2010–2019 (እ.አ.አ)
ሞክር፣ ሞክር፣ ሞክር
ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ)


ሞክር፣ ሞክር፣ ሞክር

አዳኝ ስሙን በልባችሁ ውስጥ እያስቀመጠ ነው። ለሌሎች እና ለእናንተ የክርስቶስን ንጹህ ፍቅር እየተሰማችሁ ናችሁ።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ እናንተ ለማነጋገር ላለኝ እድል ምስጋና ይሰማኛል። ይህ ጉባኤ ለእኔ ከፍ ከፍ የሚያደርግ እና የሚያነቃቃ ነበር። የተዘመረው መዝሙር እና የተነገሩት ቃላት በመንፈስ ቅዱስ ወደልባችን ተወስደዋል። የምለው በዚያው አይነት መንፈስ እንዲወሰድላችሁ እጸልያለሁ።

ከብዙ አመታት በፊት፣ በምስራቅ አሜሪካ ውስጥ ለአውራጃ ፕሬዘደንት እንደ መጀመሪያ አማካሪ አገለግል ነበር። ወደ ትትንሾቹ ቅርንጫፎቻችን በመኪና በምንሄድበት ጊዜ፣ ከአንድ በላይ በሚሆን፣ እንዲህ አለኝ፣ “ሀል፣ ከማንም ጋር ስንገናኝ፣ በታላቅ ችግር ላይ እንደሆኑ ብታስመስልላቸው፣ ከግማሽ በላይ በሚሆን ትክክል ነህ።” ትክክል ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን በአመታት ውስጥ በግምቱ በጣም የቀነሰ እንደነበረ ተማርኩኝ። ዛሬ፣ በሚያጋጥማችሁ ፈተናዎች ላበረታታችሁ እፈልጋለሁ።

የእኛ ሟች ሕይወት ለእያንዳንዳችን የፈተና እና የእድገት ምንጭ እንዲሆን አፍቃሪ ፈጣሪያችን የተነደፈ ነው። በአለም ፍጥረት ውስጥ ስለ ልጆቹን እግዚአብሔር የተናገረውን ታስታውሳላችሁ፥ “ጌታ አምላክ የሚያዛቸውን ማናቸውንም ነገሮች ሁሉ እንደሚያደርጉ ለማየት፣ በዚህ እንፈትናቸዋለን።”1

ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ፣ ፈተናው ቀላል አልነበረም። ሟች ሰውነት ስላሉ በሚመጡ መከራዎች እንጋፈጣለን። ሁላችንም የምንኖረው ሰይጣን በእውነት እና በግል ደስታ ላይ የሚዋጋው ጦርነት እየጨመረ በሚሄድበት ዓለም ውስጥ ነው። አለም እና የእናንተ ህይወት ከፍ ያለ ጭንቀት ላይ እንዳለ ይመስላችሁ ይሆናል።

የእኔ ማረጋገጫ ይህ ነው፥ እነዚህን ፈተናዎች ለእናንተ የፈቀደው አፍቃሪ እግዚአብሔር በእዚያ ውስጥ የምታልፉበት እርግጠኛ መንገድ በንድፍ አውጥቷል። የሰማይ አባት አለምን አፍቅሮ ውድ ልጁን እንዲረዳን ልኮልናል።2 ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ለእኛ ህይወቱን አሳልፎ ሰጠ። ኢየሱስ ክርስቶስ በገትሰመኔ ውስጥ እና በመስቀል ላይ የኃጢያቶቻችንን ሸከም ተሸከመ። በህይወት ውስጥ በሚኖሩት በእያንዳንዱ ፈተናዎች ያፅናናን እና ያጠናከረን ዘንድ፣ እርሱ ሁሉንም ሀዘኖች፣ ስቃዮች፣ እና የኃጢያታችንን ውጤት ገጥሞታል።3

ጌታ ለአገልጋዮቹ ያለውን ታስታውሳላችሁ፥

“እኔና አብም አንድ ነን። እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ ነው፤ እና እኔን ከተቀበላችሁ፣ እናንተ በእኔ አላችሁ እና እኔም በእናንተ አለሁ።

ስለዚህ፣ እኔ በመሀከላችሁ ነኝ፣ እና እኔም መልካሙ እረኛ፣ እና የእስራኤል ድንጋይ ነኝ። በዚህ አለት ላይ የተመሰረተም አይወድቅም።”4

ነቢያችን ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንደዚህ አይነት ማረጋገጫም ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ፣ በፈተናዎቻችን ውስጥ እንድሚመሩን በዚያ አለት ላይ ለመገንባት እና የጌታን ስም በልባችን ላይ ለማስቀመጥ የምንችልበት መንገድንም ገልጸዋል።

እንዲህም አሉ፥ “ለተወሰነ ጊዜ ተስፋ ልትቆርጡ ትችላላችሁ፣ ህይወት ቀላል እንድትሆን የተደረገች እንዳልሆነች አስታውሱ። በመንገድም ፈተናዎችን መሸከም እና ሀዘኖችን መፅናናት ያስፈልጋል። ‘ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር’ (ሉቃስ 1፥37) እንደሌለ ስታስታውሱ፣ እርሱ አባታችሁ እንደሆነ እወቁ። በእርሱ ምስል የተፈጠራችሁ፣ በብቁነታችሁ በኩል በጻድቅ እቅዳችሁ እርዳታ ለማግኘት ራዕይ ለመቀበል መብት ያላችሁ ወንድ ወይም ሴት ልጆች ናችሁ። በራሳችሁ ላይም የጌታን ቅዱስ ስም ውሰዱ። በእግዚአብሔር ቅዱስ ስምም ለመናገር ብቁ ለመሆን ትችላላችሁ (ት. እና ቃ. 1፥20 ይመልከቱ)።”5

የፕሬዘዳንት ኔልሰን ቃላት በቅዱስ ቁርባን ጸሎት ውስጥ ያሉትን ቃል ኪዳኖች፣የሰማይ አባታችን እኛ ቃል የገባናቸውን ስናደርግ የሚያሟላቸውን ቃል ኪዳኖች እንድናስታውስ ያደርጉናል።

እነዚህን ቃላት አድምጡ፥ “አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን ዳቦ ለሚቋደሱት ነፍሳት ሁሉ የልጅህን አካል በማስታወስ እንዲበሉት እና ፣ አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ እነርሱ የልጅህን ስም በላያቸው ላይ ለመውሰድ ፈቃደኞች መሆናቸውን፣ እና ሁልጊዜ እርሱን እንደሚያስታውሱና እርሱ የሰጣቸውን ትእዛዛት እንደሚጠብቁ ለአንተም ይመሰክሩ ዘንድ፣ በዚህም የእርሱ መንፈስ ሁልጊዜ እንዲኖራቸው ትባርከውና ትቀድሰው ዘንድ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቅሃለን። አሜን.”6

ለእኛ በሚቀርቡት በእያንዳንዱ ጸሎቶች ግዜ አሜን ስንል፣ ዳቦውን በመቀበል የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ስም በራሳችን ላይ ለመቀበል፣ ሁልጊዜም እርሱን ለማስታወስ፣ እና ታዕዛዛቱን ለማክበር ቃል እንገባለን። በተራም መንፈሱ ሁሌም ከእኛጋ እንዲሆን ቃል ተገብቶልናል። በእነዚህ ቃል ዳኖች ምክንያት፣ በሚያጋጥመን በማንኛውም ፈተና አዳኝ በደህንነት እና ያለፍርሀት ለመቆም የምንችልበት አለት ነው።

የቃል ኪዳን ቃላትን እና በቃል የተገብቡትን በረከቶች ሳሰላስላቸው፣ በራሳችን ላይ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለመውሰድ ፈቃደኛ መሆን ን ትርጉም እንዳለው አስባለሁ።

ፕሬዘደንት ዳለን ኤች. ኦክስ እንደገለጹት፣ “ቅዱስ ቁርባንን ስንቀበል በራሳችን ላይ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በራሳችን ላይ እንደምንወስድ አንመሰክርም።” የምንመሰክረው ይህን ለማድረግ ፈቃደኞች እንደሆንን ነው። (ት. እና ቃ. 20፥77 ይመልከቱ።) ፈቃደኛ መሆናችንን መመስከራችን፣ ከሁሉም በላይ አስፈላጊ በሆነ ሁኔታ ያን ቅዱስ ስም በራሳችን ላይ ከመውሰዳችን በፊት አንድ ነገር መድረስ እንዳለበት ሀሳብ ያቀርባል”7

ስሙን “በራሳችን ላይ ለመውሰድ” የሚሉት ቃላት፣ በመጀመሪያ ስሙን የምንወስደው ስንጠመቅ ሲሆን፣ የአዳኝን ስም መውሰድ በጥምቀት ላይ እንደማይፈጸም ይነግረናል። በህይወታችን በሙሉ፣ በተጨማሪም በቅዱስ ቁርባን ጠረጴዛ ላይ ቃል ኪዳኖቻችንን እናሳድስ እና በጌታ ቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ ቃል ኪዳን ስንገባ፣ ስሙን በራሳችን ላይ በመውሰድ እንቀጥላለን።

ስለዚህ “በራሴ ላይ ስሙን ለመውሰድ ምን ማድረግ ይገባኛል?” እና “እድገት ማድረጌን እንደኢት አውቃለሁ?” የሚሉት ሁለት ጥያቄዎች ለእኛ አስፈላጊ ይሆናሉ።

የፕሬዘዳንት ኔልሰን ቃላትም አንድ እርዳታ በሚሰጥ መልስ በሀሳብ ያቀርባሉ። ለእርሱ ለመናገር ለመቻል ዘንድ የአዳኝን ስም በራሳችን ላይ ለመውሰድ እንችላለን ብለዋል። ለእርሱ ስንናገርም፣ እርሱን እናገለግላለን። “ያላገለገለውን አለቃ፣ እና እንግዳውን፣ ከልቡ ስሜትና ሀሳብ የራቀውን፣ አንድ ሰው እንዴት ያውቃል?”8

ለእርሱ መናገር የእምነት ጸሎት ያስፈልገዋል። ያም አዳኝን በስራ ለመርዳት ምን ቃላትን ለመናገር እንደምንችል ለመማር ወደ ሰማይ አባት ከልብ የመጣ ጸሎት ያስፈልገዋል። ለዚህም ቃል ኪዳን ብቁ መሆን ያስፈልገናል፥ “በእኔም ድምፅ ሆነ ወይም በአገልጋዮቼ ድምፅ፣ አንድ ነው።”9

ነገር ግን፣ በራሳችን ላይ ስሙን ለመውሰድ ለእርሱ ከመናገር በላይ ያስፈልገዋል። እንደ እርሱ አገልጋይ ብቁ ለመሆን በልባችን መሰማት የሚገባን ስሜቶች አሉ።

ነቢዩ ሞርሞን ብቁ የሚያደርገን እና በራሳችን ላይ ስሙን ለመውሰድ የሚያስችለንን ስሜት ገልጿል። እነዚህ ስሜቶችም እምነትን፣ ተስፋን፣ እና የክርስቶስ ንጹህ ፍቅር የሆነውን ልግስና ያካትታሉ።

ሞርሞን እንደገለጸው፥

“ምክንያቱም እናንተ የዋህ በመሆናችሁ በክርስቶስ እምነት እንዲኖራችሁ እፈርዳለሁ፤ ምክንያቱም በእርሱ እምነት ከሌላችሁ ከቤተክርስቲያኑ ሰዎች ጋር ለመቆጠር ብቁ አትሆኑም።

“እናም የተወደዳችሁ ወንድሞቼ በድጋሚ ተስፋን በተመለከተ እናገራችኋለሁ። ተስፋ ከሌላችሁ እምነትን እንዴት ለማግኘት ይቻላችኋል?

“እናም ተስፋ የምታደርጉበት ምንድን ነው? እናም ተስፋ የምታደርጉበት ምንድነው? እነሆ በክርስቶስ የኃጢአት ክፍያ እናም በትንሳኤው ኃይል ለዘለዓለም ህይወት እንዲኖራችሁ ተስፋ ይኑራችሁ እላችኋለሁ፤ እናም ይህም በእርሱ ባላችሁ እምነት ለእናንተ በገባላችሁ ቃል ኪዳን መሰረት ነው።

“ስለሆነም፣ አንድ ሰው እምነት ካለው ተስፋ ሊኖረው ይገባል፤ ያለ እምነት ምንም ዓይነት ተስፋ ሊኖር አይችልም።

“እናም በድጋሚ፣ እነሆ እንዲህ እላችኋለሁ፣ የዋህ እና በልቡ የሚራራ ካልሆነ በስተቀር እምነት እና ተስፋ ሊኖረው አይችልም።

“በልቡ የሚራራ እና የዋህ ካልሆነ ግን እምነቱ እና ተስፋው ከንቱ ነው፤ ምክንያቱም በልቡ የሚራራ እናም የዋህ ካልሆነ በጌታ ፊት ተቀባይነት አይኖረውምና፤ እናም ሰው የዋህ እናም በልቡ የሚራራ፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብሎ የሚመሰክር ከሆነ እርሱ ልግስና አለው፤ ልግስና ግን ከሌለው እርሱ ከንቱ ነው፤ ስለሆነም ልግስና ሊኖረው ይገባል።

ልግስናን ከገለጸ በኋላ፣ ሞርሞን እንዲህ በማለት ቀጠለ፥

“ነገር ግን ልግስና ንፁህ የክርስቶስ ፍቅር ነው፤ እናም እስከዘለዓለም ይፀናል፤ እናም በመጨረሻው ቀንም እርሱን የያዘ መልካም ይሆንለታል።

“ስለሆነም የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች ሁሉ ላይ በሚያፈሰው በዚህ ፍቅር ትሞሉ ዘንድ በኃይል ከልባችሁ ወደ አብ ፀልዩ፤ የእግዚአብሔር ልጆች ትሆኑ ዘንድ፣ እርሱ በሚመጣበትም ጊዜ እንደእርሱ ሆነን እንዳለ እናየዋለንና፣ ይህ ተስፋም ይኖረናልና፣ ልክ እርሱ ፍፁም እንደሆነ እኛም ፍፁማን እንሆናለንና። አሜን።”10

ምስክሬም አዳኝ ስሙን በልባችሁ ውስጥ እንደሚያስቀምጥ ነው። ለብዚዎቻችሁ፣ በእርሱ ያላችሁ እምነት እያደገ ነው። ተጨማሪ ተስፋ ይሰማችኋል። ለሌሎች እና ለእናንተ የክርስቶስን ንጹህ ፍቅር እየተሰማችሁ ናችሁ።

ይህን በአለም አቀፍ በሚያገለግሉት የወንጌል ሰባኪዎች አያለሁ። ይህን ከጓደኞቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ስለየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በሚናገሩት አባላት ተመልክቻለሁ። ወንዶች፣ ሴቶች፣ እና ወጣት ሰዎች፣ እንዲሁም ልጆች ለአዳኝ እና ለጎረቤቶቻቸው ባላቸው ፍቅር ምክንያት ያገለግላሉ።

በአለም ውስጥ ስለደረሰው አደጋ በመጀመሪያ ሲሰማ፣ አንዳንዴም ባህር በመሻገርም ቢሆን፣ ያለመጠየቅ አባላት ለማዳን እቅድ ያደርጋሉ። እነርሱም አንዳንዴ የተደመሰሰው ቦታዎች ሊቀበላቸ እስከሚችሉ ድረስ መጠበቅን አስቸጋሪ አድርገው ያዩታል።

ዛሬ የምታዳምጡት አንዳንዶቻችሁ በፈተናዎቻችሁ ምክንያት እምነታችሁና ተስፋችሁ እየተሸነፉ እንዳሉ እንደሚሰማችሁ ይገባኛል። ፍቅር እንዲሰማችሁም በጉጉት ትፈልጋላችሁ።

ወንድሞችና እህቶች፣ የእርሱን ፍቅር ለመቅመስ እና ለመካፈል ጌታ በቅርባችሁ እድሎች አዘጋጅቶላችኋል። ጌታ አንድን ሰው ለእርሱ እንድታፈቅሩለት እንዲልክላችሁ በልበ ሙሉነት ለመጸለይ ትችላላችሁ። እንደ እናንተ አይነት ቀና ያሉ ፈቃደኛ ሠራተኞችን ጸሎት ይመሳል። ለእናንተ እና ለእርሱ ለምታገለግሉት ያለው የእግዚአብሔር ፍቅር ይሰማችኋል። የእግዚአብሔርን ልጆች በችግራቸው ስትረዱ፣ የራሳችሁ ችግሮችም ቀላል ይመስላሉ። እመታችሁ እና ተስፋችሁም ይጠናከራሉ።

የዚህ እውነት የአይን ምስክር ነኝ። በህይወቴ ውስጥ፣ ባለቤቴ ለጌታ ተናግራለች እናም ለእርሱ ሰዎችን አገልግላለች። ከዚህ በፊት እንዳጠቀስኩት፣ ከኤጲስ ቆጶሳችን አንዱ እንዲህ አለኝ፣ “እገረማለሁ። በአጥቢያ ውስጥ ችግር ስላለው ሰው በምሰማበት ጊዜ፣ ለመርዳት በፍጥነት እሄዳለሁ። ነገር ግን በምደርስበት ጊዜ፣ ባለቤትህ ሁልጊዜም በዚያ በመጀመሪያ ተገኝታ ነበር።” ለ56 አመታት እንኖርባቸው በነበርነው በተለያዩ ቦታዎች ውስጥ ሁሉ ይህ እውነት ነበር።

አሁን በየቀኑ አንዳንድ ቃላት ብቻ ነው ለመናገር የምትችለው። ለጌታ ባፈቀረቻቸው ሰዎች ትጎበኛለች። በየምሽት እና በጠዋትም ከእርሷ ጋር መዝሙር እዘምራለሁ እናም እንጸልያለን። ጸሎቱን እኔ እጸልያለሁ እናም መዝሙርን እኔ መዘመር አለብኝ። አንዳንዴ የመዝሙሩን ቃላት ለመዘመር አፏ ሲነቃነቅ እመለከታለሁ። የልጆችን መዝሙት ትወዳለች። በጣም ጥሩ መስሎት የሚሰማው ስሜት በዚህ መዝሙሩ ውስጥ ተጠቃልሏል፥ “እንደ ኢየሱስ ለመሆን እሞክራለሁ።”11

ባለፈው ቀን፣ “ኢየሱስ እንደሚወዳችሁ እርስ በራስ ተፋቀሩ። በምታደርጉት ሁሉ ደግነትን አሳዩ፣” የሚለውን መዝሙር ቃላት ከዘመርን በኋላ፣ በጸጥታ፣ ግን በግልፅ፣ “ሞክር፣ ሞክር፣ ሞክር” አለች። እርሱን ስታየው፣ ጌታ በልቧ ውስጥ ስሙን እንዳስቀመጠ እና እርሷም እንደ እርሱ እንደሆነ እንደምታገኘው አስባለሁ። አሁን እርሱን በችግሯ እየተሸከማት ነው፣ እናንተንም በችግራችሁ እንደሚሸከማችሁ።

አዳኝ እንደሚያውቃችሁ እና እንደሚያፈቅራችሁ ምክሬን አቀርብላችኋለሁ። የእርሱን ስም እንደምታውቁ እርሱም የእናንተን ስም ያውቃል። ችግራችሁን ያውቃል። እርሱም ይህን አጋጥሞናል። በኃጢያት ክፍያው በኩልም፣ አለምን አሸንፏል። የእርሱን ስም በራሳችሁ ላይ ለመቀበል ፈቃደኛ በመሆን፣ የብዙ ሌሎችን ሸከሞች ከፍ ታደርጋላችሁ። በጊዜም አዳኝን በተሻለ እንደምታውቁት እና በተጨማሪም እንደምታፈቅሩት ታውቃላችሁ። ስሙ በልባችሁ ውስጥ እና በትዝታችሁ ውስጥ ታትሞ ይገኛል። ይህም እናንተ የምትጠሩበት ስም ነው። ለእኔ፣ ለማፈቅራቸው፣ እና ለእናንተ ላለው አፍቃሪ ደግነቱ ስላለኝ ምስጋና የምመሰክረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

አትም