ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥር 29–የካቲት 4 ፦ “መንገዱን በፊታችሁ አዘጋጅላችኋለሁ።” 1 ኔፊ 16–22


ጥር 29–የካቲት 4 ፦ ‘መንገዱን በፊታችሁ አዘጋጅላችኋለሁ።’ 1 ኔፊ 16-22፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“ጥር 29–የካቲት 4 1 ኔፊ 16–22፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ሰዎች ሊያሆናውን ሲፈትሹ

ጥር 29–የካቲት 4 (እ.አ.አ)፦ “መንገዱን በፊታችሁ አዘጋጅላችኋለሁ”

1 ኔፊ 16–22

የሌሂ ቤተሰብ ወደ ቃል ኪዳን ምድሩ ሲጓዙ፦ “ ትዕዛዛቴን ከጠበቃችሁ መንገዱን በፊታችሁ አዘጋጅላችኋለሁ” (1 ኔፊ 17፥13) በማለት ጌታ ቃል ኪዳን ገባላቸው። በግልጽ፣ ያ ቃል ኪዳን ጉዞውን ቀላል ያደርገዋል ማለት አልነበረም—የቤተሰብ አባሎች አልተስማሙም፣ ቀስቶች ተሰበሩ፣ ሰዎች ተሰቃዩ እና ሞቱ እንዲሁም መርከብን ከጥሬ እቃዎች መገንባት ነበረባቸው። ይሁን እንጂ፣ ቤተሰቡ ችግር ወይም የማይቻሉ የሚመስሉ ጉዳዮች ሲገጥመው ጌታ በፍፁም እሩቅ እንዳልሆነ ኔፊ ተገነዘበ። እሱ ይህን አወቀ፣ እግዚአብሔር “[አማኞችን] ይመግባቸዋል፣ ያበረታታቸዋልም፣ እንዲሁም እርሱ ያዘዛቸውን ነገር መፈፀም የሚችሉበትን ዘዴ ያቀርብላቸዋል” (1 ኔፊ 17፥3)። እንደ ኔፊ እና ቤተሰቡ መጥፎ ነገሮች ለምን በጥሩ ሰዎች ላይ እንደሚፈጸሙ ካሰባችሁ፣ በዚህ ምዕራፎች ውስጥ ሃሳቦችን ማግኘት ትችላላችሁ። ነገር ግን ምናልባት የበለጠ ጠቃሚ የሚሆነውን፣ መልካም ሰዎች መጥፎ ነገሮች ሲከሰቱ ምን እንደሚያደርጉ ትመለከታላችሁ።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

የሴሚነሪ መለያ

1 ኔፊ 16–18

አዳኙ የህይወትን ፈተናዎች እንድጋፈጥ ይረዳኛል።

ልክ እንደሁላችን፣ የኔፊ ቤተሰቦች የተወሰኑ ከባድ ችግሮችን ተጋፍጠዋል። ከኔፊ በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት መከራን ስለመጋፈጥ ምን ትማራላችሁ? ስለ እሱ ልምዶች በ1 ኔፊ 16፥17–3216፥34–3917፥7–1618፥1–4፤ እና 18፥9–22. ውስጥ አንብቡ። “ፈተና፣” “የኔፊ ምላሽ” እና “ጌታ እንዴት ረዳ” በሚመስሉ ርዕሶች ስር የምታገኙትን መመዝገብ አስቡ። ለሚያጋጥሟችሁ ፈተናዎች ተግባራዊ ማድረግ የምትችሉትን ምን ተማራችሁ?

ከኔፊ እና ከቤተሰቡ ከተማራችሁ በኋላ ተጨማሪ ሃሳቦችን “ፈተናዎቼ፣” “የእኔ ምላሽ” እና “ጌታ እንዴት ይረዳኛል” በሚሉ ርዕሶች ስር መመዝገብ ትችላላችሁ። ይህን ስታደርጉ፣ እንደዚህ ዓይነት ጥቅሶችን መጥቀስ ትችላላችሁ፦ ማቴዎስ 11፥28–30ዮሐንስ 14፥26–27ሞዛያ 24፥13–15። እንደ “ለሰላም የት መሄድ እችላለሁ? [Where Can I Turn for Peace?]” (መዝሙር፣ ቁጥር 129)፣ ያለ መዝሙር በአዳኙ ላይ እምነታችሁን እና በፈተና ወቅት እርሱ የሚሰጠውን እርዳታ ሊያጠነክር ይችላል።

በተጨማሪም አንተኒ ዲ. ፐርኪንስ፣ “የሚሰቃዩ ቅዱሳትህን አስታውስ፣ ኦ የእኛ እግዚአብሔር [Remember Thy Suffering Saints, O Our God]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ) 103–5፤ “እርዳታ ይሰጣችኋል [He Will Give You Help]፣” “ጌታ የሌሂን ጉዞ መራ [The Lord Guides Lehi’s Journey]፣” “ጌታ ኔፊን መርከብ እንዲገነባ አዘዘው [The Lord Commands Nephi to Build a Ship]፣” እና “የሌሂ ቤተስብ ወደ ቃል ኪዳን ምድር በመርከብ ሄዱ [Lehi’s Family Sails to the Promised Land]” (ቪድዮዎች)፣ የወንጌል ቤተ መጽሐፍት፡- “የህይወት እርዳታ [Life Help]፣” የወንጌል ቤተ መጽሐፍት ውስጥ ይመልከቱ።

1 ኔፊ 16፥10–16፣ 23–3118፥11–22

እግዚአብሔር በትንሽ እና በቀላል መንግዶች ይመራኛል።

እግዚአብሔር የሌሂን ቤተሰብ ወደ ምድረ በዳ ሲመራ፣ የጉዞውን እያንዳንዱን ዝርዝር የሚያሳይ ካርታ አልሰጣቸውም። በምትኩ፣ በየቀኑ እንዲመራቸው ሊያሆናን ሰጣቸው። 1 ኔፊ 16፥10–16፣ 23–31 እና 18፥10–22ን ስታነቡ እግዚአብሔር ልጆቹን እንዴት እንደሚመራ የሚያሳዩ እውነቶችን መዘርዘርን አስቡ (ለምሳሌ፣ 1 ኔፊ 16፥10 እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ባልተጠበቁ መንገዶች እንደሚመራን ሊያስተምር ይችላል)። በሊያሆና እና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ምን ተመሳሳይነት ታያላችሁ? በህይወታችሁ ውስጥ “ቀላል በሆነ መንገድ” ያመጣቸው “ታላቅ ነገሮች” ምንድን ናቸው?

በተጨማሪም አልማ 37፥7፣ 38–47ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥33–34ን ተመልከቱ።

ሌሂ ሊያሆናን ሲጠቀም

ከተዘጋጃችሁ ፍርሀት አይኖራችሁም፣ በክላርክ ኬሊ ፕራይስ

1 ኔፊ 17፥1–6፣ 17–22

የእኔ ፈተናዎች በረከት ሊሆኑ ይችላሉ።

ኔፊ እና ወንድሞቹ በምድረ በዳ ተመሳሳይ ፈተናዎች ቢኖሯቸውም እንኳን፣ ልምዶቻቸው በጣም የተለያዩ ነበሩ። የኔፊን የምድረ በዳ ጉዞ ታሪክ (1 ኔፊ 17፥1–6ን ይመልከቱ) ከወንድሞቹ ታሪክ ጋር ማነፃፀር ትችላላችሁ (1 ኔፊ 17፥17–22 ይመልከቱ)። የአማኝ አመለካከት እንዲኖረው እንዲረዳው ኔፊ ምን አወቀ ወይም ምን አደረገ? ስለ ቅርብ ጊዜ ወይም አሁን ላይ ያለ ፈተና በእምነት እና በምስጋና አመለካከት መፃፍን አስቡ። ከዚህ ምን ትማራላችሁ ወይም ምን ይሰማችኋል?

በተጨማሪም ኤሚ ኤ. ራይት፣ “ክርስቶስ የተሰበረን ነገር ይፈውሳል [Christ Heals That Which Is Broken]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 81–84፤ “ያለ ችግር ምንም ጥንካሬ የለም [No Strength without Struggle” (ቪድዮ)፣ የወንጌል ቤተ መጽሐፍት ላይ ይመልከቱ።

የማሰላሰያ የጸጥታ ጊዜ። ለማሰብ፣ ለማሰላሰል፣ ለመገንዘብ ወይም ለመፃፍ ጊዜን መውሰድ ወደ መነሳሳት ሊያመራ ይችላል። የወንጌል ትምህርት ወይም መርሆዎች ከህይወታችን ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ እንድናይ ይረዳል። ሌሎችን ስታስተምሩ ስሜታቸውን እንዲገነዘቡ እና እንዲጽፉ ጊዜን ስጧቸው። ይህ ሃሳባቸውን እና ስሜታቸውን ለሌሎች እንዲያካፍሉ ፍቃደኝነታቸውን ሊጨምር ይችላል።

1 ኔፊ 19፥22–2420–22

“ሁሉንም ቅዱሳት መጽሐፍትን [ከእኔ ጋር] ማመሳሰል” እችላለሁ።

ቅዱሳት መጽሕፍት የተፃፉት ከብዙ ጊዜ በፊት ስለነበረ፣ ዛሬ ለእኛ የማይተገበሩ ሊመስሉ ይችላሉ። ነገር ግን ኔፊ የተሻለን ያውቅ ነበር። “ለእኛ ጥቅምና ትምህርት ይሆኑ ዘንድ” አለ “ሁሉንም ጥቅሶች ከእኛ ጋር አመሳሰልኩ” (1 ኔፊ 19፥23)። ይህ ኔፊ በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ እጅግ ብዙ መንፈሳዊ ኃይልን ያገኘበት እንዱ ምክንያት ነው።

1 ኔፊ 20–22ን ስታነቡ ከዚህ በታች ያሉትን አይነት ጥያቄዎች አስቡ፦

1 ኔፊ 20፥1–9እነዚህ ጥቅሶች በኢሳይያስ ጊዜ ስለነበሩ ሰዎች ምን ያስተምራሉ? ከእናንተ ጋር የሚዛመድ ነገር ምን ታገኛላችሁ?

1 ኔፊ 20፥17–22እነዚህ ጥቅሶች በኢሳይያስ ጊዜ የነበሩትን ሰዎች እግዚአብሔር እንዴት እንደመራቸው ምን ያስተምራሉ? እርሱን እንድትከተሉት እንዴት ይጋብዛችኋል?

1 ኔፊ 20–22 ውስጥ ከራሳችሁ ጋር “የምታመሳስሉትን” ነገር ምን ታገኛላችሁ?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች እትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

1 ኔፊ 16፥10፣ 28–2918፥8–13፣ 20–22

ትዕዛዛትን ስጠብቅ ጌታ ይመራኛል።

  • መንገዳችንን እንድናገኝ የሚረዱን እንደ ኮምፓስ፣ ካርታ ወይም ሌላ ነገር ካላችሁ ለልጆቻችሁ ማሳየት ትችላላችሁ። በ1 ኔፊ 16፥10፣ 28–29 ውስጥ ማንበብ ስለምትችሉት ስለ ሊያሆና ውይይትን ለመጀመር ይሄ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። ኮምፓስ ወይም ካርታ ሊሰራ የማይችልበት ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ለሌሂ ቤተሰብ ሊያሆናው አንዳንድ ጊዜ ያልሰራው ለምንድን ነው? (1 ኔፊ 18፥9–12፣ 20–22 ይመልከቱ)። ወደ እርሱ እንድንመለስ እንዲመራን የሰማይ አባት ዛሬ የሰጠን ነገር ምንድን ነው?

  • 1 ኔፊ 16፥10፣ 26–3118፥8–22፣ ውስጥ ልጆቻችሁ የተማሩትን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለመርዳት፣ ስለ አስፈላጊ ወይም ከባድ ውሳኔ እንዲያስቡ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። እግዚአብሔር ዛሬ ልክ እንደ ሊያሆና ሊመራን የሚያገለግል ምን ሰጥቶናል? (ለምሳሌ፣ አልማ37፥38–44 ይመልከቱ።) የሰማይ አባት እናንተን የመራበትን የግል ልምድ ለማካፈል አስቡ።

1 ኔፊ 16፥21–32

ለቤተሰቤ ጥሩ ምሳሌ መሆን እችላለው።

  • 1 ኔፊ 16፥21–32ን በጋራ ስታነቡ፣ የኔፊ ምሳሌ ቤተሰቡን እንዴት እንደባረከ እንዲያውቁ ልጆቻችሁን እርዱ (እንዲሁም “ጌታ የሌሂን ጉዞ መራ [The Lord Guides Lehi’s Journey]” [የወንጌል ቤተ መጽሐፍት] ቪድዮ ይመልከቱ)። ይህ እንደ ኔፊ እንዴት መሆን እንደምንችል ወደ ውይይት ሊመራ ይችላል። ለሌሎች የቤተሰብ አባላት መልካም ተፅዕኖ ለመሆን ሊያደርጉ የሚችሉትን አንድ ነገር እንዲያቅዱ ልጆቻችሁን ጋብዙ።

1 ኔፊ 17፥7–1918፥1–4

የሰማይ አባት ከባድ ነገሮችን እንዳደርግ ሊረዳኝ ይችላል።

  • ልጆች ታሪኮችን መናገር ይወዳሉ። ኔፊ ጀልባ እንዲሰራ የታዘዘበትን ታሪክ እንድትነግሩ እንዲረዷችሁ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ (1 ኔፊ 17፥7–1918፥1–4ይመልከቱ፤ በተጨማሪም “ምዕራፍ 7፦ መርከብን መስራት [Building the Ship]፣” በየመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች ውስጥ 21–22፤ ወይም “ጌታ መርከብን እንዲገነባ ኔፊን አዘዘው [The Lord Instructs Nephi to Build a Ship]” ቪድዮ [የወንጌል ቤተ መጽሐፍት] ይመልከቱ)። እነሱ “የኔፊ ድፍረት [Nephi’s Courage]ን” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 120–21) ሁለተኛ ስንኝ በጋራ ሊዘምሩ ይችላሉ። ኔፊ ጀልባ ለመገንባት ሲሞክር ወንድሞቹ ሲሳለቁበት ድፍረትን እንዲያገኝ ምን እረዳው?

  • ኔፊ ጀልባን እንዴት መሥራት እንዳለበት ስላላወቀ በጌታ መመሪያ ላይ ተደገፈ። ልጆቻችሁ 1 ኔፊ 18፥1ን ከእናንተ ጋር ካነበቡ በኋላ የዚህ ሳምንትን የአክቲቪቲ ገጽን መጨረስ ይችላሉ። ይህን ሲያደርጉ፣ ልክ ኔፊን እንደረዳው የሰማይ አባት ከባድ ነገሮችን እንድናደርግ እንዴት እንደሚረዳን ንገሯቸው።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ኔፊ እና ቤተሰቡ በጀልባ ላይ

በጣም አጎሳቆሉኝ፣ በዋልተር ሬን