አጠቃላይ ጉባኤ
ክርስቶስ ተነስቷል፤ በእርሱ ማመንም ተራራን ያነቃንቃል
የሚያዝያ 2021 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ክርስቶስ ተነስቷል፤ በእርሱ ማመንም ተራራን ያነቃንቃል

በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን በህይወታችን ከሚገኝ በላይ ታላቅ ሀይል ነው። ለሚያምኑት ሁሉም ነገሮች የሚቻሉ ናቸው።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በዚህች የፋሲካ ሰንበት እናንተን ለማነጋገር ላገኘሁት እድል አመስጋኝ ነኝ።1 የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕት እና ትንሳኤ የእያንዳንዳችንን ህይወት ለዘለአለም ቀይረዋል። እርሱን እናፈቅራለን እናም እርሱን እና የሰማይ አባታችንን በምስጋና እናመልካለን።

ባለፉት ስድስት ወራት፣ በአለም አቀፍ ወረርሸኝ እየታገልን ነበር። በህመም፣ በኪሳራ እና በተናጥል ሁኔታ ውስጥ ባላችሁ ጽናት እና መንፈሳዊ ጥንካሬዎ እደነቃለሁ። በሁሉም ሁኔታዎች፣ ጌታ ለእናንተ የማያቋርጥ ፍቅር እንዳለው እንዲሰማችሁ እጸልያለሁ። ለፈተናችሁ በጠንካራ ደቀ መዛሙርትነት ምላሽ ከሰጣችሁ፣ ያለፈው ዓመት በከንቱ አይሆንም።

ዛሬ ጠዋት በምድር ላይ ከሚኖሩ ከማንኛውም አህጉር ከመጡ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሰምተናል። በእውነት የወንጌል በረከቶች ለሁሉም ዘር፣ ቋንቋ እና ህዝብ ናቸው። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ናት። ኢየሱስ ክርስቶስ መሪያችን ነው።

ደግነቱ፣ ወረርሽኝም እንኳ ቢሆን የእሱን የእውነት ወደፊት ጉዞ ለመቀነስም አልቻለም። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በትክክል በዚህ ግራ በተጋባ፣ በተበጣባጭ እና በድካም ዓለም ውስጥ አስፈላጊ ነው።

እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጆች የኢየሱስ ክርስቶስን ፈዋሽ፣ የመቤዣነት መልእክት ለመስማት እና ለመቀበል እድሉ ይገባቸዋል። አሁን እና ለዘላለም ለደስታችን የበለጠ አስፈላጊ ሌላ መልእክት የለም።2 በተስፋ የተሞላ ሌላ መልእክት የለም። በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ አለመግባባትን ሊያስወግድ የሚችል ሌላ መልእክት የለም።

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለ እምነት የሁሉም እምነት መሠረት እና የመለኮታዊ ኃይል መተላለፊያ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው፣ “ያለእምነትም [እግዚአብሄርን] ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደእግዚአብሄር የሚደርስ እግዚአብሄር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።”3

በህይወት ውስጥ ጥሩ ነገር ሁሉ–የዘለአለም ጠቀሜታ ያለው በረከት ሁሉ–በእምነት ይጀምራል። እግዚአብሔር በህይወታችን እንዲያሸንፍ መፍቀድ የሚጀምረው እኛን ለመምራት ፈቃደኛ እንደሆነ ባለው እምነት ነው። እውነተኛ ንስሐ የሚጀምረው ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን የማንፃት፣ የመፈወስ እና የማፅናት ኃይል እንዳለው በማመን ነው።4

“የእግዚአብሔርን ኃይል እንዳትክዱ” ብሎ ነቢዩ ሞሮኒ አውጇል፣ “ምክንያቱም እርሱ፣ በሰው ልጆች እምነት መሰረት ይሰራልና።”5 የእግዚአብሔርን ሀይል በህይወታችን ውስጥ የሚከፍተው የእኛ እምነት ነው።

ቢሆንም፣ እምነትን መለማመድ የሚያጥለቀልቅ ሊመስልም ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ በጣም የምንፈልጋቸውን በረከቶች ለመቀበል የሚያስችል በቂ እምነት መሰብሰብ እንደምንችል እናስብ ይሆናል። ሆኖም፣ ጌታ እነዚያን ፍርሃቶች በመፅሐፈ ሞርሞን ነቢይ አልማ ቃላት አማካኝነት እንዲያርፉ አደረጋቸው።

ምስል
የሰናፍጭ እህል ዘር

አልማ ቃልን በቀላል እንድንሞክር እናም “ቅንጣት ያህል እምነትን ከተለማመዳችሁ፣ አዎን ከማመን በላይ የበለጠ ለመፈለግ ባትችሉም” ብሎ ጠየቀን።6 “ቅንጣት ያህል እምነትን” የሚለው ሀረግ፣ “የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት” ቢኖረን “ይህን ተራራ፣ ከዚህ ወደዚያ እለፍ [ብንለው] ያልፋል፤ [የሚሳንንም] ነገር የለም” በማለት ጌታ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የገባውን ቃል ኪዳን እንዳስታውስ ያደርገኛል።7

ምስል
ወፎች በሰናፍጭ ዘር መሃል

ጌታ ስጋዊ ደካማነትን ተረድቷል። ሁላችንም በጊዜያት እንደናቀፋለን። ነገር ግን የእኛን ታላቅ ችሎታም ያውቃል። የሰናፍጭ ዘር በትንሹ ይጀምራል ነገር ግን ወፎች በቅርንጫፎቹ ውስጥ ጎጆ እንዲሰፍሩበት ወደሚያስችል ትልቅ ዛፍ ያድጋል። የሰናፍጭ ዘር አንድ ትንሽ ግን የሚያድግ እምነትን ይወክላል።8

ጌታ ከእርሱ ፍጹም ሀይል ለመካፈል ከእኛ ፍጹም እምነትን አይጠብቅም። ነገር ግን እንድናምን ይጠይቀናል።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ በዚህች የትንሳኤ ጠዋት የምሰጣችሁ ጥሪ እምነታችሁን ለማሳደግ በዛሬ እንድትጀምሩ ነው። በእምነታችሁ በኩል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በህይወታችሁ ውስጥ ያለውን ተራራ ለማነቃነቅ ያላችሁን ችሎታ ያሳድገዋል፣9 ምንም እንኳን የግል ፈተናዎቻችሁ እንደ ኧቨረስት ተራራ ያህል ታላቅ ቢሆንም።

ተራራዎቻችሁ ብቸኝነት፣ ጥርጣሬ፣ ህመም ወይም ሌሎች የግል ችግሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ተራራዎቻችሁ ይለያያሉ፣ ሆኖም ግን ለእያንዳንዱ ተፈታታኝ ሁኔታዎች መልሳችሁ እምነታችሁን መጨመር ነው። ያም ሥራን ይጠይቃል ሰነፍ ተማሪዎች እና ሰነፍ ደቀ መዛሙርት የእምነት ቅንጣትን እንኳን ለመሰብሰብ ሁል ጊዜ ይታገላሉ።

ማንኛውንም ለማድረግ ጥረት ያስፈልገዋል። እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ለመሆነም ከዚህ የተለየ አይደለም። እምነታችሁን እና በእርሱ ያላችሁን ታማኝነት ማሳደግ ጥረት ያስፈልገዋል። ያንን እምነት እና ታማኝነት ለማሳደግ የሚረዱ አምስት ሀሳቦች ላቅርብ።

መጀመሪያ፣ አጥኑ። ተሳታፊ ተማሪዎች ሁኑ። የክርስቶስን ተልእኮ እና አገልግሎት በተሻለ ለመረዳት በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እራሳችሁን ንከሩ። ለህይወታችሁ ያለውን ኃይል እንድትገነዘቡ ዘንድ የክርስቶስን ትምህርት እወቁ። የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በእናንተ ላይ እንደሚሠራ እውነቱን ውስጣዊ አድርጉ። እሱ የእናንተን መከራ፣ የእናንተን ስህተቶች፣ የእናንተን ድክመቶች እና የእናንተን ኃጢያቶች በራሱ ላይ ወሰደ። የማካካሻ ዋጋን ከፍሏል እናም መቼም የሚገጥሟችሁን ተራራዎች ሁሉ ለማንቀሳቀስ ኃይል ሰጥቷችኋል። ያንን ኃይል በእምነታችሁ፣ በመተማመናችሁ እና እሱን ለመከተል በፈቃደኝነታችሁ ታገኙታላችሁ።

ተራራችሁን ለማንቀሳቀስ ታዕምራት ያስፈልገዋው ይሆናል። ስለታዕምራቶች ተማሩ። ታዕምራቶች የሚመጡት በጌታ ባላችሁ እምነት መሰረት ነው። ለዚያ እምነት ማዕከላዊው የሆነውም የእርሱን ፈቃድ እና የጊዜ ሰሌዳን፣ እንዲሁም በምትፈልጉት ተአምራዊ እርዳታ እንዴት እና መቼ እንደሚባርካችሁ፣ መታመን ነው። የእናንተአለማመን ብቻ ነው እግዚአብሔር በእናንተን ህይወት ውስጥ ያሉትን ተራራዎች ለማነቃነቅ በሚያስችሉ ታዕምራቶች መባረኩን የሚገድበው።10

ስለአዳኙ የበለጠ ስትማሩ በምህረቱ፣ ማለቂያ በሌለው ፍቅሩ እና በሚያጠናክረው፣ በሚፈውሰው፣ በመቤዥው ኃይሉ ላይ እምነት መጣል ቀላል ይሆናል። የሚገጥሙንን ወይም ተራራን በእምነት ከምንወጣበት ጊዜ ይልቅ አዳኙ መቼም ለእርናንተ የሚቀርብበት ጊዜ የለም።

ሁለተኛ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ለማመን ምረጡ። ስለ አብ እግዚአብሔር እና ስለውዱ ልጁ፣ ወይም ስለዳግም መመለስ እውነትነት ወይም የጆሴፍ ስሚዝ እንደ ነቢት መለኮታዊ ጥሪ ጥርጣሬ ካላችሁ፣ ለማመን ምረጡ11 እናም ታማኝ ሁኑ። ጥያቄአችሁን ወደ ጌታ እና ወደ ሌላ የእምነት ምንጮች ውሰዱ። በነቢዩ ህይወት ውስጥ ጥፋት ለማግኘት ወይም በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ልዩነትን ለማግኘት ሳይሆን ለማመን በመፈለግ አጥኑ። የሌሎችን ጥርጣሬዎች በመደጋገም የራሳችሁን ጥርጣሬ አታሳድጉ። ጌታ በመንፈሳዊ ግኝት ጉዞአችሁ እንዲመራችሁ ፍቀዱ።

ሶስተኛ፣ በእምነት ስሩ። እናንተ ተጨማሪ እምነት ቢኖራችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ስለዚያ አስቡበት። ስለዚያም ጻፉ። ከዚያም፣ ተጨማሪ እምነት የሚያስፈልገውን ነገር በማድረግ እምነትን በጭማሬ ተቀበሉ

አራተኛ፣ ቅዱስ ስርዓቶችን በብቁነት ተቀበሉ። ስርዓቶች የእግዚአብሔርን ሀይል በህይወታችሁ ውስጥ ያስከፍታሉ።12

እናም አምስተኛ፣ የሰማይ አባታችሁን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለእርዳታ ጠይቁ

እምነት ሥራን ይጠይቃል። ራእይን መቀበል ስራን ይጠይቃል። ነገር ግን “የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፣ እናም የሚፈልግም ያገኛል፤ እናም ለሚያንኳኩ ይከፈትላቸዋል።”13 እግዚአብሔር ምን እምነታችሁን ለማሳደግ እንደሚረዳ ያውቃል። ጠይቁ፣ ከዚያም እንደገና ጠይቁ።

የማያምን እምነት ለደካማ ነው ይል ይሆናል። ነገር ግን ይህ ሃሳብ የእምነትን ሀይል ይንቃል። የአዳኝ ደቀ መዛሙርት እርሱን የሚጠራጠሩ ቢሆኑ ኖሮ፣ ከእርሱ ሞት በኋላ፣ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው፣ የእርሱን ትምህርት በማስተማር ይቀጥሉ ነበርን?14 ጆሴፍ እና ሀይረም ስሚዝ እውነት መሆኑን የሚያረጋግጥ እውነተኛ ምስክርነት ካላገኙ በስተቀር የጌታን ቤተክርስቲያን በዳግም መመለስ በመከላከል የሰማዕታት ሞት ይደርስባቸው ነበርን? የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በዳግም ተመልሷል የሚል እምነት ባይኖራቸው ኖሮ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ቅዱሳን በፈር ቀዳጆች መንገድ ላይ ይሞቱ15 ነበርን? በእውነትም፣ እምነት ለማከናወን የማይቻለውን ለማይመስለው መፈፀም የሚያስችል ኃይል ነው።

ያላችሁን እምነት ዝቅ አታድርጉ። በቤተክርስቲያኑ አባል ለመሆን እና በታማኝነት ለመቆየት እምነት ያስፈልጋል። ከጥበበኞች እና ከብዙዎች አስተያየት ይልቅ ነቢያትን ለመከተል እምነት ይጠይቃል። በወረርሽኝ ጊዜ ሚስዮናዊ አገልግሎት ለመስጠት እምነት ይጠይቃል። የእግዚአብሔር ንፅህና ህግ አሁን ጊዜ ያለፈበት ነው እያለ ዓለም ሲጮህ ንጹህ ህይወት ለመኖር እምነት ይጠይቃል። በዓለማዊ ዓለም ውስጥ ላሉ ልጆች ወንጌልን ማስተማር እምነት ይጠይቃል። ለሚወዱት ሰው ህይወት ለመማፀን እምነት ያስፈልጋል እና እንዲያውም ተስፋ አስቆራጭ መልስ ለመቀበል የበለጠ እምነት ይጠይቃል።

ከሁለት አመት በፊት፣ እህት ኔልሰን እና እኔ ሳሞአ፣ ቶንጋ፣ ፊጂ፣ እና ታሂቲን ጎበኘን። በእያንዳንዱ እነዚያ የደሴት ሀገሮች ለብዙ ቀናት ከባድ ዝናብ ጥሎ ነበር። አባላት የውጪ መሰብሰቢያ ቦታዎቻቸው ከዝናቡ እንዲጠበቁ ጾመውና ጸልየው ነበር።

በሳሞአ፣ ፊጂ፣ እና ታሂቲ ውስጥ ልክ ስብሰባው ሲጀምር ዝናቡ ቆመ። በቶንጋ ውስጥ ግን ዝናቡ አልቆመም። ሆኖም 13 ሺህ ታማኝ ቅዱሳን መቀመጫ ለማግኘት ከብዙ ሰዓታት ቀደም ብለው መጡ፣ በማያቋርጥ ዝናብ ውስጥ በትዕግሥት ጠበቁ፣ እና ከዚያም በጣም በስብሰው የሁለት ሰዓት ስብሰባ ተቀመጡ።

ምስል
የቶንጋ ቅዱሳን በዝናብ ውስጥ

በእነዚያ በእያንዳንዱ የደሴቲቱ ነዋሪዎች መካከል ንቁ እምነት ሲሰራ ተመለከትን—ዝናቡን ለማቆም የሚያስችል እምነት እንዲሁም ዝናቡ ባላቆመ ጊዜ የሚፀና እምነት ተመልክተናል።

በህይወታችን ውስጥ ያሉ ተራራዎች ሁልጊዜም እኛ በምንፈልገው መንገድ ወይም ጊዜ አይነቃነቁም። ነገር ግን እምነት ሁልጊዜም ወደፊት ይገፋናል። እምነት ሁልጊዜም የአምላካዊ ኃይል ተደራሽነትን ይጨምራል።

እባካችሁ እወቁ፦ እናንተ የምታምኗቸው በዓለም ላይ ያሉ ሁሉም ነገሮች እና ሁሉም ሰዎች ቢተውአችሁም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ቤተክርስቲያኑ በጭራሽ አይጥሏችሁም። ጌታ በጭራሽ አያንቀላፋም፣ ወይም አይተኛም።16 እርሱ“ትናንትም ዛሬም ነገም ያው ነው ”17 እርሱ ቃል ኪዳኖቹን፣18 የተስፋ ቃሉን፣ ወይም ለህዝቡ ያለውን ፍቅር አይተውም። ዛሬ ተአምራቶችን ይሰራል እናም ነገም ተአምራቶችን ይሰራል።19

በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን በህይወታችን ከሚገኝ በላይ ታላቅ ሀይል ነው። ለሚያምኑት ሁሉም ነገሮች የሚቻሉ ናቸው።20

በእርሱ ላይ እያደገ የመጣው እምነት ምድርን የሚያስውቧትን የዓለት ተራሮች ሳይሆን በህይወታችሁ ውስጥ ያሉ የመከራ ተራሮችን ያነቃንቋቸዋል። የሚያብበው እምነታችሁ ተግዳሮቶችን ተወዳዳሪ ወደሌለው ዕድገትና ዕድል ለመቀየር ይረዳችኋል።

በዚህ ትንሳኤ ሰንበት፣ በጥልቅ የፍቅር እና የምስጋና ስሜቶቼ፣ “ክርስቶስ በእርግጥም ተነስቷል” በማለት አውጃለሁ። ቤተክርስቲያኑን ለመምራት ተነስቷል። በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ልጆች ሁሉ ለመባረክ ተነስቷል። በእርሱም በማመን፣ በህይወታችን ውስጥ ያሉትን ተራሮች ለማነቃነቅ እንችላለን። እንዲህ የምመሰክረው በቅዱስ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. በአንዳንድ የአለም ክፍሎች ውስጥ ሰዎች በተለያዩ ሁኔታዎች በትንሳኤ ሰንበት ላይ ሰላምታ እንደሚሰጣጡ አስታውሳለሁ። በክልል ቋንቋቸው፣ ሰላምታ የሚሰጠው “ክርስቶስ ተነስቷል!” ይላል። ሰላምታ የሚሰጠውም ሰው በመልስ፣ “በእውነትም!” ተነስቷል!) ለምሳሌ፣ የራሽያ ቋንቋ የሚናገሩት የትንሳኤ ሰላምታ የሚጀምረው “Христос воскрес” (ክርስቶስ ተነስቷል [በትንሳኤ ከሞት ተነስቷል]!) ነው፣, የሚመለሰውም “Воистину! воскрес!” (በእውነትም! ተነስቷል!)

  2. ሞዛያ 2፥41 ተመልከቱ።

  3. ዕብራውያን 11፥6Lectures on Faith [የእምነት ትምህርቶች] እንደሚለው እምነት “በሁሉም ላይ ኃይል፣ ግዛት እና ስልጣን ያለው የመጀመሪያው ታላቅ የአስተዳደር መርህ ነው” ([1985 (እ.አ.አ)]፣ 5)።

  4. ማቴዎስ 11;28–30አልማ 7፥12–13ኤተር 12፥27 ተመልከቱ።

  5. ሞሮኒ 10፥7፤ ትኩረት ተጨምሯል።

  6. አልማ 32፥27፤ ትኩረት ተጨምሯል።

  7. ማቴዎስ 17፥20፤ ትኩረቶች ተጨምሮበት፤ ደግሞም ሔላማን 12፥9፣ 13 ተመልከቱ።

  8. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥17–18 ተመልከቱ። ተፈጥሮአዊውን ሰው የማስወገዱ ዋጋ “በጌታ በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ቅድስት” መሆን ነው (ሞዛያ 3፥19)።

  9. 1 ኔፊ 7፥12 ይመልከቱ።

  10. ሞርሞን 9፥19-21ኤተር 12:30ይመልከቱ።

  11. 2 ኔፊ 33፥10–11 ይመልከቱ።

  12. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥20 ይመልከቱ።

  13. ማቴዎስ 7፥8

  14. ያለ እምነት ኃይል፣ አቢናዲ እውነት መሆኑን ያወቀውን ለመካድ ፈቃደኛ ባለመሆኑ በእሳት ይሞታልን? (ሞዛያ 17፥7–20 ተመልከቱ)። እምነታቸው ቢያወግዙ ኖሮ ህይወታቸው የበለጠ ምቾት የሚኖረው እንደሆነ እያወቁ፣ ኤተር ያለዚያ ኃይል በድንጋይ ዋሻ ውስጥ ይደበቅ ነበርን (ኤተር 13፥13–14 ተመልከቱ) እና ሞሮኒ ለብዙ ዓመታት ብቸኝነትን በጽናት ተቋቁሞ ይኖራልን (ሞሮኒ 1፥1–3 ተመልከቱ)?

  15. See Melvin L. Bashore, H. Dennis Tolley, and the BYU Pioneer Mortality Team, “Mortality on the Mormon Trail, 1847–1868,” BYU Studies, vol. 53, no. 4 (2014), 115.

  16. መዝሙር 121፥4 ተመልከቱ።

  17. ሞሮኒ 9፥9

  18. ኢሳይያስ 54፥103 ኔፊ 22፥10 ተመልከቱ።

  19. ራዕይ 9፥10–11፣ 15 ይመልከቱ።

  20. ማርቆስ 9፥23 ተመልከቱ።

አትም