2010–2019 (እ.አ.አ)
ልትድን ትወዳለህን?
ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ)


ልትድን ትወዳለህን?

በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ምክንያት፣ ንስሐ ከገባን እና ልባችንን ሙሉ በሙሉ ወደ አዳኙ ከመለስን፣ እርሱ መንፈሳዊንት ይፈውሰናል።

የእኛ ትንሹ ልጅ እና የሚስዮናዊ ጓደኛው ወደ ተልእኳቸው ጥቂት ወራት ውስጥ ጥናቱ እያጠናቅቁ ሳሉ፣ ልጄ በጭንቅላቱ ውስጥ ህመም ይሰማው ነበር። በጣም እንግዳው ነበር ተሰማው፥መጀመሪያ ላይ ግራ እጁን መቆጣጠር አቃተው፤ ከዚያም ምላሱ ደነዘዘ። የፊቱ ግራው ጎን መጠውለግ ጀመረ። እሱ መናገር ይቸገር ነበር። የሆነ ችግር እንዳለ ያውቅ ነበር። የላውቀው ነገር በሶስቱ የአእምሮ ክፍሎች ውስጥ በከባድ የደም መርጋት በሽታ ውስጥ መሆኑን ነበር። በከፊል ሽባ ሆነ ስሆን ፍርሃት መቀመጥ ጀመረ። የደም መርጋት በሽታ ተጎጂዎች እንክብካቤ የምያገኙበት ፍጥነት በፈውስ መጠ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል። የእርሱ ታማኝ ሚስዮናዊ ጓዳኛ በቆራጥነት እርምጃ ወሰደ። 911 ከተጠራ በኋላ፣ ለበረከት ሰጠው። ተአምራዊ ሆኖ፣ አምቡላንሱ በአምስት ደቂቃ ርቀት ላይ ብቻ ነበር።

ልጃችን ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ፣ የሕክምና ሰራተኛ ሁኔታውን በፍጥነት ገምግሞ፣ በጊዜ ሂደት ከበሽታው የሽባነትን ውጤቶችን ለመለወጥ ለልጃችን መድኃኒት መስጠት እንዳለበት ወሰነ።1 ነገር ግን፣ ልጃችን የደም መርጋት በሽታ በይታማም ኖሮ፣ መድሃኒቱ በአእምሮ ውስጥ ደም መፍሰስ የመሳሰሉ የከፋ መዘዞችን ሊያስከትል ይችል ነበር። ልጃችን መምራጥ ነበረበት። መድሃኒቱን ለመቀበል መረጠ። ሙሉ ማገገም ብዙ ቀዶ ጥገናዎችን እና ብዙ ወራትን ብያስፈልግም፣ የበሽታ ተፅዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ ከተቀይረ በኋላ፣ በመጨረሻም ወንድ ልጃችን ተመልሶ ተልእኮውን አጠናቀቀ።

የሰማይ አባታችን ሁሉን-ቻይ እና ሁሉን-አዋቂ ነው። አካላዊ ትግላችንንም ያውቃል። በህመም፣ በሽታ፣ እርጅና፣ አደጋዎች ወይም የልደት ችግሮች ምክንያት አካላዊ ሥቃዮቻችንን ያውቃል። ከጭንቀት፣ ብቸኝነት፣ ድብርት ወይም የአእምሮ ሕመም ጋር የተዛመዱ ስሜታዊ ሽንፈቶች እንዳሉም ያውቃል። ኢፍትሐዊ ድርጊት የተፈጸመበትን ወይም በደል የደረሰበትን እያንዳንዱን ሰው ያውቃል። ድክመቶቻችን እና የልብ ዝንባሌዎቻችንና ፈተናዎችንን እርሱ ያውቃል።

በሟች ህይወት መልካምን በክፉ በላይ እንደምንመርጥ ለማየት እንፈተናለን። ትእዛዛቱን ለሚጠብቁ፣ ከእርሱ ጋር “በማያልቀው ደስታ” አብረው ይኖራሉ።2 እንደ እርሱ ለመሆን የእኛን እድገት ይረዳን ዘንድ፣ የሰማይ አባት ሁሉንም ሀይል እና እውቀት ለልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰጥቷል። ክርስቶስ ሊፈውሰው የማይችል አካላዊ፣ ስሜታዊ ወይም መንፈሳዊ ህመም የለም።3

ከአዳኝ ምድራዊ አገልግሎት፣ ቅዱሳት መጻህፍት ኢየሱስ ክርስቶስ በአካል በሥቃይ የተሞሉትን ለመፈወስ መለኮታዊ ኃይሉን እንደተጠቀመ በርካታ ተዓምራዊ ክስተቶችን ይተርካሉ።

የዮሐንስ ወንጌል ለ 38 አመታት አቅም በሚያሳጣ የአካል ጉዳትን ተቋቁሞ የነበረን አንድ ሰው ታሪክ ይተርካል።

“ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ ፥እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ ፥– ልትድን ትወዳለህን? አለው።”

ሰውየው በጣም በሚያስፈልበት ወቅት ማንም ሰው ሊረዳው አብሮት እንዳልነበረ ምላሽ ሰጠ።

“ኢየሱስ፣ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው።

“እናም ወዲያውም ሰውዬው ዳነ፣ እና አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።”4

የሰውዬው (38 አመታት) ምን ያህል ጊዜ በግሉ እንደተጎዳ እና አዳኙ በተሳተፈ ጊዜ ፈውስ በፍጥነት እንደመጣ ያለውም ግንኙንት ልብ በሉ። ፈውሱ ወዲያውኑ ነበር።”

በሌላ ጊዜ ደግሞ፣ ገንዘቧን ሁሉ በሐኪሞች የቸረሰች፣ ለ 12 አመታት ደም ሲፈሳት የነበረች አንዲት ሴት፣ በኋላው ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች ፥ እና ወዲያው የደም ፈሳሽ ቆመ። …

“ኢየሱስም አንድ ሰው ዳስሶኛል፥ ኃይል ከእኔ እንደ ወጣ እኔ አውቃለሁና አለ።

“ሴቲቱም እንዳልተሰወረች ባየች ጊዜ፣ … እንዴት ወዲያውኑ እንደተፈወሰች … በሕዝቡ ሁሉ ፊት አወራች።”5

በአገልግሎቱ፣ ክርስቶስ በሥጋዊ አካል ላይ ኃይል እንዳለው አስተምሯል። አካላዊ ህመማችንን ክርስቶስ ሲፈውስ ጊዜውን መቆጣጠር አንችልም። ፈውስ እንደ ፈቃዱ እና እንደ ጥበቡ ይፈጸማል። በቅዱስ መጻህፍት ውስጥ አንዳንዶች ለበርካታ አስርት ዓመታት፤ ሌሎቹ፣ ሙሉ ሟች ህይወታቸውን ሲሰቃዩ ኖረዋል። የምድራዊ ሕመሞች እኛን ለማጣራት እና በእግዚአብሔር ላይ ያለንን መተማመን ሊያሳድጉልን ይችላሉ።. ነገር ግን ክርስቶስ እንዲሳተፍ ስንፈቅድ፣ ሸክማችንን ለመቋቋም የላቀ ችሎታ ይኖረን ዘንድ ሁሌም በመንፈሳዊነት ያጠነክረናል።

በመጨረሻም, ማንኛውም አካላዊ ሕመም፣ በሽታ ወይም ፍጽም አለመሆን በትንሣኤው እንደሚፈወስ እናውቃለን። ያም ለሰው ዘር ሁሉ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ስጦታ ነው።6

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋዊ አካላችን በላይ መፈወስ ይችላል። መንፈሳችንንም ሊፈውስ ይችላል። በቅዱስ ቃሉ ውስጥ ክርስቶስ መንፈሳቸው ደካማ የሆኑትን እንዴት እንደረዳቸው እና እንደፋወሳቻው እንማራለን።7 እነዚህን አጋጣሚዎች ስናሰላስል፣ ህይወታችንን ለመባረክ በአዳኝ ሀይል ተስፋችን እና እምነታችን ይጨምራል። ኢየሱስ ክርስቶስ ልባችንን ሊለውጥ፣ ከሚደርስብን ኢፍትሃዊነት ወይም ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ልፈውሰን፣ የመጣት እና የሐዘን ስሜት ለመቋቋም አቅማችን ልያጠናክረን፣ በሕይወታችን የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ለመቋቋም እንዲረዳን፣ በስሜት እየፈወሰን፣ ሰላም ልያመጣልን ይችላል።

ክርስቶስ ኃጢአት በምንሠራበት ጊዜ ሊፈውሰንም ይችላል። ሆን ብለን የአምላክን ህግ በምንጥስ ጊዜ ኃጢአት እንሠራለን።8 ኃጢአት ስንሠራ ነፍሳችን ይረክሳል። በእግዚአብሔር ፊት ምንም ርኩስ ነገር ልኖር አይችልም።9 ከኃጢአት ንጹህ መሆን መንፈሳዊው መፈወስ ነው።10

እግዚአብሔር አብ ኃጢአትን እንደምንሰረ ያውቃል፣ ነገር ግን ለመዳን እንድንችል መንገድ አዘጋጅቶልናል። ሽማግሌ ሊን ጂ ሮቢንስ እንዳስተማሩት ፥ “ንስሃ በውድቀት ጊዜያችን [የእግዚአብሔር] የመጠባበቂያ እቅድ አይደለም። ንስሃ እደምንወድቅ በመወቅ የተዘጋጃ የእርሱ ዕቅድነው።”11 ኃጢአት ስንሠራ መልካም የሆነውን ከክፉው ለመምረጥ እድሉ አለን። ኃጢአት ከሠራን በኋላ ንስሓ ስንገባ መልካም የሆነውን እንመርጣለን። በኢየሱስ ክርስቶስ እና የሃጢያት ክፍያ መስዋዕት, ንስሓ ብንገባ ከኃጢያታችን መቤዠት እናም ወደ እግዚአብሔር አብ መመለስ እንችላለን። መንፈሳዊ ፈውስ የአንድ-ወገን ስራ አይደለም-የአዳኝ የመፈወስ ኃይል እና ኃጢአተኛው ከልቡ ንስሐ መግባት ይጠይቃል። ንስሃ ላለመግባት የሚመርጡ፣ የክርስቶስ የመፈውስ ስጦታ አለመቀበሉም። ለእነሱ፣ ምንም ዓይነት መዳን አልተገኘላቸውም።12

ሰዎች ንስሓ እንድገቡ ስመክራቸው፣ በኃጢአት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ትክክለኛውን ውሳኔ ለመወሰን በመቸገራቻው ተገርሜ ነበር። መንፈስ ቅዱስ ይተዋቸዋል፣ እናም ወደ እግዚአብሔር የሚያመጣቸውን ምርጫ ለማድረግ ብዙ ጊዜ ትግል ያደርጋሉ። በኃጢአታቸው ውጤት በመጨነቅ ወይም በመፍራት፣ ለብዙ ወራትም ወይም ለዓመታት ይታገላሉ። በአብዛኛ ጊዜ ለመቀየር ወይም ይቅርታ ለማግኘት እንደማይችሉ ይሰማቸዋል። የሚወዷቸው ሰዎች ያደረጉትን ነገር ቢያውቁ፣እነርሱን መውደዳቸውን እንደሚያቆሙ ወይም እደሚተዉዋቸው ያላቸውን ፍርሃት ብዙ ጊዜ ሲናገሩ እሰማቸዋለሁ። ይህን መሰሉን አስተሳሰብ ሲከተሉ፣ እነሱ ዝም ለማለት አና የእነሱን ንስሃ ለመዘግየት ነው ይወስናሉ። እነሱ ከሚወዷቸው የበለጠ እንዳይጎዱ አሁን ንስሐ አለመግባቱ ይሸላላል በመለት እነሱ በተሳሳተ መንገድ ተሰማቸው። በአዕምሮአቸው ውስጥ አሁን ከዚህ የንስሓ ሂደት ይልቅ ከዚህ ሕይወት በኋላ መከራ መቀበል የተሻለ ነው። ወንድሞች እና እህቶች፣ የእነንተን ንስሀ መግባት መቆየት ፈጽሞ ጥሩ ሀሳብ አይደለም። ጠላት በተደጋጋሚ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለን እምነት ላይ እርምጃ ከመውሰድ ለመከላከል ፍርሃትን ይጠቀማል።

የሚወዷቸው ሰዎች ስለ ኃጢያቱ ባህሪ እውነታ ሲጋለጡ፣ ጥልቅ ቁስልም ሊሰማቸው ቢችሉም፣ ከልብ ንስሃ የሚገቡ ኃጢአተኞችን እድለወጡ እና ከእግዚአብሔር ጋር እንድታረቁ ብዙውን ጊዜ ለመርዳት ይፈልጋሉ። በእርግጥም፣ ኃጢአተኛው ኃጢአቱን ሲናዘዝ እና በሚወዷቸው እና ኃጢአቶቻቸው እንዲተዋቸው በረዱ ሰዎች ስከበቡ ሲረዳ መንፈሳዊ ፈውስ እየተፋጠነ ይሄዳል። እባካችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በተጨማሪም ወደ እርሱ ዞር የሚሉ ንጹህ የኃጢአት ሰለባዎችን በመፈውስ ታላቅ እንደ ሆነ አስታውሱ።13

ፕሬዘደንት ቦይድ ኬ. ፓከር እንዲህ አሉ “ስህተት በምንሠራበት እና ኃጢያትን ስንሰራ መንፈሳችን ተበላሽቷል። ነገር ግን እንደ ሟች አካላችን ሁኔታ ሰይሆን፣ የንስሐው ሂደት ሲጠናቀቅ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ምክንያት ምንም ጠባሳ አይኖርም። የተስፋው ቃል፣ ‘እነሆ፣ ከኃጢአቱ ንስሐ የገባ ይቅር ይባላል ፥ እኔም ጌታዬ አላስብም ይላል’ [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥42]።”14

“በሙሉ ልብ አላማ”15 ንስሐ ስንገባነ፣ “ወዲያውኑ ታላቁን የመዳን ዕቅድ በሕይወታችን ውስጥ ይፈጸማል።”16 አዳኝ ይፈውሰናል።

በሚስዮን መስክው በደም መርጋት በሽታ የተያዘውን ወንድ ልጅ የሚስዮን ጓደኛው እና የሕክምና ባለሙያዎች በፍጥነት ረዱት። ልጃችን ደም መርጋቱን የመለውጥ ሕክምናን ለመውሰድ መረጠ። ለሟችው ህይወቱ አብሮት ልኖር ይችል የነበረው የበሽታው ሽባነት ተፅዕኖ ተለወጠ። በተመሳሳይ መንገድ፣ ንስሓ ለመግባት እና የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በህይወታችን ውስጥ በፍጥነት ስናመጣ፣ የኃጢያት ውጤቶችን ወዲያው እንፈወሳለን።

ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ይህንን ጥሪ አቅርበዋል: “መንገዱን ከጣሳችሁ … ተመልሳችሁ እንዲትመጡ እጋብዛችኋለሁ። ሀሳባችሁ ምንም ቢሆን፣ ፈተናችሁ ምንም ቢሆን፣ በዚህች በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለእናንተ ቦታ አለ። እናንተ እና ገና ያለተወለዱት ትውልዶች ወደ ቃል ኪዳን መንገድ ለመመለስ አሁን በምታደርጉት ስራዎቻችሁ ይባረካሉ።”17

መንፈሳዊ ፈውሳችን አዳኛችን ያስቀመጠቸውን ሁኔታዎች እንድናሟላ ይጠይቀናን። እኛ ልንዘገይ አይገባም! እኛ ዛሬ መተግበር አለብን! መንፈሳዊ ሽባነት ዘለአለማዊ እድገታችሁን እንዳይገድብ ዛሬ ተግብሩ። በምናገርበት ጊዜ፣ በደል የፈጸማችሁትን ሰው ይቅርታ መጠየቅ እንደሚያስፈልግ ከተሰማችሁ እርምጃ እንዲወስዱ እጋብዛችኋለሁ። ያደረጋችሁትን ነገር ንገሯቸው። ይቅርታ ጠይቋቸው። በቤተመቅደስህ ብቁነታችሁ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ኃጢአት ከፈጸማችሁ፣ ዛሬ ከኤጲስ ቆጶሳችሁ ጋር እንድትመክሩ እጋብዛችኋለሁ። አትዘግዩ።

ወንድሞቼና እህቶቼ፣ እግዚአብሔር በሰማይ የሚኖር ወዳጁ አባታችን ነው። ሁሉንም ኃይልና እውቀት ለተወዳጅ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰጥቷል። በእሱ ምክንያት፣ የሰው ዘር በሙሉ አንድ ቀን ከማንኛውንም አካላዊ ሕመም ለዘላለም ይፀናል። በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ምክንያት፣ ንስሐ ከገባን እና ልባችንን ሙሉ በሙሉ ወደ አዳኙ ከመለስን፣ እርሱ መንፈሳዊንት ይፈውሰናል። ይህ ፈውስ ወዲያውኑ ሊጀመር ይችላል። ምርጫው የእኛ ነው!ሙሉ እንደረጋለን?

የኢየሱስ ክርስቶስ እንድንድን ዋጋ እንደከፈለልን እመሰክራለሁ። ነገር ግን እኛ የሰጠንን የፈውስ መድሃኒትን ለመውሰድ መምረጥ አለብን። ዛሬውኑ ውሰዱ። አትዘግዩ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. መድሀኒቱ tPA (tissue plasminogen activator) ይባላል።

  2. ሞዛያ 2፥41።

  3. ማቴዎስ 4፥24 ይመልከቱ። ክርስቶስ የታመሙ ሰዎችን፣ እንዲሁም “የተለያዩ በሽታዎች፣” “ስቃይ፣” “ክፉ መንፈስ የያዛቸውን፣” እና “ያበዱትን” ሁሉ እየፈወሰ ሄደ።

  4. ዮሀንስ 5፥5–9 ይመለከቱ፤ ትኩረት ተጨምሯል።

  5. ሉቃስ 8፥43–47 ይመለከቱ፤ ትኩረት ተጨምሯል።

  6. አልማ 40፥23ሔላማን 14፥17

  7. ሉቃስ 5፥20፣ 23–25 ይመልከቱ፤ ደግሞም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ሉቃስ 5፥23 (በሉቃስ 5፥23፣ ግርጌ ): “ኃጢያቶችን ለመሰረይ የታመመው እንዲነሳ እና እንዲራመድ ከማድረግ በላይ ታላቅ ሀይል ያስፈልገዋልን?”

  8. 1 ዮሀንስ 3፥4 ይመልከቱ።

  9. 3 ኔፊ 27፥19 ይመልከቱ።

  10. The Gospel of Jesus Christ,” Preach My Gospel: A Guide to Missionary Service, rev. ed. (2018), lds.org/manual/missionary.

  11. Lynn G. Robbins, “Until Seventy Times Seven,” Liahona, May 2018, .

  12. ሞዛያ 16፥5 ይመልከቱ።

  13. ብበዙ ጊዜዎች የጋብቻን ቃል ኪዳን እና ታማኝነት የሰበረን፣ ወደ አዳኝ ሙሉ ፈዋሽ ሀይል በህይወታቸው እንዲያገኙ፣ ቤተሰቡች በመተባበር ሲደግፉ የግለሰቦች መፈወስ ሲፋጠን ተመልክቻለሁ። በእውነት ንስሀ የገባ ነፍስ በቅንነት መቀየር ከፈለገ፣ የቤተሰብ አባላት ወንጌልን በማጥናት፣ በቅንነት በመጸለይ፣ እና ኃጢያተኛን ለመቀየር ብቻ ሳይሆን በህየታቸው የአዳኝ ፈዋሽ ሀይል የሚገባበትን በር ለመክፈት እንደ ክርስቶስ አይነት አገልግሎት እንዲያደርጉ ይረዷቸዋል። ለመደረግ ትክክል ከሆነም፣ የተጎዱትም ኃጢያት የሰራዋን ምን አብረው ለማጥናት፣ እንዴት ለማገልገል፣ እና የቤተሰብ አባላት ንስሀ የሚገባው ነፍስን ለመደገፍ እና ለማጠናከር እና ከኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ ሀይል ጥቅም እንዲያገኙ በመርዳት፣ የሰማይ መመሪያን እንዲፈልጉ ለመርዳት ይችላሉ።

  14. ቦይድ ኬ. ፓከር “የደህንነት እቅድ፣” Liahona፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 28።

  15. 3 ኔፊ 18፥32።

  16. አልማ 34፥3፤ ትኩረት ተጨምሯል።

  17. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ወደፊት አብረን ስንገፋ፣” Liahona ሚያዝያ፣ 2018 (እ.አ.አ)፣ 7።

አትም