‘‘ኑ ተከተሉኝ’’
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደቤታችን የሚመልሰንን የቃልኪዳን መንገድ ተከትለን ከሰማያዊ ወላጆቻችንና ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እንድንሆን ይጋብዘናል፡፡
የተወደዳችሁ ወንድምና እህቶቼ፣ በዚህ ሰንበት ምሽት ከእናንተ ጋር በመሆናችን ሚስቴ ዌንዲ እና እኔ ደስ ብሎናል፡፡ ካለፈው አጠቃላይ ጉባኤ በኋላ ብዙ ነገሮች ተከስተዋል፡፡ አዲስ ቤተ-መቅደሶች በኮንሰቭሰን ቺሊ፣ በባራንክዊላ ኮሎምብያ እና በሮም ጣልያን ተመርቀዋል፡፡ በነዚህ የተቀደሱ ክስተቶች ላይ የመንፈስ በብዛት መፍሰስ አጋጥሞናል፡፡
መጽሃፈ ሞርሞንን በቅርቡ ላነበቡና ደስታንና የተደበቀ ሃብትን ላገኙ ብዙ ሴቶች (እና ወንዶች) እንኳን ደስ ያላችሁ እላለሁ፡፡ ስለተፈጠሩ ተአምራት በደረሱኝ ሪፖርቶች ተነሳስቻለሁ፡፡
አሁን ላይ እንደ ዲያቆን በብቁነት ቅዱስ ቁርባንን በየእሁዱ በሚያሳልፉ የ11 አመት ወጣት ወንዶች እደነቃለሁ፡፡፡፡ የወጣት ሴቶች ፕሮግራምን በጉጉት ከሚማሩና ከሚያገለግሉ የ11 አመት ሴቶች ጋር አብረው ወደ ቤተመቅደስ ይሄዳሉ፡፡ ወጣት ወንዶችና ወጣት ሴቶች በግልጽነትና በመተማመን የወንጌልን እውነት እየሰበኩ ነው፡፡
ቤትን ያማከለ ፤ በቤተክርስትያን የተደገፈ ስርዐተ ትምህርትን ለመከተል ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመስራት ወንጌልን በቤት ውስጥ ለማስተማር እየረዱ ባሉ ህጻናትና ወጣቶች እደሰታለሁ፡፡
በአንድ ቅዳሜ ማለዳ ላይ የቤተክርስትያንን መጽሃፍ ይዞ “መንፈሴን መመገብ አለብኝ” ብሎ የጮኸውን ይህን የአራት አመቱን የብሌክ ፎቶ ተቀበልን፡፡፡፡
ብሌክ ፤ ባንተና ፣ የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እውነቶች በመጋበዝ መንፈሳቸውን ለመመገብ በመረጡ ሰዎች ጥልቅ ደስታ ይሰማናል፡፡ በቤተ-መቅደስ አምልኮና አገልግሎት ብዙዎች የእግዚአብሄርን ሃይል በህይወታቸው እየተቀበሉ መሆኑን በማወቃችንም እንደሰታለን፡፡
አብዛኛዎቻችሁ እንደምታውቁት ከሶስት ወር በፊት ልጃችን ዌንዲ ከዚህ አለም በሞት ስትለይ ቤተሰባችን አሳዛኝ የመለየት ሃዘን ገጠመው፡፡ ከካንሰር ጋር በነበራት የመጨረሻ ቀናት ትግል ውስጥ የመሰናበቻ የአባትና ልጅ ንግግር የማድረግ እድል ተባርኬ ነበር፡፡
እጆቿን ያዝኩ እናም ምን ያህል እንደምወዳትና አባቷ በመሆኔ እንዴት አመስጋኝ እንደሆንኩ ነገርኳት፡፡ “ቤተመቅደስ ውስጥ ነው ያገባሽው እናም ቃልኪዳኖችሽን በታማኝነት አክብረሻል፡፡ አንቺና ባልሽ ሰባት ልጆችን ወደ ቤታችሁ አምጥታችኋል፡፡ እናም የተሰጡ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ-መዛሙርት፣ ጠንካራ የቤተ-ክርስትያን አባላትና ፣ የበኩላቸውን ድርሻ የሚወጡ ዜጎች አድርጋችሁ አሳድጋችኋል፡፡ እነርሱም ልክ እንደዛው የሆኑ የትዳር አጋሮችን መርጠዋል፡፡ አባትሽ በጣም በጣም ይኮራብሻል። ብዙ ደስታን አምጥታችሁልኛል!”
“አባዬ አመሰግናለሁ” ብላ በዝግታ መለሰች፡፡
ልብ የሚነካ እና በእንባ የተሞላ ጊዜ ነበር፡፡ በ67 አመት ቆይታዋ አብረን ሰርተናል፣ አብረን ዘምረናል፣ አብረን በረዶ ላይ ተንሸራተናል፡፡ ነገር ግን በዚያ ምሽት እንደ ቃልኪዳኖች፣ ስርዐቶች፣ መታዘዝ፣ እምነት፣ ቤተሰብ፣ ታማኝነት፣ ፍቅር እና ዘላለማዊ ህይወት፡ የመሳሰሉ ከሁሉ በላይ አስፈላጊ ስለሆኑ ነገሮች አወራን ፡፡
ልጃችንን እጅግ አድርገን እንናፍቃታለን፡፡ ነገር ግን በተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምክንያት ስለሷ አንጨነቅም፡፡ ከጌታ ጋር ያለንን ቃልኪዳን እስካከበርን ድረስ ዳግመኛ ከሷ ጋር በመገናኘት ሃሳብ እንኖራለን፡፡ እስከዚያ ድረስ እኛ ጌታን እዚህ እያገለገልን ነው ፤ እሷ ደግሞ እዛ እያገለግገለችው ነው—ገነት ውስጥ 1
በርግጥ በዚህ አመት መጀመርያ ሚስቴ እና እኔ ፓራዳይዝን ጎብኝተን ነበር ፤ ካሊፎርኒያ ያለውን ፓራዳይዝ፡፡ ይህ ሲሆን ፣ የታቀደው ጉዟችን የመጣው ከልጃችን ህልፈት በኋላ ከአርባ በሚያንሱ ሰአታት ውስጥ ነበር። እኛ፣ ከሽማግሌ ኬቭን ደብሊው ፒርሰንን እና ሚስቱ ጁንን በቺኮ ካሊፎርኒያ ካስማ ከሚገኙ ቅዱሳን ድጋፍ አግኝተናል፡፡ እዛው ሳለን ስለ ታላቅ እምነታቸው፣ አገልግሎታቸው እና በካሊፎርኒያ ታሪክ አሰቃቂ በነበረው የሰደድ እሳት በደረሰባቸው እጦት ውስጥ እንኳን ሆነው ተዐምራት ስለመፈጠራቸው ተምረናል፡፡
እዚያው ሳለን በአደጋው ሰአት ቀድመው በጀግንነት ምላሽ ከሰጡ መሃል ጆን ከሚባል ወጣት ፖሊስ ጋር በሰፊው ተነጋገርን፡፡ በህዳር 8 ፣ 2018 (እ.ኤ.አ) በፓራዳይዝ ላይ የወረደው ድቅድቅ ጨለማ ፣ ነበልባልና ፍም በከተማው መሃል በፍጥነት ሃብትና ንብረትን እንደ ጉማሬ አለንጋ የአመድ ቁልልና የተራቆተ የሸክላ ጭስ ማውጫ አስቀርቶ እንዳወደመ አስታወሰ።6
ለ15 ሰአታት ጆን በሚያስፈራ የሚተኮስ ፍም በተሞላ ፣ ዘልቆ ለማለፍ በሚያስቸግር ጨለማ ውስጥ ሰዎችን እና ቤተሰቦችን አንድ በአንድ በደህና እንዲያመልጡ ሊረዳቸው ነዳ፡፡—የራሱን ህይወት አዳጋ ላይ በመጣል። ሆኖም በዚህ አሰቃቂ መከራ ውስጥ ጆንን ሲያስጨንቀው የነበረው “ቤተሰቦቼ የት ናቸው?” የሚለው ጥያቄ ነበር፡፡ በመጨረሻ ከረጅምና አስፈሪ የስቃይ ሰአታት በኋላ ቤተሰቦቹ በሰላም ከቦታው እንደወጡ ሰማ፡፡
የጆን ለቤተሰቦቹ የመጨነቅ ታሪክ ከናንተ መሃል የህይወታቸው መጨረሻ ሲቃረብ “ቤተቦቼ የታሉ?”ብለው ሊጠይቁ ከሚችሉ ጋር ዛሬ እንድነጋገርቀስቅሶኛል፡፡ ስጋዊ የሙከራ ጊዜያችሁን ጨርሳችሁ ወደ መንፈስ አለም በምትገቡበት በዚያን ቀን ”ቤተሰቤየት አለ?” ከሚል ልብ የሚሰብር ጥያቄ ጋር ፊት ለፊት ትጋፈጣላችሁ፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዘላለማዊ ቤታችን የምንመለስበትን መንገድ ያስተምራል፡፡ የሰማይ አባታችን ለኛ ያለውን ዘላለማዊ የእድገት እቅድ ከማንኛችንም በላይ ይረዳል፡፡ ሲጀመር የዚህ እቅድ ሁሉ መሰረት እሱ ነው፡፡ እሱ ቤዛችን ፣ ፈዋሻችንና አዳኛችን ነው፡፡
አዳም እና ሄዋን ከገነት ከተባረሩበት ጊዜ አንስቶ ፤ ክርስቶስ ኢየሱስ ሃያል የሆነውን ክንዱን እሱን ሊከተሉ የመረጡትን ሊረዳቸው ሰቷል፡፡ ምንም አይነት ሃጥያት ከሁሉም አይነት ሰዎች ቢፈጸሙም አሁንም እጆቹን ዘርግቶ እንዳለ ቅዱሳን መጻህፍት በተደጋጋሚ ዘግበዋል፡፡ 2
በያንዳንዳችን ውስጥ ያለው መንፈስ በተፈጥሮው የቤተሰብ ፍቅር ዘላለማዊ እንዲሆን ይጓጓል፡፡ የፍቅር ሙዚቃዎች ለዘላለም አብሮ ለመሆን የሚያስፈልገው ፍቅር ብቻ ነው በማለት የተሳሳተን ተስፋ ይሰጣሉ፡፡ አንዳንዶች የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ከሞት በኋላ ሁሉም ሰው ከሚወደው ሰው ጋር አብሮ እንደሚሆን ቃል ይገባል ብለው በተሳሳተ መንገድ ያምናሉ፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ አዳኙ እራሱ የእርሱ ትንሳኤ እዚ ምድር ላይ የነበረ ሁሉ በርግጥም ትንሳኤን እንደሚያገኝ እና ለዘላለም እንደሚኖር 3 ነገር ግን የከፍታን የተለየ ጥቅምን ለማግኘት ብዙ እንደሚጠበቅ በሰፊው ግልጽ አድርጎታል፡፡ መዳን የግል ጉዳይ ሲሆን ፤ ከፍታ ግን የቤተሰብ ጉዳይ ነው፡፡
በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለነብዩ ስለተነገሩ ስለነዚ ቃላት አስቡ፡ . “በቃል-ኪዳኑ መንፈስ ቅዱስ ያልተፈጸሙ እናም ያልገቡና ያልታተሙ ሁሉም ቃልኪዳኖች ፣ውሎች፣ ቦንዶች፣ ግዴታዎች፣ ቃለ-መሃላዎች፣ ቃሎች፣ ስእለቶች፣ ግኑኝነቶች፣ ትብብሮች ፣ ወይም የሚጠበቁ ነገሮች--- በዚህ መጨረሻ ላይ ያልተፈጸሙ ውሎች ሰዎች ሲሞቱ ሲለሚያበቁ ፤… ከሞት ትንሳኤ ውስጥ እና በኋላ ፍቱንነት ፣ መልካምነት ወይም ሀይል አይኖራቸውም ፡፡” 4
ስለዚህ ቤተሰብ ለዘላለም ከፍ እንዲል ምን ያስፈልጋል? ለዚያ ልዩ ጥቅም ብቁ ምንሆነው ከእግዚአብሔር ጋር ቃልኪዳኖችን በመግባት፣ እነዚህን ቃልኪዳኖች በመጠበቅ እና አስፈላጊ ስርአቶችን በመቀበል ነው፡፡
ከመጀመርያው ጀምሮ ይህ እውነት ነበር፡፡ አዳምና ሄዋን፣ ኖህና ሚስቱ፣ አብረሃምና ሳራ፣ ሌሂና ሳሪያ እና ሌሎች አለም ከተፈጠረ ጊዜ ጀምረው የነበሩ የተሰጡ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቶች ሁሉ ተመሳሳይ ቃልኪዳናትን ከእግዚአብሔር ጋር መስርተዋል፡፡ ዛሬ እንደተመለሰው የጌታ ቤተክርስትያን አባልነት በጥምቀትና በቤተ-መቅደስ የምንቀበላችውን ተመሳሳይ ስርዐቶች እነሱም ተቀብለዋል፡፡
አዳኙ ወደ ጥምቀት ውሃ እንዲከተሉት ፣ ጊዜው ሲደርስ ተጨማሪ ቃልኪዳን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገቡና ለነዝያ ተጨማሪ ስርዐቶች ታማኝ እንዲሆኑ ሁሉንም ይጋባዛል ፡፡ ከቤተሰቦቻችን እና ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ከፍ ለማለት የምንፈልግ ከሆነ እነዚህ ሁሉ ያስፈልጋሉ፡፡
የልቤ ሃዘን ብዙ የምወዳቸው፣ የማደንቃቸው እና የማከብራቸው ሰዎች የሱን ጥሪ ውድቅ ማድረጋቸው ነው፡፡ “ኑ ተከተሉኝ “ የሚለዉን የኢየሱስ ክርስቶስን ልመና ችላ ይላሉ፡፡5
እግዚአብሔር ለምን እንደሚያነባ እረዳለሁ፡፡6 ለእንደዚህ አይነት ጓደኞችና ዘመዶች እኔም አነባለሁ፡፡ እነሱ ለቤተሰባቸውና ለዜግነት ግዴታቸው የተሰጡ አስደናቂ ወንዶችና ሴቶች ናቸው፡፡ በልግስና ጊዜያቸውን፣ ሃይላቸውን እና ንብረታቸውን ይሰጣሉ፡፡ በጥረታቸው ምክንያንት አለም የተሻለች ቦታ ናት፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ቃልኪዳን ላለ መግባት መርጠዋል፡፡ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ከፍ የሚያደርጋቸውን እና ለዘላለም አብሮ የሚያስራቸውን ስርዐት አልተቀበሉም፡፡7
እነሱን መጎብኘት ብችልና የሚያስችለውን የጌታን ህጎች ከቁምነገር እንዲቆጥሩ ብጋብዛቸው አንዴት ደስ ይለኝ ነበር፡፡ አዳኙ ምን ያህል እንደሚወዳቸው፣ እኔም እንደምወዳቸው እና ምን ያህል ቃልኪዳን ጠባቂ ሴቶችና ወንዶች “የደስታ ሙላት”8 እንደሚቀበሉ እንዲሰማቸው ምን ማለት እንደሚገባኝ አስባለሁ፡፡
ከዚህ በኋላ እንደነሱ ከእግዚአብሔር ጋር ቃልኪዳን ለመመስረት ካልመረጡ አስደናቂ ሴቶችና ወንዶች ቦታ ቢኖራቸውም ያ ቦታ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደገና ሚገናኙበት እና የመኖር እድል የሚሰጡበት እና ለዘላለም የሚሻሻሉበት ቦታ እንዳልሆነ መረዳት አለባቸው፡፡ ያ የሀሴት ሙላት ፤ በፍጹም የማያልቅ እድገት እና ደስታ የሚያገኙበት ቦታ አይደለም፡፡9 እነዚያ ፍጹም የሆኑ በረከቶች የሚመጡት ከፍ ባለው ሰማያዊ ግዛት ውስጥ ከእግዚአብሔር ዘላለማዊ አባታችን፣ ከልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እና አስደናቂ፣ የሚገባቸው እና ብቁ የሆኑ የቤተሰቦቻችን አባላት ጋር ነው፡፡
ለቁጥብ ጓደኞቼ እንዲህ እላለሁ —
“በዚህ ህይወት ለማንኛውም ሁለተኛ ምርጥ ነገር ተስማምታችሁ አታውቁም፡፡ ሆኖም የእየሱስ ክርስቶስን የተመለሰ ወንጌል ሙሉ በሙሉ መቀበልን ስትቃወሙ ሁለተኛ ምርጥ ነገርን እየመረጣችሁ ነው፡፡
አዳኙ ‘በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ’ ብሏል፡፡10 ሆኖም ግን ከእግዚአብሔር ጋር ቃልኪዳን አለመግባትን ስትመርጡ ከሁሉም ጥራት ለሌለው መኖርያ ለዘላለም እየተስማማችሁ ነው፡፡
ቁጥብ ጓደኞቼን በተጨማሪ እንዲህ ስል እለምናለሁ
“ልባችሁን ለእግዚአብሔር አፍስሱ፡፡ እነዚህ ነገሮች እውነት እንደሆኑ ጠይቁ፡፡ ቃሉን ለማጥናት ጊዜ ውሰዱ፡፡ የእውነት አጥኑ! በእውነት ቤተሰቦቻችሁን የምትወዱ ከሆነና ለዘላለም ከነሱ ጋር ከፍ ማለት ምትፈልጉ ከሆነ ዋጋውን አሁን ክፈሉ፡፡ እነዚህን ዘላለማዊ እውነታዎች ለማወቅና በነሱ ለመቆየት ተግታችሁ አጥኑ እናም በጥልቀት ጸልዩ፡፡
“በእግዚአብሔር ማመናችሁን እንኳን እርግጠኛ ካልሆናችሁ እዚያው ጀምሩ፡፡ የእግዚአብሔር ልምምድ በሌለበት ፤ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን መኖር ሊጠራጠር እንደሚችል ተረዱ፡፡ ስለዚህ ራሳችሁን ከሱ ጋር መገናኘት መጀመር በምትችሉበት ቦታ ላይ አድርጉ፡፡ ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፡፡ የእግዚአብሔርን እጅ በህይወታችሁ እና በአካባቢያችሁ እንድታዩ ጸልዩ፡፡ እሱ በእውነት እዚያ እንደሆነና የሚያውቃችሁ እንደሆን እንዲነግራችሁ ጸልዩ፡፡ ስለናንተ ምን እንደሚሰማው ጠይቁት፡፡ ከዚያም አዳምጡ፡፡”
አንድ ውድ የሆነ ጓደኛዬ ከእግዚአብሔር ጋር የተወሰነ ልምምድ ነበረው፡፡ ነገር ግን ካረፈችው ሚስቱ ጋር ለመሆን ይጓጓል፡፡ እንድረዳው ጠየቀኝ፡፡ የክርስቶስን አስተምሮት እና ወንጌል ቃልኪዳኖች ፣ ስርዐቶች እና በረከቶች እንዲረዳ ከምስዮናዊዎቻችን ጋር እንዲገናኝ አበረታታሁት፡፡
ያንንም አደረገ፡፡ ነገር ግን እነሱ የመከሩት መንገድ ብዙ ለውጦችን በህይወቱ እንዲያደርግ እንደሚያስፈልገው ተሰማው፡፡ እንዲህ አለ “እነዚያ ትዕዛዛት እና ቃልኪዳኖች ለኔ በጣም ከባድ ናቸው፡፡ እናም አስራት መክፈል አልችልም እናም ቤተክርስትያን ውስጥ ለማገልገል ጊዜ የለኝም፡፡” ከዚያም “ከሞትኩ በኋላ እባክህን ሚስቴና እኔ ዳግም አብረን እንድንሆን አስፈላጊውን የቤተመቅደስ ስራ ስራልኝ“ ብሎ ጠየቀኝ፡፡
ደስ የሚለው ነገር እኔ የዚህ ሰውዬ ዳኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን በህይወት ሳለ የመጠመቅ፣ ክህነት የመቀበልና የቤተመቅደስ በረከት የማግኘት እድል የነበረው ነገር ግን ሆን ብሎ የተቃወመው ሰው የውክልና የቤተመቅደስ ስራን ውጤታማነት እጠራጠራለሁ፡፡
ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤታችን የሚመልሰንን የቃልኪዳን መንገድ ተከትለን ከሰማያዊ ወላጆቻችንና ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እንድንሆን ይጋብዘናል፡፡ “ኑ፣ ተከተሉኝ” ብሎ ይጋብዘናል።
አሁን እንደ ቤተክርስትያኑ ፕሬዘደንትነት ከቤተክርስትያኑ ራሳችሁን ያራቃችሁትን እና የአዳኙን ቤተክርስትያን መመለሱን ለማወቅ እስካሁን ያልጣራችሁትን እለምናችኋለሁ፡፡ ለራሳችሁ ለማወቅ መንፈሳዊውን ስራ ስሩ ፤ እናም እባካችሁ አሁን ስሩ፡፡ ጊዜ የለንም፡፡
እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ እመሰክራለሁ! ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ቤተክርስትያኑ እና የወንጌሉ ሙላት ህይወታችንን እዚህና በሚመጣው አለም በደስታ ሊባርከን ተመልሷል፡፡ ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።