2010–2019 (እ.አ.አ)
የቆሰሉ
ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ)


የቆሰሉ

በምድራዊ አስከፊ ፈተናዎች፣ በትእግስት ወደፊት እንግፋ፣ እናም የአዳኝ የመፈወስ ኃይል ብርሃን፣ መረዳትን፣ ሰላምና ተስፋን ያመጣላችኋል።

በመጋቢት 22፣ 2016(እ.ኤ.አ) ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት በፊት በብራሰልስ አውሮፕላን ማረፊያ ሁለት የአሸባሪ ቦምቦች ፈንድተዋል። ሽማግሌ ሪቻርድ ኖርቢ፣ ሽማግሌ ሜሰን ዌልስ፣ እና ሽማግሌ ጆሴፍ ኤምፒ በክሊቭላንድ ኦሃዮ ውስጥ ለተሰጣት የወንጌል ተልዕኮ ለመሸኘት እህት ፋኒ ክሌንን ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ወስደው ነበር። ሠላሳ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፤ ሁሉም ሚስዮናውያኑ ቆስለዋል።

በጣም የቆሰለው የ66 ዓመቱ ሽማግሌ ሪቻርድ ኖርቢ ነበር ከባለቤቱ ከእህት ፓም ኖርቢ ጋር በማገልገል ነበር።

ሽማግሌው ኖርቢ ያንን ጊዜ ላይ ሲያንጸባርቅ፤

በፍጥነት፣ ምን እንደተፈጠረ አወኩኝ።

“ለደህንነት ለመሮጥ ሞከርሁ፣ ነገር ግን ወዲያውኑ ወደኩኝ። … ግራ እግሬ በክፉኛ ተጎድቶ ማየት እችል ነበር። ጥቁር የሸረሪት ድር የሚመስለው ጥቀርሻ ከሁለቱም እጆቼ ሲወርድ አየሁ። በእርጋታ ጎተትኩት፣ ግን ጥቀርሻ አለመሆኑን ተረዳሁ፣ ነገር ግን ቆዳዬ በእሳት ተቃጥሎ ነበር። ጀርባዬ በመጎዳቱ ምክንያት ነጭ ሸሚዜዬ ወደ ቀይ እየተቀየረ ነበር።

“ምን እንደተከሰተ ሃሳቤን እንደሞላኝ፣ በጣም ጠንካራ ሀሳብ አደረብኝ፣… አዳኝ የት እንዳለሁ፣ ምን እንደደረሰ፣ እና በዚያ ቅጽበት ያጋጠመኝን ያውቅ ነበር።1

ምስል
ሪችርድ ኖርቢ በታቀደ ኮማ

ለሪቻርድ ኖርቢ እና ለባለቤቱ ፓም ወደፊት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ነበሩ። በታቀደ ኮማ ውስጥ፣ ቀዶ ጥገና፣ ኢንፌክሽንና ከፍተኛ አለመተማመን ውስጥ ሆኖ ተቀመጠ።

ሪቻርድ ኖርቢ ኖረ፣ ነገር ግን የእሱ ሕይወት ፈጽሞ አንድ ዓይነት አልነበረም። ከሁለት ተኩል አመት በኋላ፣ ቁስሎቹ ገና እያገገሙ ነበር፤ በጉዳት ላጣው የእግር ክፍሎቹ በደጋፊ ብረት ተተክተዋል፤ እያንዳንዱ እርምጃ ከብሩሰልስ አውሮፕላን ማረፊያው ክስተት በፊት የተለየ ነው።

ምስል
ሪቻርድ እና ፓም ኖርቢ

ለምን ይሄ በሪቻርድ እና በፓም ኖርቢ ላይ ተከሰተ?2 ለቃል ኪዳናቸው እውነተኛ ነበሩ፣ በአይቮሪ ኮስት ሌላ የወንጌል ስብከት አገልግሎት አድርገው ነበር፣ እናም አስደናቂ ቤተሰብን አሳደጉ። አንድ ሰው መረዳት በሚቻል መልኩ “ይህ ተገቢ አይደለም! ሊል ይችላል። ይህ ትክክል አይደለም! ህይወታቸውን ለኢየሱስ ወንጌል በሚሰጡበት ውቅት፣ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?”

ይህም ሟችነት ነው።

ሁኔታው ልዩ ቢሆንም፣ አሳዛኝ ሁኔታዎች፣ ያልተጠበቁ ፈተናዎች እና ሙከራዎች፣ አካላዊም ሆነ መንፈሳዊ፣ ለእያንዳንዳችን ይመጡብናል ምክንያቱም ይህ ሟችነት ነውና።

በዚህ ጉባኤ ክፍል ስለነበሩት አነጋጋሪዎች በዚህ ጠዋት ሳስብ፣ ሁለቱ ልጆች እና ሶስቱ የልጅ ልጆች ሳይጠበቅበት ወደ ሰማይ ቤታቸው እንደተመለሱባቸው ተረዳሁኝ። ማንም በሽታን ወይም ሀዘን እዲገደብ የተደረገላቸው አልነበሩም፣ እናም እንደተነገረው፣ በዚህም ሳምንት፣ ሁላችንም የምናፈቅራቸው በምድር የነበሩ መላእክ፣ እህት ባርብራ ባለርድ፣ በመጋረጃው አልፈው ሄዱ። ፕሬዘደንት ባለርድ፣ በዚህ ጠዋት የሰጡትን ምስክርነት በምንም አንረሳም።

ደስታን እንሻለን። ሰላምን እንፈልጋለን። ፍቅርን ተስፋ እናደርጋለን። ጌታም አስደናቂ የበረከቶችን ብዛት ያዘንብብናል። ሆኖም ግን፣ ከደስታ ጋር ተጣምሮ የሚገኝ፣ አንድ ነገር በእርግጠኝነት ያለ ነገር ቢኖር፣ አንዳንድ ክስተቶች፣ ሰዓታት፣ ቀናት፣ አንዳንዴም ለአመታት ነፍሳችሁ ቆስሎ በሚጎዳበት ጊዜ ይሆናል።

ቅዱሳት መጻህፍት እንደሚያስተምሩት መራራውን እና ጣፋጩን እንቀምሳለን3 እንዲሁም “በሁሉም ነገሮች ተቃራኒ” እንደሚኖር ይናገራሉ።4 እየሱስ እንዳለው “[አባታችሁ] በክፉውም በመልካሙም ላይ ጸሃይን ያወጣል እና በጻድቃንም በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባል”።5

የነፍስ መቁሰል ለህብታም ወይም ለደሀ፣ ለአንድ ባህል፣ ለአንድ ብሔር ወይም ለአንድ ትውልድ ልዩ ሆነው የተሰጡ አይደሉም። ለሁሉም ይመጣሉ እናም ከዚህ ስጋዊ ህይወት የመማር አካል ናቸው።

ጻድቃን በሽታ የማይዛቸው አይደሉም

ዛሬ የእኔ መልእክት በተለይ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለሚጠብቁ፣ የእግዚአብሄርን ቃል ኪዳን ለሚጠብቁ፣ እና ልክ እንደ ኖርቢ ቤተሰብ ወይም በዚህ አለም አቀፍ ተሰብሳቢዎች መካከል እንደሚገኙ ሌሎች ወንዶች፣ ሴቶች፣ እና ልጆች፣ ባልተጠበቁ እና ባስቸጋሪ ፈተናዎች እና ችግሮች ላጋጠማችሁ ነው።

ቁስላችን ከተፈጥሮ አደጋ ወይም ድንገተኛ አደጋ ሊመጣ ይችላል፡፡ የጻድቅ ሚስትን እና ህፃናት ህይወትን የሚለውጥ ከከዳተኛ ባል ወይም ሚስት ይመጡ ይሆናል። ቁስሎቹ የሚመጡት ከመከፋት፣ ካልታወቀ ህመም፣ ከስቃይ ወይም ከምንወደው ሰው ከጊዜ በፊት መሞት፣ የቤተሰብ አባል የእርሱን ወይም የእርሷን እምነት በመጣሏ ባለ ሀዘን፣ ጉዳዮች የዘለአለም ጓዳኛን ባለማምጣታቸው ባለ ብቸኛነት፣ ወይም በብዙ መሮ ተስፋ በሚያስቆርጡ፣ የሚያሰቃዩ “አይኖች ለማየት የማይችሏቸው [ሀዘኖች]”6 ምክንያት ነው።

ችግሮች የሕይወት አካል እንደሆኑ እያንዳንዳችን እንገነዘባለን፣ ግን በግል ወደ እኛ ሲመጡ፣ ትንፋሻችንን ሊወስዱ ይችላሉ። ሳንፈራው ዝግጁ ልንሆን ይገባል። ሐዋሪያው ጴጥሮስ እንዲህ አለ፣ “በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደመጣባችሁ አትደነቁ።”7 ከደስታ እና ሃሴት ደማቅ ቀለሞች ጋር አብሮ ያለ፣ ጥቁር ቀለም ያለው የመከራ እና የችግር ገመዶች በአባታችን እቅድ ውስጥ በጥልቀት ተሳስረዋል። እነዚህ ትግሎች፣ አስቸጋሪ ቢሆኑም ብዙውን ጊዜ ታላቅ አስተማሪዎቻችን ይሆናሉ።8

የሔላማን 2060 ወጣት ወታደሮች ተዓምራዊ ታሪክ በምንናገርበት ወቅት፣ ይህንን ጥቅስ እንወዳለን፤ “በእግዚአብሔር ቸርነት፣ እናም ለመገረማችን፣ እናም ደግሞ ለሠራዊታችን ደስታ፣ አንድም ነፍስ አልጠፋብንም ነበር።”

ሆኖም ግን አረፍተነገሩ እንደዚህ ቀጠለ፣ “እናም ከእነርሱ መካከልም በብዙ ያልቆሰለ አንድም ነፍስ አልነበረም።”9 ከ2060ዎቹ መካከል እያንዳንዱ ብዙ ቁስሎን አገኙ፣ እናም እያንዳንዳችንም በህይወት ጦርነት፣ በስጋምይሁን በመንፈስ፣ ወይም በሁለቱም እንቆስላለን።

ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛ መልካም ሰማርያ ነው።

በምንም ተስፋ አትቁረጡ፣ ነገር ግን የነፍስ ቁስላችሁ፣ ምንጩ ምንም ቢሆን፣ መቼም ቢሆኑ የትኛውም ቦታ ቢከሰት፣ ለአጭር ወይም ለረጅም ጊዜ ቢቀጥሉ፣ እናንተ በመንፈሳዊነት እንድትጠፉ አይደለም። በመንፈሳዊ ህይወት ለመዳን እና በእግዚአብሔር ላይ በመተማመን እንድትበለጽጉ ነው።

እግዚአብሔር ከእርሱ ተለይተን ለመኖር መንፈሳችን አልፈጠረም። ጌታችን እና አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስሌት በሌለው የኃጢያት ክፍያ አማካይነት፣ ከሞት እኛን ከማዳን እና ለኃጢአታችን ይቅር ማለቱ ብቻ ሳይሆን፣ ነፍሳችን ከቆሰለባቸው ሥቃዮች እና ህመሞች እኛን ለማዳን ዝግጁ ነው። 10

ምስል
ጥሩው ሰማርያው

አዳኝ መልካሙ ሳምራዊ ነው፣11፣ “የተሰበረውን ልብ ለመፈወስ”12 የተላከውም። ሌሎች እኛን ሲያሳልፉ እሱ ወደኛ ይመጣል። በርህራሄ፣ ፈዋሽ እጁን በቁስላችን ላይ ያስቀምጣል እንዲሁም ያስረዋል። ይሸከመናል። እናም ያስብልናል። “ወደኔ ኑ … እኔም እፈውስላችኋለሁ” ብሎ ይጎተጉተናል።13

“እናም [ኢየሱስ] በመከራና በሁሉም ዓይነት ህመምና ፈተናዎች በመሰቃየት ይሄዳል፤ … የህዝቡን ህመምና በሽታ በራሱ ላይ ይወስዳል … [በራሱም ላይ] በሽታዎች፥ በምህረት ተሞልቶ፣ ይወስዳል።”14

ኑ፣ እናንተ ሃዘንተኞች፣ ከምትማቅቁበት ቦታ ሁሉ።

ወደ ምህረት ወንበር ኑ፣ በጥንካሬም ተንበርከኩ።

እዚህ የተጎዱ ልብዎቻችሁን አምጡ፣ እዚህ የሚያስጨንቁትን ተናገሩ።

ሰማይ መፈወስ የማይችለው ሀዘን ምድር የላትም።15

በታላቅ ስቃይ ጊዜ፣ ጌታ ለነቢዩ ጆሴፍ እንዲህ አለው፣ “እነዚህ ነገሮች በሙሉ ለአንተ አጋጣሚዎች ይሆናሉ፣ እናም ለአንተም ጥቅም ይሆናልሉ።”16 አሰቃቂ ቁስሎች ለእኛ ጥቅም የሚሆኑት እንዴት ሊሆን ይችላል? በምድራዊ አስከፊ ፈተናዎች፣ የአዳኝ የመፈወስ ኃይል ብርሃን፣ መረዳትን፣ ሰላምና ተስፋን ያመጣል።17

ተስፋ አትቁረጡ።

በሙሉ ልባችሁ ጸልዩ። በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በእሱ እውነታ፣ በእሱ ጸጋ ላይ ያላችሁን እምነት አጠናክሩ። ቃላቱን አጥብቃችሁ ያዙ፣ “ጸጋዬ ለአንተ ብቁ ነው፤ ጥንካሬዬ በደካማነት ፍጹም ይሆናልና።”18

አስታውሱ፣ ንስሃ ታላቅ መንፈሳዊ መድሃኒት ነው።19 ትእዛዛትን ጠብቁ እናም ለመፅናኛው ብቁ ሁኑ፣ አዳኝ ቃል የገባውን አስታውሱ፣ “ያለአፅናኚ አልተዋችሁ፥ ወደ እናንተ እመጣለው።”20

የቤተመቅደስ ሰላም የቆሰለ ነፍስን የሚያሰክን ቅባት ነው። በተቻለ መጠን ወደ ጌታ ቤት ቤተ መቅደስ ከተቆሰለ ልባችሁ እና የቤተሰቦቻችሁ ስሞች ይዛችሁ ተመላለሱ። ቤተመቅደስ በሟችነት ውስጥ ያለን አጭር ጊዜን በዘለአለማዊው መመልከቻ ገጽ ያሳያል። 21

በቅድመ-ህይወትዎ ውስጥ ብቁነታችሁን ማረጋገጣችሁን ወደ ኋላ ዞር ብላችሁ ተመልከቱ። ብርቱ የእግዚአብሄር ልጅ ናችሁ፣ እናም በእርሱ እርዳታ፣ በዚህ በወደቀ ዓለም ውስጥ ያለውን ውጊያ ድል ማድረግ ትችላላችሁ። ከዚህ ቀደም ይህን አድርጋችኋል፣ እና እንደገና ማድረግ ትችላላችሁ።

ወደፊት ተመልከቱ። መከራችሁና ሐዘናችሁ በጣም እውን ናቸው፣ ነገር ግን ለዘላለም አይኖሩም።22 ጨለማው ምሽታችሁ ያልፍል፣ ምክንያቱም “ወልድ … ፈውስን በክንፎቹ ይዞ [ተነስቷልና]።23

የኖርቢ ቤተሰብ እንዲህ አሉኝ፣ “መበሳጨት አልፎ አልፎ ይመጣል ነገር ግን ለመቆየት ፈጽሞ አይፈቀድለትም።”24 ሐዋሪያው ጳውሎስ እንዲህ ብሏል፣ “በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፣ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፣ እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፣ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም። “25 ተዳክማችሁ ይሆናል ነገር ግን ተስፋ መቁረጥ የለባችሁም።26

በሚያሰቅቅ በምትቆስሉበትም፣ የአዳኝን ቃል ኪዳን በማመን፣ ወደሌሎች ለእርዳታ ትደርሳላችሁ “ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል።”27 የሌሎችን ቁስል የሚያክመው ተቆሳይ በምድር ላይ የእግዚአብሔር መላእክቶች ናቸው።

ከትንሽ ጊዜዎች በኋላ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የማይቀየር እምነት ካላቸው፣ የተስፋ እና ሰላም ሰው፣ በእግዚአብሔር ቢወደዱም የነፍስ ቁስሎች ካላመለጧቸው ከውድ ነቢያችን፣ ከፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንሰማለን።

በ1995 (እ.አ.አ) ሴት ልጃቸው ኤሚሊ እርጉዝ እያለች ነቀርሳ እንዳለባት ታወቀ። ጤናማ የሆነ ሕፃኗ በምትወልድበት ጊዜ ሁሉ ተስፋና ደስታ ቀኖች ነበሩ። ይሁን እንጂ ካንሰር ተመልሶ መጣ፣ የሚወዷት ኤሚሊ ከ37 አመት ልደቷ በሁለት ሳምንት በኋላ፣ አፍቃሪ ባልዋ እና አምስት ትንንሽ ልጆቿን ትታ ከዚህ ህይወት አለፈች።

ምስል
ፕሬዘዳንት ኔልሰን በ1995 (እ.አ.አ) ሲናገሩ

በአጠቃላይ ጉባኤ፣ እሷ ካለፈች ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ ፕሬዘደንት ኔልሰን እንዲህ በማለት ተናግረዋል፣ “ለሴት ልጃችን ተጨማሪ ነገር ለማድረግ ከምችለው በላይ የሃዘን እንባዬ ከምኞቴ ጋር ፈሰዋል። … የትንሣኤ ኃይል ቢኖረኝ፣ እሷን ለማምጣት እፈተን ነበር። … [ኢየሱስ ክርስቶስ] ግን እነዚህን ቁልፎች አለው፣ ለኤሚሊ … እና ለሁሉም ሰዎች በጌታ በራሱ ሰአት ይጠቀምባቸዋል።”28

ምስል
ፕሬዘዳንት ኔልሰን በፖርቶሪኮ ውስጥ

ባለፈው ወር፣ በፖርቶ ሪኮ ውስጥ ያሉትን ቅዱሳን በመጎብኘት እና ባለፈው ዓመት አሰቃቂውን አውሎ ንፋስ በማስታወስ ፕሬዚዳንት ኔልሰን በፍቅር እና ርህራሄ ጋር ተናግረዋል፥

“[ይህ] የሕይወታችን ክፍል ነው። ለዚህ ነው እኛ እዚህ ያለነው። አካል ለመኖር እና ለመሞከር እና ለመፈተን እዚህ አለን። እነዚህ ፈተናዎች አንዳንዶቹ አካላዊ ናቸው፣ አንዳንዶቹ መንፈሳዊ ናቸው፣ እናም እዚህ ያሉት ፈተናዎቻችሁ አካላዊም እና መንፈሳዊም ናቸው።“29

“ተስፋ አልቆረጣችሁም። በእናንተ [በጣም] እንኮራለን። እናንተ ታማኝ ጻድቃን ብዙ አጥታችኋል፣ ነገር ግን በሁሉም ነገር በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት አላችሁ።“30

“የአምላክን ትእዛዛት በማክበር በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንኳ ደስታ ልናገኝ እንችላለን.”31

እምባውዎች ሁሉ ይጠረጋሉ

ወንድሞቼና እህቶቼ, በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን ማሳደግ ተጨማሪ ጥንካሬ እና ታላቅ ተስፋን እንደሚያመጣላችሁ ቃል እገባላችኋለሁ። ለእናንተ ለጻድቃን የነፍሳችን ፈዋሽ በእሱ ጊዜ እና በመንገዱ ቁስላችሁን ሁሉ ይፈውሳል።32 ምንም ዓይነት ኢፍትሀዊነት፣ ስቃይ፣ መከራ፣ ሀዘን፣ መከራ፣ ሥቃይ፣ ቁስለት ምንም እንኳን ጥልቅ ቢሆንም፣ ሰፊ ቢሆንም ምንም ያህል የሚያም ቢሆንም፣ እነዚህም ከምቾቱ፣ ከሰላሙ፣ እና ከዘለአለማዊ ተስፋው ጋር የተዘረጉት እና የቆሰሉት እጆቹ ወደ እርሱ ዘንድ ይቀበሉናል። በዚያን ቀን፣ በሐዋርያው ​​ዮሐንስ እንደመሰከረው፣ “በታላቁ መከራ” ተፈትነው የሚመጡ ጻድቃን33 “በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ነጭ ልብስ ለብሰው” ይቆማሉ። በጉ ‘[በመካከላችን] ይኖራል’ … እግዚአብሔርም [እንባችሁን] ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል.34 ያም ቀን ይመጣል። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. የግል ንግግር፣ ሰኔ 26፣ 2018 (እ.አ.አ)።

  2. በዚህ ዓመት ቀደም ብሎ በተደረገ ውይይት ውስጥ ሪቻርድ ኖርቢ “ለተሰጠን መልስ እንሰጣለን” አለኝ። ከማስታወሻው ውስጥ ይህን ተካፈለ፥ “እያንዳንዳችን የሚሰጠን ሙከራ እና ፈተናዎች አዳኝን የበለጠ ለመገንዘብ እድል እና አጋጣሚ ይሰጣሉ እና የሃጢያት ክፍያ መስዋዕቱን በጥልቀት ለመገንዘብ ይረዳሉ። የምንሞረከዘው በእርሱ ላይ ነው። እርሱን ነው የምንፈልገው። የምንደገፈው በርሱ ላይ ነው። መተማመናቸን በርሱ ላይ ነው። እርሱን ነው በፍጹም ልባችን ያለምንም መቆጠብ የምንወደው፣። አዳኙ የሟችነት አካል የሆኑትን ሁሉንም አካላዊ እና ስሜታዊ ህመሞች ሸፍኗል። ህመሙን ከእኛ ይወስዳል። ሀዘናችንን ይወስዳል።”

  3. ትምህርት እና ቃል ኪዳን 29፥39 ተመልከቱ።

  4. 2 ኔፊ 2፥11

  5. ማቴዎስ 5፣45።

  6. “Lord, I Would Follow Thee,” Hymns, no. 220.

  7. 1 ጴጥሮስ 4፥12።

  8. “ጌታ አምላካቸው የሚያዛቸውን ማናቸውንም ነገሮች ሁሉ እንደሚያደርጉ ለማየት፣ በዚህ እንፈትናቸዋለን” (አብርሐም 3፥25፤ ደግሞም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥4-5 ይመልከቱ)።

  9. አልማ 57፧25።

  10. ከጓደኛ እንዲህ ጻፈልኝ፤ “በስሜታዊነት ‘ጨለማ እና ድባብ’ ለአምስት ዓመታት በተለያየ ደረጃ ላይ የሚደረግ ውጊያ በአቅም፣ በእምነት እና በትዕግስት መጨረሻ ጫፍ ለመድረስ ይረዳችኋል። ከቀናት ‘ስቃይ’ በኋላ ይደክማችኋል። ከሳምንታት ‘ስቃይ’ በኋላ አቅማችሁ ይሟጠጣል። ከወራት ‘ስቃይ’ በኋላ የቆማችሁበትን መሬት መሳት ትጀምራላችሁ። ከብዙ ዓመታት ‘ስቃይ’ በኋላ ለወደፊቱ መቼም ቢሆን እንደማትሻሻሉ ታስባላችሁ። ተስፋ እጅግ በጣም ውድ እና ምእናባዊ ስጦታ ይሆናል። በአጭሩ ይህ ፈተና እንዴት እንዳለፍኩት እርግጠኛ አይደለሁም፣ አዳኝ ብቻ ካልሆነ በስተቀር። ይህ ብቸኛው ማብራሪያ ነው። እኔ ከማወቄ በስተቀር ይህን እንዴት እንደማውቅ ልገልጽ አልችልም። በእሱ ምክንያት፣ ይህንን አለፍኩኝ።”

  11. ሉቃስ 10፥30-35ተመልከቱ።

  12. ሉቃስ 4፥18ደግሞም ኢሳያስ 61፥1 ተመልከቱ።

  13. 3 ኔፊ 18፥32።

  14. አልማ 7፥11-12 “He descended below all things, in that he comprehended all things” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥6)

  15. “ኑ፣ እናንተ ሃዘንተኞች” መዝሙር ቁጥር 115።

  16. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122፥7።

  17. “የእግዚአብሔርን ታላቅነት ታውቃለህ፤ እናም እርሱ መከራህን ወደ በረከት ይለውጥልሃል” (2 ኔፊ 2:2)። “እምነታቸውን በእግዚአብሔር ላይ ያደረጉ ሁሉ፣ በፈተናቸው፣ እናም በችግራቸው፣ እናም በስቃያቸው እንደሚደገፉ፣ እናም በመጨረሻው ቀን ከፍ እንደሚደረጉ አውቃለሁ።” (አልማ 36:3)።

  18. 2 ቆሮንቶስ 12፥9።

  19. See Neil L. Andersen, “The Joy of Becoming Clean,” Ensign, Apr. 1995, 50–53.

  20. ዮሐንስ 14፥18።

  21. “በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ካደረግን፣ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን” (1 ቆሮንቶስ 15:19)።

  22. በመፅሐፈ ሞርሞን የመጀመሪያ አንቀፅ ውስጥ፣ ኔፊ እንዲህ ገለጸ፣ “በዘመኔም ብዙ መከራን ብመለከትም” (1 ኔፊ1:1)። ቀጥሎም ኔፊ እንዲህ አለ፣ “ወደ አምላኬ ተመለከትኩኝ፣ እናም ቀኑን ሙሉ እርሱን አመሰገንኩኝ፤ እናም በመከራዬ የተነሳ በጌታ ላይ አላጉረመረምኩም” (1 ኔፊ 18:16)።

  23. 3 ኔፊ 25፥2{120}።

  24. የግል ንግግር፣ ጥር 26፣ 2018 (እ.አ.አ)።

  25. 2 ቆሮንቶስ 4፥8-9

  26. ፕሬዘደንት ሂዮው ብ. ብራውን፣ እስራኤልን እየጎበኙ እያሉ፣ አብርሐም ለምን ልጁን እንዲሰዋ እንደታዘዘ ተጠየቁ። እንዲህ መለሱ፣ “አብርሐም ስለአብርሐም አንድ ነገር መማር ነበረበት” (in Truman G. Madsen, Joseph Smith the Prophet [1989], 93)።

  27. ማቴዎስ 16፣25።

  28. Russell M. Nelson, “Children of the Covenant,” Ensign, May 1995, 32.

  29. Russell M. Nelson, in Jason Swensen, “Better Days Are Ahead for the People of Puerto Rico,” Church News, Sept. 9, 2018, 4.

  30. Russell M. Nelson, in Swensen, “Better Days Are Ahead,” 3.

  31. Russell M. Nelson, in Swensen, “Better Days Are Ahead,” 4.

  32. See Russell M. Nelson, “Jesus Christ—the Master Healer,” Liahona, Nov. 2005, 85–88.

  33. ራዕይ 7፥14።.

  34. ራእይ 7፥13፣ 15፣ 17 ይመልከቱ።

አትም