2010–2019 (እ.አ.አ)
የሙታን ቤዛነት ራዕይ
ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ)


15:20

የሙታን ቤዛነት ራዕይ

ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ. ሥሚዝ የተቀበሉት ራዕይ እውነት እንደሆነ እመሰክራለሁ። እያንዳንዱ ሰው ይህ እውነት እንደሆነ ለማወቅ እንደሚችል እመሰክራለሁ።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ንግግሬን ያዘጋጀሁት ውድ ባለቤቴ፣ ባርብራ፣ ከመሞቷ ብዙ ጊዜ በፊት ነበር። ቤተሰቤ እና እኔ ለፍቅራችሁ እና በደግነት ለረዳችሁን እናመሰግናለን። በዚህ ጠዋት እናንተን ሳነጋግር ጌታ እንዲባርከኝ እጸልያለሁ።

በጥቅምት 1918 (እ.አ.አ)፣ ከ100 አመታት በፊት፣ ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ ግርማዊ ራዕይን ተቀበሉ። በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከነበራቸ የ65 አመት አገልግሎት በኋላ፣ እናም በህዳር 19 ቀን 1918 (እ.አ.አ) ከመሞታቸው ጥቂት ሳምንታት በፊት፣ በክፍላቸ ተቀምጠው ስለክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እና ሐዋርያው ጳውሎስ አዳኝ ከተሰቀለ በኋላ በመንፈስ አለም ውስጥ ስላገለገለበት ያሰላስሉ ነበር።

እንዲህም ጻፉ፥ “ሳነብም … በጣም ተነካሁ።፡… ስለእነዚህ … ነገሮች ሳሰላስል፣ የመረዳት አይኖቼ ተከፈቱ፣ እና የጌታ መንፈስ አረፈብኝ፣ እና የሙታን ሰራዊትን አየሁ።”1 የዚህ ራዕይ ሙሉ ቃላት በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል 138 ውስጥ ተመዝግበዋል።

ይህንን አስደናቂ መገለጥ ለመቀበል የጆሴፍ ኤፍን የህይወት ሙሉ ዝግጅታቸውን መረዳት እንድንችል እስቲ አንዳንድ ጀርባዎችን ላቅርብ።

ጆሴፍ እና ሀይረም ስሚዝ በፈረስ ላይ ተቀምጠው

የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት በነበሩበት ጊዜ፣ በ1906 (እ.አ.አ) ናቩን ጎበኙ እናም በ5 አመታቸው ስነለበራቸው ትዝታ አሰላሰሉ። እንዲህም አሉ፣ “[አጎቴ ጆሴፍ እና አባቴ ሀይረም] ወደ ካርቴጅ ለመሄድ በፈረስ በሚጓዙበት ጊዜ ቆሜበት የነበረው በዚህ ቦታ ነበር። ከፈረሱ ሳይወርድ አባቴ ከኮርቻው ወደታች ዝቅ ብሎ ከመሬት አነሳኝ። ደህና ሁን በማለት ሳመኝ እናም እንደገና አስቀመጠኝ እናም እየጋለበ ቤደ።”2

ጆሴፍ ኤፍ. እንደገና ያዩአቸው፣ ሰኔ 27, 1844 በካርቴጅ እስር በጭካኔ ከተገደሉ በኋላ ሰማእታት ጎን በጎን በተኙበት እንዲያዩ ዘንድ እናታቸው፣ ሜሪ ፊልዲንግ ስሚዝ ባነሷቸው ጊዜ ነበር።

ከሁለት አመት በኋላ፣ ጆሴፍ ኤፍ. ከቤተሰባቸውና ከታማኝ እናታቸው፣ ሜሪ ፊልዲንግ ስሚዝ፣ ጋር በናቪ የነበረውን ቤታቸውን ትተው ወደ ውዊንተር ኮርተርስ ሄዱ። ምንም እንኳን ስምንት አመታቸ ባይሆኑም፣ ጆሴፍ ኤፍ. አንዱን የበሬ ቀንበሮች ከሞንትሮስ፣ አየዋ ወደ ዊንተር ኮርተርስ እና ከዚያም በኋላ በ10 አመታቸው ወደደረሱበት ወደ ሶልትሌክ ሸለቆ መንዳት ነበረባቸው። እናንተ ወንድ ልጆች እና ወጣት ወንዶች በወጣትነት ጊዜ በጆሴፍ ኤፍ. ላይ የነበረውን ሀላፊነት እና ተስፋ እንደምታደምምጡ እና እንድምትረዱ ተስፋ አለኝ።

ከአራት አመት በኋላ፣ በ1852 (እ.አ.አ)፣ በ13 አመታቸው፣ ጆሴፍን እና ወንድምና እህቶቹን የሙት ልጅ በማድረግ ውድ እናቱ ሞቱ።3

ጆሴፍ ኤፍ. በሀዋዪ ደሴት እንደ ወንጌል እንድሰብኩ በ15 አመታቸው በ1854 (እ.አ.አ) ተጠሩ። ከሶስት አመት በላይ የቆየው ይህም የወንጌል ስብከት አገልግሎት በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በህይወት የማገልገላቸው መጀመሪያ ነበር።

ወደ ዮታ ሲመለሱም፣ ጆሴፍ ኤ. በ1859 (እ.አ.አ) ትዳር ያዙ።4 ለሚቀጥሉት ጥቂት አመታት፣ ህይወታቸው በስራ፣ በቤተሰብ ሀላፊነት፣ እና በሁለት ተጨማሪ የወንጌል ስብከት አገልግሎት ተሞልቶ ነበር። በሐምሌ 1፣ 1866 (እ.አ.አ)፣ በ27 አመታቸው፣ በብሪገም ያንግ እንደ ሐዋርያ ሲሾሙ የጆሴፍ ኤፍ. ህይወት ለዘለአለም ተቀየረ። በሚቀጥለው አመት ጥቅምት በአስራ ሁለት ሐዋሪያት ውስጥ የነበረውን ባዶ ቦታ ሞሉ።5 በ1901 (እ.አ.አ) ራሳቸው ፕሬዘደንት ከመሆናቸው በፊት፣ ለብሪገም ያንግ፣ ጆን ቴይለር፣ ዊልፈርድ ዉድረፍ፣ እና ለሎሬንዞ ስኖው አማካሪ በመሆን አገለገሉ።6

ጆሴፍ ኤፍ. እና ባለቤታቸው ጁሊና የመጀመሪያ ልጃቸውን፣ መርሲ ጆሰፊን፣ ወደ ቤተሰባቸው ተቀበሉ።7 የሞተችው በሁለት ከግማሽ አመቷ ነበር። ከአጭር ጊዜ በኋላም፣ ጆሴፍ ኤፍ. እንዲህ ጻፉ፣ “የእኔ … ውዷ ጆሴፍን ከሞተች አንድ ወር ሆኖታል። አቤቱ! እርሷ እስከ ሴትነት እስክትደርስ ላድናት እችል ዘንድ። ሁልጊዜም ትናፍቀኛለች እናም ብቸኛም ነኝ። … ትትንሾቼን እስከዚህ ማፍቀሬ ትክክል ካልሆነ እግዚአብሔር ደካማነቴን ይማረኝ።8

በእርሳቸው ህይወት፣ ፕሬዘደንት ስሚዝ አባታቸውን፣ እናታቸውን፣ አንድ ወንድማቸውን እና ሁለት እህቶቻቸው፣ ሁለት ባለቤቶች፣ እና አስራ ሶስት ልጆች አትጥተው ነበር። በሀዘን አና የሚወዱትን ማጣት ጠንቅቆ የሚያውቅ ነበር።

ልጃቸው አልበርት ጄሲ ስሞት፣ ጆሴፍ. ኤፍ. ወደጌታ እንዲያድነው እንደለመኑ እና ፣ “ለምን ነው እንደዚህ የሆነው? በማለት ጌታን እንደጠየቁ ለእህይታቸው ማርታ አን ፃፉላት። አቤቱ፣ እግዚአብሔር ለምን እንደሂይ መሆን አለበትን?”9

በዚያ ጊዜ ጸሎት ቢኖራቸውም፣ ጆሴፍ ኤፍ. ስለዚህ ጉዳይ ምንም መልስ አላገኙም።10 ማርታ አንን ስለሞት እና መንፈስ አለም ርዕስ እንዲህ ነገሯቸው፣ “ሰማያት በእራሳችን በላይ እንደሚገኙ ነሀሶች [ይመስላሉ]።” ይህም ቢሆን፣ ስለጌታ ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን ፅኑ እና የማይነቃነቅ እምነት ነበራቸው።

በጌታ ጊዜም፣ ፕሬዘደንት ስሚዝ እንዲመጡላቸው የፈለጓቸው ተጨማሪ መልሶች፣ መፅናኛ፣ እናም መረጃ ወደ እርሳቸው በጥቅምት 1918 (እ.አ.አ) በተቀበሉት አስደናቂ ራዕይ መጡ።

ያም አመት ለእርሳቸው በልዩ አሳዛኝ ነበር። በታላቁ የአለም ጦርነት ላይ የነበረው የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ20 ሚልዮን በላይ ያድግ ነበር። በተጨማሪም፣ ወረርሽኝ በዓለም ዙሪያ ወደ 100 ሚልዮን ሰዎችን እየገደለ ነበር።

ሽማግሌ ሀይረም ማክ ስሚዝ

በዚያ አመትም፣ ፕሬዘደንት ስሚዝ ሶስት የቤተሰብ አባላትን አጥተው ነበር። የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ምልዓተ ጉባኤ አባልሽማግሌ ሀይረም ማክ ስሚዝ፣ የእርሳቸው የመጀመሪያ ልጅ እና አያቴ፣ ትርፍ አንጀታቸው ተቀድዶ በድንገት ሞቱ።

ፕሬዘደንት ስሚዝም እንደጻፉት፥ “መናገር አልችልም—በሀዘን [ደንዝዣለሁ]! ልቤ ተሰብሯል፤ እናም ለህይወት ይንቀጠቀጣል! … አቤቱ! እርሱንም አፈቅራለሁ! ለዘለአለም በተጨማሪም አፈቅረዋለሁ። እንደዚህም ይሆናል እናም እንዲሁም ለሁሉም ወንዶች እና ሴቶች ልጆቼ ነው፣ ነገር ግን እርሱ የመጀመሪያ የተወለደው ልጄ፣ ለመጀመሪያ ደስታ ያመጣልኝ ልጅ እና በሰዎች መካከል መጨረሻ የሌለው፣ ተከባሪ ስም ነው። ከነፍሴ ዝልቅ ለእርሱ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ! ነገር ግን … አቤቱ! እርሱን እፈልገው ነበር! ሁላችንም እንፈልገው ነበር! ለቤተክርስቲያኗ በጣም ጠቃሚ ነበር። … እና አሁን … አቤቱ! ምን ለማድረግ እችላለሁ! … አቤቱ! እግዚአብሔር እርዳታ ስጠኝ!”11

በሚቀጥለው ወር፣ የፕሬዘደንት ስሚዝ የሴት ልጅ ባለቤት፣ አሎንዞ ካይዘር፣ በአሰቃቂ አደጋ ምክንያት ሞተ።12 ፕሬዘደንት ስሚዝ በማስታወሻቸው እንዲህ ጻፉ፣ “ይህ መጥፎ እና ልብ ሰባሪ የሞተበት አደጋ፣ እንደገና በቤተሰቦቼ ላይ በሙሉ ጨለማ አሸፈነ።”13

ከሰባት ወሮች በኋላም፣ በመስከረም 1918 (እ.አ.አ)፣ የፕሬዘደንት ስሚዝ የልጃቸው ሚስት እና የአያቴ፣ ኢዳ ቦውማን ስሚዝ፣ ለአምስተኛዋ ልጅ፣ አጎቴ ሀይረምን፣ ከወለደች በኋላ ሞተች።14

እንደዚህም ነበር፣ በጥቅምት 3፣ 1918 (እ.አ.አ)፣ በአለም ውስጥ ጦርነት እና በሽታ ምክንያት ስለሞቱት ሚልዮኖች እና በራሳቸው ቤተሰቦች ሞት ምክንያት ከባድ ሀዘን ደርሶባቸው፣ ፕሬዘደንት ስሚዝ “የሙታን ቤዛነት ራዕይ” ተብሎ የሚታወቀውን የሰማይ ራዕይ ተቀበሉ።

ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ

በሚቀጥለው ቀን በጥቅምት አጠቃላይ ጉባኤ የመጀመሪያ ስብሰባ መክፈቻ ላይ ስለራዕዩ ጠቀሱ። የፕሬዘደንት ስሚዝ ጤንነት እየወደቀ ነበር፣ ግን ለትንሽ ጊዜ ተናገሩ፥ “በዚህ ጠዋት በአዕምሮዬ ላይ ስላረፉት ብዙ ነገሮች ለመናገር ለመሞከር አልችልም፣ ወይም አልደፍርም፣ እናም የጌታ ፈቃድ ሆኖ፣ በአዕምሮዬ ያሉትን፣ እናም በልቤ የሚገኙትን፣ ነገሮች ለእናንተ ለመንገር ለወደፊት ጊዜ አስተላልፈዋለሁ። [ባለፉት] አምስት ወራት ለብቻዬ አልኖርኩም። በጸሎት፣ በአምልኮ፣ በእምነት እና በልብ ውሳኔ መንፈስ እኖር ነበው፤ እናም ከጌታ መንፈስ ጋር ሁልጊዜም ተነጋግሬአለሁ።”15

በጥቅምት 3 የተቀበሉት ራዕይ ልባቸውን አፅናና እናም ለብዙዎቹ ጧቄዎቻቸው መልሶች ሰጧቸው። እኛ እና የምናፈቅራቸው ስንሞትና ወደመንፈስ አልም ስንሄድ ስለሚጠብቁን ወደፊታችን ይህን ራዕይ በማጥናት እና በየቀኑ የምንኖርበትን መንገድ ትርጉም በማሰላሰል እኛም ለመፅናናት እና ለመማር እንችላለን።

ፕሬዘደንት ስሚዝ ከተመለከቷቸው ብዙ ነገሮች መካከል አዳኝ በመስቀል ከሞተ በኋላ ታማኞችን በመንፈስ አለም የጎበኘበት ነበር። ከራዕዩ እጠቅሳለሁ፥

“እነሆ፣ ከጻድቃን መካከል ሀይሎቹን አደራጀ እና ሀይል እና ስልጣንን የተላበሱ መልእክተኞቹን መደበ፣ እና እንዲሄዱና የወንጌሉን ብርሀን በጭለማ ላሉት፣ እንዲሁም ለሁሉም [ወንዶች እና ሴቶች] ሰዎች መንፈሶች እንዲወስዱ ሀላፊነትን ሰጣቸው፤16 እና በዚህም ወንጌሉ ለሙታን ተሰብኮ ነበር። …

“እነዚህም በእግዚአብሔር እምነትን፣ ለኃጢአት ንስሀ መግባትን፣ ለኃጢአት ስርየት የውክልና ጥምቀትን፣ እጆችን በመጫን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ተምረው ነበር።

“እና እንደሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር ይኖሩ ዘንድ ራሳቸውን ብቁ ለማድረግ የሚያስፈልጋቸውን የወንጌል መሰረታዊ መርሆችን ሁሉ ተምረው ነበር። …

“ሙታን ሰውነታቸው ከመንፈሳቸው ለረዥም ጊዜ መለየቱን እንደ ባርነት ተመልክተውታልና።

“እነዚህንም ጌታ አስተማረ፣ እና ከትንሳኤው በኋላ ወደ አባቱ መንግስት በመግባት፣ በህያውነት እና በዘለአለም ህይወት አክሊል ይጫንላቸው ዘንድም እንዲመጡ ሀይልን ሰጣቸው፣

“እና ከዚህም በኋላ በጌታ ቃል እንደተገባው በአገልግሎታቸው እንዲቀጥሉ፣ እና ለሚወዱትም ተጠብቀው የነበሩትን በረከቶች ሁሉ ተካፋይ እንዲሆኑ።”17

የጆሴፍ እና የሀይረም ስሚዝ ሀውልት

በራዕይም፣ ፕሬዘደንት ስሚዝ አባታቸውን፣ ሀይረምን፣ እና ነቢዩ ጆፌፍ ስሚዝን አዩ። እንደ ትንሽ ልጅ በናቩ እነርሱን ካዩአቸው 74 አመታት ሆኖ ነበር። ውድ አባታቸውን እና አጎታቸውን በመመልከት ምን ደስታ እንደነበራቸው ለማሰብ እንችላለን። መንፈሶች ሁሉ የሟች ሰውነታቸውን አመለካከት እንደሚይዙ እና ቃል ለተገባለት ትንሳኤ በጉጉት እንደሚጠብቁ በማወቃቸው የተነሳሱ እና የተፅናኑ መሆን ይገባቸው ነበር። ራዕዩም የሰማይ አባት ለልጆቹ ያለውን እቅድ እና የክርስቶስ የሚያድን ፍቅር እና የኃጢያት ክፍያው ተመዛዛኝ የሌለው ሀይል ጥልቀትና ስፋት በሙሉ ገልጿል።18

በዚህ በ100ኛ አመታዊ በአል ይህን ራዕይ በሙሉነት እና በሀሳብ እንድታነቡት እጋብዛችኋለሁ። ይህን ስታደርጉ፣ በሙሉ እንድትረዱበት እና የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ለልጆቹ ያለውን የደህንነት እና የደስታ እቅዱን በሙሉ ለመረዳት ጌታ ይባርካችሁ።

ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ. ሥሚዝ የተቀበሉት ራዕይ እውነት እንደሆነ እመሰክራለሁ። እያንዳንዱ ሰው ሊያነበው እና ይህ እውነት እንደሆነ ለማወቅ እንደሚችል እመሰክራለሁ። ይህን እውቀት በዚህ ህይወት የማይቀበሉትም በመንፈስ አለም ሁሉም በሚደርሱበት ጊዜ በሙሉነቱ በእርግጥ ለማወቅ ይችላሉ። በዚያም፣ ሁሉም እግዚአብሔርን እና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ለታለቁ የደህንነት እቅድ እና ሰውነት እና መንፈስ በምንም ላለመለያየት እንደገና ለሚገናኝበት ትንሣኤ ለመነሳት ቃል ኪዳን ያፈቅሯቸዋል እናም ያሞግሷቸዋል።19

እህት ባለርድ

የእኔ ውድ ባርብራ የት እንዳለች እና እንደገና፣ ከቤተሰባችን ጋር፣ ለዘለአለም አብረን እንደምንገኝ በማወቄ ምን ያህል ምስጋና አለኝ። የጌታ ሰላም በአሁን እና በዘለአለም ይደግፈን ዘንድ በትሁት የምጸልይየው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥6፣ 11።

  2. Joseph F. Smith, in Preston Nibley, The Presidents of the Church (1959), 228.

  3. Joseph Fielding Smith, Life of Joseph F. Smith (1938), 13.

  4. ለቫይራ ክላርክን በ1859 (እ.አ.አ)፣ ጁሊና ላምብሶንን በ1866 (እ.አ.አ)፣ ሳራ ሪቻርድን በ1868 (እ.አ.አ)፣ ኤድና ላምብሶንን በ1871 (እ.አ.አ)፣ አሊስ ኪምባልን በ1883 (እ.አ.አ)፣ እና በሜሪ ሽዋርትዝን በ1884 (እ.አ.አ) አገቡ።

  5. ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ እንደ ቀዳሚ አመራር ተጨማሪ አማካሪ ተጠሩ (ብሪገም ያንድ፣ ሒበር ሲ. ኪምባል እና ዳንኤል ዌልስ)። ደግሞም ለሶስት የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንቶች፣ በተጨማሪም እንደ ፕሬዘደንቶች ጆን ቴይለር፣ ዊልፈርድ ዉድረፍ፣ እና ሎሬንዞ ስኖው ቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ አገለገሉ።

  6. ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ በብሪገም ያንግ መንግስት ውስጥ እንደ አማካሪ እና በጆን ቴይለር፣ ዊልፈርድ ዉድረፍ፣ እና ሎሬንዞ ስኖው መንገስት ውስጥ እንደ ቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ አገለገሉ። እርሳቸውም በመጀመሪያ ጊዜ እንደ ፕሬዘደንት ከመጠራታቸው በፊር እንደ ቀዳሚ አመራር አማካሪ ያገለገሉ ናቸው።

  7. የጆሴፍ ኤፍ. የመጀመሪያ ልጅ መርሲ ጆሴፊን የተወለደችው ሐምሌ 14፣ 1867 (እ.አ.አ) ነበር፣ እናም በሰኔ 6፣ 1870 (እ.አ.አ) ሞተች)።

  8. Joseph F. Smith, journal, July 7, 1870, Church History Library, The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints, Salt Lake City, Utah.

  9. Joseph F. Smith to Martha Ann Smith Harris, Aug. 26, 1883, Church History Library; see Richard Neitzel Holzapfel and David M. Whitchurch, My Dear Sister: The Letters between Joseph F. Smith and His Sister Martha Ann (2018), 290–91.

  10. በብዚ ሁኔታዎች፣ ጌታ ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝን በግል ህይወታቸው እና እነ ሐዋርያና እንደ ቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት አገልግሎታቸው በሚያነሳሱ ህልሞች፣ መግለጫዎች፣ እና ራዕዮች መርቷቸዋል። ከጌታ የመጡ እነዚህ ውድ ስጦታዎችም በማስታወሻቸው፣ በስብከታቸው፣ በትዝታቸው፣ እና በቤተክርስቲያኗ ይፉ መዝገቦች ውስጥ ተመዝግበዋል።

  11. Joseph F. Smith, journal, Jan. 23, 1918, Church History Library; spelling and capitalization modernized; see Joseph Fielding Smith, Life of Joseph F. Smith, 473–74.

  12. See “A. [P.] Kesler Is Killed in Fall from a Building,” Ogden Standard, Feb. 5, 1918, 5.

  13. Joseph F. Smith, journal, Feb. 4, 1918, Church History Library.

  14. See “Ida Bowman Smith,” Salt Lake Herald-Republican, Sept. 26, 1918, 4.

  15. Joseph F. Smith, in Conference Report,Oct. 1918, 2.

  16. ስለ“የእኛ ግርማዊ እናት ሔዋን” እና “እውነተኛ እና ህያው እግዚአብሔርን [ስለሚያመልኩ]… ታማኝ ሴት ልጆች” ጥቅሰቶች (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥39) ይመልከቱ።

  17. ትምህርት እና ቅል ኪዳኖች 138፥30; 33-34፣ 50-52።

  18. የራዕዩ የመጀመሪያ ፅሁፍ የተገኘው በDeseret News የህዳር 30፣ 1918 (እ.አ.አ) ህትመት ላይ ፕሬዘደንት ስሚዝ በህዳር 19 ከሞቱ 11 ቀናት በኋላ ነበር። ይህም በImprovement Era ውስጥ በታህሳስ እናም በጥር 1919 (እ.አ.አ) በRelief Society Magazine፣Utah Genealogical and Historical Magazine፣Young Women’s Journal፣ እናም በMillennial Star ውስጥ ታትመው ነበር።

  19. ምንም እንኳን የጥፋት ልጆች ከሞት ቢነሱም፣ ለሰማይ አባት እና ለኢየሱስ ክርስቶስ የግርማ መንግስት እንደሚቀበሉት ፍቅር እና ማሞገስን አይሰጡም። አልማ 11፥41ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥32–35