የመዝጊያ ነጥቦች
እግዚአብሔርን እና ልጆቹን በመጋረጃው በሁለቱም በኩል እንድናገለግል ሕይወታችንን እንስጥ እና በድጋሚ እንስጥ፡፡
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፤ ለዚህ ታሪካዊ ጉባኤ መዝጊያ ስንቃረብ፤ ጌታን ስለ እርሱ ምሪት እና ስለ ጥበቃው እናመሰግነዋለን፡፡ እነዚህ መልዕክቶች አስተምረውናል እናም አንፀውናል፡፡ እነዚህ መልዕክቶች አስተምረውናል እናም አንፀውናል፡፡
ለተናጋሪዎች ርዕስ አልተሰጣቸውም ነበር፡፡ እያንዳንዳቸው መልዕክታቸውን ለማዘጋጀት ለግል ራዕይ ፀልየዋል፡፡ ለእኔ፤ እነዚህ መርሆች እርስ በእርስ መገጣጠማቸው የሚያስደንቅ ነው፡፡ በምታጠኗቸው ጊዜ፤ ጌታ በአገልጋዮቹ አማክኝነት ምን ሊያስተምራችሁ እንደፈለገ ለመማር ጣሩ፡፡
መዝሙሩ በክብር የተሞላ ነበር፡፡ ብቃታቸውን አንድ ላይ በማድረግ የጌታ መንፈስ በሁሉም ክፍለ ጊዜ እዲመጣ ላደረጉት ለብዙ ሙዚቀኞች ጥልቅ የሆነ ምስጋና አለን፡፡ እናም እርሱም ፀሎቶቹን እናም ምእመናኑን በሁሉም ክፍለ ጊዜ ባርኳል፡፡ በእውነት፤ለሁላችንም ጉባኤው ዳግም መንፈሳዊ ግብዣ ሆኗል፡፡
የሁሉም አባል ቤት የጌታ መንፈስ የሚኖርበት እውነተኛ የእምነት መጠለያ እንዲሆን እንመኛለን እናም እንፀልያለን፡፡ ምንም እንኳ ብጥብጥ በዙሪያችን ቢከበን፤ አንድ ቤት ጥናት፤ ፀሎት እና እምነት በአንድ ላይ ከፍቅር ጋር የሚጣመሩበት ሰማያዊ ስፍራ መሆን ይችላል፡፡ በእውነት የጌታ ደቀመዛሙር መሆን እንችላለን፤ የትም ብንሆን ሰለ እርሱ በመቆም እና በመናገር፡፡
የእግዚአብሔር አላማ የእኛ አላማ መሆን አለበት፡፡ ልጆቹ መርጠው ወደ እርሱ እንዲመለሱ ይፈልጋል፤ ተዘጋጅተው፤ብቁ ሆነው፤ በኃይል ተሞልተው ፤ ታትመው እናም ቤተመቅደስ ውስጥ ለገቡት ቃልኪዳን ታማኞች ሆነው፡፡
በአሁን ወቅት 162 የተቀደሱቤተመቅደሶች አሉን። ቀደም ሲል የነበሩት ለውድ ፈርቀዳጆች ለእምነታቸው እና ለራዕይአቸው እንደ ሀውልት ቆመዋል፡፡ እያንዳንዱ በእነርሱ የተሰራ ቤተመቅደስ ታላቅ ግላዊ መስዋትነት እና የጥረት ውጤት ነው፡፡ እያንዳንዱ በፈርቀዳጆች የስኬትአክሊል ላይ እንደሚያበራ ጌጥ ይቆማል፡፡
እነርሱን እንድንከባከባቸው የእኛ የተቀደሰ ኃላፊነት ነው ፡፡ ስለዚህ፤ እነዚህ ፈርቀዳጅ ቤተመቅደሶች በቅርቡ እንዲሻሻሉ እና እንዲታደስ ይድረጋል እናም፤ አንዳንዶቹ ፤ከፍተኛ ጥገና ይደረግላቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ቤተመቅደሶች ልዩ የሆነውን ታሪካዊነታቸውን በተቻል አቅም እንዲጠበቁ ጥረቶች ይደረጋሉ፤ መሳጭ ውበታቸውን እናም ከረጅም ጊዜ በፊት ካለፉት ትውልዶች የሆኑትን ልዩ የእጅ ስራ ውጤቶችም ይጠበቃሉ፡፡
የሴንት ጆርጅ ዩታ ቤተመቅደስ ዝርዝር ቀደም በሎ ተገልፆአል፡፡ የሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ፤ የቤተመቅድስ አደባባይ እና ተያይዞ ያለውን አካባቢ እስከ ቤተክርስቲያን ፅህፈት ቤት ህንፃ ድርስ ስላሉት ስለእነዚህ የጥገና እቅዶች አርብ በ 19 ሚያዚያ 2019 እኤአ ገለፃ ይደረጋል ፡፡
የማንታይ እና ሎገን ዩታ ቤተመቅድሶችም በሚቀጥሉት ዓመታት ይታደሳሉ፡፡ እነዚህ እቅዶችም ተዘጋጅተው ሲያበቁ ፤ እንዲሁ ይገለፃሉ፡፡
ይህ ስራ ቤተመቅደሶቹ ለተወሰነ ጊዜ ዝግ እንዲሆኑ ይጠይቃል። የቤተክርስቲያን አባላት በአቅራቢያቸው በሚገኙ በሌላ ቤተቅደሶች የቤተመቅደስ አገልግሎቶችን እና አምልኮወችን መካፍል መቀጠል ይችላሉ፡፡ እያንዳንዱ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ፤ እያንዳንዱ ታሪካዊ ቤተመቅደስ በድጋሚ ይቀደሳል፡፡
ወንድሞች እና እህቶች፤ በቤተክሪሰቲያን ውስጥ ቤተመቅደስን በጣም የተቀደሰ መዋቅር አድርገን እንመለከታለን። የአዲስ ቤተመቅደስ ግንባታን እቅድ ስናስተዋውቅ፤ ቅዱስ የሆነ የታሪካችን ክፍል ይሆናል፡፡ አሁን እባካችሁ በጥንቃቄ እና አክብሮት አዳምጡ፡፡ የማስተዋውቀው ቤተመቅድሰ ቦታ ለእናንተ ልዩ ከሆነ፤ ምክሬ በቀላሉ እራሳችሁን በመጎንበስ ፀጥ ባለ ፀሎት ከልባችሁ እንድታመሰግኑ ነው፡፡ እኛ ምንም አይነት ስሜታዊ ድምጽ የተቀደስውን የእዚህ ጉባኤ ተፈጥሮ እና የጌታ ቅዱስ ቤተመቅደሶችን እንዲያውክ አንፈልግም፡፡
ዛሬ ስለሚገነቡ ተጨማሪ ቤተመቅደሶች ስናስተዋውቅ ደስ ይለናል፤ የሚገነቡትም በሚከተሉት ስፍራዎች ይሆናል።
ፓጎ ፓጎ፣ አሜሪካን ሳሞአ፤ ኦኪናዋ ከተማ፣ ኦኪናዋ፤ ኔአሁ፣ ቶንጋ፤ ቶሌ ሸለቆ፣ ዩታ፤ ሙሴ ሃይቅ፣ ዋሽንግተን፤ ሳንፔድሮ ሱላ፣ ሆንዱራስ፤ አንቶፋጋስታ፣ ቺሊ፤ ቡዳፔስት፣ ሃንጋሪ፡፡
አመሰግናለሁ ውድ ወንድሞች እና እህቶች፡፡
ስለ አዲስ ወይም ስለ አሮጌ ቤተመቅድሶች ስናውራ፤ እያንዳንዳችን የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ደቀ መዝሙርነታችን በተግባር የሚታይ ይሁን፡፡ በእርሱ ላይ ባለን እምነት እና መመካት ሕይወታችንን እናደስ፡፡ በየቀኑ በምንገባው ንሰሀ የሃጥያት ዋጋ ክፍያውን ኃይል እናግኝ፡፡ እናም እግዚአብሔርን እና ልጆቹን በመጋረጃው በሁለቱም በኩል እንድናገለግል ሕይወታችንን እንስጥ እና በድጋሚ እንስጥ፡፡
በረከቴን እና ፍቅሬን እተውላችኋለሁ፤ በዚህ በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ ዕራይ እንደሚቀጥል ዋስትና እሰጣችኋለሁ፡፡ ይቀጥላል “የእግዚአብሔር እቅድ እስከሚከናወን፣ እና ታላቁ ይሆዋ ስራው ተፈፅሟል እስከሚል” ድረስ፡፡ 1
እንዲህም እባርካችኋለሁ እናም እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ ምስክሬን እሰጣችኋለሁ! ኢየሱስ ክርስቶስ ነው! ይህች የእርሱ ቤተክርስቲያን ናት። እኛ ህዝቦቹ ነን። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።