ሴቶች እና በቤት ውስጥ ወንጌልን መማር
በቤት ውስጥ ወንጌልን በመማር ላይ ታላቅ ትኩረትለማድረግ በሚያካትታቸው ውስጥ ታላቅ ክፍል እንደት እንደሚኖራችሁ ለማወቅ አዳኝ የእናንተ ፍጹም ምሳሌ ነው።
ውድ እህቶቼ፣ ከእናንተ ጋር መገናኘቱ አስደሳች ነው። ይህ ለየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አስደናቂ ጊዜ ነው። እግዚአብሔር ቃል እንደገባው በቤተክርስቲያኑ ላይ እውቀቶችን እያፈሰሰ ነው።
እርሱ ያለውን ታስታውሳላችሁ፥ “እስከመቼ ጊዜ የሚደበላለቀው ውሀ ንጹህ ሆኖ ሊቆይ ይቻለዋል? የትኛውስ ሀይል ሰማያትን ሊያቆም ይችላል? በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ራሶች ላይ ሁሉን የሚገዛው ከሰማይ እውቀቶችን ማፍሰሱን ከሚያቆም፣ ሰው ደካማ ክንዶቹን ዘርግቶ የሚዙሪን ወንዝ ከተወሰነለት መንገዱ ያቆም ዘንድ ወይም ተቃራኒው እንዲዞር ለማድረግ ቢሞክር ይቀለዋል።”1
ጌታ እውቀትን የመካፈሉ ክፍልም ዘለአለማዊ እውነቶችን በህዝቦቹ ራሶች እና ልቦች ላይ ማፍሰሱን ማፋጠኑ ነው። በዚህ ታዕምራታዊ ፍጥነትም የሰማይ አባት ሴት ልጆች ዋና ድርሻ እንዳላቸው ግልፅ አድርጓል። የታዕምራቱ አንዱ ማስረጃ ህያው ነቢዩ እንዴት በወንጌል ትምህርትን በቤት እና በቤተሰብ ውስጥ እንዲከናወን ታላቅ ትኩረር እንዲሰጥ መምራቱ ነው።
“ጌታ በቅዱሳኑ ላይ እውቀቶችን ለማፍሰስ ለመርዳት እንዴት ታማኝ እህቶች ቀዳሚ ሀይሎች ያደርጋቸዋል?” ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል። ጌታም መልሱን በ“ቤተሰብ፡ ለአለም የተላለፈ አዋጅ” ውስጥ ሰጥቷል። ቃላትን ታስታውሳላችሁ፣ ነገር ግን አዲስ ትርጉም ለማየት እና ጌታ አሁን የሚሆኑት እነዚህን አስደሳች ለውጦች አስቀድሞ እንዳየ ለመገንዘብ ትችሉ ይሆናል። በአዋጁ ውስጥ፣ ለእህቶች በቤተሰብ ውስጥ ዋና የወንጌል አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሀላፊነትን በእነዚህ ቃላት ሰጣቸው፥ “እናቶች በቀደምትነት ልጆቻቸውን የመንከባከብ ሀላፊነት አለባቸው።”2 ይህም የወንጌል እውነት እና እውቀትን መንከባከብን ያካትታል።
አዋጁም እንዲህ ይቀጥላል፥ “በእነዚህ ቅዱስ ሀላፊነቶችም፣ አባቶች እና እናቶች በእኩል አጋርነታቸው የመረዳዳት ሀላፊነት አለባቸው።”3 ለመንፈሳዊ እድገታቸው እና እውቀትን ለማግኘት እኩል እድል እኩል ናቸው፣ እናም እርስ በርስ በመተባበር አንድነት አላቸው። በአንድነት ከፍ ከፍ በሚደረጉበት መለኮታዊ ዕጣዎቻቸው እኩል ናቸው። በእርግጥም፣ ወንዶች እና ሴቶች በብቻቸው ከፍ ከፍ ለመደረግ አይችሉም።
ታዲያ በእኩልነት እና በእኩልነት ግንኙነት ውስጥ ያለች የእግዚአብሔር ሴት ልጅ፣ እጅግ በጣም አስፈላጊ ንጥረ-ነገር፣ ማለትም ከሰማይ የመጣ የእውነት እውቀትን፣ ለመመገብ ለምን ዋና ሀላፊነትን ተቀበለች? በአስተያየቴ፣ በዚህ ዓለም ቤተሰቦች ከተፈጠሩ ጀምሮ ይህ የጌታ መንገድ ነበር።
ለምሳሌ፣ አዳም ሁሉንም የእግዚአብሄር ትዕዛዛት ለማክበር እና ቤተሰብን ለመመሥረት ከእውቀት ዛፍ ፍሬ ለመብላት እንዳለበት እውቀት የተቀበለችው ሔዋን ነበረች። በመጀመሪያ ወደ ሔዋን ለምን እንደመጣ አላውቅም፣ ነገር ግን አዳምና ሔዋን እውቀት በአዳም ላይ ሲፈስ ፍጹም አንድነት ነበራቸው።
ጌታ የሴቶች የመንከባከብ ስጦታዎችን የሚጠቀምበት ሌላ ምሳሌም የሄለማንን ልጆች ያጠናከረበት መንገድ ነው። ታሪኩን በማነብበት ጊዜ በጉሮሮዬ ውስጥ እብጠት ይሰማኛል እናም ለወታደራዊ አገልግሎት ከቤት ስወጣም እናቴ የተናገረችው መፅናናት የሚሰጥ ቃሏን አስታውሳለሁ።
ሔላማን እንደጻፈው፥
“አዎን፣ በእናቶቻቸውም ጥርጣሬ ከሌለባቸው እግዚአብሔር እንደሚጠብቃቸው ተምረዋል።
“እናም እናቶቻቸው የተናገሩትን ቃላት እንዲህ ሲሉም ነገሩኝ፥ እናቶቻችንም ይህን እንደሚያውቁት ጥርጣሬ አልነበረንም።”4
ጌታ በቤት ውስጥ የመንከባከብን ዋና ሀላፊነት ለምን ለታማኝ እህቶች እንደሰጠ ባላውቅም፣ ከመውደድ አቅም ጋር የተያያዘ እንደሆነ አምናለሁ። ከራስዎ ይልቅ የሌላውን ሰው ፍላጎቶች ለመረዳት ከፍተኛ ፍቅር ይጠይቃል። ለዛም ለምትንከባከቡት ሰው የክርስቶስ ንጹህ ፍቅር ይህ ነው። ያ የደግነት ስሜት የሚመጣው ለመንከባከብ የተመረጠ ሰው ነው ለኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ውጤት ብቁ በመሆን ነው። እናቴ ምሳሌ የነበረችበት፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር መፈክርም ለእኔ የሚያነሳሳ ይመስለኛል፥ “ልግስና በምንም አትወድቅም።”
እንደ እግዚአብሔር ሴት ልጆች፣ የሌሎችን ፍላጎቶች ለመለየት እና ለማፍቀር የሚያስችል ውስጣዊ እና ታላቅ አቅም። ያ ደግሞ፣ ወደ መንፈስ ቅዱስ ሹክሹክቶች የበለጠ ስሜት እንዲኖራችሁ ያደርጋል። ጌታ እውቀትን፣ እውነትንና ድፍረትን ሊያፈስባቸው ይችል ዘንድ ምን እንድታስቡ፣ ምን እንድትናገሩ እና ሰዎችን ለመንከባከብ ምን እንደምታደርጉ መንፈስ ቅዱስ ሊመራችሁ ይችላል።
ድምጼን የምትሰሙት እህቶች እያንዳንዳችሁ በህይወት ጉዞዋችሁ ልዩ ቦታ ላይ ነው ያላችሁት። አንዳንዱ በአጠቃላይ የሴቶች ስብሰባ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገኙ ወጣት ሴቶች ናቸው። ጥቂቶቹ ወጣት ሴቶች እግዚአብሔር ተንከብካቢ እንዲሆኑ እንደሚጠብቃቸው እየተዘጋጁ ናቸው። አንዳንዶች ገና ልጆች የሌሏቸው ገና የተጋቡ ናቸው፣ ሌሎችም አንድ ወይም ተጨማሪ ልጆች ያሏቸው ወጣት እናቶች ናቸው። አንዳንዶቹ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆች ያሏቸው እናቶች እና ሌሎች በወንጌል መስበኪያ መስክ ውስጥ ያሉ ልጆች ያሏቸው ናቸው። አንዳንዶች በእምነታቸው የተዳከሙና ከቤታቸው የራቁ ልጆች አሏቸው። አንዳንዶች ያለ ታማኝ ባለቤት በብቻቸውን ይኖራሉ። አንዳንዶች አያቶች ናቸው።
ነገር ግን፣ የግል ጉዳያችሁ ምንም ቢሆን፣ በወደፊትም ፣ በዚህ አለምም፣ ወይም በመንፈስ አለም ውስጥ፣ እናንተ የእግዚአብሔር ቤተሰብ እና የራሳችሁ ቤተሰብ ክፍል—አስፈላጊ ቁፍል—ናችሁ። ክእእግዚአብሔር በአደራ የተሰጣችሁም በፍቅራችሁ እና በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ እምነት በኩል የምትችሉትን ያህል የእርሱን እና የእናንተን የቤተሰብ አባላት እንድትንከባከቡ ነው።
የእናንተ ተግዳሮትም ማንን፣ እንዴት እና መቼ ለመንከባከብ እንደሆነ ማወቅ ነው። የጌታ እርዳታ ያስፈልጋችኋል። የሌሎችን ልብ ያውቃል፣ እናም የእናንተን እንክብካቤ ለመቀበል ዝግጁ ሲሆኑ ያውቃል። የእምነት ጸሎታችሁ ለስኬታማነታችሁ ዋና ቁልፍ ነው። በእርሱ አመራር በመቀበል ለመመካት ትችላላችሁ።
ይህን ማበረቻቻ ሰጥቷል፥ “እንደምትቀበሉ በማመን በእምነት አባቴን በስሜ ጠይቁ እናም ለሰው ልጆች አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ የሚገልጠውን መንፈስ ቅዱስ ይኖራችኋል።”5
ከጸሎት በተጨማሪ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን በማስተኮር ማጥናትም በመንከባከብ ሀይል የማደጋችሁ ክፍል ይሆናል። ይህም ቃል ኪዳን ነው፥ “ነእንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፣ ነገር ግን ዘወትር የህይወትን ቃል በአዕምሮዎቻችሁ ውስጥ አከማቹ፣ እና ይህም በዚያች ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰው ተመዝኖ የሚሰጠው ይሰጣችኋል።”6
ስለዚህ ተጨማሪ ጊዜ ለመጸለይ፣ ለማሰላሰል፣ እና በመንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ለማተኮር ጊዜ ትወስዳላችሁ። የእውነት እውቀት በእናንተ ላይ ይፈሳል እናም ቤተሰባችሁ ሌሎችን የምትንከባከቡበት ሀይል ይጨምራል።
እንዴት በተሻለ እንደምትንከባከቡ የምትማሩበት ቀስ ያለ እንደሆነ የሚመስልባችሁ ጊዜ ይመጣል። ይህም ለመፅናት እምነት ያስፈልገዋል። አዳኝ ይህን ማበረታቻ ልኮላችኋል፥
“ስለዚህ መልካም በማድረግ ላይ አትዛሉ፣ የታላቁን ጋብቻ መሰረት እየጣላችሁ ነውና። እናም ከትንንሾቹ ነገሮች ታላቅ የሆነው ይወጣል።”
“እነሆ፣ ጌታ ልብን እና ፍላጎት ያለውን አዕምሮ ይፈልጋል፤ እናም ፍላጎት ያለው እና ታዛዡም በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት የፅዮን ምድርን በረከት ይበላሉ።”7
በዚህ ምሽት መገኘታችሁም ሌሎችን ለመንከባከብ ጌታ የሚሰጣችሁን ሀላፊነት ለመቀበል ፈቃደኞች እንደሆናችሁ መረጃ ነው። ይህም በዚህ ምሽት ከሁሉም በላይ ታናሽ ለሆኑትም እውነት ነው። ማንን በቤተሰባችሁ ውስጥ ለመንከባከብ እንደሚያስፈልጋችሁም ለማወቅ ትችላላችሁ። በእውነት ፍላጎት ከጸለያችሁ፣ ስም ወይም ፊት በአዕምሮአችሁ ይመጣላችሁል። ምን ለማድረግ እና ምን ለማለት ለማወቅ ከጸለያሁ፣ መስል ይሰማችኋል። ታዛዥ በምትሆኑበት በእያንዳንዱም ጊዜ፣ የመንከባከብ ሀይላችሁ ያድጋል። የራሳችሁ ልጆች ለምትንከባከቡበት ቀናት ትዘጋጃላችሁ።
በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆች እናቶች ለመንከባከብ ፈቃደኛ የማይመስለውን ወንድ ወይም ሴት እንዴት መንከባከብ እንደሚችሉ ለማወቅ መጸለይ ይችላሉ። ልጅዎ የሚያስፈልገውን የመንፈሳዊ ተፅኖ ማን ሊኖረው እና ሊቀበለው የሚችልን ለማወቅ ለመጸለይይ ትችላላችሁ። እግዚአብሔር እንደዚህ አይነት በልብ የሚሰሙ የሀሳብ ጸሎቶችን ይሰማል እናም ይመልሳል፣ እንዲሁም እርዳታን ይልካል።
ደግሞም፣ በዚህ ምሽት አንድ አያት በልጆቿ እና በልጅ ልጆቿ ጭንቀቶችና እና ችግሮች የልብ መሰበር ይሰማት ይሆናል። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ከሚገኙ ከቤተሰብ ልምዶች ድፍረትና መመሪያን ልታገኙ ትችላላችሁ።
ከአዳም እና ሔዋን ጊዜ ጀምሮ፣ በአባት እስራኤል በኩል፣ እናም በመፅሐፈ ሞርሞን እያንዳንዱ ቤተሰብም፣ መልስ ስለማይሰጡ ልጆች ላለው ሀዘን አንድ እርግጠኛ ትምህርት አለ፥ በምንም ማፍቀርን አታቁሙ።
የሰማይ አባቱን ትዕቢተኛ ልጆች ሲመግብ የአዳኝ ማበረታቻ የተግባር ምሳሌ አለን። እኛ እና እነርሱ ስቃይን ስናመጣም እንኳ፣ የአዳኝ እጅ አሁንም ተዘርግትዋል።8 በ3 ኔፊ ውስጥ ለመንከባከብ ያለው ጤታማነት ለሞከረላቸው መንፈሳዊ ወንድሞቹ እና እህቶቹ ተናግሯል፥ “አቤቱ … ሰዎች፣ የእስራኤል ቤት የሆናችሁ፣ ዶሮ ጫጩትዎችዋን በክንፎችዋ እንደምትሰበስብ ስንት ጊዜ ሰበሰብኳችሁ እናም መገብኳችሁ።”9
በሁሉም የቤተሰብ ሁኔታ እና በተለያዩ ባሕሎች ሁሉ የሚገኙ በእያንዳንዱ የህይወት ጉዞ ውስጥ ላሉ እህቶች፣ አዳኝ በቤት እና በቤተሰብ ውስጥ የወንጌል ትምህርት የበለጠ ትኩረት ለመስጠት እንዴት ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ የሚያሳይ ምሳሌ ነው።
በተፈጥሮ ያላቹህን የበጎ አድራጎት ስሜት በቤተሰብህ ውስጥ በእንቅስቃሴዎች እና አሰራሮች ላይ ለውጣችሁ ታመጣላቹህ። ያም ታላቅ መንፈሳዊ እድገትን ያመጥል። ከቤተሰብ አባላቶቻችሁ ጋር እና ለእነርሱ ስትጸልዩ፣ ለእነርሱ እናንተ እና አዳኝ ያላችሁ ፍቅር ይሰማችኋል። ያንን ስትፈልጉ መንፈሳዊ ስጦታችሁ እየጨመረ ይሄዳል። የቤተሰብ አባሎችዎ በታላቅ እምነት ስትጸልዩም ይህ ይሰማቸዋል።
ቤተሰቦች ቅዱሳት መጻህፍትን ጮክ ብለው ለማንበብ በሚሰበሰቡበት ጊዜ፣ አስቀድማችሁ እነዚህን አንብባችሁ እና እራሳችሁን ለማዘጋጀት ጸልያችኋል። መንፈስ አዕምሮአችሁን እንዲያብራራ ለመጸለይ ጊዜዎችን ታገኛላችሁ። ከዚያም፣ ለማንበብ የእናንተ ተራ ሲሆንም፣ የቤተሰብ አባላት ለእግዚአብሔር እና ለቃላቱ ያላችሁ ፍቅር ይሰማችኋል። በእርሱ እና በመንፈሱ እንክብካቤን ያገኛሉ።።
የምትጸልዩበት እና እቅድ ካላችሁ ይህም መንፈሳዊ በረከት በማንኛውም የቤተሰብ መሰብሰብ ሊመጣ ይችላል። ይህም ጥረት እና ጊዜን ይወስዳል፣ ነገር ግን ያም ታዕምራቶችን ያመጣል። በልጅነቴ እናቴ ያስተማረችኝን አስታውሳለሁ። በአዕምሮዬ ስለሐዋርያ ጳውሎስ ጉዞ የሰራችው በቀለም የተቀባ ካርታን አያለሁ። ያን ለማድረግ እንዴት ጊዜ እና ሀይል እንዳገኘች ይገርመኛል። እናም እስከዚህ ቀን ድረስ ለዚያ ታማኝ ሐዋርያ በነበራት ፍቅሯ ተባርኬአለሁ።
በዳግም በተመለሰችው ቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉት በቤተሰቦቻችሁ ላይ በሚፈሰው እውነት አስተዋፅዖ ለማድረግ እያንዳንዳችሁ መንገድ ታገኛላችሁ። እያንዳንዳችሁ ትጸልያላችሁ፣ ታጠናላችሁ፣ እና የእናንተ ልዩ አስተዋፅዖ ምን እንደሆነ ለማወቅ ታሰላስላላችሁ። ነገር ግን ይህን አውቃለሁ፥ እያንዳንዳችሁ፣ ክእግዚአብሔር ወንድ ልጆች ጋር በእኩልነት ተሳስራችሁ፣ የእስራኤል መሰብሰብን በሚያፋጥኑት እና የእግዚአብሔር ቤተሰብን ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መመለስ በሚያዘጋጁ በወንጌል ትምህርት እና ህይወት ታዕምራት ውስጥ ታላቅ ክፍል ይኖራችኋል። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።