2010–2019 (እ.አ.አ)
ወላጆች እና ልጆች
ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ)


13:14

ወላጆች እና ልጆች

የሰማይ አባታችን ታላቅ የደስታ እቅድ እናንተ ማን እንደሆናችሁ እና የህይወታችሁ አላማ ምን እንደሆነ ይነግራችኋል።

ውድ እህቶቼ፣ ይህን የአጠቃላይ ጉባኤ የስምንት አመት እና ከዚያ በላይ እድሜ ላላቸው ሴቶች የስብሰባ ክፍል መሆኑ እንዴት አስደናቂ ነው። ከእህት መሪዎች እና ከፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ የሚያነሳሱ መልእክቶችን ሰምተናል። ፕሬዘደንት አይሪንግ እና እኔ በፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን አመራር ስር መስራትን እንወዳለን፣ እናም የእርሳቸውን ነቢያዊ መልእክትም በጉጉት እንጠብቃለን።

፩.

ልጆች ከእግዚአብሔር ከሚመጡት ስጦታዎች ሁሉ በላይ ታላቅ ዋጋ ያላቸው—የእኛ ዘለአለማዊ እድገታችን ናቸው። ነገር ግን፣ ብዙ ሴቶች ልጆች ለመውለድ ወይም ለመንከባከብ በማይፈልጉበት ጊዜ ነው የምንኖረው። ብዙ ወጣት ጎልማሳዎች የጊዜአዊ ፍላጎቶች እስከሚሟሉ ድረስ ጋብቻን ያዘገያሉ። የሚያገቡት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሰዎች እድሜ በሁለት አመት ጨምሮ ሄዷል፣ እናም ለቤተክርስቲያን አባላት የሚወለዱት የልጆች ቁጥርም ቀንሷል። ዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች ሀገሮች በማደግ በጡረት ያሉትን ጎልማሳዎን የሚረዱ ልጆ ቁጥር በመቀነሱ በችግር ላይ ነው ያሉት።1 ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከሚወለዱት ልጆች ከመቶ 40 የሚሆኑት ካላገቡ እናቶች የተወለዱ ናቸው። እነዚያ ልጆች ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው። እነዚህ አዝማሚያዎች የአባታችን መለኮታዊ የደህንነት ዕቅድ ላይ ይቃረናሉ።

፪.

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሴቶች እናት መሆን ለእነርሱ ከሁሉም በላይ ቅድሚያ ያለው እና የመጨረሻ ደስታቸው እንደሆነ ተረድተዋል። ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ ሒንክሊ እንዳሉት፥ “ሴቶች በአብዛኛው ታላቅ ሙሉነታቸውን እና ታላቅ ደስታቸውን የሚያዩት በቤት እና በቤተሰብ ውስጥ ነው። እግዚአብሔር በሴቶች ውስጥ በጸጥታ ጥንካሬ፣ በንጥረት፣ በሰላም፣ በመልካምነት፣ በምግባር፣ እና በፍቅር የሚገለፃንድ መለኮታዊ ነገር ተክሏል። እናም እነዚህ ሁሉ አስደናቂ ባሕርያት እውነተኛ እና ከሁሉም በላይ የሚያረካ ውጤት የሚገለጹበት በእናትነት ነው።”

እንዲህም ቀጠሉ፣ “ማንኛዋም ሴት ልትሰራው ከከምትችላት ታላቅ ስራ ውስጥ ልጆቿን በጻድቅነት እና በእውነት መንከባከብ እና ማስተማር እና ማኖር እና ማበረታታት እና ማሳደግ ነው። ምንም ነገር ብትሠራም፣ ከዚያ ጋር የሚወዳደር ሌላ ምንም ነገር የለም።2

እናቶች፣ ውድ እህቶች፣ በማንነታችሁ እና ለሁላችንም በምታደርጉት እናፈቅራችኋለን።

በ2015 (እ.አ.አ) “ለእህቶቼ ልመና” የሚል ርዕስ ባለው አስፈላጊ ንግግራቸው፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳሉት፥

“ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን የሚገቡ፣ እና ከዛ የሚጠብቁ፣ በእግዚአብሔር ሀይል እና ስልጣን መናገር የሚችሉ ሴቶች በሌሉበት የእግዚአብሔር መንግስት ሙሉ አይደልም እና ሊሆንም አይችልም!

“በእምነታቸው ጠቃሚ ነገሮችን እንዲከሰቱ ማድረግ የሚችሉ ሴቶች ያስፈልጉናል እናም በዚህች በሃጢያት የታመመች አለም ውስጥ ቅንነትን እና ቤተሰቦችን የሚከላከሉ ብርቱ ሴቶች … ዛሬ ያስፈልጉናል። በቃልኪዳን መንገድ ለእግዚአብሔር ልጆች እረኛ ለመሆን ቁርጠኝነት ያላቸው ሴቶች፤ የግል መገለጥን እንዴት መቀበል እንደሚችሉ የሚያውቁ ሴቶች፤ የቤተመቅደስ ቡራኬ ሀይልን እና ሰላምን የሚረዱ ሴቶች፤ ልጆችን እና ቤተሰቦችን ለመጠበቅ እና ለማጠንከር የሰማይ ሀይላት እንዴት እንደሚጠሩ የሚያውቁ ሴቶች፣ ያለፍራቻ የሚያስተምሩ ሴቶች ያስፈልጉናል።”3

እነዚህ የተነሳሱ ትምህርቶች “ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ” ውስጥ የተመሰረቱ ናቸው፣ በዚህም በዳግም የተመለሰችው ቤተክርስቲያን ምድር ከመፍጠሩ በፊት በነበረው በፈጣሪ እቅድ ዋና ክፍል የነበሩትን ትምህርቶች እና ልምዶች ታረጋግጣለች።

፫.

አሁን የዚህ አድማጮች ወጣቶች አነጋግራለሁ። ውድ እህቶቼ፣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ በዳግም ስለተመለሰ ወንጌል ባላችሁ እውቀትምክንያት፣ እናንተ ልዩ ናችሁ። እውቀታችሁ የማደግን ፈተናዎች ለመፅናናት እና ለማሸነፍ ያስችላችኋል። ከወጣትነት ጀምሮ፣ እንደ ጽሁፍ፣ እን መናገር፣ እናም ማቀድ አይነት ችሎታችሁን በገነቡ ፕሮግራሞች እና ድርጊቶች ተሳትፋችኋል። የሚከበር ጸባይን እና እንዴት ለመዋሸት፣ ለማታለል፣ ለመስረቅ፣ እና መጠጥ ወይም አደንዛዥ እፅን ለመጠቀም ያሉን ፈተናዎች ለመቋቋም ተምረናል።

የእናንተ ልዩነት በኖርዝ ኬሮላይና ዩንቨርስቲ የአሜሪካ ወጣቶቸና ሀይማኖት ጥናት ውስጥ ተለይቶ ታውቋል። በCharlotte Observer በተጻፈው አንቀጽም “የሞርሞን ወጣቶች ከሁሉም በላይ ይቋቋሙታል፥ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እነርሱ በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙት በመቋቋም ታሸንፋሉ” የሚል ርዕስ ነበረው። አንቀጹም እንዲህ ዘጋ፣ “ሞርሞኖች አደገኛ ጸባዮችን በማስወገድ፣ በትምህርት መልካም በመሆን እና ስለወደፊት አዎንታዊ አመለካከት በመኖር ከሁሉም የተሻሉ ናቸው።” አብዛኛውን ወጣቶቻችንንበቃል ጥያቄ ያነጋገረው በዚህ ጥናት አንዱ ፈታሺ እንዳለው፣ “ከተመለከትነው እያንዳንዱ ምድብ ግልጽ የሆነ ንድፍ ነበር፣ ሞርሞኖች መጀመሪያ ነበሩ።”4

የእድገት ችግሮችን ለምን ለመቋቋም ችላችኋል? ወጣት ሴቶች፣ ይህም የሰማይ አባታችንን የደስታ ታላቅ እቅድ ስለምትረዱ ነው። ይህም ማን እንደሆናችሁ እና ስለህይወታችሁ እቅድ ይነግራችኋል። ያ ግንዛቤ ያላቸው ወጣቶች ችግሩን በመፍታት መጀመሪያ እና መልካሙን በመምረጥ መጀመሪያ ናቸው። ከማደግ ላይ ያሉትን ሁሉንም ችግሮች ለማሸነፍ የጌታ እርዳታ ለማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ።

ውጤታማ የሆናችሁበት ሌላ ምክንያትም የሚያፈቅራችሁ የሰማይ አባት ልጆች መሆናችሁን መረዳታችሁ ነው። “ውድ ልጆች፣ እግዚአብሔር ቅርባችሁ ነው” የሚለውን መዝሙር ታውቁት ይሆናል። ሁላችን የዘመርነው እና የምናውቀው የመጀመሪያው አንቀጽ ይህ ነው፥

ውድ ልጆች፣ እግዚአብሔር ቅርባችሁ ነው፣

በቀን እና በምሽት ይመለከታችኋል፣

እናም እናንተን በማግኘት እና በመባረክ ይደሰታል፣

መልካሙን በማድረግ ከጣራችሁ።5

በእነዚህ አንቀጾች ውስጥ ሁለት ትምህርቶች ይገኛሉ፥ መጀመሪያ፣ የሰማይ አባታችን በቅርባችን ይገኛለናም በቀን እና በምሽት ይጠብቀናል። አስቡበት! እግዚአብሔር ያፈቅረናል፣ በቅርባችን ይገኛል፣ እናም ይጠብቀናል። ሁለተኛ፣ “መልካም በማድረግ በምንጥርበት” እኛን በመባረክ ይደሰታል። በፍርሀታችን እና በፈተናዎቻችን መካከል ይህ ምን አይነት መፅናኛ ነው!

አዎን፣ ወጣት ሴቶች፣ እናንተ የተባረካችሁ እና አስገራሚ ናችሁ፣ ነገር ግን “መልክድረግ መልካምን ለማድረግ በምትጥሩበት” ፍላጎታችሁ እናንተ ልክ እንደ ሰማይ አባት ልጆች ሁሉ ናችሁ።

በዚህ ስለተለያዩ ብዙ ነገሮች ምክር ልሰጣችሁ እል እችል ነበር፣ ነገር ግን ስለሁለት ብቻ ለመናገር መርጫለሁ።

የመጀመሪያ ምክሬም የእጅ ስልኮችን በሚመለከት ነው። በቅርብ በአገር አቀፍ ውስጥ በነበረው ጥናት ውስጥ በአሜሪካ ከሚኖሩት ወጣቶች ግማሾቹ እጅ ስልካቸውን በመጠቀም የበዛ ጊዜ እናሳልፋለን እንዳሉ ተገኝቷል። ከመቶ 40 የሚሆኑትም ከእጅ ስልካቸው በሚለዩበት ጊዜ ጭንቀት ተሰምቷቸዋል።6 ይህም ከወንዶች ይልቅ በሴቶች በጣም የተለመደ ነበር። ወጣት እህቶቼ—እናም ጎልማሳዎቹ እህቶቼ—በእጅ ስልኮች አጠቃቀማችሁን እና ጥገኝነታችሁን መወሰን ህይወታችሁን ይባርካል።

ሁለተኛው ምክሬ ከዚህም ይበልጥ አስፈላጊ ነው። ለሌሎች ደግ ሁኑ። ደግነት አብዛኛዎቹ ወጣቶቻችን አሁንም የሚያደርጉት ነው። በአንዳንድ ህብረተሰቦች ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ የወጣት ቡድኖች መንገዱን ለሁላችንም አሳይተዋል። የወጣት ህዝቦቻችን ፍቅር እና እርዳታ ለሚፈልጉ በሚሰጧቸው የደግነት ስራ ተነሳስተናል። በብዙ መንገዶች እናንተም ያን እርዳታ ትሰጣላችሁ እናም ያን ፍቅር እርስ በራስ ታሳያላችሁ። ሁሉም የእናንተን ምሳሌ እንዲከተሉ ምኞታችን ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ፣ ጠላት ሁላችንም ደግነት የጎደለው እንድንሆን እንደሚፈትነን እናውቃልን ይፈተናለን፣ እናም አሁንም በልጆችና ወጣቶች መካከል ብዙ የእንደዚህ አይነት ምሳሌዎች አሉ። የማያቋርጥ ደግነት መጉደል፣ እንደ ጉልበተኝነት፣ በሰው ላይ እንደ መደባበር፣ ወይም ሌሎችን ለመቃቅውም እንደመቀላቀል አይነት በርካታ ስሞች ይታወቃል። እነዚህ ምሳሌዎች በክፍል ጓደኞች ወይም ጓደኞች ላይ ሆን ብለው ስቃይ ያመጣሉ። ወጣት እህቶቼ፣ ለሌሎች ጨካኝ መሆን ጌታን የሚያስደስት አይደለም።

ይሄ ሌላ ምሳሌ ነው። በስደት ወደ ዩታ የመጣ፣ ልዩ በመሆኑ፣ በተጨማሪም አንዳንዴ የሀገሩን ቋንቋ በመናገሩ ስለተሳለቀበት አንድ ወጣት ሰው አውቅ ነበር። ሀብታ ባላቸው ወጣዎች ተበጥብጦ ለ70 ቀናት ወደ እስር ቤት እንዲገባና፣ ከአገር ለማስወጣት ጉዳይ እንዲጀመርበት ድረስ አሳድደውት ነበር። ብዙዎቹ እንደ እናንተ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የሆኑት እነዚህ ወጣት ቡድኖች ይህን እንዲያደርጉ ምን እንዳደረሳቸው አላውቅም፣ ነገር ግን የእነርሱ ክፉነት ውጤትን ለማየት ችያለሁ፣ ያም ከእግዚአብሔር ልጆች አንዱ ለሆነው ወጪና አሳዛኝ አጋጣሚ ነው። የበደለኛነት ድርጊቶች አነስተኛ እርምጃዎች ከፍተኛ ቅጣት ሊኖራቸው ይችላል።

ያን ታሪክ ስሰማ፣ በቅርብ የአለም አቀፍ የወጣቶች ስብሰባ ውስጥ ነቢያችን ፕሬዘደንት ኔልሰን ካሉት ጋር አመዛዘንኩት። እናንተን እና ሌሎች ወጣቶች በእስራኤል መሰብሰብ እንድትረዱ በመጠየቅ እንዲህ አሉ፥ “ልዩ ሁኑ፤ ከአለም ተለዩ። እናንተ የአለም ብርሀን መሆን እንደሚገባችሁ እናንተ እና እኔ እናውቃለን። ስለዚህ፣ ጌታ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙር እንድትመስሉ፣ እንድትናገሩ፣ እንድትሰሩ፣ እና እንድትለብሱ ይፈልጋችኋል።”7

ፕሬዘዳንት ኔልሰን አባል እንድትሆኑ የጋበዟቸው የወጣቶች ሰራዊት ለእርስ በራስ ክፉ አይሆኑም። እነሱ ለሌሎች ለመድረስ እና ለሌሎች ፍቅር እና አሳቢነት ለመያዝ የአዳኝን ትምህርት ይከተሉታል፣ እንዲሁም አንድ ሰው እኛን ሲበድለንም ሌላኛውን ጉጭ እናዞርለን።

እናንተ በተወለዳችሁበት ጊዜ ባደረጉት የአጠቃላይ ጉባኤ ንግግር ውስጥ፣ ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ “በወንጌሉ ለመኖር የሚጥሩ ቆንጆ ወጣት ሴቶችን” አሞገሱ። እናንተን ለመግለፅ በሚሰማኝ አይነት፣ እርሳቸውም እነርሱን እንዲግ ገለጹ፥

“እነርሱ ለእርስ በራስ ደግ ናቸው። የእርስ በእርስ በራስ ጥንካሬን ይፈልጋሉ። ለወላጆቻቸው እና ለመጡበት ቤት ጥሩ ስም ናቸው። ወደ ሴትነት እየቀረቡ ናቸው እናም በህይወታቸው ሁሉ አሁን የሚያነሳሳቸውን ሀሳቦች ይሸከማሉ።”8

እንደ ጌታ አገልጋዮች፣ ለእናንተ ለወጣት ሴቶች፣ አለማችን የእናንተ መልካምነት እና ፍቅር ትፈልጋለች እላችኋለሁ። ለእርስ በራስ ደግ ሁኑ። ኢየሱስ እርስ በራስ እንድንፈቃቀር እና ሌሎችን እኛ ለመያዝ በምንፈልግበት አይነት እንድንንከባከብ አስተምሮናል። ደግ ለመሆን ስንጥር፣ ወደ እርሱ እና ወደ እርሱ አፍቃሪ ተፅዕኖ እንቀርባለን።

ውድ እህቶቼ፣ በግል ወይም በቡድን በማንኛውም ክፋት ወይም ጥፋት የምትካፈሉ ከሆናችሁ፣ ለመቀየር እና ሌሎች እንዲቀየሩ ለማበረታታት አሁን የልብ ውሳኔ አድርጉ። ያም ምክሬ ነው፣ እናም ይህን የምሰጣችሁ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ነው ምክንያቱም የእርሱ መንፈስ መንፈሱ ስለዚህ አስፈላጊ ርዕስ ከእናንተ ጋር እንድነጋገር አነሳስቶኛል። እርሱ እንደሚወደን እርስ በራስ እንድንዋደድ ስላስተማረን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አዳኛችን፣እመሰክራለሁ። ይህን እናደርግ ዘንድ የምጸልየው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. See Sara Berg, “Nation’s Latest Challenge: Too Few Children,” AMA Wire, June 18, 2018, wire.ama-assn.org.

  2. Teachings of Gordon B. Hinckley (1997), 387, 390; see also M. Russell Ballard, “Mothers and Daughters,” Liahona, May 2010, 18 (in Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society [2011], 156).

  3. Russell M. Nelson, “A Plea to My Sisters,” Liahona, Nov. 2015, 96; see also Russell M. Nelson, “Children of the Covenant,” Ensign, May 1995, 33.

  4. ይህ ጥናት “Soul Searching: The Religious and Spiritual Lives of American Teenagers,” Mar. 13, 2005, newsobserver.com የታተመው በኦክስፎርድ ዮኒቨርስቲ ህትምት ነው።

  5. “Dearest Children, God Is Near You,” Hymns, no. 96.

  6. See “In Our Opinion: You Don’t Need to Be Captured by Screen Time,” Deseret News, Aug. 31, 2018, deseretnews.com.

  7. Russell M. Nelson, “Hope of Israel” (worldwide youth devotional, June 3, 2018), 8, HopeofIsrael.lds.org.

  8. Gordon B. Hinckley, “The Need for Greater Kindness,” Liahona, May 2006, 60–61.