እረኛ መሆን
የምታገለግሏቸው እንደ ጓደኛ እንዲያዩአችሁ እና በእናንተ ተከላካይና ታማኝ ሰው እናላቸው እንዲረዱ ተስፋ አለኝ።
ከአንድ አመት በፊት፣ በችሊ ውሰጥ ያገኘሁት አንድ ህፃን ልጅ በፍቴ ላይ ፋገግታን አመጠ። “ሰለም፣” አለኝ፣ “ዴቪድ እባለለሁ። በአጠቃለይ ጉበኤ ላይ ስለ እኔ ትነጋርያለሽን?”
በጻጥታ ግዜያት፣ የዴቪድ ያልተጠበቀ ሰለምታውን አሰላስላለሁ። ሁላችንም ተዋቂዎች ለመሆን እንፈልጋለን። ዝንባሌ ያለን፣ ሌሎች የሚያስታውሱን እና የምንወደድ ሆኖ እንዲሰማን እንፋልጋለን።
እህቶችና ወንድሞች፣ እያንዳንዳችሁ አስፋለጊ ናችሁ። ምንም እንኳን በአጠቃለይ ጉበኤ ስለ እናንቴ ባይወራም፣ አዳኝ ያውቃችኋል እናም ይወዳችኋል። ይህ እውነት መሆኑን መወቅ ከፋለገችሁ፣ “በእጆቹ መዳፍ ላይ እንዳስቀራፃችው”1 ማሰብ ብቻ ነው የሚያስፈልጋችሁ።
አዳኛችን እንደሚወደን በማወቅ፣ እኛ ደግሞ ለእሱ ያለንን ፍቅር በተሻለ መንጋድ መሳየት የምንችልበትን መንገድ ይኖርላርምን? ብለን እናስብበት ይሆናል።
አዳኝ ጴጥሮስን እልዲህ ብሎ ጠየቀው፣ “ትወደኛለህን … ?”
ጴጥሮስም መልሶ “አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ግልገሎቼን አሰማራ አለው።”
ይህን ጥያቄ፣ “ትወደኛለህን?” ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ጊዜ ሲጠየቅም፣ ጴጥሮስም አዘነ፣ ግን ፍቅሩንም አረጋገጠ፥ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ኢየሱስም። በጎቼን አሰማራ።”2
ጴጥሮስ፣ አፍቃሪ የክርስቶስ ተከተይ መሆኑን አላረጋገጠምን? በበሕሩ ደርቻ ለይ በነበራቸው የመጀመሪያ ግኑኝነት ጀምሮ፣ የአሳ ማጥመጃ መረቡን “ወዲያው” ትቶ አዳኝን ተከተለ።3 ጴጥሮስ እውነተኛ የሰዎች አጥማጅ ሆነ። በአደኙ የግል አገልግሎት ጊዜ አብሮ በመሆንና የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለሌች በማስተመር የታመነ ደቀመዝሙር ነበር።
አሁን ግን ከሞት የተነሣው ጌታ ከእንግዲህ ከጴጥሮስ ጎን እንደማይሆን አውቆ፣ እንዴት እንደሚያገለግልና መቼ ማገልገል እንደለበት አሳየው። በአዳኝ አለመኖር፣ ጴጥሮስ የመንፋስ ቅዱስ አቅጣጫን መሻት፣ የራሱን ራዕይ መቀበል፣ ከዚያም ለመስራት እምነትና ድፍረት እንዲኖረው ያስፈልጋል። በበጎቹ ላይ በማተኮር፣ አዳኝ እሱ እዛ ቢሆን የሚያደርገውን ጴጥሮስ እንዲያደርግ ፈለገ። ጴጥሮስን እራኛ እንድሆን ጠየቀው።
ባለፈዉ ሚያዝያ፣ ፕሬዝደንት ራስል ኤም. ኔልሰን የአባታችንን በጎች ይበልጥ በተቀደሰ መንገድ እንድንመግባቸውና ስናደርግም በአገልግሎት መልክ እንድሆን ጥሪ አቅርበውልን ነበር።4
ይህንን ግብዣ በሚገባ ለመቀበል፣ የእረኛ ልብ ሊኖረን ይገባል እናም የጌታን በጎች ፍላጎት ማወቅ አስፈላጊ ነው። ስለዚህ እንዴት ነው ጌታና እንድንሆን የሚፈልጉትን አይነት እረኞች መሆን የምንችለው?
ልክ እንደ ሌሎች ጥያቄዎች ሁሉ፣ ወደ መልካም እራኛው፣ ወደ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ መመልከት እንችላለን። የአዳኙ በጎች የሚታወቁና የተቆጠሩ እንደሆኑ እንማራለን፤ እናም ይጠበቃሉ፤ እናም ወደ እግዚአብሔር እቅፍም ተሰብስበዋል።
የሚታወቁና የሚቆጠሩ
የአደኛችንን ምሳሌ ለመከተል ስንጥር፣ በመጀመርያ የእርሱን በጎች ማወቅና መቁጠር ይኖርብናል። አንድም ሰው እንደይረሳና ሁሉንም የጌታ በጎች ለመቁጠር የተወሰኑ ግለሰቦችና ቤተሰቦች ተመድበውልናል። ቁጠራው ግን ስለ ቁጥሮች አይደለም፤ እያንዳንዱ ሰው ለእርሱ በሚያገለግለው ሰው አማከኝነት የአዳኝን ፍቅር እንዲሰማው ማድረግ ነው። በዚያ መንገድም፣ ሁሉም በአፍቃሪው አባታችን እንደሚታወቁ ይገነዘበሉ።
በቅርብ ጊዜ አንዲት የሷን እድሜ አሚስት እጥፍ የሚሆናትን እህት እንድታገለግል ከተመደበች ወጣት ሴት ጋር ተገነኘሁ። አብረው በጋራ ለሙዚቃ ፍቅር እንዳላቸው አወቁ። ይህች ወጣት ሴት ሲትጎበኝ፣ ዘፈኖችን አንድ ላይ ይዘፍናሉ እናም ስለሚወዱት ሙዚቃም ያወራሉ። ሁለቱንም የሚባርከውን ጓደኝነት እየፋጠሩ ናቸው።
እናንተ የሚታገለግሉት ሰው እናንተን እንደ ጓደኛ ሊያዩዓቹ እንደሚችሉ እና በእናንተም ሁኔታቸውንም በሚገባ የተረዳ ፤ ደህንነታቸውን እና ተስፋቸውንም የሚያውቅ ሰው እንድዳለቸው መተማመን እንደሚችሉ ተስፋ አደርገለሁ።
እኔም ሆንኩኝ ጓደኛዬ የማናቀቃትን እህት እንድናገለግል በቅርቡ ሀለፊነት ተቀብዬ ነበር። የ16 እድሜ ካላት የአገልግሎት ጓደኛዬ ጄስ ጋር ስንመከከር በጥበብ፣ “እሷን ማዎቅ አለብን” ብላ ሀሳብ አቀረበች።
ወዲያውኑ የራስ ፎቶ እና የመግቢያ የእጅ ስልክ መልእክት በቀደም አስፈላጊ እንደሆን ወሰንን። እኔ ስልኩን ይዤ ጄስ ደግሞ አዝራሩን ነክታ ፎቶ አነሳችን። የእኛ የመጀመሪያ አገልግሎት እድል የጓደኝነት ጥረት ነበር።
ለመጀመሪያ ጊዜ ስንጎበኛትም፣ ስለእርሷ በምንጸልይበት ውስጥ እንድናገባ የሚምትፈልግው ነገር እንዳለ ጠየቅናት። የግል ፈተናዎቿን ተካፈለች እናም ጸሎተችንን እንደምትቀበልም ተናገረች። ግልፅነቷና በእኛ መተማመኗ በፍጥነት ፍቅርን አመጠ። በየቀኑ ጸሎቴ እርሷን ማስታወስ ምን ያህል አስደሳች እድል ነው።
በምትጸልዩበት ጊዜ ስለምታገለግሉት ሰዎች የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ይሰማችኋል። ያንን ፍቅር ለእነርሱም አካፍሉ። የእርሱን በጎች ለመመገብ የእርሱን ፍቅር በእናንተ በኩል እንዲሰመቸው ከማድራግ የበለጠ መንገድ ምን አለ?
የተጠበቁ
የእረኛውን ልብ የሚገኝበት ሁለተኛው መንገድ የእርሱን በጎች መጠበቅ ነው። እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት፣ ማንኛውን ነገሮች ለማነቃነቅ፣ ለማስተካከል፣ ለመጠገን፣ እና እንደገና ለመገንባት እንችላለን።። የተቸገሩትን ለመርደትና ኩኪ ለመስጠት ፋጣኞች ነን። ግን ሌላ ተጨማሪ አለ?
በጎቸችን በፍቅር እንደምንንከባከባቸው እና እንደምንረደቸው ያውቀሉን?
በማቴዎስ 25 ውስጥ እንደምናነበው፥
“እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ … ፥
“ተርቤ አብልታችሁኛል፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል፤ እንግዳ ሆኜ ተቀበላችሁኝ
“እና ቅዱሳን እንዲህ ብለው ይመልሳሉ፣ ጌታ ሆይ፣ መቼ ተርበህ አይተንህ አበላንህ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?
“እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ?”5
ወንድሞች እና እህቶች፣ ቁልፉ ቃል ማያት ነው። ጻድቃኖች የተቸገሩትን ያዩት ይመለከቱና ያስተውሉ ስለ ነበር ነው። እኛም ለመርደት፣ ለማፅናናት፤ ለማክበርና እንዲሁም ለማለም ንቁ ተመልካቾች መሆን እንችላለን። በምናደርግበት ጊዜ፣ በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ “ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት” በማለት የተገባው ቃል ለእኛም ሊሆን ይችላል።6
ጆን ብለን የምንጠራው ጓደኛችን ጎልቶ የማይታየውን የሌለውን ሰው ፍላጎት ስናይ ሊሆን ስለሚችል ነገር አካፍሎናል፥ “በአጥቢያዬ ውስጥ ያለች አንድ እህት ራሷን ለመግደል ሞክራ ነበር። ከሁለት ወር በኃላ፣ ከእኔ ምልአተ ጉባኤ እንዲህ ያለውን አሰቃቂ ሁኔታ ለመፍተት በለቤቷን ማንም እንደልቀረበው አወቅኩኝ። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ እኔም ምንም አላደርኩም። በመጨረሻም ለምሳ እንዲመጣ በለቤቷን ጠያቅኩት። ዓይናፋር ሰው ነበር፣ ብዙን ጊዜ ይቆጠባልም። ሆኖም ግን እኔ፣ ‘ሚስትህ ራሷን ለመገል ሞክራ ነበር። ይሄ ለአነተ ከባድ መሆን አለበት። ስለዚህ መነጋገር ትፈልገጋለህን?’ ቢዬ ስጠይቀው፣ እሱም በግልጽ አለቀሰ። ጥልቅና ወዳጃዊ ውይይት ነበረን እናም በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አስደናቂ ቅርበትና እምነትን አፋራን።”
ጆን ጨምሮ እንዲህ አለ፣ “የእኛ አዝማሚያ በሃቀኝነትና በፍቅር ወደዚያ ቤት እንዴት መሄድ እንደዳለብን ከማሰብ ይልቅ ምግቦችን ብቻ ስለማምጣት ነው የምናስበው።”7
በጎቻችን እየተጎዱ፤ እየጠፉ ወይንም ሆን ብሎ በተሳሳተ መንገድ እየጠፉ ሊሆኑ ይችላሉ፤ እንደ እረኞቻቸው፣ ፍለጎታቸውን ማያት የመጀመሪያዎች ልንሆን እንችላለን። ሳንፈርድባቸው ልናዳምጣቸውና ልንወዳቸው እንችላለን እናም የመንፈስ ቅዱስን የማስተወል እርዳታ ተጠቅመን ተስፋንና እርዳታን መስጠት እንችላለን።
እህቶችና ወንድሞች ሆይ፣ እናንተ በሚታደርጉት የደግነት ተግባሮች ምክንያት ይህች አለም የበለጠ በተስፋና በደስታ የተሞላች ናት። የሚነገለግለውን ሰው ፍለገጎትና እንዴት ፍቅሩን መስተለለፍ እንደሚንችል ለመዎቅ የጌተን አቅጣጫ ስትፈልጉ አይናችሁን ትከፍታላችሁ። ቅዱስ የአገልግሎት ሀለፊነታችሁ የመነሳሳትን መለኮታዊ መብት ይሰጣችኋል። በራስ መተማመን መነሳሻን ትፈልጋላችሁ።
ወደ እግዚአብሔር እቅፍ መሰብሰብ
ሶስተኛ፣ በጎቻችን ወደ እግዚአብሔር እቅፍ እንዲሰበሰቡ እንፈልጋለን። ይህን ለማድረግ፣ በቃል ኪዳን መንገድ ላይ የት እንዳለን እና በእነርሱ የእምነት ጉዞም ከእነርሱ ጋር አብሮ ለመጓዝ ፈቃደኛነታችንን ማሰብ ይገባናል። ቅዱስ ልዩ እድላችንም ልባቸውን ለማወቅና እነርሱን ወደ አዳኙ መጠቆም ነው።
በፊጂ ውስጥ ያለችው እህት ጆሲቭኒ በቃል ኪዳን መንገዷ ወደ ፍት ማያት ቸግሯት ነበር። የሷ ጓደኛ ጆሲቭኒ ቅዱሳት መጻፍትን አይታ ለመንበብ ስትቸገር አየቸት። ለማንበብ የሚረዱትን አዲስ መነጽሮችንና በመፅሐፍ ሞርሞን ውስጥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገሩትን ሁሉንም ጥቅሶችን እንድተሰምርበት ደመቅ ቢጫ እርሳስ ለጆሲቭኒ ሰጠቻት። ቅዱሳት መጻህፍቶችን እንድታነብ ለመረደትና በቀላል የአገልግሎት ፍላጎት የተጀመረው ጆሲቪኒ ከተጠመቀች ከ28 ዓመት በኋላ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤተ-መቅደስ መሄድ እንድትችል ራድቷታል።
በጎቻችን ጠንከራ ወይንም ደካማ ቢሆኑም፣ እየተደሰቱ ወይንም እየተጨነቁ ቢሆንም፣ ማንም ብቻውን እንደማይሄድ ማረጋገጥ እንችላለን። በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የትም ቢሆኑ ልንወደቸው፣ እናም ድገፋ ልንሰጣቸውና ወደ ሚቀጥለው ደራጀ እንዲራመዱ ልናበረታታቸው እንችላለን። ስንጸልይና ልባቸውን ለማወቅ ስንፈልግ፣ የሰማይ አባታችን እንደሚመራንና መንፈስ ቅዱስም ከእኛ ጋር እንደሚሄድ እመሰክራለሁ። በፊታቸው በሚሄድበት ጊዜ “በዙሪያቸው ያሉት መላእክቶች” የመሆን አጋጣሚ አለን።8
ጌተ እርሱ እንደሚያደርገው የእሱን በጎች እንድንመግብ፣ መንጋዎቹን እንድንጠብቅ ይገብዘናል። ለሁሉም ዘሮች፣ ለእያንዳንዱ ሀገሮች፣ እረኞች እንድንሆን ይጋብዘናል። (እናም አዎን፣ ሽማግሌ ኡክዶርፍ፣ የጀርመን በግ ጠባቂዎችንም እንወዳለን እናም እንፈልጋለ።) በዚህም ምክንያት ወጣት ሰዎቹ እንዲቀላቀሉት ይፈልገል።
ወጣቶቻችን ጠንከራ እረኞቻችን ሊሆኑ ይችላሉ። ፕሬዝዳንት ራሰል ኤም. ኔልሰን እንዳሉት፣ እነርሱ “ጌታ ወደዚህች አለም ከላካቸው ምርጦቹ ናቸው።” የተከበሩ መናፍስት፣ አዳኝን የምከተሉ “ምርጥ ተጫዋቶቻችን” ናቸው።9 እነዚህ እረኞች ለበጎቹ እንክብካቤ ሲሰጡ ምን ያህል ኃይል እንደሚኖራቸው መገመት ትችላላችሁን? ከእነዚህ ወጣቶች ጋር ጎን ለጎን ስናገለግል፣ ድንቅ እናያለን።
ወጣት ሴቶችና ወጣት ወንዶች፣ እንፈልጋችኋለን። የአገልግሎት ምድብ ከሌላችሁ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ወይንም የሽማግሌዎች ምልአተ ጉባኤ ፕሬዘደንትን አነገግሩ። በጎቹ እንዲታወቁና እንዲቆጠሩ፤ እንዲጠበቁና ወደ እግዚአብሔር እቅፍ እንዲሰበሰቡ ለማራገገጥ ፍቀደኛ ስለሆናችሁ እነርሱም ይደሰተሉ።
መንጋዎቹን መግበን፣ በተወደደ በአደኛችን ፊት የምንንበርከክበት ቀን ሲመጣም፣ ልክ እንደ ጴጥሮስ መልስ መስጠት እንችል ዘንድ ፃልያለሁ፥ “አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው።”10 እነዚህ፣ የአንተ በጎች፣ የተወደዱ ናቸው፣ ደህና ናቸው፣ እናም በቤታቸው ናቸው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።