የእውነትና የፍቅር የወንጌል ብርሃን
የወንጌል እውነት እና የፍቅር ብርሃን ዛሬ በመላው ምድር ላይ ብሩህ ሆኖ እየበራ እንደሆነ እመሰክራለሁ።
“ህዝቦች ሁሉ አድምጡ!” የሚለው ውቡ የኋለኛው ቀን የቅዱስ መዝሙር ያለጥርጥር ቅንዓት እና ደስታ ወደ ዓለም ሁሉ የሚሄድ የወንጌል ሙላትን ይይዛል። በዚህ መዝሙር እንዲህ እንዘምራለን፦
የዚህ የደስታ ጽሑፍ ደራሲ ሉዊስ ኤፍ. ሞንች ጀርመናዊ ሰው ነበር፤ ለመዝሙሩ በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉ ቃላትን የጻፈው በአውሮፓ ውስጥ በሙሉ ጊዜ ሚስዮናዊ አገልግሎቱ ወቅት ስዊዘርላንድ ውስጥ በነበረበት ወቅት ነበር።2 የየዳግም መመለስን ዓለም አቀፋዊ ተፅእኖ በመመልከቱ የሚመነጨውን ደስታ በሚከተሉት የመዝሙሩ ቃላት በግልፅ ተገልጧል፦
በጨለማ ውስጥ በመፈለግ ህዝቦች አልቅሰዋል፤
ንጋት በመጠበቅ ፣ ንቃታቸውን ጠብቀዋል።
አሁን ሁሉም ደስ ይላቸዋል፤ ረጅሙ ሌሊት አልፏል።
እውነት እንደገና በምድር ላይ አለች!3
ከ200 ዓመታት በፊት በጀመረው የዳግም መመለስ ሂደት ምክንያት፣ “የወንጌል እውነትና ፍቅር ብርሃን”4 አሁን በመላው ምድር ላይ እየበራ ይገኛል። ነቢዩ ጆሴፍ በ1820 እና ከዚያም በኋላ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተማሩት፣ እግዚአብሔር “ለሰው ሁሉ በልግስና ይሰጣል እንጂ አይነቅፍም”።5
በዚህ በመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያኗ ከተደራጀች ብዙም ሳይቆይ ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ ተናገረው እንዲህ በማለት ለእኛ ያለውን ከፍተኛ ፍቅር አሳይቷል፦
“ስለዚህም እኔ ጌታ በምድር ነዎሪዎች ላይ የሚመጣውን መቅሰፍት በማወቄ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊን ጠራሁት እናም ከሰማይም ተናገርኩት እንዲሁም ትእዛዛትን ሰጠሁት፤
ዘለአለማዊ ቃልኪዳኔ ይመሰረት ዘንድ፤
እና በኋላም፧ “የወንጌሌ ሙላት በደካሞች እና በተራ ሰዎች … እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ይታወጅ ዘንድ።”6
ይህ ራዕይ ከተቀበለ ብዙም ሳይቆይ ሚስዮናውያን ተጠርተው ወደ ብዙ የዓለም ሀገሮች መላክ ጀመሩ። ልክ በነቢዩ ኔፊ እንደተጠበቀው፣ በዳግም የተመለሰው የወንጌል መልእክት “ሀገሮች፣ ነገዶች፣ ቋንቋዎችና ህዝቦች” መሰበክ ጀመረ።7
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በ1830 (እ.አ.አ) በሰሜናዊ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኝ አነስተኛ ግንድ ውስጥ በመደበኛነት ተደራጀች።
ቤተክርስቲያኗ ከመጀመሪያዎቹ ስድስት አባላት ወደ አንድ ሚሊዮን ለማደግ 117 ዓመታት — እስከ 1947 (እ.አ.አ) ድረስ ፈጅቷል። ሚስዮናውያን ከቀድሞዎቹ ቀናት ጀምሮ እስከ የአገሬው ተወላጅ አሜሪካዊያን ግዛቶች፣ እስከ ካናዳ ድረስ እና በ1837 (እ.አ.አ) ከሰሜን አሜሪካ አህጉር ባሻገር እስከ እንግሊዝ ድረስ ላሉት የቤተክርስቲያኗ ገጽታ ነበሩ። ብዙም ሳይቆይ ሚስዮናውያን በአውሮፓ አህጉር እና እስከ ሕንድ እና የፓስፊክ ደሴቶች ድረስ ይሰሩ ነበር።
“የሁለት ሚሊዮን አባላት ከ16 ዓመታት በኋላ ብቻ ማለትም በ1963 (እ.አ.አ) እና በስምንት ዓመት ደግሞ ሦስት ሚሊዮን ደርሷል።”8
ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን በቅርቡ የቤተክርስቲያኗን ፈጣን እድገት ጎላ አድርገው ሲናገሩ፣ “ዛሬ በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የጌታ ስራ በተቀላጠፍ ፍጥነት ወደፊት እየገሰገሰ ነው። ቤተክርስቲያኗ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ፣ ወደር የማይገኝለት የወደፊት ህይወት ይኖራታል።”9
የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት በዳግም መመለስ፣ የጌታ ህያው ቤተክርስቲያን እንደገና በምድር ላይ መደራጀቷ እና ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ያለው አስደናቂ እድገት የክህነት በረከቶች በመላው ምድር እንዲገኙ አድርገዋል። ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስተሳስሩን እና በቃል ኪዳኑ ጎዳና ላይ የሚያኖሩን የተቀደሱ ሥነ-ሥርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች “የእግዚአብሔርን ኃይል” በግልጽ ያሳያሉ።10 ለህያዋን እና ለሙታን በእነዚህ ቅዱስ ሥርዓቶች ስንሳተፍ እስራኤልን በመጋረጃው በሁለቱም በኩል ሰብስበን ምድርን ለአዳኝ ሁለተኛ ምጽዓት እናዘጋጃለን።
በመጋቢት 1973 (እ.አ.አ) እኔ እና ወላጆቼ ከትውልድ አገራችን አርጀንቲና ወደ ቤተመቅደስ ለመታተም ተጓዝን። በዚያን ጊዜ በሁሉም የላቲን አሜሪካ ውስጥ ቤተመቅደሶች ስላልነበሩ በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ውስጥ ለመታተም ባአጠቃላይ ከ6000 ማይል (ከ9,700 ኪሜ) በላይ በረርን። ምንም እንኳን በወቅቱ የሁለት ዓመት ልጅ ብሆንም እና ያንን ልዩ ተሞክሮ ሙሉ በሙሉ ባላስታውስም፣ ከዚያ ጉዞ ሦስት በጣም የተለያዩ ምስሎች በአእምሮዬ ውስጥ ተተክለዋል እናም ከዚያ በኋላ ቆይተዋል።
በመጀመሪያ፣ ከአውሮፕላኑ መስኮት አጠገብ እንደተቀመጥኩ እና ከታች ያሉትን ነጭ ደመናዎች እንዳየሁ አስታውሳለሁ።
እነዚያ ቆንጆ፣ ብሩህ ደመናዎች ግዙፍ የጥጥ ኳሶች እንደ ሆኑ በአእምሮዬ ይጸናል።
ሌላው በአእምሮዬ ውስጥ የቀረው ምስል በሎስ አንጀለስ አካባቢ በሚገኘው የመዝናኛ ፓርክ ውስጥ ጥቂት አስቂኝ የሚመስሉ ገጸ ባሕሪዎች ነበሩ። እነዚያ ገጸ-ባህሪያትን ለመርሳት ከባድ ነው።
ግን እጅግ የላቀ ጠቀሜታ ይህ ብሩህ እና የማይረሳ ምስል ነው፦
ባልና ሚስቶች እና ቤተሰቦች ለጊዜ እና ለዘለአለም ጥምረት በሚከናወኑበት የሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ቅዱስ ክፍል ውስጥ መሆኔን በግልጽ አስታውሳለሁ። የቤተመቅደሱን ቆንጆ መሠዊያ አስታውሳለሁ እና በክፍሉ ውጫዊ መስኮት በኩል የሚበራ ብሩህ የፀሐይ ብርሃንን አስታውሳለሁ። ያኔ የእውነት እና የፍቅር የወንጌል ብርሃን ሙቀት፣ ደህንነት እና ማጽናኛ ተሰምቶኛል፣ ከዚያም በኋላ ይህ ስሜትን በመስማት ቀጥያለሁ።
ከ20 ዓመታት በኋላ እንደገና ለመታተም ወደ ቤተመቅደስ በገባሁ ጊዜ ተመሳሳይ ስሜቶች ተረጋግጠውልኝ ነበር—በዚህ ጊዜ እንደገና እጮኛዬ እና እኔ ለጊዜ እና ለዘለአለም ታትመን ነበር። ሆኖም፣ በዚህ አጋጣሚ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ማይሎችን መጓዝ አላስፈለገንም ነበር፣ ምክንያቱም የቦነስ አይረስ አርጀንቲና ቤተመቅደስ ተገንብቶ እና ተመርቆ ስለነበረ እንዲሁም ከቤታችን በመኪና አጭር ርቀት ብቻ ነበረው።
ከሠርጋችን እና ከቤተመቅደስ ጥምረታችን ከሃያ ሁለት ዓመታት በኋላ፣ ወደ እዛው ቤተመቅደስ የመመለስ በረከት ነበረን፣ ነገር ግን በዚህ ጊዜ ከቆንጆ ሴት ልጃችን ጋር ነበር፣ እናም እንደ ቤተሰብ ለጊዜ እና ለዘለአለም ተጣመርን።
በእነዚህ በህይወቴ በጣም ቅዱስ የሆኑ ጊዜያት ውስጥ ላይ እንዳልሁ ሳስላስል፣ በጥልቅ፣ በሚዘልቅ ደስታ ዝዬ ነበር። የግለሰባችንን ፍላጎቶች እና ከልብ የመነጨ ፍላጎቶቻችንን የሚያውቅ ርህሩህ የሰማይ አባት ፍቅር ተሰማኝ እና ሲሰማኝም ይቀጥላል።
በመጨረሻው ቀናት እስራኤልን ስለመሰብሰብ ሲናገር፣ ጌታ ያህዌህም እንዲህ ብሏል፣ “ህጌንም በልቡናቸው አኖራለሁ፣ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።”11 ከልጅነቴ ጀምሮ የጌታ ሕግ በቅዱስ ቤቱ ውስጥ በሚገኙ ቅዱስ ሥርዓቶች አማካኝነት በልቤ ውስጥ በጥልቀት መቀረጽ ስለጀመረ ለዘላለም አመሰግናለሁ። እርሱ አምላካችን መሆኑን ማወቅ፣ የእርሱ ሕዝቦች መሆናችን እና በዙሪያችን ያሉት ሁኔታዎች ምን ቢሆኑ ታማኝ ከሆንን እና የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች የምንታዘዝ ከሆንን፣ “እርሱ በዘለዓለማዊው ፍቅር ክንዶች ተከብቤአለሁ።”12
በጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) የሴቶች አጠቃላይ ጉባኤ ወቅት፣ ፕሬዘዳንት ኔልሰን “አንዳችን ለሌላው ለማገልገል፣ ወንጌልን ለማወጅ፣ ቅዱሳንን ፍጹም ለማድረግ እና የሞቱትን በቅዱስ ቤተመቅደስ ለመዋጀት የምናደርገው ጥረት ነው” ብለዋል።13
እንዲሁም በዚያው አጠቃላይ ጉባኤ ወቅት ፕሬዘዳንት ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “በእርግጥ፣ የወንጌል ዳግም መመለስ ዘውዱ ቅዱስ ቤተመቅደስ ነው። ቅዱስ ስርዓቶቹና ቃልኪዳኖቹ ስዎች ለአዳኛችንን ዳግም ምፃአት ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ ቁልፍ ናችው።”14
በመካሄድ ላይ ያለው የወንጌል ዳግም መመለስ በተቀላጠፈ ፍጥነት ቤተመቅደሶችን በመገንባት እና በመምረቅ ቀጥሏል። በመጋረጃው በሁለቱም በኩል ስንሰባሰብ፣ ለማገልገል እና ቤተመቅደሳችን በህይወታችን ውስጥ አስፈላጊ እንዲሆን መስዋእት ስንከፍል፣ ጌታ በእውነት እኛን እየገነባን ነው—እሱ የቃል ኪዳኑን ህዝብ እየገነባ ነው።
አቤቱ፣ ከላይ ካለው ዙፋን እንዴት ክቡር ነው
የእውነትና የፍቅር የወንጌል ብርሃን ያበራል!
እንደ ፀሐይ ብሩህ፣ ይህ የሰማይ ጨረር
ብርሃኑ ዛሬ መላ ምድርን ያበራል።15
የእውነት እና የፍቅር የወንጌል ብርሃን ዛሬ በመላው ምድር ላይ ብሩህ ሆኖ እንደበራ እመሰክራለሁ። በነቢዩ ኢሳይያስ የተተነበየው “አስደናቂ እና ግሩም ስራ”16 እና በኔፊ የታየውም17 በእነዚህ ፈታኝ ጊዜዎች እንኳን በቀለጠፈ ፍጥነት እየተከናወነ ነው። ጆሴፍ ስሚዝ በትንቢት እንዳወጀው፣ “የእውነት ሰንደቅ አላማ ተተክላለች፤ ማንም ያልተቀደሰ እጅ የስራውን እድገት ማቆም አይችልም፤ … የእግዚአብሔርም ዓላማ እስኪሳካ እናም ታላቁ ያህዌ ሥራው ተጠናቋል እስኪል ድረስም።”18
ወንድሞች እና እህቶች፣ እኛ እራሳችንን እና ቤተሰቦቻችንን የሰማያዊውን ድምፅ፣ የአዳኛችንንም ድምጽ ለመስማት ዛሬ ፈቃደኞች እንሁን። ወደ እርሱ ፊት በሚመልሰው ጎዳና ላይ በጽናት የሚያቆዩንን ቃል ኪዳኖች ከእግዚአብሔር ጋር እንግባ እናም እንጠብቅ፣ እንዲሁም በወንጌሉ ታላቅ ብርሃን እና እውነት በረከቶች ደስ ይበለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።