አጠቃላይ ጉባኤ
በስሙ ባርኩ
የሚያዝያ 2021 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


በስሙ ባርኩ

ክህነትን የመቀበል ዓላማችን ሰዎችን በስሙ ለጌታ እንድንባርክ ለማስቻል ነው።

ውድ ወንድሞቼ፣ በእግዚአብሔር ክህነት አገልጋዮች፣ በዚህ ምሽት ለእናንተ መናገሬ ለእኔ ክብር ነው። ለእናንተ ጥልቅ አክብሮት እና ምስጋና አለኝ። እናንተን ሳናግር እና ስለታላቅ እምነታችሁ ስሰማ፣ ይበልጥ በጠነከሩ ኮረሞች እና ይበልጥ ታማኝ በሆኑ የክህነት ተሸካሚዎች፣ በይበልጥ እየጨመረ የመጣ የክህነት ሃይል በአለም ላይ እንዳለ እምነቴ ነው።

በዚህ ምሽት ቆይታዬ ውስጥ፣ በግል የክህነት አገልግሎታችሁ እንዲሁም የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ለምትፈልጉት እናገራለሁ። በማገልገል ጥሪያችሁን ለማጉላት ያላችሁን ሃላፊነት ታውቃላችሁ።1 ነገር ግን ጥሪያችሁን ማጉላት ለእናንተ ምን ማለት እንደሆነ ልታስቡ ትችላላችሁ።

የክህነት አገልግሎታቸውን ማጉላት ምን ማለት እንደሆነ እርግጠኛነት በበለጠ የማይሰማቸው ሊሆን ስለሚችል በአዲሶቹ ዲያቆናት እጀምራለሁ። አዲስ የተሾሙ ሽማግሌዎችም ለማዳመጥ ይፈልጉ ይሆናል። እና በመጀመሪያዎቹ የአገልግሎት ሳምንቶቹ ውስጥ ያለ ኤጲስ ቆጶስም እንዲሁ ፍላጎት ሊኖረው ይችላል።

ወደ ዲያቆን ጊዜአቶቼ ወደ ኋላ መለስ ብዬ መመልከቴ ለእኔ ትምህርት ነው። አሁን የምጠቁመወን ያኔ አንድ ሰው ነግሮኝ ቢሆን ብዬ እመኛለሁ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ወደ እኔ በመጡት በሁሉም የክህነት ሃላፊነቶች ሁሉ—በአሁኑ ጊዜ የምቀበላቸውን እንኳን ጨምሮ ሊረዳ ይችል ነበር።

ዲያቆን ሆኜ የተሾምኩበት ቅርንጫፍ በጣም ትንሽ ከመሆኑ የተነሳ እኔ ብቸኛው ዲያቆን እና የእኔ ወንድም ብቸኛው መምህር ነበርን። በቅርንጫፍ ውስጥ እኛ ብቸኛው ቤተሰብ ነበርን። መላው ቅርንጫፍ በእኛ ቤት ነበር የሚገናኘው። ለወንድሜ እና ለእኔ የክህነት መሪ የነበረው እራሱ ገና ክህነት የተቀበለ አዲስ አባል ነበር። አምናለሁ ያኔ የእኔ ብቸኛው የክህነት ሃላፊነት በእራሴ ሳሎን ክፍል ውስጥ ቅዱስ ቁርባን ማሳለፍ ነበር።

ቤተሰቤ ወደ ዩታ ሲዛወሩ፣ ብዙ ዲያቆናት ባሉበት ትልቅ አጥቢያ ውስጥ እራሴን አገኘሁ። እዚያ በመጀመሪያ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዬ ላይ፣ ዲያቆናት—እንደ ጦር ሰራዊት መስለው—ቅዱስ ቁርባንን ሲያሳልፉ በተስተካከለ መልኩ ልክ እንደሰለጠነ ቡድን ሲንቀሳቀሱ አየሁ።

በጣም ከመፍራቴ በቀጣዩ እሁድ ወደ አጥቢያው ህንፃ ማንም ሳያየኝ ብቻዬን ለመሆን ቀድሜ ሄድኩ። በሶልት ሌክ ከተማ ውስጥ የዬልክረስት ዋርድ እንደነበረ እና መሬት ላይ ሃውልት እንደነበረው አስታውሳለሁ። ቅዱስ ቁርባን ለማሳለፉ ቦታዬን ስይዝ አለመውደቅን እንዴት እንደማውቅ ለእርዳታ ከሃውልቱ በስተጀርባ ሄጄ ከልብ ፀለይኩ። ያ ፀሎቴ ተመልሶ ነበር።

ነገር ግን በክህነት አገልግሎታችን ለማደግ ስንሞክር የመጸለያ እና የማሰቢያ የተሻለ መንገድ እንዳለ አሁን አውቃለሁ። ግለሰቦች እንዴት ክህነትን እንደሚሰጣቸው ከመረዳቴ የመጣ ነው። ክህነትን የመቀበል ዓላማችን ሰዎችን በስሙ ለጌታ እንድንባርክ ለማስቻል ነው።2

ያ ማለት በተግባር ምን ማለት እንደሆነ የተማርኩት ዲያቆን ከሆንኩ ከዓመታት በኋላ ነበር። ለምሳሌ፣ እንደ ሊቀ ካህን፣ በእንክብካቤ ማዕከል የቅዱስ ቁርባን ስብሰባን እንድጎበኝ ተመደብኩ። ቅዱስ ቁርባን እንዳሳልፍ ተጠየኩ። ቅዱስ ቁርባንን ስለማሳልፍበት ሂደት ወይም ትክክለኛነት ከማሰብ ይልቅ የእያንዳንዱን አዛውንት ሰው ፊት ተመለከትኩ። አብዛናዎቹ እያነቡ እንደነበር ተመለከትኩ። አንድ ሴት እጄን ያዘች፣ ወደላይ ቀና ብላ፣ እንዲህ አለች፣ “ኦ፣ አመሰግናለሁ፣ አመሰግናለሁ።”

ጌታ በእርሱ ስም የተሰጠውን የእኔን አገልግሎት ባረከው። የዛ ቀን የእኔን ክፍል እንዴት በአግባቡ እንደምወጣ ከመፀለይ ይልቅ እንደዚያ ያለ ተአምር እንዲመጣ ፀልዬ ነበር። ሰዎች በፍቅር አገልግሎቴ አማካኝነት የጌታ ፍቅር እንዲሰማቸው ፀልዬ ነበር። ይሄ ለማገልገል እና በእርሱ ስም ሌሎችን ለመባረክ ቁልፉ እንደሆነ ተማርኩ።

የዛን ፍቅር ያስታወሰኝ የቅርብ ተሞክሮን ሰምቼ ነበር። በ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ሁሉም የቤተክርስቲያን ስብሰባዎች በተቋረጡበት ወቅት፣ አንድ አገልጋይ ወንድም ከኤልደርስ ኮረም ፕሬዝዳንት የተሰጠውን ተልእኮ በመቀበል ለሚያገለግላት እህት ቅዱስ ቁርባንን የመባረክ እና የማሳለፍ ሃላፊነትን ተቀበለ። ቅዱስ ቁርባንን ለማቅረብ ሲደውልላት፣ በእንዲህ ያለ አደገኛ ጊዜ ውስጥ ከራሱ ቤት መውጣቱን በመጥላት እንዲሁም ነገሮች በፍጥነት ወደ መደበኛው እንደሚመለሱ በማመኗ እያቅማማች ተቀበለች።

በዚያ እሁድ ጠዋት ወደ ቤቷ ሲደርስ፣ ጥያቄ ነበራት። ወደ ቀጣዩ ቤት በመጓዝ እና ከ87 አመት እድሜ ከነበራቸው ጎረቤቷ ጋር ቅዱስ ቁርባንን መካፈል ይችሉ ይሆን? ከኤጲስ ቆጶሱ ፍቃድ በማግኘት፣ እርሱ ተሰማማ።

ለብዙ፣ ለብዙ ሳምንታት፣ እና በጣም ጠንቃቃ በሆነ ማህበራዊ ርቀትን እና ሌሎች የደህንነት እርምጃዎችን በመውሰድ፣ ያ አነስተኛ የቅዱሳን ቡድን በየሳምንቱ እሁድ ለቀላል የቅዱስ ቁርባን አገልግሎት ይሰበሰብ ነበር። ጥቂት ቁርጥራጭ ዳቦ እና የኩባያ ዉሃ—ነገር ግን በአፍቃሪው እግዚአብሔር መልካምነት ብዙ እንባዎች ፈሰው ነበር።

ከጊዜ በኋላ፣ አገልጋዩ ወንድም፣ ቤተሰቡ እና የሚያገለግላቸው እህት ወደ ቤተክርስቲያን መመለስ ችለዋል። ነገር ግን የ87 አመት መበለት ጎረቤት፣ ጥንቃቄ ከማብዛት፣ ቤት መቆየት ነበረባቸው። አገልጋዩ ወንድም—የተሰጠው ተልእኮ ለጎረቤታቸው እንጂ ለእድሜ ባለፀጋ እህት እንዳልነበረ አስታውሱ— የጌታን እራት ቅዱስ ቁርባን ለማስተዳደር የቅዱሳን ጽሑፎችን እና ትንሽ ዳቦ በእጅ በመያዝ እስከ ዛሬ ድረስ በየቀኑ እሁድ በፀጥታ ወደ ቤታቸው ይመጣል።

የክህነት አገልግሎቱ፣ በእዚያ በእንክብካቤ ማእከል ውስጥ እንደ እኔ፣ የሚሰጠው ከፍቅር የተነሳ ነው። በእርግጥ፣ አገልጋዩ ወንድም በቅርቡ ሊረዳቸው የሚችል በአጥቢያ ውስጥ ሌሎች ካሉ ብሎ ኤጲስ ቆጵሱን ጠየቀ። የክህነት አገልግሎቱን ከፍ ለማድረግ ያለው ፍላጎት በጌታ ስም እና እርሱ ብቻ በሚያውቀው መንገድ ስላገለገለ አድጓል። አገልጋዩ ወንድም የጌታውን ፍቅር እንዲያውቁ፣ እኔ እንዳደረኩት፣ ፀልዮ እንደነበረ አላውቅም፣ ግን አገልግሎቱ በጌታ ስም ስለነበረ ውጤቱ አንድ ነበር።

ለታመመ ወይም በችግር ጊዜ ውስጥ ላለ ሰው የክህነት በረከትን ከመስጠቴ በፊት እንደዛ ስጸልይ ተመሳሳይ አስደናቂ ውጤት ይመጣል። የክህነት በረከትን ለመስጠት ለእኔ እድል ከመስጠት ይልቅ ስራቸውን መስራት እንዲችሉ ቶሎ ብዬ ከመንገዱ ዞር እንድል—ከማጣደፍ በላይ ቶሎ እንድል—ባዘዙኝ ትዕግስት የሌላቸው ዶክተሮች—ሲያጣድፉኝ ይህ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ ተከሰተ። ቆየሁና በረከቱን ሰጠው። እናም በዛን ቀን የባረኳት ዶክተሮች ትሞታለች ያሉት ያቺ ትንሽዬ ልጅ ኖረች። ያ ቀን የገዛ ስሜቶቼ እንቅፋት እንዲሆን ስላልፈቀድኩኝ ነገር ግን ጌታ ያቺ ልጅ በረከት እንድታገኝ እንደፈለገ ስለተሰማኝ በዚህ ጊዜ አመስጋኝ ነኝ። እናም በረከቶቹ ምን እንደነበሩ አወቅኩኝ፦ እንድትፈወስ ባረኳት። እርሷም ተፈወሰች።

ለመዳን በረከት ተስፋ በማድረግ አልጋው ላይ በሞት የተቃረበን ሰው የቤተሰብ አባላት አልጋውን ከበውት በረከትን ስሰጥ ብዙ ጊዜ ተከስቷል። ምንም እንኳን የቅፅበት ጊዜ ቢኖረኝ፣ ጌታ በስሙ መስጠት የምችለውን እርሱ ያቀረበውን በረከት ለማወቅ ሁሌም እጸልያለሁ። እናም እኔ ያንን ሰው እንዴት እንድባርክ እንደሚፈልግ ለማወቅ እጠይቃለሁ እንጂ እኔ ወይም በአጠገብ የቆሙት ሰዎች የምንፈልገውን አይደለም። የእኔ ተሞክሮ በረከቱ ሌሎች ለራሳቸው ወይም ለሚወዱት ሰው የሚመኙት ባይሆንም እንኳ፣ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ተቀባይነት እና ማጽናኛን ለማግኘት መንፈስ ልቦቻቸውን ይነካል።

ፓትሪያርኮች ጌታ ለአንድ ግለሰብ የሚፈልገውን በረከት ለመስጠት ለምሬት ሲፆሙ እና ሲፀልዩ ይኸው አይነት መነሳሳት ይመጣል። እንደገና፣ እኔን ያስገረመኝን እና በረከቱን የሚቀበለውን ሰውም ያስገረመ በረከት ሲሰጥ ሰምቻለሁ። በግልፅ፣ በረከቱ ከጌታ ነበር—በውስጡ የያዘው ማስጠንቀቂያ እንዲሁም በእርሱ ስም የተሰጡትን ቃልኪዳኖች ጨምሮ። የፓትሪያርኩ ፀሎት እና ፆም በጌታ ምላሽ አግኝቷል።

እንደ ኤጲስ ቆጶስ፣ እርሱ የሚያቀርባቸውን መነሳሳቶች ያለ እኔ ፍርድ ግርዶሽ በመጠበቅ፣ የብቁነት ቃለ መጠይቆችን ሳደርግ ለግለሰቡ ጌታ የፈለገው እንዲሰማኝ መፀለይን ተማርኩ። ጌታ፣ በፍቅር፣ አንድን ሰው በማስተካከል ሊባርክ ሲፈልግ ያ ከባድ ይሆናል። ጌታ የሚፈልገውን እናንት እና ሌላኛው ግለሰብ ከምትፈልጉት ለመለየት ጥረት ይጠይቃል።

የክህነት አገልግሎትን በህይወት ጊዜያችን እንዲሁም ከዛ በላይ ማጉላት እንደምንችል አምናለሁ። ለእርሱ ለምናገለግለው ሰው ምን እንደሚፈልግ በተሻለ ለማወቅ እንድንችል የጌታን ፈቃድ ለማወቅ በመጣር በትጋት እና ድምፁን ለመስማት በምናደርገው ጥረት ላይ የሚመረኮዝ ይሆናል። ያ ማጉላት በትንሽ ደረጃዎች ይመጣል። ዘግይቶ ሊሆን ይችላል የሚመጣው፣ ነገር ግን መምጣቱ አይቀርም፡፡ ጌታ ይህን ለእኛ ቃል ይገባል፤

“እነዚህን የተናገርኩባቸውን ሁለት ክህነቶች በማግኘት እና ጥሪያቸውን ለማጉላት ታማኝ የሆኑት፣ ሰውነታቸውን በማደስ በመንፈስ ይቀደሳሉና።

“እነርሱም የሙሴ እና የአሮን ወንድ ልጆች፣ እናም የአብርሐም ዘር፣ እና ቤተክርስቲያንና መንግስት፣ እናም በእግዚአብሔር የተመረጡ ይሆናሉ።

“እና ደግሞም ይህን ክህነት የሚቀበሉትም ሁሉ እኔን ይቀበሉኛል፣ ይላል ጌታ።”3

የክህነት ቁልፎች ለጆሴፍ ስሚዝ ዳግም እንደተመለሱ የእኔ ምስክረነት ነው። በፊታችን ለተገለጡት እና ላሉት ታላቅ ክስተቶች የክህነት አገልግሎትን ዳግም ለመመለስ ከሰማይ የጌታ አገልጋዮች ተገለጡ። እስራኤል ትሰበሰባለች። የጌታ ህዝቦች ለእርሱ ክብራዊ የዳግም ምፅዓት ይዘጋጃሉ። ዳግም መመለስ ይቀጥላል። ጌታ የበለጠ ፍላጎቱን ለነብያቱ እና ለአገልጋዮቹ ይገልጣል።

ጌታ ከሚያደርገው ታላቅ ስራ አንፃር ትንሽነት ሊሰማችሁ ይችላል። ያ ከተሰማችሁ፣ በፀሎት ጌታ እናንተን እንዴት እንደሚያያችሁ እንድትጠይቁ እጋብዛችኋለሁ። እርሱ በግል ያውቃችኋል፣ ክህነትን በእናንተ ላይ ሰቷል፣ እና መነሳት እና ክህነትን ማጉላት ለእርሱ ትርጉም አለው ምክንያቱም ይወዳችኋል እና የሚወዳቸውን ሰዎች በስሙ እንድትባርኩ ያምናችኋል።

የእርሱ ፍቅር እና አመኔታ ሊስማችሁ እንዲችል እባርካችኋለሁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

አትም