግዚአብሔርን በመምረጥ እና በእርሱ ስራዎች በመሳተፍ ላይ ነው። እኛም የሚቀጥለውን ድርሻ በራሳችን ለመስራት ስንሞክር፣ ምርጫችንን በትክክል መምረጥን እንለማመዳለን። የቀድሞ ሁለት የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዝደንቶች እንዳሉት፣ “ሁልጊዜ ማባበል እና እርማት እንደሚፈልጉ ህጻናት መሆን የለብንም።”24 አይደለም፣ እግዚአብሔር ጎልማሳ ሰዎች እንድንሆን እና ራሳችንን እንድንገዛ ይፈልገናል።
የአብን እቅድ ለመከተል መምረጥ በሱ መንግስት ውስጥ ወራሾች ለመሆን ብቸኛው መንገድ ነው፤ ከዛን ነው እኛ ካለሱ ፍቃድ በተቃራኒ እንደማንጠይቅ አመኔታን የሚያሳድርብን።25 ነገር ግን ማስታወስ ያለብን ነገር “ሁሉን የሚያውቅን ልጅ እንደማስተማር የሚከብድ ነገር የለም።“ ስለዚህ በጌታ መንገድ፣ እና በአገልጋዮቹ ለመማር ፍቃደኞች መሆን አለብን። እኛ የተወደድን የሰማይ ወላጆች ልጆች መሆናችንን ማመን እንችላለን እናም ሊቆረቆሩልን የተገባን እናም እርግጠኛ መሆን ያለብን “ በራሳችን” ማለት ብቸኞች ነን ማለት አይደለም።26
የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢይ ያዕቆብ እንዳለው፣ ከእርሱ ጋር እኔም እንዲህ እላለሁ፥
ስለዚህ፣ ልቦቻችሁን አስደስቱ፣ እናም በራሳችሁ ፡— ዘለዓለማዊውን ሞት ወይንም የዘለዓለማዊውን ህይወት መንገድ ለመምረጥ እንደምትችሉ አስታውሱ።
“ስለዚህ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ[እና እህቶቼ] ሆይ፣ እራሳችሁን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር አስታርቁ፣ እንጂ ከዲያብሎስ ፈቃድና ከስጋ ጋር አይደለም… ፤ እናም ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቃችሁ በኋላ የምትድኑት በእግዚአብሔር ፀጋ ብቻ እንደሆነ አስታውሱ።”27
ስለዚህም፣ እምነትን በክርስቶስ ምረጡ፣ ንስሃን ምረጡ፣ ለመጠመቅ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ለመቀበል ምረጡ፣ በመጨረሻም ቅዱስ ቁርባንን በብቁነት ለመቀበል ተዘጋጁ፣ በቤተ መቅደስ ቃልኪዳናትን ለመግባት እናም ህያው የሆነውን እግዚአብሄርን እና ልጆቹን ለማገልገል ምረጡ። ምርጫዎቻችን ማንነታችንን እናም ወደፊት ማንን እንደምንሆን ይወስናሉ።
በያዕቆብ በረከቶች በመጨረስም፤ “ስለዚህ፣ እግዚአብሔር በትንሣኤው ኃይል ከሞት ያስነሳችሁ… ከዘለዓለማዊው ሞት በኃጢአት ክፍያው፣ ለዘለዓለም የእግዚአብሔርን መንግስት እንድትወርሱና፣ በፀጋውም መለኮት እንድታመሰግኑት ያድርጋችሁ።”28 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።