በላያችን ላይ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ለመውሰድ።
እርሱ እንደሚያየው በመየት፣ እርሱ እንደሚያገለግለው በማገልገል፣ እና ወደ ቤት እንድንመለስና እንድንደሰት ጸጋው በቂ እንደሆነ በማመን በራሳችን ላይ የኢየሱስ ክስቶስን ስም በእምነት እንድንውሰድ።
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በቅርቡ፣ ቤተክቲያኗን በተገለጸላት ስሟ እንድንጠራት የፕሬዝዳንት ኔልሰ ጥሪ ላይ ሳሰላስል፣ አዳኙ ስለ ቤተክርቲያኗ ስም ኔፊያኖችን ወዳስተማረበት ቦታ ተመለከትኩ።1 የአዳኙን ቃሎች ሳነብ፣ ህዝቦቹን “በራሳችሁ ላይ የክርስቶስን ስም ውሰዱ” ብሎ በነገራቸው ነገር ተደመምኩኝ።2 ይህ ነገር ወደ እራሴ ተመልክቼ “የአዳኙን ስም እርሱ እንደሚፈልገኝ በራሴ ላይ ወስጃለውን” ብዬ እንድጠይቅ አደረገኝ።3 ዛሬ ለጥያቄዬ ምላሽ የተቀበልኩትን መነሳሳቶች ለማካፈል እፈልጋለው።
መጀመሪያ፣ የክርስቶስን ስም በላያችን ላይ መውሰድ ማለት እግዚአብሔር እንደሚያየው ለማየት እንጥራለን ማለት ነው።4 እግዚአብሔር እንዴት ነው የሚያየው። ጆሴፍ ስሚዝ እንዲህ አለ፣ “አንዱ የሰው ዘር ክፍል ልላውን ያለ ምህረት ሲፈርድበትና ሲያንቋሽሽ፣ ታላቁ የአለም ወላጅ መላውን የሰው ቤተሰብ በአባታዊ እንክብካቤ እና ወላጃዊ ዕይታ ይመለከታል ምክንያቱም የእርሱ ፍቅር ለመረዳት ይከብዳል።”5
ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ታላቅ እህቴ አረፈች። አስቸጋሪ ሂወት ነበራት። ወንጌልን ለመኖር ትቸገር ነበር እንዲሁም ንቁ ተሳታፊ አልነበረችም። ባለቤቷ ከአራት ልጆቿ ጋር ትዳራቸውን ትቶ ኮበለለ። በራፈችበት አመሻሽ ላይ ልጆቿ በተገኙበት ክፍል ውስጥ በሰላም ወደ ቤቷ እንድትመለስ በረከት ሰጥተዋት። የእህቴን ህይወት በፈተናዎቿ እና ንቁ አለመሆን ላይ አብዝቼ እንደተረጎምኩት በዛን ጊዜ ተገነዘብኩኝ። በዛ ምሽት ላይ እጆቼን በእራሷ ላይ ስጭን፣ ከመንፈስ ብዙ ግሰፃዎችን ተቀበልኩኝ። ስለመልካምነቷ ተረዳሁኝ እንዲሁም እግዚአብሔር እንደሚያያት ማለትም በወንጌል እና በህይወት እንደምትቸገር ሳይሆን እኔ ያላየዋቸውን ከባድ ነገሮች እንዳሳለፈች አድርጌ እሷን ለማየት ፈቀድኩኝ። ታላላቅ እንቅፋቶች ቢገጥማትም አራት ቆንጆዎች እና ገራሚ ልጆችን እንዳሳደገች ድንቅ እናት አየኋት። ባለቤቷ ከሞተባት ጀምሮ ለእናታችን ጊዜዋን ወስዳ ጓደኛ በመሆን እንደተንከባከበቻት አየኋት።
ከእህቴ ጋር በነበረኝ በዛ የመጨረሻ ምሽት ላይ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ እንደጠየቀኝ አምናለሁ፣ “በዙሪያህ ያለ ሰው ሁሉ ቅዱስ ፍጡር እንደሆነ ማየት አትችልምን?”
ፕሬዘደንት ብሬገም ያንግ እንዳስተማሩት፥
“ወንዶችንና ሴቶችን እንደራሳቸው ሳይሆን እንደማንነታቸው እንዲረዷቸው ቅዱሳኖችን ልማፀን እፈልጋለሁ።6
ሰንት ጊዜ ነው እንዲህ የተባለው፣ ‘ይህ ሰው ስህተት ሰርቷል ስለሆነም ቅዱስ መሆን አይችልም።’ አንዳንዶች ሲምሉ እና ሲዋሹ … [ወይም] ሰንበትን ሲሰብሩ እንሰማለን። … እንደዚህ ዓይነት ሰው ላይ አትፍረዱ፣ ምክንያቱም ስለእነሱ ጌታ ያለውን እቅድ አታውቁምና። … [ነገር ግን] ቻሏቸው።”7
አዳኛችን እናንተንና ሸክማችሁን ሳይገነዘብ በእርሱ ላይ ያሳልፋል ብላችሁ ትችላላችሁን? አዳኙ ሳምራዊውን፣ የዘሞተችውን፣ ግብር ሰብሳቢውን፣ ለምጻሙን፣ የአዕምሮ በሽተኛውን፣ እና ሃጢያተኛውን በተመሳሳይ ዓይን አየ። ሁሉም የእርሱ አባት ልጆች ነበሩ። ሁሉም ለመዳን የሚችሉ ነበሩ።
በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ቦታቸው ምን እንደሆነ ከሚጠራጠሩ ወይም በማንኛውም ሁኔታ ከሚሰቃዩትን ዞር ብሎ ሲሄድ በዓዕምሮአችሁ ልታዩ ትችላላችሁን?8 እኔ አልችልም። በክርስቶ አይኖች እያንዳንዱ ነፍስ ዘላለማዊ ዋጋ አለው። ማንም ሰው በቅድመት እንዲወድቅ አይመደብለትም። ዘላለማዊ ህይወት ለሁሉም ይቻላል።9
ከእህቴ አልጋ ጎን ከተቀበልኩት የመንፈስ ግሳፄ ጎን ለጎን ታላቅ ትምህርትን ተማርኩኝ፤ እርሱ እንደሚያየው ስናይ፣ የእኛ ድል ዕጥፍ ድርብ ይሆናል ማለትም የምንነካቸው ሰዎች ደህንነት እንዲሁም የእራሳችን ደህንነት።
ሁለተኛ የክርሰቶስን ስም በላያችን ላይ ለመውሰድ እግዚአብሔር ማየት እንደሚችለው ማይት ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን ስራውን መስራትና እርሱ እንዳገለገለው ማገልገል አለብን። በእግዚአብሔር ሁለት ታላቅ ትእዛዛት ስር እንኖራለን፣ ለእግዚእሔር ፈቃድ እራሳችንን አሳልፈን እንሰጣለን፣ እስራኤልን እንሰበስባለን፣ እንዲሁም “ብርሃናችን ከሰዎች ፊት” እንዲበራ እናደርጋለን።10 የተመለሰውን ቤተክርስያኑን ስርዓቶችንና ቃልኪዳኖችን እንቀበላለን እንዲሁም እንጠብቃለን።11 ይህን ስናደርግ፣ እግዚአብሔር እራሳችንን፣ ቤተሰባችንን፣ እና የሌሎችን ህይወት እንድንባርክ ኃይል ይሰጠናል።12 እንዲህ ብላችሁ እራችሁን ጠይቁ፣ “የሰማይን ኃይል በህይወቱ ውስጥ የማይፈልግን ሰው አውቃለውን።?”
እራሳችንን ስናነጻ እግዚአብሔር በመካከላችን አስደናቂ ስራን ይሰራል።13 ልቦቻችንን በማንጻት እራሳችንን እንቀድሳለን።14 እርሱን በምንሰማበት ወቅት፣15 ለሃጢያቶቻችን ንስሃን ስንገባ፣16 ስንለወጥ፣17 እና እርሱ እንደወደደው ስንወድ ልቦቻችንን እናጻለን።18 አዳኙ እንዲህ ጠየቀ፣ “የሚወዷችሁን መልሳችሁ ብትወዱ ምን ታተርፋላችሁ?”19
በቅርቡ በሽማግሌ ጄምስ ኢ ታልሜጅ አንድ የህይወት ተሞክሮ ውስጥ በዙሪያዬ ያሉትን ሰዎች እንዴት መውደድ እና ማገልገል እንደምችል ቆም ብዬ እንድገነዘብ ተማርኩኝ። ወጣት ፕሮፌሰር ሳለ ሐዋርያ ከመሆኑ በፊት እና በ1892 (እ.አ.አ) በነበረው ገዳይና ተላላፊ በሽታ ጫፍ ላይ፣ ሽማግሌ ታልሜጅ የቤተክርስቲያን አባል ያልነበሩትን እንዲሁም በበሽታው የተመቱ በአቅራቢያው የሚኖሩ አንድ እንግዳ ቤተሰብን አገኘ። በበሽታው የተጠቃ ቤት ውስጥ በመግባት ማንም ሰው እራሱን አደጋ ላይ መጣል አልፈለገም። ሽማግሌ ታልሜጅ ይሁን እንጂ በፍጥነት ወደ ቤቱ ውስጥ ገባ። አራት ልጆችን፤ የሁለት ዓመት ካጋማሽ ልጅ መኝታ ላይ ሞቶ፣ የአምስት አመት እና የአስር አመት ልጆች በከፍተኛ ህመም ውስጥ ሆነው፣ እነዲሁም የደከመን የአስራ ሶስተ ዓመት ልጅ አገኘ። ወላጆቹ በድካምና ሃዘን እየተሰቃዩ ነበር።
ሽማግሌ ታሜጅ የሞተውን እና በህይወት ያሉት አለበሰ፣፣ ቤቱን ጠረገ፣ ቆሻሻ ልብሶችን አወጣ እናም በበሽታው የተሸፈኑትን የቆሸሹ የጨርቅ ማድረቂያዎችን አቃጠለ። ቀኑን ሙሉ ሲሰራ ውሎ በነጋታው ጠዋትም ተመልሶ ሄደ። የአስር አመቱ ልጅ በምሽቱ አረፈ። የአምስት ዓመቷን ልጅ አንስቶ አቀፋት። በመላው ፊቱ እና ልብሶቹ ላይ ደም የተቀላቀለበትን ሃክታ አሳለች። እንዲህ ብሎ ፃፈ፣ “ወደ መሬት ላቀምጣት አልቻልኩም” እናም እስከምታርፍ ድረስ በእጆቹ ላይ ያዛት። ሶስት ልጆቹን በመቅበር ተባበረ እናም በሃዘን ለተሞሉት ቤተሰብ ምግብና ንፁ ልብሶች እንዲያገኙ አስተባበረ። ወደ ቤት በሚመለስበት ወቅት፣ ወንድም ታልሜጅ ልብሶቹን አውልቆ ጣለ፣ በዚንክ ውህድ ውስጥ ሰውነቱን ታጠበ፣ ከቤተሰቦቹ እራሱን አገለለ እንዲሁም ከበሽታው በጥቂቱ ተሰቃየ።20
በዙሪያችን ብዙ ህይወቶች በችግር ውስጥ ናቸው። ቅዱሳኖች የአዳኙን ስም ቅዱስ በመሆን እና ሁሉንም ሰዎች በማገልገል በላያቸው ላይ ይወስዳሉ። ይህን ስናደርግ ህይወቶች ይድናሉ።21
በመጨረሻም፣ የእርሱን ስም በላያችን ላይ ለመውሰድ እርሱን ማመን እንዳለብን አምናለው። እሁድ በተካፈልኩት ስብሰባ ላይ አንድ ወጣት ሴት እንዲህ ብላ ጠየቀች፣ “የወንድ ጓደኛዬ እና እኔ ተለያየን፣ ከዛ ቤተክስቲያኑን ለመተው ወሰነ። ደስተኛ እንዳልነበረ ነገረኝ። ይህ እንዴት መሆን ይችላል?”
አዳኙ ይህን ጥያቄ ለኔፊያቶች እንዲህ ሲል መለሰው፣ “ነገር ግን በወንጌሌ ላይ [ህይወታችሁ] ካልታነፀች እናም በሰዎች ስራ ላይ ከታነፀች እንዲሁም በዲያብሎስ ስራ ላይ፣ እውነት እላችኋለው እስከጊዜው በስራቸው ደስታን ያገኛሉ፤ እናም ከጥቂት ጊዜም በኋላ ፍፃሜአቸው ይሆናል፣ እናም ይፈረካከሳሉ፣ መመለስ በማይቻልበት እሳት ውስጥም ይወድቃሉ።”22 ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውጪ ምንም ደስታ የለም።
በዛ ስብሰባ ላይ ግን በከፍተኛ ሸክም እና በሚከብዳቸው ትእዛዞች የሚቸገሩ ስለማቃቸው ብዙ መልካም ሰዎች ማሰብ ጀመረኩኝ። እራሴን እንዲህ ጠየቅኩኝ፣ “አዳኙ ለእነሱ ምን ተጨማሪ ነገር ሊላቸው ይችላል?”23 “እኔን ታመኑኛላችሁ?” ብሎ እንደሚጠይቃቸው አምናለው።24 ደም ይፈሳት ለነበረችው ሴት እንዲህ አላት፣ “እምነትሽ አድኖሻል፣ በሰላም ሂጂ።”25
ከምወዳቸው ጥቅሶች መካከል አንዱ ዮሐንስ 4፡4 ነው፣ እሱም “በሳማርያ ሊያልፍ ግድ ሆነበት” ይላል።
ለምንድን ነው ያን ጥቅስ የምወደው? ምክንያቱም ኢየሱስ ወደ ሳማርያ መሄድ ግድ አልነበረበትም። የሰዓቱ አይሁዶች ሳማርያኖችን ይጠሉ ነበር እናም በዙሪያው ነበር አልፈው የሚሄዱት። ነገር ግን ኢየሱስ ቃል የተገባለት መሲህ እርሱ እንደሆነ ለአለም ለማወጅ ለመሄድ መረጠ። ለዚህ መልዕክት፣ የተነፈጉ ህዝቦችን ብቻ ሳይሆን የመረጠው ነገር ግን በዛን ሰዓት ከበታቾችም የበታች ተደርጋ የምትቆጠርን አንዲት በሃጢያት ትኖር የነበረችን ሴት። ኢየሱስ ይህን ያደረገው እያንዳንዳችን የእርሱ ፍቅር ከፍርሃታችን፣ ከሱሳችን፣ ከጥርጣሬአችን፣ ከፈተናዎቻችን፣ ከሃጢያቶቻችን፣ ከተሰበረው ቤተሰባችን፣ ከጭንቀታችን፣ ከጎዳና ተዳዳሪነታችን፣ ከተመሳሳይ ቁስሎቻችን፣ ፆታ ፍላጎታችን፣ ከበሽታዎቻችን፣ ከድህነታችን፣ ከጭቆበናችን፣ ድሀነታችን፣ መጎሳቆላችን፣ ተስፋ መቁረጣችን፣ እና ከብቸኝነታችን በላይ እንደሆነ እንድናውቅ እንደሆነ አምናለው።26 ምንንም ነገር እና ማንንም ሰው ለመፈወስ እና ነፃ ለማውጣት እንደማይሳነው ሁላችንም እንድናውቅ ይፈልጋል።27
ጸጋው በቂ ነው።28 እርሱ ብቻ ከሁሉም ነገሮች በታች ወርዷል። የሃጢያት ክፍያው ኃይል በህይወታችን ውስጥ ማንኛውንም ሸክም የማሸነፍ ኃይል አለው።29 በውኃው ጉድጓድ የነበረችው ሴት መልዕክት የህይወታችንን ሁኔታ እንደሚያውቅ30 እና የትም ቦታ ብንቆምም ከእርሱ ጋር መራመድ እንደምንችል ነው። ለእሷ እና ለእያንዳንዳችን እርሱ ይህን ይላል፣ “እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግ ለዘላለም አይጠማም፣ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ።”31
በማንኛውም የህይወት ጉዞ ውስጥ ሊፈውሳችሁ እና ነፃ ሊያወጣችሁ ከሚችለው ከአዳኙ ለምን ፊታችሁን ታዞራላችሁ? እርሱን ለማመን ማንኛውንም ዓይነት ክፍያ ብትከፍሉ አዋጭ ነው። ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በሰማይ አባትና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት ለመጨመር እንምረጥ።
ክእነፍሴ ጥልቀት፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣ በህያው እና እውነተኛ ነቢይ የምትመራ፣ የአዳኙ ቤተክርስቲያን እንደሆነች እመሰክራለሁ። እርሱ እንደሚያየው በመየት፣ እርሱ እንደሚያገለግለው በማገልገል፣ እና ወደ ቤት እንድንመለስና እንድንደሰት ጸጋው በቂ እንደሆነ በማመን በራሳችን ላይ የኢየሱስ ክስቶስን ስም በእምነት እንድንወስድ ጸሎቴ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።