2010–2019 (እ.አ.አ)
የነፍሶች እረኝነት
ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ)


15:11

የነፍሶች እረኝነት

በፍቅር ለሌሎች እንደርሳለን ምክንያቱም ያ አዳኛችን ያዘዘን ነውና።

በቅርብ ጊዜ ከጓደኛዬ ጋር በነበረኝ ንግግር፣ በወጣትነቱና እንደ አዲስ የቤተክርስቲያኗ አባል እንደተጠመቀ፣ በድንገት አጥቢያው ውስጥ አባል መሆን እንዳልተሰማው ነገረኝ። ያስተማሩት ወንጌል ሰባኪዎች ወደ ሌላ ቦታ ሄደዋል፣ እናም በውጪ እንዳለ ሰው ስሜት ተሰማው። በአጥቢያው ጓደኞች ሳይኖሩት፣ የድሮ ጓደኞቹን አገኘ እናም ከእነርሱም ጋር ከቤተክርስቲያኗ ተሳታፊነት የሚወስዱ ነገሮችን ማድረግ ጀመረ—እንደዚህም ሆኑ ከመንጋዎች መራቅ ጀመረ። በአይኑ እምባዎች ኖሮት፣ የአጥቢያ አባል የሚያገለግል እጅ ወደ እርሱ በመዘርጋቱ እና በሙቅ ተቀባይ መንገድ እንዲመለስ በመጋበዙ እንዴት ጥልቅ ምስጋና እንደሚሰማው ገለጸ። በጥቂት ወራት ውስጥም፣ በመንጋዎች መጠበቂያ ውስጥ፣እራሱን እና ሌሎቹን በማጠናከር ተመለሰ። ይህን ወጣት ሰው ለፈለጉት፣ አሁንም እንደ ሰባዎች አመራር አባል በኋላዬ ለሚቀመጡት እረኛ፣ ለሽማግሌ ካርሎስ ኤ. ጉዶይ፣ ምስጋናችን ታላቅ አይደለምን?

እንዴት እንዲህ አይነት ትንሽ ጥረት የዘለአለም ውጤት እንዳለው አስገራሚ አይደለምን? ይህ እውነት በቤተክርስቲያኗ አገልግሎት ጥረት ውስጥ መካከለኛው ነው። የሰማይ አባት የእኛን ቀላል፣ የየቀኑ ጥረትን ይወስዳል እናም ታዕምራታዊ ወደሆነም ነግር ይለውጠዋል። ፕሪእዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን “እርስ በራስ በምንንከባከብበት መንገድ ጌታ አስፈላጊ ለውጦችን አድርጓል፣1 ብለው ያስተዋወቁበት፣ እናም “አዲስ፣ ቅዱስ የሆነ ሌሎችን የመንከባከብ እና የማገልገል ዘዴዎችን እንጠቀማለን። ለእነዚህ ጥረቶች “ማገልገል”ብለን እንጠራቸዋለን”2 በማለት ከለጹ ስድስት ወር አልፏል።

ፕሬዘዳንት ኔልሰን ደግመውም እንዲህ ገለጹ፥ “የጌታ እውነተኛ እና ህያው ቤተክርስቲያን ምልክት ሁልጊዜም ለእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጆች እና ለቤተሰቦቻቸው በሚደረግ የተደራጀ፣ የተመራ የአገልግሎት ጥረት ነው። ይህች የእርሱ ቤተክርስቲያን ስለሆነች፣ እኛም እንደ አገልጋዮቹ፣ ልክ እርሱ እንዳደረገው፣ አንዱን እናገለግላለን። በስሙ፣ በሀይሉ እና በስልጣኑ፣ እናም በእርሱ አፍቃሪ ደግነት እናገለግላለን።”3

ከዚያ ማስተዋወቂያ ጀምሮ፣ የእናንተ መልስ አስገራሚ ነበር! እነዚህን ለውጦች በህያው ነቢያችን አመራር ስር በአለም አቀፍ በእያንዳንዱ ካስማዎች ስጥ በታላቅ ውጤት እንደተከናወኑ መረጃዎች ተቀብለናል። ለምሳሌ፣ የሚያገለግሉ ወንድሞች እና እህቶች ቤተሰቦች ተመድቦላቸዋል፣ አብረው የሚያገለግሏቸውም፣ እንዲሁም ወጣት ወንዶች እና ሴቶች፣ ተደራጅተዋል፣ እናም የአገልግጋይ የቃል ጥያቄ እየተፈጸሙ ናቸው።

ከትላንትና ራዕያዊ ማስታወቂያ—“በቤት እና በቤተክርስቲያን ውስጥ መካከል የሚገኝ አዲስ እና የተመዛዘነ ግንኙነት”4—ከመገለጹ ከስድስት ወር በፊት፣ የአገልግሎት ራዕያዊ ማስታወቂያ መሰጠቱ በአጋጣሚ አይደለም። በጥር ጀምሮ፣ በቤተክርስቲያን አምልኮት አንድ ሰዓይ ቀናሽ ስናሳልፍ፣ በአገልግሎት የተማርናቸው በሙሉ ከቤተሰብ እና ከምናፈቅራቸው ጋር ሁሉ ያንን ባዶ ጊዜ በከፍተኛ፣ በቅዱስ፣ በቤት-በተመሰረተ የሰንበት ቀን አጋጣሚዎች ለሞምላት እንችላለን።

እነዚህ ድርጅቶች በቦታ ተመስርተው፣ “በጌታ መንገር እያገለገልን እንዳለን እንዴት እናውቃለን?” በማለት እንጠይቅ ይሆናል። መልካም እረኛውን በሚፈልገው መሰረት እየረዳነው ነውን?

ከፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ ጋር በቅርብ በነበረን ውይይት፣ ቅዱሳን በእነዚህ ልዩ ለውጦች ራሳቸን በማስተካከላቸው አሞግሰዋል፣ ነገር ግን ደግሞም አባላት አገልግሎት “ጥሩ” ከመሆን በላይ እንደሆነ እንዲያቁም የልብ ፍላጎታቸውን ገልጸዋል። ይህም ጥሩ መሆን አስፈላጊ አይደለም ለማለት አይደለም፣ ነገር ግን የአገልግሎት እውነተኛ መንፈስን የሚረዱት ጥሩ ከመሆን በላይ እንደሆነ ያውቃሉ። በጌታ መንገድ ሲከናወን፣ ልክ ለሽማግሌ ጉዶይ እንዳደረገው፣ አገልግሎት እስከ ዘለአለም ድረስ የሚሰሙ መልካም ተፅዕኖዎች ይኖሩታል።

“አዳኝ በፍቅር ምክንያት ሲያገለግል፣ በምሳሌ ማገልገል ምን ማለት እንደሆነ አሳይቷል። … እርሱም … ሁሉም እንዲከተሉት በመጋበዝ በአካባቢው የሚገኙትን አስተማረ፣ ጸለየ፣ አፅናና፣ እናም ባረከ። … እንደ ቤተክርስቲያኗ አባላት፣ እርሱ እንደሚያደርገው—‘ቤተክርስቲያኗን ሁልጊዜ በመጠበቅ፣’ ‘እና ክዕነርሱ ጋር በመሆን እና በማጠናከር፣’ ‘የእያንዳንዱን አባል ቤት በመጎብኘት፣’ እያንዳንዱ የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ በመርዳት ለማገልገል በጸሎት ሲፈልጉ [በከፍተኛ እና በቅዱስ መንገድ] ያገለግላሉ”5

እውነተኛ እረኝ በጉን እንደሚወድ፣ እያንዳንዱን በስም እንደሚያውቅ፣ እና “ስለእነሱ እንደሚያስብ” እንረዳለን።6

በጎች በተራራ ላይ

የድሮ ጓደኛዬ ክብት በማርባት ህይወቱን ሁሉ አሳለፈ፣ ይህን ክብቶች እና በጎች የማሳደግ ከባድ ስራ በሯኪ ተራራዎች ላይ ነበር የሚሰራው። በጎችን በማሳደግ ላይ ያለውን ፈተናዎች እና አደጋዎች ከእኔ ጋር ተካፈለ። በጸደይ መጀመሪያ ላይ፣ በተራራ ላይ የነበረ በረዶ ከመለጠ በኋላ፣ 2 ሺህ የሚሆኑትን የቤተሰቡን መንጋዎች ለበጋ ወደ ተራራው እንደሚያስገባቸው ገለጸ። በዚያም፣ ከበጋ የግጦሽ መሬት ወደ ክረምት ግጦሽ መሪት እስከሚወሰዱበት መከር ድረስ በጎቹን ይጠብቅ ነበር። ትልቅ መንጋዎችን መጠበቅ አስቸጋሪ እንደሆነ፣ ከባድ ቀናት እና በለሊት መቆየት የሚያስፈልገው—ጸሀይ ከመውጣቷ በፊት መነሳት እና ጨመላ ከህነ በኋላ መጨረስ እንደሚያስፈልገው ገለጸ። በብቻው ይህን ለማድረግ አይችልም ነበር።

ከብት የሚያረባ ከበግ ጋር

ሌሎቹ ልምምድ ያላቸው ሌሎች መንጋዎችን በመጠበቅ ረዱይረዳሉ፥ ልምድ ያላችው የገበሬ እጆች ከአጋሮቻቸው ጥበብ እየተጠቀሙ በነበሩ ወጣት እጆች ታግዘው የተደባለቁትን ጨምሮ። እንዲሁም ሁለት ያረጁ ፈረሶቹ ላይ፣ ሁለት በስልጠና ውስጥ የነበሩ የፈረስ ግልገሎቹ ላይ፣ ሁለት የበግ እረኛ ውሾቹ ላይ፣ እናም ሁለት ወይም ሶስት የበግ እረኞች ቡችሎቹ ላይ ተደገፈ። በጋውን ሙሉ ጓደኛዬ እና ቡድኑ፣ ንፋስ እና ወጀቦች፣ ህመም፣ ጉዳቶች፣ ድርቅ፣ እንዲሁም ማንኛውም ሰው ሊገምተው የሚችል እያንዳንዱን ችግር ተጋፈጡ። የተወሰኑ ዓመታቶች ላይ በጎቹን በህይወት ለማቆየት በጋውን ሁሉ ውሃ ያግዙ ነበር። ከዛ በኋላ በየዓመቱ በልግ መጨረሻ ላይ፣ የክረምት አየር ሲያስፈራራ በጎቹ ከተራራ ላይ ተወስደው ተቆጥረው ነበር፣ ከሁለት መቶ በላይ የጠፉ እና ያልተገኙም ነበሩ።

በጎችን እየጠበቁ
የበግ መንጋዎች

በፀደይ ወቅት መጀመሪያ ላይ ሁለት ሺ በተራራ ላይ ከነበሩ መንጋዎች ከአንድ ሺ ስምንት መቶ በታች ቀንሰው ነበር። አብዛኛዎቹ የጠፉት በጎች በበሽታ ወይም በተፈጥሮ ሞት አልነበረም፣ ነገር ግን በአዳኝ የተራራ አንበሶች እና ተኩላዎች ነበር። እነኚህ አዳኞች እራሳቸውን ከእረኛቸው ጥበቃ ስር በማግለል ከመንጋው ጥበቃ ፈርጥጠው የወጡትን የበግ ግልገሎች ነበር በአብዛኛው ያድኑ የነበሩት። አሁን የገለፅኩትን በመንፈሳዊ አግባብ ለጥቂት ጊዜ ታስቡታላችሁን? እረኛው ማነው? መንጋውስ ማን ነው? እረኛውን የሚያገለግሉትስ እነማን ናቸው።

መልካሙ እረኛ

ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ራሱ ብሏል፣ “ እኔ መልካም እረኛ ነኝ፣ እናም በጎቼን አውቃለሁ፣ … እናም ህይወቴንም ለበጎቼ አሳልፌ ሰጠሁ። 7

ኢየሱስ በጎቹን ሲመግብ

ነብዩ ኒፋይም እየሱስ ”በጎቹን ይመግባል፣ እናም በእርሱ ውስጥም ግጦሽን ያገኛሉ ብሎ አስተማር።”8 “እግዚአብሔር እረኛዬ መሆኑን”፣9 እና እያንዳዳችን በአርሱ እንደምንታወቅ እና በእርሱ ጥበቃ ስር እንደሆንን በማወቄ የማይነጥፍ ሰላምን አገኛለሁ። የህይወትን አውሎ ንፋስን እና ወሽንፍር ዝናብን፣ ህመምን፣ ጉዳትን፣ እናም ድርቀትን ሲያጋጥመን፣ ጌታ አምላካችን ያገለግለናል። ነፍሳችንንም ይመልሳል።

ልክ ጓደኛዬ በአረጁ እና በለጋ ሰራተኞች፣ ፈረሶች እና የበግ ውሾች ታግዞ በጎቹን እንደጠበቀ ሁሉ፣ በተመሳሳይ መልኩ ጌታም ድግሞ መንጋዎቹ ውስጥ ላሉት በጎቹን የመንከባከብ ፈታኝ ስራ እርዳታን ይፈልጋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያገለግል

የተወዳጁ የሰማይ አባት ልጆች እንደመሆናችን እናም በመንጋው እንዳለን በጎች፣ በክርስቶስ እንደግለሰብ ስለመገልገላችን በረከት እንደሰታለን። በተመሳሳይ መልኩ፣ እኛ እራሳችን እንደ እረኛነታችን፡ በአጠገባችን ላሉ የአገልግሎት እርዳታ የማቅረብ ሃላፊነት አለብን። “አገልግሉኝ እናም በስሜ ሂዱ ፣ እናም … በጎቼንም አንድ ላይ ሰብስቡ”10 ለሚለው የጌታ ቃል እንታዘዛለን።

ማን ነው እረኛ? እያንዳንዱ ወንድ፣ ሴት፣ እናም በእግዚአብሄር መንግስት ያሉ ልጆች ሁሉ እረኞች ናቸው። ጥሪ አያስፈልግም። ከተጠመቅንበት ውሃ ስንወጣ ጀምሮ፣ ለዚህ ስራ ታዘናል። በፍቅር ለሌሎች እንደርሳለን ምክንያቱም ያ አዳኛችን ያዘዘን ነውና። አልማ ትኩረት እንደሰጠው፥ “… የትኛው እረኛ ነው ብዙ በጎች እያሉት፣ ተኩላዎችስ ገብተው መንጋዎቹን እንዳይበሉበት የማይጠብቃቸው? እርሱ አያባርርምን?”11 ሁልጊዜም ጎረቤቶቻችን በስጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ ጭንቀት ላይ ሲሆኑ ልንረዳቸው እንሮጣለን። የእርስ በራሳችንን ሸክሞች እንሸከማለን፡ ይቀሉ ዘንድ። ከሚያዝኑት ጋር እናዝናለን። አፅናኝ የሚፈልጉትን እናፅናናለን። 12 ጌታ በፍቅር ይህን ከእኛ ይፈልጋል። እናም መንጋውን እንዴት እንደተንከባከብን በሃላፊነት የሚይዘን ቀን ይመጣል።13

እረኛው ጓደኛዬ ሌላ ስለበግ ጥበቃ እና እንክብካቤ በጣም አስፈላጊ ነገርን አካፈለ። በበለጠም ገለፀ እነኛ የጠፉት በጎች አብሶ ለአዳኞቹ የተጋለጡ እንደሆኑ ገለጸ። በእርግጥም፣ ከእርሱ እና ከቡድኑ ካላቸው ጊዜ ከመቶ 15ቱ የጠፉትን ለመፈለግ የተመደበ ነው። ቶሎ ብለው የጠፉትን በጎች ብዙ ከመንጋው እርቀው ሳይሄዱ ካገኙት፣ በጉ የመጎዳት እድሉ ያነሰ ነው። የጠፉትንን ንበጎች ማግኘት በጣም ብዙ ትዕግስት እና ስነስርዓት ያስፈልገዋል።

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት፣ በጣም የሚስብ አንቀፅ በሃገር ጋዜጣ ውስጥ አግኝቼ፡ አስቀምጬው ነበር። የመጀመሪያ ገጽ ርዕሱ “ቋራጥ ውሻ የጠፉትን በጎች አይተውም” በማለት ይነበብ ነበር።14 ይህ አንቀፅ ከጓደኛዬ ንብረት ቅርብ የነበረ ድርጅት በበጋ ወቅት ወደኋላ ቀርተውበት ስለነበሩ በትንሽ ስለሚቆጠሩ በጎች ይገልፃል። ከሁለት ወይም ከሶስት ወር በኋላ፣ በተራራ ላይ በበረዶ ተከበው እና ታገተው መሄጃ አጡ። በጎቹም ወደኋላ ሲቀሩ፣ ውሻውም ከነሱ ጋር ቀረ፣ በጎቹን መጠበቅ እና መከላከል የሱ ገዴታ ነበርና። ጥበቃውን ትቶ አይሄደም! እዛም ቀረ—የጠፉት በጎች ዙሪያ ለወራቶች በብርድ እና በበረዷማ አየር እየዞረ ፣ ከተኩላ ፣ እና ከተራራ አንበሶች፣ ወይም ከሌሎች በጎቹን ሊጎዱ ከሚችሉ አዳኞች በመጠበቅም። በጎቹን አግዶ እና መርቶ ወደ መጋቸው እና ወደ እረኛቸው ማምጣት እስኪችል ድረስ እዚያ ቆየ። በዚህ ጽሑፍ የመጀመሪያ ገጽ ላይ የተቀመጠው ምስል አንድ ሰው በዚህ የበግ ጠባቂ ውሻ አይን እና ጸባይ ገጸ-ባህሪውን እንዲመለከት ያስችለዋል።

የበግ ጠባቂ ውሻ አይን እና ጸባይ ላይ ያለ ገጸ-ባህሪ

እረኛ ፣ አገልጋይ እህት እና ወንድሞች እንደመሆናችን ስለ ሃላፊነታችን የበለጠ ሃሳብን የሚሰጡ ምሳሌን እና መመሪያዎችን ከአዳኛችን በአዲስ ኪዳን ውስጥ እናገኛለን።

“መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?

“ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል።”

ወደቤት ሲያመጣችሁ፣ ለአንድ እና ለሁሉም እንዲህ ይላል፣ “የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ።”15

በምሳሌ ውሰጥ ያስትማርውን ትምህርት ስናጠቃልል፣ ይህንን ዋጋ የማይገኝለትን ምክርን እናገኛለን።

  1. የጠፉትን በጎች ማወቅ።

  2. እስኪገኙ ድረስ እንፈልጋቸዋለን።

  3. ሲገኙም፣ ወደቤት ለማምጣት ጀርባችን ላይ መሸከም ሊኖርብን ይችላል።

  4. እንደተመለሱም በጓደኛ እንከባቸዋለን።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ታላቅ ፈተናዎቻችን እና ታላቅ በረከቶቻችን የሚመጡት የጠፉትን በጎች ስናገለግል ሊሆን ይችላል። የቤተክርስትያን አባሎች በመፅሃፈ ሞርሞን ውስጥ “ህዝባቸውን ጠበቁ ፣ እናም ፃድቅ ስለሆኑ ነገሮች መገቧቸው።”16 እኛም አገልግሎት “በመንፍስ መመራት እንዳለበት፣ … ለመቀየር የሚችል፣ እና … ለእያንዳንዱ አባልም እንደሚያስፈልገው በግል መደረግ እንዳለበት በማስታወስ፣” ምሳሌቸውን መከተል እንችላለን። እንዲሁም “ግለሰብን እና ቤተሰብን ለቀጣይ ስነስርዓት ፣ ቃልኪዳናቸውን የሚጠብቁበት … ፣ እናም ራሳቸውን የሚችሉበትን” እርዳታ መፈለግ ወሳኝ ነው።17

እያንዳንዱ ነፍስ በእግዚአብሔር ዘንድ ውድ ነው። የእርሱ ግላዊ የማገልገል ጥሪው ለእርሱ እጅግ የላቀ ዋጋ እና አስፈላጊነት አለው፣ ስራው እና ክብሩ ነውና። ይህም በእውነት የዘላለም ስራ ነው። እያንዳንዱ ልጆቹ በእርሱ እይታ ዘንድ የማይገመት ብቃት አላቸው። መገምት እንኳን በማትችሉበት ፍቅሩ እናንተን ይወዳችኋል። ልክ እንደታማኙ የበግ ጠባቂ ውሻ፣ በነፋስ ፣ በነጎድጓድ ዝናብ ፣ በበረዶ፣ እናም በብዙ ነገር ውስጥ እናንተን ሊጠብቃችሁ በተራራው ላይ ይኖራል።

ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ባለፈው ጉባኤ እንዳስተማሩን፥ “ለአለም [እናም እኔ “ለአገልጋይ መጋዎቻችን” ብዬ ልጨምር] ያለን መልእክት ቀላል እና ልባዊ ነው፥ በመጋረጃው ሁለት በኩል ያሉትን የእግዚአብሔር ልጆችን ሁሉ ወደ አዳኛቸው እንዲመጡ፣ የቤተመቅደስ በረከቶችን እንዲቀበሉ፣ በደስታ እንዲጸኑ፣ እናም ለዘለአለም ህይወት ብቁ እንዲሆኑ እንጋብዛለን።”18

ለዚህ ነብያዊ እራዕይ እይታችንን ከፍ እናድርግ፣ ነፍሶችን ወደቤተመቅደስ እና በመጨረሻም ወደ አዳኛችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እናግድ ዘንድ። ታምራትን እንድንሰራ አይጠብቀንም። ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ወደ እርሱ እንድናመጣ ብቻ ነው የሚጠይቀን፣ እርሱ ነፍስን የማዳን ሃይል አለውና። እንዳዛ ሰናደርግ፣ ይህንን የተስፋ ቃል እናገኛለን፥ “እናም ዋናው እረኛ ሲከሰት፣ የማይጠፋ የክብር ዘውድ ትቀበላላችሁ።”19 ስለዚህ—እናም ስለአዳኛችን እና ቤዛችን ኢየሱስ ክርስቶስ—የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።