ራስ ወዳጅ ባልሆነ አገልግሎት የሚመጣ ደስታ
የሰማይ አባታችንንም ሆነ ሌሎችን በፍቅር እንደምናገለግል እንዲሁም በሁሉም ነገሮች የእርሱን ፈቃድ እንደምናደርግ ቃል ገብተናል።
ባለፈው አጠቃላይ ጉባኤ በኋላ፣ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ ጥያቄ ቀረቡኝ፥ “እነዚያ መቀመጫዎች የሚመቹ ናቸውን?” ሁልጊዜም መልሴ አንድ ነበር፥ “እነዚያ መቀመጫዎች መናገር ከሌለብሽ በጣም የሚመቹ ናቸው።” እውነት ነው፣ አይዸለምን? በዚህ ጉባኤ መቀመጫዬ እስከዚህም የሚመች አልነበረም፣ ነገር ግን ዛሬ ማታ ለእናንተ ለመናገር በምችልበት በረከት እና ክብር በጣም አመስጋኝ ነኝ።
አንዳንዴ ስናገለግል በተለያዩ መቀመጫዎች ላይ እንቀመጣለን። ጥቂቶቹ በጣም የሚመቹ ሲሆኑ ሌሎቹም አይመቹም፣ ነገር ግን የሰማይ አባታችንንም ሆነ ሌሎችን በፍቅር እንደምናገለግል እንዲሁም በሁሉም ነገሮች የእርሱን ፈቃድ እንደምናደርግ ቃል ገብተናል።
ከጥቂት አመታት በፊት፣ የቤተክርስቲያኗ ወጣቶች እንዲህ ተምረዋል፣ ‘በእግዚአብሔር አገለግሎት ስትሄዱ’ [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4፥2]፣ ከሁሉም ይበልጥ ታላቅ በሆነ ጉዞ ላይ ናችሁ። እግዚአብሔርን ስራውን ለማፋጠን እየረዳችሁ ናችሁ፣ እናም ያ ታላቅ፣ አስደሳች፣ እና አስደናቂ ተሞክሮ ነው።”1 ለየትኛውም እድሜ የሚሆን ጉዞ ነው፣ እንዲሁም ደግሞ የተወደዱት ነቢያችን “የኪዳን መንገድ”2 ብለው በጠሩት የሚወስደን ጉዞ ነው።
በሚያሳዝን ሁኔታ ግን የምንኖረው ራስ ወዳድ በሆነ ዓለም ውስጥ ሲሆን ሰዎች “ዛሬስ እኔ ማንን ማገልገል እችላለሁ?” ወይም “እንዴት ነው ጌታን በጥሩ ሁኔታ በጥሪዬ ለማገልገል እችላለሁ?” ወይም “የተቻለኝን ሁሉ ለጌታ እየሰጠሁ ነውን?” ብለው ከመጠየቅ ይልቅ “ለእኔ ምን አለ?” ብለው ይጠይቃሉ።
በሕይወቴ ውስጥ ከራስ ወዳድነት ነጻ የሆነ አገልግሎት ትልቅ ምሳሌ እህት ቪክቶሪያ አንቶኒቲ ናት። በአርጄንቲና ውስጥ እያደግሁ ሳለሁ ቪክቶሪያ ከመጀመሪያዎቹ ክፍል መምህራኔ አንዷ ነበረች። በእያንዳንዱ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ፣ ለመጀመሪያ ክፍል ስንሰበሰብ፣ ቸኮሌት ኬክ ታመጣልን ነበር። ሁሉም ኬኩን ይወዱ ነበር—ከእኔ በስተቀር ሁሉም። የቸኮሌት ኬክ አልወድም ነበር! እና ኬኩን ከእኔ ጋር ለመካፈል ብትሞክርም፣ ሁልጊዜ ያቀረበችውን ግብዣ አልተቀበልኩም ነበር።
አንድ ቀን ከሌሎች ልጆቹ ጋር የቸኮሌት ኬክን ከተካፈለች በኋላ፣ እኔ እንዲህ ጠየቅኳት፣ “ለምንድን ነው የተለየ ጣዕም - እንደ ብርቱካን ወይም ቫኒላ የማታመጪው?”
ትንሽ ከሳቀች በኋላ፣ እንዲህ ጠየቀችኝ፣ “አንቺስ ለምን ትንሽ ቁራሽ የማትቀምሺው? ይህ ኬክ የተሰራው በልዩ ንጥረ ነገር ነው፣ እና አንቺ ብትሞክሪው፣ እንደምትወጂው ቃል እገባለሁ!”
በዙሪያው ተመከትኩኝ፣ እናም ለእኔ በሚያስደንቅ ሁኔታ፣ ሁሉም ኬኩን ይደሰቱበት ይመስል ነበር። ለመሞከር ተስማማሁኝ። ምን እንደደረሰ ለመገመት ትችላላችሁን? ወደድኩት! ቸኮሌት ኬክን የተደሰትኩበት የመጀመሪያ ጊዜ ይህ ነበር።
ከብዙ አመት በኋላ፣ የእህት አንቶኒቲ ቸኮሌት ኬክ ውስጥ የምስጢር ንጥረ ነገራቸው ምን እንደነበር ያወቅሁት። ልጆቼ እና እኔ እናቴን በየሳምንቱ እንጎበኝ ነበር። ከእነዚህ ጉብኝቶች በአንዱ፣ እናቴ እና እኔ የቸኮሌት ኬክ እንደሰትበት ነበር፣ እናም ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት የቸኮሌት ኬክን ለመውደድ እንደቻልኩኝ ታሪክን ነገርኳት። ከዚያም ስለዚህ ተጨማሪ ታሪክ አብራርታ ነገረችኝ።
“አየሽ ክሪስ”፣ አለች እናቴ፣ “ቪክቶሪያ እና ቤተሰቧ ብዙ ምንጮች አልነበሯቸውም፣ እናም በየሳምንቱ ራሷን እና ልጆቿን ወደ መጀመሪያ ክፍል ለመውሰድ የአውቶቡስ ቲኬት ከመግዛት እና ቸኮሌት ኬክ ለመጀመሪያ ክፍሏ ለመስራት ንጥረ ነገሮችን ከመግዛት መካከል መወሰን ነበረባት። ሁልጊዜ ከአውቶቡስ በላይ ቸኮሌት ኬክን መርጣለች፣ እናም እርሷ እና ልጆቿ የአየር ሁኔታ ምንም ቢሆን፣ በእያንዳንዱ አቅጣጫ ከ3 ኪሎ ሜትር በላይ በእግር ተጉዘዋል።
በዚያ ቀን ለቸኮሌት ኬኳ ይበልጥ ምስጋና አገኘሁ። ከሁሉም በላይ፣ በቪክቶሪያ ኬክ ውስጥ ሚስጥራዊው ንጥረ ነገርም እርሷ ለምታገለግላቸው ያላት ፍቅር እና ለእኛ የነበራት ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ መስዋዕት እንደሆነ አውቅሁኝ።
የቪክቶሪያን ኬክ መለስ ብዬ መለስ ብዬ ማሰብ ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ግምጃ ቤት ሲሄድ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረውን ከራስ ወዳድነት የራቀን የመሰዋትነትን ትምህርት ለማስታወስ ይረዳኛል። ታሪኩን ታውቁታላችሁ። ሽማግሌ ጄምስ ኢ. ታልሜጅ እንዳስተማሩት 13 ሳጥኖች ነበሩ “እናም በእነዚህ ውስጥ ሰዎች በሳጥኖቹ ላይ በተጻፉት መጠቆሚያዎች መሰረት [ለተለያዩ] አላማዎች በኩራቶችን ያስቀምጣሉ።” ኢየሱስ በኩራት ለመስጠት የተደረደሩትን የተለያዩ ሰዎች ተመለከተ። አንዳንዶች ስጦታዎችን “በልብ እቅድ” ሰጡ፣ ሌሎችም ለመታየት፣ እና ለበኩራቶቻቸው ሙገሳ ለማግኘት ፈልገው “ታላቅ የወርቅ እና ብር ድምሮችን” ጣሉ።
“ከብዙዎቹ መካከል አንድ ድሀ መበለት ነበረች፣ እርሷም … በሳንጣው ውስጥ ናስ ተበው የሚጠሩ ሁለት ሳንቲሞች ጣለች፤ የእርሷ በኩራት በአሜሪካ ገንዘብ ከግማሽ ሳንቲም በታች ነበር። ጌታም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ ደሀ መበለቷን እና ምን እንዳደረገች አመለከተ እናም እንዲህ አለ፥ ‘እውነት እላችኋለሁ፥ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች። ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና፥ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ መተዳደሪያዋን ሁሉ ጣለች አላቸው።’ [ማርቆስ 12፥43–44]።”3
ይህች መበለት በወቅቱ በነበረው ህብረተሰብ ውስጥ ታዋቂ ቦታ አልነበራትም። እሷ በጣም አስፈላጊ ነገርን ይዛ ነበር፥ ዓላማዋ ንጹህ ነበር እናም እርሷ ያላትን ሁሉ ሰጥታለች። ምናልባትም የሰጠችው ከሌሎቹ ያነሱ፣ ከሌሎቹ በላይ ጸጥተኛ ሆና፣ ከሌሎቹ ልዩ ሆና ነው። በአንዳንዶች አስተያየት፣ የሰጠችው ብዙ አልነበረም፣ ነገር ግን “የልብን ሐሳቦችና ምኞቶች በሚያውቅ”4 አዳኝ ዘንድ ግን ሁሉንም ነው የሰጠችው።
እህቶች፣ ሳንጠቅጥ ለጌታ ያለንን ሁሉ እንሰጣለን? የሚያድግ ትውልድ ጌታን መውደድ እና ትእዛዛቱን መጠበቅ መማር ይችል ዘንድ ጊዜያችንን እና ችሎታችንን እንሰጣለንን? በአካባቢያችን ለሚገኙ እና ለተመደብንባቸው በእርዳታ እና በትጋት፣ በሌላ ለመጠቀም የሚቻለውን ጊዜን እና ሀይልን በመስዋዕት በመስጠት እያገለገልን ነን? ሁለቱን ታላቅ ትእዛዛት፣ እንዲሁም እግዚአብሔርን ለማፍቀር እና ልጆቹን ለማፍቀ፣ እየኖርንባቸው ነውን?5 በአብዛኛው ጊዜ ያም ፍቅር በአገልግሎት ይታያል።
ፕሬዘደንት ዳለን ኤች. ኦክስ እንዳስተማሩት፥ “አዳኛችን ራስ ወዳጅ ባልሆነ አገልግሎት እራሱን ሰጠ። ሌሎችን ለማገልገል እያንዳንዳችንም ራስ ወዳጅ የሆኑ ፍላጎታችንን በመተው እርሱን መከተል እንደሚገባን አስተማረን።”
እንዲህም ቀጠሉ፥
“ራሳችንን በሌሎች አገልግሎት የመርሳት የሚታወቀው ምሳሌ ቢኖር … ወላጆች ለልጆቻቸው የሚያደርጉት መሰዋዕትነት ነው። እያንዳንዱን ልጆች ለመውለድ እና ለማሳደግ የግል ቅድሚያ እና ምቾትን በማጣት ይሰቃያሉ። አባቶች ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ ህይወታቸውን እና ቅድሚያቸውን ያስተካክላሉ።
“… እኛም ደግሞ እንዲሁም አካለ ስሰንኩል የሆኑ የቤተሰብ አባላትን እና ያረጁ አዛውንት ወላጆችን በሚንከባከቡትን እንደሰታለን። የዚህ አገልግሎት አማንኛውም ድርጊት፣ ለእኔ ምን አለበት? ብሎ አይጠይቅም። ሁሉም ራስ ወዳድነት ለሌለው አገልግሎት የግል ምቾትን ወደ ጎን ማድረግን ያስፈልገዋል። …
“[እናም] ይህም ሁሉ የሚገልጸው ለምናገኘው ሳይሆን ለምንሰጠው ስንሰራ እና ስናገለግል በተጨማሪ ደስተኞች ተደሳች እና በተጨማሪ የምንረካ መሆናችንን የተረካን የየሚገልፅ ዘለአለማዊ መርሆን ነው።
“አዳኛችን ራሳችንን ራስ ወዳጅነት በሌለው ሌሎችን በማገልገል ለማጣት አስፈላጊ የሆነውን መስዋዕቶች በማድረግ እንድንከተለው አስተሮናል።”6
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንደዚህም አስተምረዋል፣ “ምናልባት ከመምህር ጋር የፊት ለፊት ግንኙነት ሲኖረን፣ ‘ምን ያህል ሀላፊነቶች ነበራችሁ?’ ሳይሆን ነገር ግን ‘ምን ያህል ሰዎች ረዳችሁ?’ ተብለን እንጠየቅ ይሆናል። በእምነትም፣ እርሱን ህዝቦቹን በማገልገል እስከምታገለግሉት ድረስ ጌታን በምንም ለማፍቀር አትችሉም።”7
በሌላ አባባልም፣ እህቶች፣ በሚመች መቀመጫ መቀመጣችን ወይም ዝገት ባለው መቀመጫ ላይ በመጨረዛው ተርታ ላይ ተቀምጠን ስብሰባውን ለመፈጸም የምንታገል መሆናችን ምንም አያደርግም። አስፈላጊ ከለሆነ፣ የሚያለቅስ ህጻንን ለማፅናናት ወጣ የምንል መሆኑም ግድ የለውም። ከሁሉም በላይ የሚበጀው እርሱን ለማገልገል በመፈለግ መምጣታችን፣ የምናገለግላቸውን ማወቃችን እና በደስታ ሰላምታ መስጠታችን፣ እና ራሳችንን በሚታጠፈው ወንበር ላይ በአጠገባችን ለተቀመጡት ማስተዋወቃችን፣ እነርሱን ለማገለገል የተመደብን ባንሆንም በጓደኝነት ወደእነርሱ መድረሳችን ነው። የምናደርገውን ሁሉ በልዩ የአገልግሎት ንጥረነገሮች፤ ከፍቅርና ከመስዋዕት ጋር በማጣመር ማድረጋችን በጣም ያስፈልገዋል።
ውጤታማ ለመሆን ወይም ውሳኝ የመጀመሪያ ክፍል አስተማሪ ለመሆን የቸኮሌት ኬክ መስራት እንደሌለብን ተረዳሁ፣ ምክንያቱም ይህ ስለኬኩ አልነበረም። ይህም ለስራው ምክንያት ለሆነው ፍቅር ነው።
ፍቅር በመስዋዕት በኩል፣ እንዲሁም በአስተማሪ መስዋዕት እናም ከሁሉም በላይ በእግዚአብሔር ልጅ ፍጹም እና ዘለአለማዊ መስዋዕት፣ ቅዱስ እንደሚደረግ እመሰክራለሁ። እርሱ ህያው እንደሆነ እመሰክራለሁ! አፈቅረዋለሁ እናም እርሱ እንደሚያፈቅረው እና እንደሚያገለግለው ለማድረግ ራስ ወዳጅ የሆነ ፍላጎትን ለመተው ፍላጎት አለኝ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።