አብ
እያንዳንዳችን እንደ አብ ለመሆን አቅም አለን። ይህንን ለማድረግ፣ በወልድ ስም አብን ማምለክ አለብን።
ባለቤቴ ሜሊንዳ በህይወትዋ ሙሉ፣ በሙሉ ልብ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመሆን ጥራልች። አዎን፣ ከውጣትነትዋ ጀምሮ፣ የሰማይ አባትን ባህሪይ ባለመረዳትዋ ምክንያት ፍቅሩን እና በረከቱን ለመቀበል ብቁ እንዳሆነች ተሰምቷታለ። እንደአጋጣሚ ሆኖ፣ ሜሊንዳ የተሰማት ሀዘን ሳያግታት ተእዛዛትን መከተልዋን ቀጠለች። ከጥቂት አመታት በፊት፣ እግዚያብሄር ለልጆቹ ያለውን ፍቅር እና የእርሱን ስራ ለመስራት ፍጹም ላልሆኑት ጥረቶቻችን ያለውን ምስጋና፣ በተሻለ ሁኔታ የእግዚያብሄርን ባህሪይ እንድትረዳ ባደረጓት ከበድ ባሉ ነገሮች ውስጥ አለፈች።
ይህም እንዴት ተጽእኖ እንዳሳደረባት እንደዚህ ብላ ታብራራለች፣ አሁን የእግዚያብሄር እቅድ እንደሚሰራ፣ ለእኛ ስኬት ዋጋ እያወጣ እንደሆነ፣ እንዲሁም ወደ እርሱ ፊት እንድንመለስ የሚያስፈልገንን ትምህርቶቸ እና የህይወት ተሞክሮዎች እንደሚያዝጋጅ የእርግጠኝነት ስሜት ይሰማኛል። እራሴን እና ሌሎችን እግዚያብሄር በሚያየን መንገድ ከበፊቱ በተሻለ መንገድ ማየት ችያለሁ። በብዙ ፍቅር እና ባነሰ ፍራቻ ንስሃ መግባት፣ ማስተማር፣ ማገልገል ችያለሁ። መጨናንቅ እና አለመረጋጋት ሳይሆን ሰላምና በራስ መተማመን ይሰማኛል። ሰዎች እኔ ላይ እየፈረዱ ሳይሆን እየደገፉኝ እንደሆነ ነው ሚሰማኝ። እምነቴ ከቀድሞው በተሻለ እርግጥ ነው። የአባቴን ፍቅር በተደጋጋሚ እና በጠለቀ ሁኔታ ይሰማኛል።1
“[የሰማይ አባትን] ባሀሪይ፣ ፍጹምነት፣ እና ጸባያት ትክክለኛ ግንዛቤ መያዝ” የዘላለም ህይወት ክብርን ለማስገኘት በቂ ለሆነው እምነትን ወደ ማዳበር ብዙ ጥቅም አለው።2 የሰማይ አባት ባህሪን በትክክለኛ መንገድ መረዳት እራሳችንን እና ሌሎችን የምናይበትን መንገድ ይቀይራል እንዲሁም እግዚያብሄር ለልጆቹ ያለውን ድንቅ ፍቅር እና እንደርሱ እንድንሆን እኛን ለመርዳት ያልውን ታላቅ መሻት እንድንረዳ ይረዳናል። የእርሱን ባህሪይ በትክክለኛ መንገድ አለማየት ወደ እርሱ ፊት ተመልሰን የመሄድ አቅም እንክዋን እንደሌለን አድርጎ እንዲሰማን ያደርገናል።
የዛሬ አላማዬ ሁላችንንም ስለ ሁላቸንንም ስለፈቀደልን አባት ቁልፍ ትምህርት ነጥቦችን ማስትማር ነው፣ ነገር ግን በተለይም እግዚያብሄር እንደሚወዳአቸው ለሚጠራጠሩ ሰዎች፣ ትክክለኛ ባሀሪውን በተሻለ መንገድ እንዲረዱ እናም ታላቅ እምነት በእርሱ፣ በልጁ፣ እናም ለእኛ ባለው እቅድ ላይ ታላቅን እምነእ እንዲያሳድጉ ነው።
የቅድመ ምድር ህይወት
በቅድመ ህይወት አለም ውስጥ፣ ከሰማይ ወላጆጃችን በመንፈስ ተወለድን፣ እናም እንደ ቤተሰብ ከእነርሱ ጋር አብረን ኖርን።3 ያውቁናል፣ አስተምረውናል፣ እናም ወደውናልም።4 ልክ እንደ ሰማይ አባታችን ለመሆን በጣም ፈልገን ነበር። ሆኖም፣ ይህን ለማድረግ፣ የሚቀጥሉት ሊኖሩን እንደሚገባ ተገነዘብን፥
-
የከበረ፣ ህያው የሆነ፣ አካላዊ ሰውነቶችን።5
-
በመጋባት እና በክህነት ስልጣን በማታተም ቤተሰቦችን በመፍጠር፤6 እናም
-
እውቀተን፣ ሀይልን፣ እናም መለኮታዊ ባህሪያትን ሙሉ በማግኘት።7
ስለሆነም፣ አብ የፈጠረው እቅድ በተወሰኑ ሁኔታዎች ላይ ፍቃድ ይሰጠናል8 ህያው እና በትንሳኤ ሰአት የሚከብሩ ሰውነቶችን ለመቀበል፣ በሟች ህይወት ውስጥ ማግባትን እና ቤተሰብ መመስረትን ወይም፣ ከሟቸነት ህይወት በኋላ እድሉን ላላገኙ ታማኝ ለሆኑት እንዲያገቡ፣9 ወደ ፍጹምነት ማደግ፣ እናም በስተመጨረሻም ወደ ሰማይ ወላጆቻችን መመለስ እና ከእነሱ ጋር እና ከቤተሰቦቻችን ጋር በመክበር ሁኔታ ውስጥ እናም በዘላለም ደስታ መኖር።10
ቅዱሳን መጽሀፍ ይህን የምዳን እቅድ ብለው ይጠሩታል።11 ለዚህም እቅድ በጣም አመስጋኞች ነበርን፣ እናም እቅዱ ለኛ ሲቀርብልን በደስታ ጮህን።12 እያንዳንዳችን፣ መለኮታዊ ባህሪያቶችን እንድናዳብር የሚረዱንን ልምዶች እና የሟችንት ፈተናዎችን ጨምሮ የእቅዱን ቅድመ ሁኔታ ተቀብለናል።13
ሟች ህይወት
በሟችነት ውስጥ፣ የሰማይ አባት በእቅዱ ውስጥ እንድናድግ የሚያስፈልጉንን ሁኔታዎች ያቀርብልናል። አባት ኢየሱስ ክርስቶስን በስጋ ወለደ፣ 14 እናም የሟችነት ተልእኮውን እንዲያሟላ መለኮታዊ እርዳታን አቀረበለት። በተመሳሳይ ሁኔታ የሰማይ አባት እያንዳንዳችንን ትዛዛቱን ለመጠበቅ እንድንጥር ይረዳናል።15 አባት ምርጫን ሰቶናል።16 ሀይወቶቻችን በእርሱ እጆች ውስጥ ናቸው፣ እናም ቀኖቻችን የታውቁ ናችው፣”አንሰውም አይቆጠሩም።”17 እርሱን ለሚወዱ ሁሉ ነገር ለመልካም እንደሚስሩ እርሱ አረጋግጧል።18
የእለት እንጀራችንን የሚስጠን የሰማይ አባት ነው፣19 ይህም የምንበላውን ምግብ እና የሱን ትእዛዛት ለመጠበቅ የሚያስፈልገንን ትንካሬንም ያካተተ ነው።20 አባት መልካምን ስጦታ ይሰጣል።21 ጸሎታችንን ይሰማል እናም ይምልስልናል።22 የሰማይ አባት ስንፈቅድለት ከክፉ ያውጣናል።23 ስንሰቃይ ለእኛ ያለቅሳል።24 በስተመጨረሻም፣ በረከቶቻቸን ሁሉ ከአብ ነው የሚመጡት።25
እኛ መልካም ፌን እንድናፈራ፣ የሰማይ አባት በጥንካሬዎቻችን፣ በድክመቶቻችን፣ እናም በምርጫዎቻችን ላይ መሰረት በማድረገ ይመራናል እናም የሚያስፈልገውን ልምድ ይሰጠናል።26 አባት ስለሚወደን ባስፈላጊው ጊዜ ይቆጣናል።27 እሱ ‘’መካሪ’’ ነው፣28 ከጠየቅነው የሚያማክረንም።29
መንፈስ ቅዱስን እና ጥቅሙን ወደ ህይወታችን የላከልን የሰማይ አባት።30 በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ አማካኝነት፣ ክብር ወይም የእውቅት አቅም፣ ብርሃን፣ እናም የእግዚያብሄር ሀይል በእኛ ላይ ሊኖሩ ይቻላቸዋል።31 አይኖቻችን ሁሉ ወደ እግዚአብሄር ክብር እስኪያተኩሩ ድረስ በብርሃን እና በእውንት ለማደግ ስንጥር፣ የሰማይ አባትበዚህ ህይወት ወይም በሚቀጥለው ህይወት ለዘላለም ሊያትመን እና ፊቱን ለእኛ ሊገልጽ የገባውን የመንፈስ ቅዱስ ቃል ይልክልናል።32
ከምድር ህይወት በኋላ
ከምድር ህይወት በኋላ ባለው የመንፈስ አለም፣ የሰማይ አባት የመንፈስ ቅዱስን ከለላ ማድረጉን እና ወንጌል ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች የወንጌል አገልጋዮችን መላኩን ይቀጥላል። ጸሎኦችን ይመልሳል እናም በውክልና መዳንን መቀበል የሚሹትን ይረዳል።33
አባት ኢየሱስ ክርስቶስን ከፍ አድርጎን ትንሳኤን እንዲያመጣ ስልጣንን ሰጥቶታል፣34 ይህም ሟች ያልሆኑ አካላትን የመቀበል መንገድ ነው። የአዳኝ ማዳን እና ትንሳኤ በኢየሱስ ክርስቶስ በምንፈረድበት ወደ እግዚያብሄር ፊት ይመልሰናል።35
በጥቅሙ፣ እናም ምህረቱ፣ እናም በቅዱሱ መሲህ ማይ ሚታመኑ፣36 ልክ እንደ አባት የከበረ አካላትን ይቀበላሉ37 እናም በጭራሽ በማያልቀው የደስታ ሁኔታ ውስጥ ከእርሱ ጋር አብረው ይኖራሉ።38 እዛም፣ አባት እምባዎችን ሁሉ ያብሳል39 እናም እንደ እርሱ የመሆን ጉዟችን ላይ መርዳቱን ይቀጥላል።
እንደምትመለከቱት፣ የሰማይ አባት ሁሌም ለእኛ ይገኝልናል።40
የአብ ባህሪይ
እንደ አብ ለመሆን የእርሱን ባህሪ ጸባያት ማሳደግ አለብን። የሰማይ አባት ፍጹምነት እና ባህሪያት የሚከተሉትን ያካትታሉ፥
-
አባት መጨረሻ የሌለው እና ዘላለማዊ ነው።41
-
እርሱ ፍጹማዊ ፍትህ ያልው፣ መሃሪ፣ ደግ፣ ታጋሸ ነው፣ እናም ለእኛ ምርጡን ብቻ ነው ሚፈልግልን።42
-
የሰማይ አባት ፍቅር ነው።43
-
ቃል ኪዳኖቹን ይጠብቃል።44
-
አይለዋውጥም።45
-
ሊዋሽ አይችልም።46
-
አባት አያዳላም።47
-
ሁሉ ነገሮችን ያውቃል፣ ያለፉትን፣ አሁን ያለውን እናም የወደፊቱንም፣ ከመጀመሪያው ጅምሮ።48
ወንድምች እና እህቶች፣ እርሱን መተማምን እና በእርሱ ላይ መሞከዝ እንችላለን። ምክንያቱም፣ ዘላልማዊ የሆነ ምልከታ አለው፣ የሰማይ አባይ እኛ ማየት የማንችላቸውን ነገሮች ማየት ይችላል። ደስታው፣ ስራው፣ እናም ክብሩ ለእኛ ሟች ያለመሆንን እና ዘላልማዊ ክብርን ማምጣት ነው።53 የሚያደርገው ነገር ሁሉ ለእኛ ጥቅም ሲል ነው። እኛ ለራሳችን ከምንፈልገው በላይ የእኛን ዘላለማዊ ደስታ ለእኛ ይፈልጋል።54 እናም ‘’ለእና እና ለምንወዳቸው ጥቅም ሲባል ካስፈላጊው በላይ አስቸጋሪ ጊዜያትን እንድናሳልፍ አይጠብቅብንም”55 በውጤቱም፣ እኛ ላይ ባለመፍረድ እና ባለመውቀስ፣ እኛ እንድናድግ እኛን መርዳት ላይ ያተኩራል ።56
እንደ አባታችን ወደ መሆን
እንደ እግዚአብሔር የመንፈስ ወንድ እና ሴት ልጆች፣ እያንዳንዳችን እንደ አባት የመሆን አቅም አለን። ይህንንም ለማድረግ፣ በወልድ ስም አባትን ማምለክ አለብን።57 ይህንንም የምናደርገው ልክ አዳኝ እንደነበረው ለአባት ፈቃድ ታዛዥ ለመሆን በመጣር፣58 እናም ንሰሃ መግባታችንን በመቀጠል ነው።59 እነኚህን ነገሮች ስናደርግ፣ ‘’የአባትን ሙሉነት እስክንቀበል ድረስ፣ ጸጋን በጸጋ ላይ’’ እንቀበላለን፣60 እንዲሁም በባህሪያት፣ በፍጹምነት፣ እና በጸባይ እንጎናጸፋለን።61
እንደ ሟች ማን እንደሆንን እና የሰማይ አባት ያለበት ደረጃ መካከል ያለው ልዩነት በማየት፣ እንዳንዶች እንደ አባት መሆን የማይቻል አርገው ቢሰማቸው የሚያስገርም አይደለም። ይህም ቢሆን፣ ቅዱሳን መጽሀፍት ግልጽ ናቸው። በእምንት ወደ ክርስቶስ የሙጥኝ ብንል፣ ንሰሀ ብነገባ፣ እናም በታዛዥነት የእግዚያብሄርን ጸጋ ብንሻ፣ በስተመጨረሻም እንደ አባት እንሆናለን። ታዛዥ ለመሆን የሚጥሩ ሰዎች “በጸጋ ላይ ጸጋ እንደሚቀበሉ” እና በስተመጨረሻም “የሱን ሙላት እንደሚቀበሉ” ባለው እውነታ ታላቅ የሆነ ምቾት ይሰማኛል።62 በሌላ አባባል፣ በራሳችን እንደ አባት መሆን አንችልም።63 ይልቁኑ፣ በጸጋ ስጦታዎች አማካኝነት ይመጣል፣ አንዳንዱ ትልቅ ነገር ግን አብዛኛው ትንሽ፣ ያም ሙላት እስኪኖረን ድረስ አንዱ አንዱ ላይ ይጨመራል። ነገር ግን፣ ወንድሞች እና እህቶች፣ ያም ይመጣል!
የሰማይ አባት እናንተን እንዴት ዘላለማዊ ክብር እንደሚያጎናጽፍችሁ እንደሚያውቅ እንድታምኑ እጋብዛችኋለሁ፣ የእለት ተእለት የሱን የድጋፍ እርዳታ እሹ፣ እናም የእግዚያብሄር ፍቅር ባልተሰማችሁ ጊዜ እንክዋን በክርስቶስ እምነት ወደፊት ግፉ።
እንደ አባት ስለመሆን ብዙ ያልተረዳናቸው ነገሮች አሉ።64 ነገር ግን እንደሰማይ አባት ለመሆን መጣር መሰዋትነትን ሁሉ የሚገባው እንደሆነ በእርግጠኝነት እመሰክራለሁ።65 በዚህ የሟች ህይወት ውስጥ የምንከፍለው መስእዋት ምንም ትልቅ ቢሆን፣ በቀላሉ መለኪያ ከሌለው ሃሴት፣ ደስታ፣ እና በእግዚያብሄር ፊት ስንቆም ከሚሰማን ፍቅር ጋር አይወዳደርም።66 እንድትከፍሉ የተጠየቃችሁትን መስዋትነት ይገባዋል ወይ ብላችሁ ለማመን የከብዳችሁ ከሆነ፣ አዳኝ እንዲህ በማለት ይጠራችኋል፣ “አባት ለናንት ያዘጋጀውን ታላቅ በረከቶች ገና አልተረዳችሁም፤ ሁሉን ነገር አሁን መሸከም አትችሉም፤ ቢሆንም፣ ደስተኞች ሁኑ፣ ምክንያቱም እኔ በመንገዱ መራችኋለሁ።”67
የሰማይ አባታችሁ እናንተን እንደሚወዳችሁ እና ከእርሱ ጋር እናንተ አብራችሁ እንድትኖሩ እንደሚፈልግ መሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።